9 months ago
ሰንጋተራ – ጉራጌ ሰፈር
#ethiopia | ከታች ፎቶው የተያያዘው የመላኩ ተገኝ (ዶክተር) ግለ ታሪክ፣ የዚያ ትውልድ የወቅቱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ትዝታንና ትውስታን መሰረት ተደርጎ የተጻፈ ባለ 300 ገጽ መጽሐፍ ነው።
በዚህ መጽሐፍ ላይ በ1940ዎቹ በአዲስ አበባ በተለይም ሰንጋ ተራ የሚኖሩ ጉራጌዎች ባህሪይ፣ ጠባይ እና የወቅቱ የአኗኗር ዘይቤ በጥቂቱ እንዲህ ሰፍሯል።
................
"እኔና ወንድሜ የተወለድነው ሰንጋተራ ከ'ደሬ ውኃ ስንቁ'' ሰፈርና ጉራጌ ሰፈር” መሀል ባለው በ'ብላታ በቀለ ግቢ ውስጥ ነው። እኔ ትዝ የሚለኝ ግን ጉራጌ ሰፈር ስንኖር ነው። ደሬ ጉራጌ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው ዛሬ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ካለበት በስተጀርባ የነበረው ሰፈር ነው። ወይን ("ንብ ባንክ እና ዙርያ ገባው" አካባቢ)
የኛ ቤት በጉራጌ ሰፈር ዋናው መንገድ ላይ ሲሆን በጣም ብዙ ሰው የሚመላለስበት ነበር። ግመሎችን የሚነዱና ሸቀጥ በአህያ የጫኑ ነጋዴዎች ወደ መርካቶ ሲሄዱ፣ የኦርማ–ጋራዥ ሠራተኞችና ተማሪዎች በበራችን ሲያልፉ ትዝ ይለኛል።
ደጃፍ እናቴ የምትሠራውን እየሠራች ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን እመለከት ነበር። ለዓይን ያዝ ሲያደርግ የጎረቤታችን የወንድሙ አባት ክራራቸውን ሲጫወቱ የሚያመሹት ነገር ዛሬም ድረስ አልተረሳኝም።
ጠዋት ጠዋት እማማ ትክከሏ #“በላለዴ ምጣ" ሳይሉ አያልፉም ነበር።
ከበስተኋላችን ከሚኖሩት ጎረቤቶች ደግሞ ጠዋት ጠዋት ላም ስትታለብ፣ ቡና ሲወቀጥ፣ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ሲዘገጃጁ ይሰማል፤ በሰንጋ ተራ።
አብዛኛው ነዋሪ ትሑትና ሰው አክባሪ ነበር።
በሳምንቱ በተወሰኑ ምሽቶች መንደርተኛው ሁሉ አቶ ባለሜና እማማ ትክከሏ ቤት ይሰባሰባል። ቡና በትልቅ ጀበና ይፈላል፤ የበቆሎ ቆሎ ቁርስ ይቆላል።
ትላልቁ ሰው ቡና ሲጠጣ እኛ ኩታሮቹ ቆሏችንን እንበላና ከበሮ ይመጣል። ከዚያ በኋላ በጉራጊኛ ዘፈንና ጭፈራ ቤቱ ይደምቃል። እኔም ወንድ ልጅ መጨፈር ያለበትን የጉራጊኛ ጭፈራ ስልት ተማርኩ።
ያኔ የነበሩ ጓደኞቼ አይረሱኝም። ፍቅሬ፣ ጉልላት፣ ፍቃዱ፣ እነ ገረመው ዘርጋው፣ ፍቃዱ ወልዴ፣ ግርማ ጣሴና አስራት ጣሴ ታላላቆቻችን ነበሩ። እናቴ ከጉራጌ ሰፈር ሴቶች ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ስለነበራት ጉራጊኛ ልቅም አድርጋ ትናገር ነበር።"
#enkssm #ethiopianhistoryandtourism

Comments