10 months ago
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጻሕፍቱን በዓለም አቀፉ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ ስም ሰየመ
📌ታዋቂው የግብርና ሳይንቲስት ፕሮፌሰር
ፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ የአፍሪካ ወጣቶች ለአህጉሪቱ ለውጥ በፈጠራና በትምህርት እንዲነሱ ጥሪ አቀቅርበዋል
#ethiopia | በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ-ጥሩ የሆኑት የዕፅዋት ተመራማሪና የዓለም የምግብ ሽልማት ተሸላሚው ፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ፣ የአፍሪካ ወጣቶች የዕውቀትና የፈጠራ ባለቤት በመሆን የአህጉሪቱን ትንሳኤ እንዲያረጋግጡ አሳሰቡ።
ፕሮፌሰሩ ይህንን ያሉት በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው "የአፍሪካ ወጣቶች ለአፍሪካ ለውጥ" በሚል ርዕስ ለተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ባደረጉት አነቃቂ ንግግር ነው።
🏫 የዕውቀትና የቴክኖሎጂ አስፈላጊነት
ፕሮፌሰር ገቢሳ በንግግራቸው ወቅት እንደ አሜሪካ፣ አውሮፓ እና የእስያ ነብሮች (Asian Tigers) ያሉ የበለጸጉ ሀገራት ለስኬት የበቁት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ መሆኑን ጠቅሰዋል። "ከ400 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የአፍሪካ ወጣት ትምህርት ላይ በማተኮር የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ ይገባል" ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ወጣቱ ዓለም አቀፍና አካባቢያዊ ችግሮችን ለመፍታት ራሱን በቴክኖሎጂ ማስታጠቅ እንዳለበት አሳስበዋል።
⌛️ "ስኬት በስነስርዓት ይገኛል"
ፕሮፌሰሩ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበሩበት ወቅት የነበራቸውን የጥናትና የጊዜ አጠቃቀም ልምድ ለወጣቶቹ አካፍለዋል።
"ትኩረቴን ትምህርቴ ላይ አደርግ ነበር፣ በትርፍ ጊዜዬም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰርቼ ተጨማሪ ገቢ አገኝ ነበር፤ ለራስ ማዝናኛ ደግሞ ቅርጫት ኳስ እጫወት ነበር" በማለት ስኬት የሚገኘው ጊዜን በአግባቡ በመጠቀምና በጠንካራ ስራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ለፕሮፌሰሩ የተሰጠ ታላቅ ክብር🎖
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል የሱፍ፣ ፕሮፌሰሩ ልምዳቸውን ለወጣቱ ለማካፈል በመምጣታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዩኒቨርሲቲው ለፕሮፌሰር ገቢሳ እጄታ ያለውን ክብር ለመግለጽም፡-
* የቤተ-መጻሕፍት ስያሜ፡ የዩኒቨርሲቲው ማዕከላዊ ቤተ-መጻሕፍት በፕሮፌሰሩ ስም እንዲሰየም ተደርጓል።
* ዲጂታል ኤግዚቢሽን፡ የፕሮፌሰሩን ከ260 በላይ የምርምር ጽሑፎች፣ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንትና ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ያገኟቸውን ሽልማቶች እንዲሁም የህይወት ታሪካቸውን የሚያሳይ ዲጂታል ኤግዚቢሽን ተመርቋል።
ፕሮፌሰር ገቢሳ እና ቤተሰቦቻቸው በስሟቸው የተሰየመውን ቤተ-መጻሕፍት ይበልጥ ለማዘመንና ለማጠናከር ቃል ገብተዋል። "ይህ ቤተ-መጻሕፍት ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ወሳኝ ነው፤ እኔና ቤተሰቤም እንዲሻሻል በጋራ እንሰራለን" ብለዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #haramayauniversity #professorgebisaejeta #agriculture #innovation #africanyouth #education #worldfoodprize

Comments