2 months ago
"ማዕቀቡ የተቋሙን ነፃነት የሚጋፋ ግልጽ ጥቃት ነው!"
#ethiopia | ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ዳኞች ላይ የጣለውን ማዕቀብ “የተቋሙን ነፃነት የሚጋፋ እና ግልጽ ጥቃት” ሲል ገልጾታል።
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሜሪካ በዳኞቹ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እና አባል ሀገራት እንዲወጡ የምታደርገውን ቅስቀሳ በጽኑ ኮነነ።
እንደ አሶሼትድ ፕረስ ዘገባ ከሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ቶሞኮ አካኔ እና በከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ አብዱላዬ ሴዬ ላይ የሃብት እገዳና የጉዞ እገዳ ጥሏል።
በዚህ እርምጃ የትራምፕ አስተዳደር ማዕቀብ የጣለባቸው የፍርድ ቤቱ ዳኞች ቁጥር 9 የደረሰ ሲሆን ይህም የፍርድ ቤቱን ግማሽ ያህል ዳኞች ያካተተ ነው ተብሏል።
አሜሪካ እና እስራኤል የዚህ ፍርድ ቤት አባል አይደሉም በመሆኑም ፍርድ ቤቱ አባል ባልሆኑ ሀገራት ዜጎች እና መሪዎች ላይ ምርመራ ማካሄዱ የሉአላዊነት ጥሰት እና ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም ነው ስትል አሜሪካ ገልጻለች።
ፍ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ሕግን በሚያስከብሩ የፍትህ አካላት ላይ የሚሰነዘር ማስፈራሪያ እና ጫና የመላው ዓለም አቀፍ የሕግ ስርዓትን አደጋ ላይ ይጥላል ብሏል።
አክሎም በፍርድ ቤቱ አባላት ላይ የሚደረጉ ጫናዎች ዓለም አቀፍ ፍትህን እና የተበደሉ ዜጎችን ተስፋ ለማጨናገፍ የተደረጉ ናቸው ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል።
በተጨማሪም የትራምፕ አስተዳደር አባል ሀገራት ከስምምነቱ እንዲወጡ እያደረገ ያለውን ዘመቻ በመቃወም ፍርድ ቤቱ ይህ እርምጃ የጋራ የፍትህ እሴቶችን እና የሕግ የበላይነትን አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠንቅቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #international #criminal #court #america #sanction #foreignminister #justice

ፕሬዝዳንቷ ከየትኛውም የአሜሪካ ተቋም ጋር ግኑኝነት እንዳያደርጉ ታገዱ
*አሜሪካ በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ላይ ማዕቀብ ጣለች
#ethiopia | የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ጃፓናዊቷ ዳኛ ቶሞኮ አካኔ ላይ ማዕቀብ ጥሏል።
ማዕቀቡ በአሜሪካ የሚገኝ ማንኛውም ሀብታቸው እንዲታገድ እና ከአሜሪካ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲሁም ከማንኛውም የአሜሪካ ዜጋ/ተቋም ጋር የንግድና የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የሚያደርግ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ የአሜሪካ እና እስራኤል ባለስልጣናት ለመክሰስ እና ለማሰር የሚደረገውን ጥረት በመምራታቸው ምክንያት የተጣለ እርምጃ ነው ብለዋል።
ፍርድ ቤቱ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና በቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ ውጥረቱ እየተባባሰ መጥቷል።
አሜሪካ የፍርድ ቤቱ አባል አይደለችም።
ነገር ግን የትራምፕ አስተዳደር ፍርድ ቤቱ የሀገራትን ሉአላዊነት እና የአሜሪካን እንዲሁም የእስራኤልን ጥቅም የሚጋፋ ነው በማለት ይከሱታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #usa #international #court #president #japan #sanction #criminal

1 year ago
ያሳዝናል 😭
#ethiopia | ልጅቷ ዩክሬናዊት ስደተኛ ናት። በነገራችን ላይ..ገ*ዳ*ዩ ልጅቷን አያውቃትም። እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ ነው የገDeላት። Iryna ትባላለች። ሀገሯ ዩክሬን በጦርነት እየታመሰ ስለሆነ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ወደ አሜሪካ የመጣች ስደተኛ ናት። ይህ የወንጀል ድርጊት የተፈፀመው August 22 እለት ነበር ፤ ። የልጅቷ አሟሟት በጣም ነው ልብ የሚሰብረው 😢 She was fatally stabbed to death 💔
.
ገ ዳ ዩ ይህንን ወንጀል ለምን እንደፈፀመው ራሱ አይታወቅም። ከልጅቷ ጋር ትውውቅ የላቸውም ምንም ነገር የላቸውም። ፀብም የላቸውም። አያውቃትም። Iryna ዩክሬን ውስጥ ባለው ጦርነት ምክንያት ወደ አሜሪካ የመጣችው Safe የሆነ ኑሮ እኖራለሁ ብላ አስባ ነበር 💔 ግን በአጭር ተቀጨች።
.
ይህቺ የ 23 አመት ወጣት አሜሪካ በስደት በቆየችባቸው ጥቂት ወራት ውስጥ በጎረቤቶቿ እንዲሁም በስራዋ አካባቢ በአጠቃላይ በኮሚኒቲው እጅግ የምትወደድ ልጅ ነበረች። ከዩክሬን እንደመጣች መጀመርያ Caregiver ነበር የምትሰራው። ከዛ በኋላ Zeppedis pizzeria የሚባለው ፒዛ ቤት ውስጥ ሼፍ በመሆን አገልግላለች። ህይወቷን መስመር ለማስያዝ የምትጥር ምስኪን ስደተኛ ወጣት ናት።
የመጀመርያ መኪናዋን ቅርብ ጊዜ ገዝታ ስለነበር.. Driving license ለማውጣት ፕሮሰስ ላይም ነበረች። She was known for her Generosity and Hard work. ጠንካራ ሰራተኛ ናት። ጥቃቱን የፈፀመባት ሰው ከዚህ በፊት ከ 15 በላይ Criminal Record ያለበትና ፤ ከረጅም ጊዜ እስር በኋላ በ 2011 ከእስር ቤት የተለቀቀ ግለሰብ ነው።
ፍራኦል ሀበሻ

Comments