23 days ago
"ገንዘቤ ባንክ ውስጥ ተቀምጦ ከምሞት የካንሰር ህመምተኞች ይታከሙበት!"
#ethiopia | በጡረታ የተገለሉት ህንዳዊቷ ዶክተር በህይወት ዘመናቸው የቆጠቡትን ገንዘብ ለካንሰር ታካሚዎች እንዲሆን ለግሰዋል።
የቀድሞ የህንድ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም የነበሩት እኚህ አዛውንት አቅም የሌላቸው ሴቶች የካንሰር ህክምና ማግኘት እንዲችሉ የቆጠቡትን ሙሉ ገንዘባቸው ለግሰዋል።
በህክምና ሙያ ዘመናቸው የካንሰር ህክምና ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ምክንያት በርካታ ሴቶች ሲሰቃዩ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም ገንዘባቸው በባንክ አካውንት ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ እነዚህን ሴቶች መርዳቱ የበለጠ ጥቅም እንዳለው ወስነዋል።
ወደ 350,000 ዶላር የሚጠጋው ይህ የገንዘብ የገንዘብ ልገሳ በካንሰር ህክምና ላይ ለሚገኙና ለተቸገሩ ሴት ታካሚዎች ይውላል ነው የተባለው።
አዛውቷ ሰዎችን በመንከባከብ ሁለት አስርት ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ በህይወታቸው የቆጠቡትን አብዛኛውን ገንዘብ ያንኑ ደግ ተግባራቸው ለማስቀጠል አውለውታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #drlakshmibai #inspiration #womenhealth #generosity #cancercare #aiims #humanity #healthcarehero #philanthropy

8 months ago
በህንድ 33 ህፃናት ላይ የፆታ ጥቃት የፈፀሙ ባልና ሚስት የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው
በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት የሚገኝ ፍርድ ቤት፣ ላለፉት አስር ዓመታት በ33 ህፃናት ላይ ዘግናኝ የፆታ ጥቃት ሲፈጽሙ በነበሩ ባልና ሚስት ላይ የሞት ቅጣት ማስተላለፉ ተስምቷል።
ተከሳሾቹ የቀድሞ የመንግስት መሃንዲስ የነበሩት የ50 ዓመቱ ራም ብሃዋን እና ባለቤቱ ዱርጋቫቲ ሲሆኑ ዕድሜያቸው ከ3 እስከ 13 የሆኑ 33 ህፃናት በስጦታና በቪዲዮ ጌም በመደለል ወደ ቤታቸው በመውሰድ ለዓመታት ጥቃት መፈጸም እና ድርጊቱን በቪዲዮ በመቅረጽ ለ47 አገራት ለሚገኙ ድረ ገፆች ምስላቸውን ሲሸጡ ነበር ተብሏል።
ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ህፃናት ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ አንዳንዶቹም የዓይን እይታቸውን እስከማጣት ደርሰዋል።
በአሁኑ ወቅት ተጎጂዎቹ በዴልሂ በሚገኝ ከፍተኛ የሕክምና ተቋም (AIIMS) የሥነ-ልቦና እና የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛልም ተብሏል።
ወንጀሉ ሊጋለጥ የቻለው እ.ኤ.አ. በ2020 ኢንተርፖል ባደረገው የዲጂታል ክትትል እና ለህንድ የምርመራ ቢሮ (CBI) በሰጠው ጥቆማ ሲሆን የባንዳ ፍርድ ቤት ዳኛ ፒ.ኬ. ሚሽራ ወንጀሉን "እጅግ አሰቃቂ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ተከሳሾቹ ለፈጸሙት ድርጊት የመታረም ዕድል የሌላቸው መሆኑን በመጥቀስ የሞት ቅጣቱን አጽድቀዋል።
ምንጭ፦ BBC / The Times of India

Comments