1 month ago
ማንቸስተር ዩናይትድ ፊቱን ወደ ሌላኛው ብራዚላዊ አዙሯል
#ethiopia | ዩናይትዶች ብራዚላዊው የቼልሲ አማካይ አንድሬ ሳንቶስን ለማስፈረም የመጀመሪያ የዝውውር እንቅስቃሴያቸውን ጀምረዋል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የመሀል ሜዳ ክፍሉን ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ዩናይትድ አሁን የ22 ዓመቱን ብራዚላዊ አማካይ አንድሬ ሳንቶስን በዝውውር ዕቅዱ ውስጥ አካቷል።
እስካሁን ለተጫዋቹ ይፋዊ የገንዘብ ጥያቄ ባይቀርብም የክለቡ ተወካዮች ስለ ተጫዋቹ የዝውውር ሁኔታ መረጃዎችን እየሰበሰቡ ይገኛሉ ተብሏል።
የተጫዋቹ ባለቤት የሆኑት ቼልሲዎች ተጫዋቹን ለሽያጭ አይቀርብም ብለው አለማሳወቃቸው ዩናይትዶች ፍላጎታቸው እንዲጨምር አድርጓል።
ቼልሲዎች የፈለጉትን የገንዘብ መጠን ከቀረበላቸው ተጫዋቹን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።
አንዳንድ ምንጮች እንዳሉት ከሆነ ለተጫዋቹ እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደርስ ዋጋ ቼልሲዎች እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
አንድሬ ሳንቶስ በቼልሲ በሞይሰስ ካይሰዶ እና በኤንዞ ፈርናንዴዝ ጥላ ስር በመውደቁ በቂ የመጫወቻ ጊዜ ለማግኘት ወደ ሌላ ክለብ መሄድ እንደሚፈልግ ተጠቅሷል።
ቶናሊን ለቶትንሃም አሳልፎ የሰጠው ኒውካስትል ዩናይትድም የተጫዎቹ ፈላጊ መሆኑም ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #manchesterunitedfc #chelsea #andreysantos #fabrizioromano

Comments