2 months ago
"ማዕቀቡ የተቋሙን ነፃነት የሚጋፋ ግልጽ ጥቃት ነው!"
#ethiopia | ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ዳኞች ላይ የጣለውን ማዕቀብ “የተቋሙን ነፃነት የሚጋፋ እና ግልጽ ጥቃት” ሲል ገልጾታል።
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሜሪካ በዳኞቹ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እና አባል ሀገራት እንዲወጡ የምታደርገውን ቅስቀሳ በጽኑ ኮነነ።
እንደ አሶሼትድ ፕረስ ዘገባ ከሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ቶሞኮ አካኔ እና በከፍተኛ ዓቃቤ ሕግ አብዱላዬ ሴዬ ላይ የሃብት እገዳና የጉዞ እገዳ ጥሏል።
በዚህ እርምጃ የትራምፕ አስተዳደር ማዕቀብ የጣለባቸው የፍርድ ቤቱ ዳኞች ቁጥር 9 የደረሰ ሲሆን ይህም የፍርድ ቤቱን ግማሽ ያህል ዳኞች ያካተተ ነው ተብሏል።
አሜሪካ እና እስራኤል የዚህ ፍርድ ቤት አባል አይደሉም በመሆኑም ፍርድ ቤቱ አባል ባልሆኑ ሀገራት ዜጎች እና መሪዎች ላይ ምርመራ ማካሄዱ የሉአላዊነት ጥሰት እና ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም ነው ስትል አሜሪካ ገልጻለች።
ፍ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ ሕግን በሚያስከብሩ የፍትህ አካላት ላይ የሚሰነዘር ማስፈራሪያ እና ጫና የመላው ዓለም አቀፍ የሕግ ስርዓትን አደጋ ላይ ይጥላል ብሏል።
አክሎም በፍርድ ቤቱ አባላት ላይ የሚደረጉ ጫናዎች ዓለም አቀፍ ፍትህን እና የተበደሉ ዜጎችን ተስፋ ለማጨናገፍ የተደረጉ ናቸው ሲል ውሳኔውን ተቃውሟል።
በተጨማሪም የትራምፕ አስተዳደር አባል ሀገራት ከስምምነቱ እንዲወጡ እያደረገ ያለውን ዘመቻ በመቃወም ፍርድ ቤቱ ይህ እርምጃ የጋራ የፍትህ እሴቶችን እና የሕግ የበላይነትን አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠንቅቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #international #criminal #court #america #sanction #foreignminister #justice

Comments