3 months ago
የአፍሪካ ፎርዋርድ 2026 ጉባኤ፦ ከአሮጌው የእርዳታ ዘይቤ ወደ አዲስ የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ትብብር
*****************
በፈረንሳይ እና በአፍሪካ አህጉር መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመው "አፍሪካ ፎርዋርድ" ጉባኤ በኬንያ መዲና ናይሮቢ በደመቀ ሁኔታ መጀመሩን ገልጸናል።
"አፍሪካ ፎርዋርድ፡ የአፍሪካ-ፈረንሳይ አጋርነት ለፈጠራ እና ለዕድገት" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፣ ለበርካታ ዓመታት ሲተገበር ከቆየውና "ፍራንኮ-አፍሪካ" ተብሎ ከሚጠራው የተለመደ ግንኙነት ወጥቶ ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት ያካተተ አዲስ ስትራቴጂ ለመቅረጽ ያለመ ታሪካዊ መድረክ ነው።
ጉባኤው ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ባልሆኑ እንደ ኬንያ ባሉ ሀገራት መካሄዱ፣ ፈረንሳይ ከአህጉሪቱ ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማስፋትና ከአዳዲስ የኢኮኖሚ ማዕከላት ጋር ለመተሳሰር የጀመረችውን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የጉባኤው ዋነኛ ግብም በአፍሪካ እና በፈረንሳይ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን እና በጋራ ክብር ላይ የተመሰረተ እኩል አጋርነትን መፍጠር እንደሆነ ታውቋል።
የዘንድሮው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ በሰባት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየመከረ ይገኛል።
አፍሪካን የጥሬ ዕቃ ላኪ ከመሆን አውጥቶ ወደ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ ማዕከልነት ለማሸጋገር የሚያስችለው የኢነርጂ ሽግግር፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለአፍሪካ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያሻሽሉ የሚጠይቀው የፋይናንስ ሥርዓት ለውጥ እና የባሕር ላይ ኢኮኖሚ ልማት በውይይቱ ከተነሱት ዐበይት ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።
በዘላቂ ግብርና እና የምግብ ዋስትና፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እንዲሁም ጠንካራ የጤና ሥርዓት በመገንባት ረገድ አህጉሪቱ የራሷን ክትባትና መድኃኒት ማምረት የምትችልበትን ሁኔታ በዝርዝር እየተመለከተ ይገኛል።
ሰላምና ደኅንነትን እንደ ልማት መሠረት በመውሰድ አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ጥረቶችን መደገፍም ሌላው የውይይቱ አንኳር ሆኖ ቀርቧል።
በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የጉባኤው አስተናጋጅ የሆኑት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
እንደ ሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ያሉ መሪዎችም በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ የመሪነት ሚናቸውን እየተወጡ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ንግድ ድርጅት መሪዎች መገኘት ለውይይቱ ዓለም አቀፋዊ ክብደት ሰጥቶታል።
ከፖለቲካ መሪዎቹ ባሻገር እንደ አሊኮ ዳንጎቴ እና ስትራይቭ ማሲዪዋ ያሉ የአፍሪካ ባለሀብቶች ከፈረንሳይ ኩባንያዎች ጋር በቀጥታ ኢንቨስትመንት ዙሪያ እየመከሩ ነው።
ይህም ጉባኤው ከተለመደው የፖለቲካ ንግግር ባለፈ ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ ትብብር መሸጋገሩን የሚያረጋግጥ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።
በለሚ ታደሰ
#africa #france #africaforward2026 #economiccooperation #partnership #ebc

Comments