2 months ago
የቲክቶክ ንጉስ ካቢ ላሜ የግል አካውንቱ ውስጥ ድንቡሎ የለውም ተባለ
#ethiopia | በቲከቶክ ማኅበራዊ ገጽ ላይ ንግግር ሳይጠቀም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማዝናናት የሚታወቀው ካቢ ላሜ፣ አሁን ላይ የግል ህይወቱና የፋይናንስ አያያዙ አነጋጋሪ ሆኗል።
በተለይም ከባለቤቱ ጋር እያደረገ ያለው የፍቺ ሂደት፣ የኮከቡን ያልተጠበቀ የሀብት አያያዝ ምስጢር ይፋ አድርጓል።
ምንም እንኳን የካቢ ላሜ አጠቃላይ የተጣራ ሀብት 20 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት ቢገለጽም፣ በፍቺ ሂደቱ ወቅት የቀረቡ የፍርድ ቤት ሰነዶች ግን ሌላ እውነትን አመልክተዋል።
እንደ ሰነዶቹ ገለጻ፣ ካቢ ላሜ በራሱ ስም የተመዘገበ ምንም ዓይነት ዋና ንብረት ወይም የባንክ ሂሳብ የለውም።
የምርመራ ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ የካቢ ላሜ የቅንጦት ቤቶችና አብዛኛው የፋይናንስ ይዞታዎች የተመዘገቡት በአባቱ ስም ነው።
ይህ ዓይነቱ አካሄድ በታዋቂ ሰዎች ዘንድ የተለመደ የሀብት መከላከያ ስልት እንደሆነ ይነገራል። ዓላማውም በፍቺ ወቅት የሚመጣን የሀብት ክፍፍል ወይም ከፍተኛ የቀለብ ክፍያን (Alimony) ለመቀነስ ታስቦ የሚደረግ መሆኑ ይገመታል።
ይህ ግኝት በፍርድ ቤቱ ቀጣይ ውሳኔ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የፍርድ ቤቱ ባለሙያዎች ይህንን የሀብት ሽግግር እንደ "ንብረትን የመደበቅ ሙከራ" ካዩት፣ ኮከቡ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ወይም የሀብት ክፍፍል ሊገጥመው ይችላል።
በማኅበራዊ ገጾቹ ላይ ሁሌም ዝምታን የሚመርጠው ካቢ፣ በዚህ አነጋጋሪ የገንዘብ ጉዳይ ላይ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#መናኸሪያfm #getutemesgen #getu #khabylame #tiktok #celebritynews #finance #divorce #wealthmanagement #internationalnews #ካቢላሜ #ቲከቶክ #ዜና #ኢትዮጵያ