2 days ago
#dessie
አቶ ዱባለ አብራሬ የደሴ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።
የደሴ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን አዲስ ከንቲባ ሹመት አፀደቀ።
በዚህም የወልዲያ ከተማ ከንቲባ የነበሩትን አቶ ዱባለ አብራሬን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
የደሴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #addisababa የደሴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተሹመዋል። መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ለበርካታ ትውልዶች በሚቺጋኑ ካላማዙ ኮሌጅ ከኢኮኖሚክስ መምህርነትም የዘለለ አሻራ ያሳረፉት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ አህመድ ሁሴን የህይወት ጉዟቸውን የሚያወሳ አዲስ መጽሐፍ አሳትመዋል። ፕሮፌሰሩ በኮሌጁ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ፣ የአካባቢ ጥበቃ ትምህርት መስራች፣ እንዲሁም የኮሌጁ ከፍተኛ የማስተማር ክብር የሆነው የፍሎረንስ ጄ. ሉካሴ ሽልማት ተሸላሚ በመሆን ትልቅ ታሪክ ሰርተዋል። ሆኖም ከተማሪዎቻቸው አዕምሮ የማይጠፋው ማዕረጋቸው ሳይሆን፣ ለተማሪዎቻቸው ስኬት የነበራቸው ልባዊ ፍላጎት፣ ያበረከቱት የላቀ የምክር አገልግሎት እና ደግነታቸው ነው።
አሁን ደግሞ "ዘ ዴሴ ኪድ" (The Dessie Kid) በተሰኘው አዲሱ ማስታወሻቸው፣ ከኢትዮጵያ ደሴ ከተማ የልጅነት ጊዜያቸው አንስቶ አህጉራትን እስካቋረጠው የአካዳሚክ የህይወት ጉዟቸው ድረስ ያለውን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብለው ዳስሰውታል። መጽሐፉ ፕሮፌሰሩ በጃፓን ዋሴዳ ዩኒቨርሲቲ፣ በዚምባብዌ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም በቦትስዋና ዩኒቨርሲቲ ያሳለፉትን ጊዜያት ጨምሮ፣ ስለ ጽናት፣ ምስጋና፣ ቤተሰብ እና ህይወታቸውን ስለቀረጹ ሰዎች ጥልቅ የሆነ ግላዊ ምልከታን የያዘ ነው።
ፕሮፌሰሩ ይህንን ማስታወሻ ለመጻፍ ስላነሳሳቸው ምክንያት ሲገልጹ፣ ዓለማዊ ትምህርት ገና ባልተስፋፋበት ወቅት፣ መደበኛ ትምህርት ከሌላቸው ቤተሰቦች የተገኘ አንድ ልጅ እንዴት በአሜሪካ የአካዳሚክ ዓለም ውስጥ ስኬታማ ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት መሆኑን ይናገራሉ። በተለይም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የክርስትና ትምህርት ተጽዕኖ አለባቸው ተብሎ በሚታሰብበት ማህበረሰብ ውስጥ አድገው ይህንን ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታሪካቸውን ልዩ ያደርገዋል።
ጸሃፊው አክለውም ታሪካቸው የተለመደውን የስደተኞች ህይወት የሚያስተጋባ ቢሆንም፣ መጽሐፉን የጻፉት የግል ስኬታቸውን ለማክበር አለመሆኑን ያብራራሉ። ይልቁንም፣ ማንም ሰው ብቻውን ስኬት ላይ እንደማይደርስ በማመን፣ ህይወታቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ እንዲሁም በትክክለኛው ጊዜ በደረሱላቸው ሰዎች እና ተቋማት ደግነት የተቀረጸ መሆኑን ለማሳየት ነው። መጽሐፉ በዋናነት የተጻፈው ቤተሰቦቻቸው ታሪካቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲሁም በጉዟቸው ላይ ለረዷቸው መምህራን፣ ጓደኞች እና ተማሪዎች ምስጋና ለማቅረብ ነው።
በካላማዙ ኮሌጅ ያሳለፉት 34 ዓመታት በሙያ ህይወታቸው ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንዳለው የሚያወሱት ፕሮፌሰሩ፣ ኮሌጁ ሙያዊ ክህሎታቸውን ከማሳደግ ባሻገር ማንነታቸውን ሙሉ በሙሉ የተቀበለ እና ያከበረ የመጀመሪያው ተቋም እንደነበር ይመሰክራሉ። ኮሌጁ ከነጭ-ተኮር ተቋምነት ወደ አካታች እና ብዝሃነት ወዳለው ማህበረሰብ ሲቀየር በዓይናቸው ማየታቸውም በህይወታቸው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጡት ክስተቶች አንዱ ነው።
ጡረታ ከወጡ በኋላ ጊዜያቸውን ከልጅ ልጆቻቸው ጋር በማሳለፍ በማንበብ እና ከህይወት አጋራቸው ጋር በመጓዝ ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር አህመድ፣ ይህን መጽሐፍ ለማጠናቀቅ ወደ ስድስት ዓመታት ገደማ እንደፈጀባቸው ገልጸዋል። የህትመት እና የስርጭት ሂደቱንም የጥራት ደረጃውን ለመጠበቅ ሲሉ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ወጪ እንዳከናወኑት ጠቁመው፣ አንባቢያን መጽሐፉን ለዚሁ ዓላማ ከተዘጋጀው ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

8 months ago
የምስራች ለደሴ እና አካባቢው ነዋሪዎች፦ የኩላሊት እጥበት ማዕከል ግንባታ በይፋ ተጀመረ! 🏗️✨
#ethiopia | በደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረው የኩላሊት እጥበት (Dialysis) ማዕከል ግንባታ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። ይህ ፕሮጀክት በክልሉ ያለውን የጤና አገልግሎት ክፍተት በመሙላት ረገድ ትልቅ ተስፋ ሰንቋል።
ቁልፍ ነጥቦች፦
💰 በጀት፦
ለግንባታውና ለማሽኖች ግዢ በአጠቃላይ 187 ሚሊዮን ብር ተመድቧል። ከዚህ ውስጥ 95 ሚሊዮን ብሩ ቀደም ሲል ለወሎ ቴርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ ከህዝብ የተሰበሰበ መሆኑ ታውቋል።
⏳ የጊዜ ገደብ፦
ግንባታውን በ 3 ወራት ውስጥ በፍጥነት አጠናቆ ስራ ለማስጀመር ታቅዷል።
🌍 ተደራሽነት፦
ሆስፒታሉ ከአማራ ክልል ባለፈ ለአፋር እና ለትግራይ አጎራባች አካባቢዎች (ለ10 ሚሊዮን ዜጎች) አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ፣ ማዕከሉ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገውን እንግልትና ወጪ ያስቀራል።
🙏 የታሪክ አሻራ፦
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አወል ሰይድ እንደገለጹት፤ ማዕከሉ ከ15 ዓመት በፊት ገንዘባቸውን ላዋጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደ ማስታወሻ የሚቆጠር ነው።
በጥላሁን አበበ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሚገነባው ይህ ማዕከል፣ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቆ ለወገኖቻችን ደራሽ እንዲሆን እንመኛለን።
#dessie #wollouniversity #healthnews #dialysiscenter #ethiopia #amharahealth #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
ደሴ : 5 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች 🚌⚡️
#ethiopia | የደሴ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማዘመንና ችግሩን ለመፍታት የገዛቸውን 5 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች በዛሬው ዕለት ተረክቧል።
የአውቶቡሶቹ ፋይዳ፡-
✅ ለነዳጅ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ያስቀራሉ።
✅ የአየር ንብረት ብክለትን በመቀነስ "አረንጓዴ ትራንስፖርት"ን ያበረታታሉ።
✅ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት በመቅረፍ ለነዋሪው እፎይታ ይሰጣሉ።
አውቶቡሶቹ በቅርቡ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ተሰማርተው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩም ተገልጿል።
#dessie #electricbus #greentransport #ethiopia #development

1 year ago
"ዳዊት እደግማለኹ ቁሜ ገረገራ
እመቤቴ ማርያም ኢትዮጵያን አደራ"
የተባለበት ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳም ነው- ወሎ ገረገራ መድኃኔዓለም ገዳም። የሚገኘው ሰሜን ወሎ መቄት ነው። አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፤ ዋልድባ ገዳምን ከማቅናታቸው በፊት ከ700 እሰከ 800 መነኮሳትን ይዘው መጥተው የመሠረቱት ገዳም ነው።
ሐምሌ 3 ለ 4/2017 አጥቢያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ገዳሙ ጉዳት ደረሰበት። እሰካኹን ድረስ ቤተክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ ሊናድ ገደል ላይ ተንጠልጥሎ ይገኛል። በፍጥነት ካልደረስንለት ዐይናችን እያዬ ይወድቃል።
ይኽንን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት መስከረም 9/2018 ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰብ እናካኺዳለን።
በዩቱበሮቹ
በቋንቋዬነሽ ሚዲያ
በነጋሽ ሚዲያ
በሎዛ ሚዲያ
በ21 ሚዲያ
በቲክቶከሮቹ
በልደተቃል
በፋሲል ይርጋ
በሶስና ባዬ
በኪያ
በቅዱስ ኤፍሬም
በቅዱስ ተዋሕዶ
በአርኪ
በደምረው
በጎልድ
በቤቲ
በእነዚኽ ስልኮች ይደውሉ
+251920108478 zelalem Mulatu
+251911437928 Zewudu Geta
+251977683435 Ayalneh Mekbib
+251922744050 Tesfaye Dessie
+17022027422 Misganaw Mulaw USA
በእነዚኽ አካውንቶች ይለግሱ
1000712625957 CBE
9421112255316017 Abay Bank
https://gofund.me/c4f3b61e...

Sponsored by
Surafel
Comments