21 days ago
ከሚስቱ ጭቅጭቅ ለማምለጥ ደንቆሮ እና ዲዳ መስሎ የኖረው ሰው ጉድ
#ethiopia | በአሜሪካዋ ኬንቴኪ ግዛት ነዋሪ የሆነው ይህ ግለሰብ ለ30 አመታት ያህል በውሸት መስማትም ሆነ መናገር ተሳነኝ ብሎ ከሚስቱ ጋር ኖሯል።
ይህ ግለሰብ ከባለቤቱ ጋር ዘወትር የሚፈጠሩ ጭቅጭቆችና ንዝንዞችን ለማስቀረት ሲል ለ30 ዓመት መስማትም ሆነ መናገር ተሳነኝ" ብሎ ደንቆሮ እና ዲዳ መስሎ ኖሯል።
ትዳር የመቻቻል እና የውይይት ውጤት ነው" የሚለውን አባባል እሱ ዘንድ ቦታ አልነበራቸውም።
ይህ ሰው ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ከባለቤቱ ጋር በሚያደርጋቸው ማናቸውም ግንኙነቶች በሙሉ ምንም አይነት ድምፅ ሳያወጣ በምልክት ቋንቋ እና በጽሁፍ ብቻ እየተግባባ ህይወቱን ሲገፋ ቆይቷል ነው የተባለው።
ሆኖም ግን በአንድ ካፌ ውስጥ ከጓደኛው ጋር በደስታ ሲያወራና እና ሲስቅ ባለቤቱ በድንገት አግኝታው ምስጢሩ ለ30 ዓመት ደብቆት የኖረው ሚስጥር ተጋለጠ።
ላለፉት 30 ዓመታት "ምንም ድምፅ አይሰማውም መናገርም አይችልም" ብላ ስታዝንለት የነበረችው ባለቤቱ የባሏን ድምፅ እና ሳቅ ስትሰማ ህልም እንጂ እውነት አልመስል አላት።
ምስጢሩ ወዲያውኑ በመጋለጡ እና ላለፉት 30 ዓመታት በሙሉ በተሰራባታ ትልቅ ማታለል ክፉኛ የተናደደችው ባለቤቱ ወዲያውኑ የፍቺ ጥያቄ አቅርባለት ሊለያዩ ችለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #america #oddnews #amazingstories #hearing #worldnews #deaf

1 month ago
የልጇን የእናትነት ህልም እውን ያደረገችው እናት!
#ethiopia | በ61 ዓመቷ የልጅ ልጅዋን በማኅፀኗ አርግዛ የልጇን የእናትነት ሕልም እውን ያደረገችው እናት መነጋገርያ ሆናለች።
አንዲት እናት ለልጇ ልትሰጣት የምትችለው ትልቁ ስጦታ ምን ሊሆን ይችላል?
በቺካጎ የምትኖረው ክሪስቲን ኬሲ ለአመታት ልጅ ለመውለድ ጥረት ስታደርግ ለቆየችው ልጇ ሳራ ኮነል ያደረገችው ተአምር እውነተኛ የእናትነት ፍቅርን ምን እንደሆነ አሳይቷል።
ሳራ እና ባለቤቷ ልጅ ማግኘት ተስኗቸው በብዙ ፈተና ውስጥ ካለፉ በኋላ ክሪስቲን የልጇን ጭንቀትና ህመም ተረድታ ህፃኑን በማኅፀኗ አርግዛ ለመውለድ ወሰነች።
የሕክምና ባለሙያዎች የሳራን እንቁላል እና የባለቤቷን ዘር በማቀላቀል በቤተ ሙከራ ፅንሱን ካዘጋጁ በኋላ ክሪስቲን የወሊድ ማቆሚያ እድሜዋ ካለፈች በኋላም ቢሆን ለዕርግዝና የሚያዘጋጅ የሆርሞን ሕክምና እንድትወስድ አደረጉ።
በ61 ዓመቷ እርግዝናውን በሙሉ ጤንነት በመጨረስ በቀዶ ሕክምና የልጅ ልጅዋን በሰላም ተገላግላለች።
ለሳራ ይህ አጋጣሚ ለዓመታት ስትመኘው የነበረውን ልጅ የማቀፍ ህልሟን እውን ያደረገ ሲሆን ለእናቷ ደግሞ በ61 ዓመቷ ለልጇ ልትሰጣት የምትችለውን ትልቁን የእናትነት ስጦታ ያበረከተችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኗል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #motherlylove #inspiration #surrogacyjourney #familyfirst #amazingstories

Comments