2 days ago
የእናቱን ውለታ በ10 ሚሊዮን ዶላር የዘከረው ጆርዳን!
#ethiopia | ማይክል ጆርዳን የእናቱን ውለታ ለማሰብ ለሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አደረገ
ኮከቡ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን ለተማረበት የሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ጆርዳን ይህንን ድጋፍ ያደረገው እናቱ ለማህበራዊ አገልግሎት እና ቤተሰቦችን ለመደገፍ የነበረት ከፍተኛ ፍቅርና አስተዋጽኦ ለመዘከር እና ለማክበር እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ እርዳታ በትምህርት ቤቱ ታሪክ ውስጥ ከተደረጉት የገንዘብ ድጋፎች በሙሉ ትልቁ ድጋፍ እንደሆነ ተነግሯል።
ለእናቱ መስዋዕትነት እና አሪያነት እውቅና ለመስጠትም በትምህርት ቤቱ ስር የሚገኘው ዓለም አቀፍ የምርምር ማዕከል በስሟ ተሰይሟል።
ይህ ድጋፍ በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ተማሪዎችን እና መምህራንን ለመደገፍ ይውላል ነው የተባለው።
በተለይም በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ያለውን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ እና ለአደጋ የተጋለጡ ህፃናትና ቤተሰቦችን ለመደገፍ ለሚደረጉ የምርምርና የተግባር ስራዎች ላይ ይውላል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #michaeljordan #delorisjordan #uncsocialwork #motherlylove

1 month ago
የልጇን የእናትነት ህልም እውን ያደረገችው እናት!
#ethiopia | በ61 ዓመቷ የልጅ ልጅዋን በማኅፀኗ አርግዛ የልጇን የእናትነት ሕልም እውን ያደረገችው እናት መነጋገርያ ሆናለች።
አንዲት እናት ለልጇ ልትሰጣት የምትችለው ትልቁ ስጦታ ምን ሊሆን ይችላል?
በቺካጎ የምትኖረው ክሪስቲን ኬሲ ለአመታት ልጅ ለመውለድ ጥረት ስታደርግ ለቆየችው ልጇ ሳራ ኮነል ያደረገችው ተአምር እውነተኛ የእናትነት ፍቅርን ምን እንደሆነ አሳይቷል።
ሳራ እና ባለቤቷ ልጅ ማግኘት ተስኗቸው በብዙ ፈተና ውስጥ ካለፉ በኋላ ክሪስቲን የልጇን ጭንቀትና ህመም ተረድታ ህፃኑን በማኅፀኗ አርግዛ ለመውለድ ወሰነች።
የሕክምና ባለሙያዎች የሳራን እንቁላል እና የባለቤቷን ዘር በማቀላቀል በቤተ ሙከራ ፅንሱን ካዘጋጁ በኋላ ክሪስቲን የወሊድ ማቆሚያ እድሜዋ ካለፈች በኋላም ቢሆን ለዕርግዝና የሚያዘጋጅ የሆርሞን ሕክምና እንድትወስድ አደረጉ።
በ61 ዓመቷ እርግዝናውን በሙሉ ጤንነት በመጨረስ በቀዶ ሕክምና የልጅ ልጅዋን በሰላም ተገላግላለች።
ለሳራ ይህ አጋጣሚ ለዓመታት ስትመኘው የነበረውን ልጅ የማቀፍ ህልሟን እውን ያደረገ ሲሆን ለእናቷ ደግሞ በ61 ዓመቷ ለልጇ ልትሰጣት የምትችለውን ትልቁን የእናትነት ስጦታ ያበረከተችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኗል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #motherlylove #inspiration #surrogacyjourney #familyfirst #amazingstories

Comments