30 days ago
ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት፡- ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የአፍሪካን የታሪክ አቅጣጫ እየቀየረች ይገኛል
***********************
አፍሪካ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሌሎች ሀገራት ፈጠራዎችና ምርቶች ተጠቃሚ ብቻ ሆና የኖረችበት ዘመን ማብቂያው የተቃረበ ይመስላል።
ይህን ታሪካዊ ምዕራፍ በግንባር ቀደምትነት እየመራች የምትገኘው ደግሞ ኢትዮጵያ ናት። በፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ የምትገኘው ሀገራችን፣ የአህጉሪቱን የመጀመሪያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመገንባት የአፍሪካን የቴክኖሎጂ አቅጣጫ ቀይራለች።
በ2012 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ሀገራችን በዘመናዊው የቴክኖሎጂ ዓለም የራሷን ቦታ እንድትይዝ የተጣለ ጠንካራ መሠረት ነው።
ኢንስቲትዩቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ዓላማው ኢትዮጵያን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ከመሆን አውጥቶ ወደ ፈጣሪነትና አበልጻጊነት ማሸጋገር ነበር።
ተቋሙ እንደ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛና ሶማሊኛ ያሉ ሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታሉ ዓለም ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የድምፅና የጽሑፍ ትርጉም ቴክኖሎጂዎችን አበልፅጓል።
በተጨማሪም የካንሰር ህመም ምርመራዎችን፣ የኤክስሬይ (X-ray) እና የምስል ትንተናዎችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመደገፍ የሕክምና አገልግሎትን ፈጣንና ትክክለኛ የሚያደርጉ ስልተ-ቀመሮችን አዘጋጅቷል።
በግብርና የሰብል በሽታዎችን አስቀድሞ ከመለየት ጀምሮ፣ በሳይበር ደኅንነትና በፋይናንስ ዘርፍ የማጭበርበር ድርጊቶችን የሚከላከሉ ሀገር በቀል አሰራሮችም ተዘርግተዋል።
ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎችን በቀጥታ ከመግዛትና ከመጠቀም ተላቅቃ የራሷን ባህል፣ ቋንቋና ፍላጎት ያገናዘቡ መፍትሔዎችን ማበልጸጓ የቴክኖሎጂ ነፃነቷን የሚያረጋግጥ ትልቅ እርምጃ ነው። ይህም ጉዞ ኢትዮጵያን በአፍሪካ የዲጂታል ዘመን ግንባር ቀደም መሪ ያደርጋታል።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #ethiopiaai #artificialintelligence #techindependence #digitalethiopia #africarising

Comments