4 hours ago
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች
የስፔን ላሊጋ
04:00 | ማላጋ ከ ኤስፓኞል
የጀርመን ቡንደስሊጋ
03:30 | ዶርትሙንድ ከ ወርደር ብሬመን
የፈረንሳይ ሊግ 1
03:45 | ሌንስ ከ ሊዮን
የሳውዲ ፕሮ ሊግ
03:00 | አል-ናስር ከ ድሪያህ
የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
09:00 | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከ አዳማ ከተማ
10:00 | ሀላባ ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
04:00 | ማላጋ ከ ኤስፓኞል
03:30 | ዶርትሙንድ ከ ወርደር ብሬመን
03:45 | ሌንስ ከ ሊዮን
የሳውዲ ፕሮ ሊግ
03:00 | አል-ናስር ከ ድሪያህ
09:00 | ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከ አዳማ ከተማ
10:00 | ሀላባ ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
13 hours ago
“ ከሊቨርፑል ጋር መጫወት ሁልጊዜም የተለየ ነው ” ሀላንድ
የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ የእሁዱ የሊቨርፑል ጨዋታ የተለየ ጨዋታ መሆኑን ተናግሯል።
“ ከሊቨርፑል ጋር መጫወት ሁልጊዜም የተለየ ነው ሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተለዩ ናቸው "ሲል ሀላንድ አስተያየቱን ሰጥቷል።
በአንፊልድ ስታዲየም መጫወት የተለየ መሆኑን የገለፀው ሀላንድ “ እዛ ሄጄ ሽንፈትንም ማሸነፍንም አቻንም አይቼዋለሁ ”ብሏል።
ስለ ማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች የተናገረው ሀላንድ “ በህይወት ውስጥ ምንም ቢፈጠር በጋራ መቆም አለብን “ ሲል ገልጿል።
@tikvahethsport kidusyoftahe

16 hours ago
ማክስ ዶውማን ሦስት የጊነስ የዓለም ክብረ ወሰኖችን ተረከተለት ፦
⭐ በቻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ ጨዋታ ላይ የተሰለፈ ትንሹ ተጫዋች — 15 ዓመት ከ308 ቀናት።
⚽ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ግብ ያስቆጠረ ትንሹ ተጫዋች — 16 ዓመት ከ73 ቀናት።
🏆 ፕሪሚየር ሊጉን ያሸነፈ ትንሹ ተጫዋች — 16 ዓመት ከ144 ቀናት።

20 hours ago
ውድ ዋጋ ያላቸው የፕሪሚየር ሊግ ምርጥ 11 !
→ ከአርሰናል 5 ተጨዋች
→ ከማንችስተር ሲቲ 4 ተጨዋች
→ ከሊቨርፑል 1 ተጨዋች
→ ከቸልሲ 1 ተጨዋች
@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
→ ከአርሰናል 5 ተጨዋች
→ ከማንችስተር ሲቲ 4 ተጨዋች
→ ከሊቨርፑል 1 ተጨዋች
→ ከቸልሲ 1 ተጨዋች
@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በእግር ኳሱ ዓለም "ይህ ገና ጅምር ነው" የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ እንደተራ የተስፋ ቃል ሲወረወር ይሰማል፤ ከሚኬል አርቴታ አንደበት ሲወጣ ግን የልብ ትርታን የሚያደምቅ የእውነተኛ ራዕይ ነጸብራቅ ሆኖ ይስተጋባል። የሰሜን ለንደኑን ታላቅ ክለብ አርሰናልን ከእንቅልፉ ቀስቅሶ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ያደረገው ስፔናዊው አሰልጣኝ፣ በኤምሬትስ ስታዲየም እስከ 2030 ዓ.ም. ድረስ የሚያቆየውን አዲስ እና የተሻሻለ ኮንትራት በይፋ ፈርሟል።
ከቢቢሲ ስፖርት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአዲሱ ስምምነት መሠረት የአርቴታ ደመወዝ ከነበረበት በዓመት £10 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍ ብሎ፣ ተጨማሪ የ£5 ሚሊዮን ፓውንድ ማበረታቻዎችን (ቦነስ) ያካተተ ሆኗል። ይህ አሃዝ አርቴታን በዓለም ላይ ከፍተኛ ክፍያ ከሚያገኙት እንደ አትሌቲኮ ማድሪዱ ዲዬጎ ሲሞኔ እና የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተርታ የሚያሰልፈው ነው።
"ልዩ የሆነ ማሰሪያ"
የ44 ዓመቱ አርቴታ በታህሳስ 2019 ወደ ክለቡ ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ ያሳለፈውን ጊዜ ሲያስታውስ፣ ቃላቱ በጥልቅ ስሜት የታጀቡ ነበሩ። "ይህ ክለብ ልዩ ነው፤ ባህሪው እና በውስጥህ የሚፈጥረው ስሜት ወደር የለውም። አብረን የጀመርነው ጉዞ በመቀጠሉ ትልቅ ክብር ይሰማኛል" ሲል ተናግሯል።
ባለፈው የውድድር ዘመን አርሰናልን ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ማድረግ የቻለው አርቴታ፣ በግንቦት ወር በፓሪስ ሴንት-ዠርሜን ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ላይ የደረሰበት መሪር ሽንፈት ይበልጥ እንዳጠነከረው ይታመናል። "ቀድሞውንም ቢሆን የህይወት ዘመን ትዝታ የሚሆኑ አፍታዎችን ፈጥረናል፤ በጣም የሚያስደስተው ግን፣ ገና ብዙ ታሪክ ለመስራት ይህ መጀመሪያችን መሆኑ ነው" ሲል አርቴታ የወደፊት ተስፋውን ገልጿል።
የስርወ-መንግስት ግንባታ
ይህ የአርቴታ አዲስ ፊርማ ድንገተኛ አልነበረም። የቀድሞው ኮንትራቱ በዘንድሮው የውድድር ዘመን መጨረሻ ላይ የሚያበቃ መሆኑ፣ የድርድር ሂደቱ ላይ መጠነኛ ፍጥነት እንዲኖር አድርጎት ነበር እንጂ፣ አርቴታ ከክለቡ ለመለየት አስቦ አያውቅም። የእርሱ ዋነኛ የልብ ትርታ፣ በአርሰናል ውስጥ ጠንካራ እና የማይበገር የእግር ኳስ ስርወ-መንግስት (Dynasty) መገንባት ነው።
የክለቡ የጋራ ሰብሳቢዎች የሆኑት ስታን እና ጆሽ ክሮንኬም ይህንን እውነት በሚገባ ተረድተውታል። "ከሚኬል ጋር ልዩ የሆነ ቁርኝት አለን። በ2019 ወደ ክለቡ ከተመለሰ ጊዜ ጀምሮ ባስመዘገብነው ውጤት እጅግ እንኮራለን። እርሱ የአርሰናልን እሴቶች በሚገባ የተረዳ እና በልቡ የተሸከመ ሰው ነው" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
አርቴታ የገነባው ታላቅ ቡድን በአውሮፓ እግር ኳስ መድረክ ላይ አንጸባራቂ ኮከብ ሆኖ ብቅ ብሏል። የአሰልጣኙ መቆየት ደግሞ የዚህን የድል ጉዞ መሰረት ይበልጥ ያጸናዋል። አርሰናል በታሪክ ማህደሩ ላይ አዳዲስ እና ደማቅ ምዕራፎችን ለመጻፍ ዝግጁ ነው፤ አርቴታም ይህንን ጉዞ ከፊት ሆኖ ለመምራት ቃል ኪዳኑን አድሷል። ታሪክስ ምን ይዞ ይሆን? ጊዜ የሚመልሰው ይሆናል።
የመድፈኛው ደጋፊ በአርቴታ መቆየት ምን ተሰማችሁ?

Sponsored by
Surafel
3 days ago
አርሰናል ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች ይፋ ሆነዋል። ✅
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
7 days ago
#official
የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋች እና አሰልጣኝ እጩዎች ታውቀዋል።
ማን ያሸንፋል ???

የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት የብራይተን አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ተመርጠዋል።
አሰልጣኙ ቡድኑን እየመሩ በወሩ ካደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።
ብራይተኖች በዚህ ወር ምርጥ ተጨዋች ፣ አሰልጣኝ እና የወሩ ምርጥ ጎል ሽልማቶችን መውሰድ ችለዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 2026/27 የውድድር ዘመን የመስከረም ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ይፋ ሆነዋል። በዚህም መሰረት :- ⏩ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር ⏩ አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ እና ⏩ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በእጩነት ቀርበዋል። @Tikvahethsport kidusyoftahe

8 days ago
🚨 የሊቨርፑል ደጋፊዎች ከብሔራዊ ቡድን እረፍቱ በኋላ የሚደረገውን ትልቁን የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ ከወዲሁ በጉጉት እየጠበቁ ነው።
በማህበራዊ ሚዲያ ያሉ ደጋፊዎች በአንፊልድ እጅግ ጠንካራ TIFO እና ከባድ የስታዲየም ድባብ እንደሚኖር እየጠበቁ ነው።
ብዙዎቹ ደጋፊዎች በማንቸስተር ሲቲ የፋይናንስ ጥሰቶች ተፈጽመዋል በተባለበት ዘመን ከአንድ በላይ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን እንደተነጠቁ ይሰማቸዋል።
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
በማህበራዊ ሚዲያ ያሉ ደጋፊዎች በአንፊልድ እጅግ ጠንካራ TIFO እና ከባድ የስታዲየም ድባብ እንደሚኖር እየጠበቁ ነው።
ብዙዎቹ ደጋፊዎች በማንቸስተር ሲቲ የፋይናንስ ጥሰቶች ተፈጽመዋል በተባለበት ዘመን ከአንድ በላይ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን እንደተነጠቁ ይሰማቸዋል።
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et
9 days ago
"እኔ ቆምኩ አልቆምኩ የሚመጣ የውጤት ለውጥ የለም" - አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
#ethiopia | አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በቅርቡ ትናንት ከስፖርት ጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በቡድናቸው አጨዋወት፣ በሜዳ ላይ በሚያሳዩት እንቅስቃሴ እና በግብ ማስቆጠር ችግሮች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ በጨዋታ 90 ደቂቃ ውስጥ ከወንበራቸው ተነስተው መመሪያ ሲሰጡ ለምን እንደማይታዩ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ይህ የራሳቸው የቆየ አሰራር መሆኑን ገልጸዋል።
በልምምድ ወቅት በቂ ዝግጅት እንደሚሰሩና በጨዋታው ወቅት ተጫዋቾቹ የተማሩትን እንዲተገብሩ ነጻነት እንደሚሰጧቸው ያስረዱት አሰልጣኙ፣ ጣልቃ የሚገቡት ታክቲካዊ ስህተቶች ሲፈጠሩ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም አጋዥ አሰልጣኙ በዚሁ ሂደት ውስጥ የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ቡድኑ ተደጋጋሚ የግብ ማስቆጠር ችግር ለምን እንደገጠመው ለተነሳላቸው ጥያቄ፣ ችግሩ እድል ከመፍጠር ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ አብራርተዋል። ቡድኑ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በተደጋጋሚ እንደሚደርስ የገለጹት አሰልጣኝ ዮሐንስ፣ ነገር ግን የተፈጠሩትን እድሎች ወደ ግብነት የመቀየር ኃላፊነቱን ተጫዋቾች በአግባቡ እየተወጡ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
በተለይም አንዳንዴ ተጫዋቾች የተሻለ ቦታ ላይ ላለ አጋራቸው ኳስን አሳልፎ ከመስጠት ይልቅ፣ ራሳቸው አግብተው አድናቆትን ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት የግብ እድሎች እንደሚባክኑ ተችተዋል።
በመጨረሻም የግብ አግቢ (ስትራይከር) እጥረትም የብሔራዊ ቡድኑ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ ሀገሪቱ እግርኳስ ችግር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሀገር ውስጥ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አግቢ የሚባሉት ተጫዋቾች እንኳን ከ30 በላይ ጨዋታዎችን አድርገው የሚያስቆጥሩት ከ13 እስከ 14 ግቦችን ብቻ መሆኑን በማንሳት፣ የችግሩን ሀገር አቀፋዊ ስፋትና አሳሳቢነት አመላክተዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ክፉኛ ያናወጠው የማንቸስተር ሲቲ የፋይናንስ ደንብ ጥሰት ቅሌት የስፖርቱን ዓለም ዋነኛ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል። ፕሪሚየር ሊጉ ማክሰኞ ዕለት ይፋ ባደረገው ውሳኔ ክለቡ ከ2009 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ830 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በድብቅ ወደ እግር ኳስ እንቅስቃሴው ለማስገባት ከንግድ አጋሮቹ ጋር "የማስመሰል" ኮንትራቶችን በመፍጠር ጥፋተኛ ሆኖ አግኝቶታል። ክለቡ አሁንም ጥፋት አላጠፋሁም ቢልም፣ በዚህ የዘጠኝ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሶስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ ስምንት ታላላቅ ክብሮችን አሳክቷል።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አምበል ሮይ ኪን በሰጠው አስተያየት፣ በዚያን ጊዜ የተገኘው ድል "በማጭበርበር" የመጣ በመሆኑ የሲቲ ተጫዋቾች ስኬት ዋጋ ቢስ መሆኑን ተናግሯል። ኪን ለ አይቲቪ ስፖርት ሲናገር፣ "እኔ ተጫዋች ብሆን ኖሮ፣ መቶ በመቶ ሜዳሊያዎቹን በቆሻሻ መጣያ ውስጥ እጥላቸው ነበር። ድሉ የተገኘው በማጭበርበር ነው። ብዙዎችን እንደሚጎዳ እያወቁ አድርገውታል" ሲል በቁጣ ተናግሯል።
በሌላ በኩል፣ የቀድሞው የዩናይትድ ኮከብ ዌይን ሩኒ፣ የከተማቸው ተቀናቃኝ የሆነው ሲቲ ዋንጫው ቢነጠቅ እንኳን፣ ዩናይትድ ዋንጫውን በምትኩ ሊቀበል አይገባም የሚል አቋም አንጸባርቋል። እ.ኤ.አ. በ2011/12 የውድድር ዘመን ከሲቲ በመቀጠል ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ሩኒ እና ጓደኞቹ ዋንጫው ቢሰጣቸው ደስተኛ እንደማይሆን ተናግሯል። ሪዮ ፈርዲናንድ እና ዴቪድ ዴህያ ዋንጫው ወደ ዩናይትድ ሊመጣ ይገባል የሚል አንድምታ ያለው ሀሳብ ቢያጋሩም፣ ሩኒ ግን የተለየ እይታ አለው።
"እውነቱን ለመናገር ያንን የፕሪሚየር ሊግ ሜዳሊያ ብቀበል ምቾት አይሰማኝም። በዚያ የውድድር ዘመን ሊጉን ለማሸነፍ የሚያስችል በቂ ስራ አልሰራንም" ያለው ሩኒ፣ "ከ15 ዓመት በኋላ ሲቲ ስላጭበረበረ ብቻ ሜዳሊያ መቀበል አልፈልግም። ጥያቄው ሁለተኛ ስለወጣሁ ሜዳሊያ እፈልጋለሁ ወይ? ነው፤ በፍጹም አልፈልግም" ብሏል።
ምንም እንኳን ሩኒ ሜዳሊያውን ባይፈልግም ማንቸስተር ሲቲ ግን ከባድ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚገባ ያምናል። "ሲቲ ወደ ታችኛው ሊግ ሲወርድ እንደምናይ አስባለሁ" ያለው የ40 ዓመቱ ሩኒ አክሎም፣ "እኔ ብሆን ኖሮ እስከሚችሉት ዝቅተኛ ሊግ አውርጄ፣ ለቀጣዮቹ ሶስት እና አራት ዓመታት በዝውውር ገበያ ላይ ምን ያህል ገንዘብ ማውጣት እንደሚችሉ ጥብቅ ገደብ እጥልባቸው ነበር። ወደ ሻምፒዮንሺፕ ብቻ ማውረድ ትልቅ ቅጣት ቢሆንም ቶሎ ይመለሳሉ፤ ነገር ግን የ20 ነጥብ ቅጣት ለሶስት ተከታታይ አመታት ቢጣልባቸው ተጫዋቾች እዚያ መቆየት አይፈልጉም" በማለት ከባድ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል።
ፕሪሚየር ሊጉ በሲቲ ላይ የሚወስነው የመጨረሻ የቅጣት አይነት ገና ይፋ ያልተደረገ ሲሆን፣ ክለቡም በውሳኔው ላይ ይግባኝ ለማለት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

13 days ago
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጠበቆች ማንቸስተር ሲቲ በ 114 ክሶች ጥፋተኛ ነው ከተባለ በኋላ በባስ ኤቲሃድ ስታድዮም ጋር ሄዶ ደስታቸውን ገልፆዋል።😁😁
@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et
13 days ago
የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ክስ ሊመሰርቱ ነው !
ማንችስተር ሲቲ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ መባሉን ተከትሎ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ወደ ክስ ሊገቡ እየተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።
የተወሰኑ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ቀደም ብለው በሥራቸው የተመሰከረላቸውን ጠበቆች መቅጠራቸው ተነግሯል።
ክለቦቹ ማንችስተር ሲቲ ከተቀጣ ምን መጠየቅ እንደሚችሉ ጠበቆቹን ሲያማክሩ እንደቆዩ ተዘግቧል።
አብዛኞቹ የሊጉ ክለቦች በዚህ ጉዳይ እርስበርስ እየተመካከሩ እንደሚገኙ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

14 days ago
ሰንደርላንድ ወሳኝ ተጨዋቹ ተጎዳ !
ኔዘርላንዳዊው የሰንደርላንደሰ የፊት መስመር አጥቂ ብሪያን ብሮቤይ የ ሀምስትሪንግ ጉዳት አጋጥሞታል።
ተጨዋቹ ኔዘርላንድ ከጀርመን እያደረገች በምትገኘው ጨዋታ በጉዳት ተቀይሮ ወጥቷል።
ብሪያን ብሮቤይ ሰንደርላንድ ከማንችስተር ሲቲ ባደረገው ጨዋታ ሀትሪክ መስራቱ አይዘነጋም።
በተጨማሪም የፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ተመርጧል።
@Tikvahethsport kidusyoftahe

15 days ago
የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 2026/27 የውድድር ዘመን የመስከረም ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ይፋ ሆነዋል።
በዚህም መሰረት :-
⏩ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር
⏩ አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ እና
⏩ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በእጩነት ቀርበዋል።
@Tikvahethsport kidusyoftahe
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 2026/27 የውድድር ዘመን የመስከረም ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ይፋ ሆነዋል።
በዚህም መሰረት :-
⏩ አሰልጣኝ ፋብያን ሁርዜለር
⏩ አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ እና
⏩ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በእጩነት ቀርበዋል።
@Tikvahethsport kidusyoftahe
15 days ago
የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 2026/27 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።
በዚህም መሰረት :-
⏩ ሞሀመድ ቤሎሚ
⏩ ጃይደን ቦግል
⏩ ፓስካል ግሮስ
⏩ አሌክሳንደር አይሳክ
⏩ ጄርሚ ጃክዌት
⏩ ኮስቱላስ
⏩ ኬቪን ሻድ እና
⏩ አንቶይን ሴሜንዮ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 2026/27 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።
በዚህም መሰረት :-
⏩ ሞሀመድ ቤሎሚ
⏩ ጃይደን ቦግል
⏩ ፓስካል ግሮስ
⏩ አሌክሳንደር አይሳክ
⏩ ጄርሚ ጃክዌት
⏩ ኮስቱላስ
⏩ ኬቪን ሻድ እና
⏩ አንቶይን ሴሜንዮ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
15 days ago
Sponsored by
Surafel
17 days ago
ሚኬል አርቴታ ከአርሴናል ጋር የረጅም ጊዜ ውል ስምምነት ላይ ደረሰ
የአርሴናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በኤሚሬትስ የሚቆያውን አዲስ የረጅም ጊዜ ውል ለመፈረም ከአርሴናል ጋር ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሱ ተረጋገጠ።
የ42 ዓመቱ ስፓኒሽ አሰልጣኝ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር ያለው የወቅቱ ውል በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ የሚያበቃ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን በተደረሰው አዲስ ስምምነት መሰረት በክለቡ የመቆየት እድሜውን ወደ አንድ አስርት ዓመት (10 ዓመታት) የሚያጠጋጋው ይሆናል።
አርቴታ በ2019 አርሴናልን ከተረከበ ወዲህ ክለቡን ወደ ድል እና ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ተፎካካሪነት የመለሰ ሲሆን፣ የክለቡ አስተዳደርም በአሰልጣኙ የረጅም ጊዜ ፕሮጀክትና ስኬት ላይ ያለውን ሙሉ እምነት በዚህ አዲስ ውል አጽንቷል።
ውሉ በይፋ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚፈረም ይጠበቃል።

18 days ago
ማንቸስተር ዩናይትድና ፉልሃም 1-1 ተለያዩ
#ethiopia | በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቸስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር 1-1 አቻ ተለያይቷል።
በክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ፣ ፉልሃም በ63ኛው ደቂቃ በማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በራሱ መረብ ላይ በተቆጠረች ግብ መሪነቱን ወስዷል።
ዩናይትድ ግን ጨዋታው ወደ መገባደጃው ሲደርስ በ89ኛው ደቂቃ ማቲያስ ኩኛ ባስቆጠራት ግብ ውጤቱን አመጣጥኗል።
ይህ ውጤት ማንቸስተር ዩናይትድ በአምስት የሊግ ጨዋታዎች ያስመዘገበው ሁለተኛው አቻ ውጤት ሲሆን፣ ቡድኑ በ5 ነጥቦች 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፉልሃም በበኩሉ በውድድር ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ አቻ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን፣ በ1 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
#epl #premierleague #manchesterunited #fulham #matchday #football #sports #ebc

19 days ago
🔴ከመቶ አለቃ ወደ ብርጋዴር ጄኔራል
የፕሪሚየር ሊጉ የስልጣን ሽግግር
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያደርግ የመጨረሻው የስልጣን ሹመት ሽግግርን ከመቶ አለቃ ወደ ብርጋዴር ጄኔራል አድርጎል።
አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ በተከናወነበት የዛሬ ምርጫ
ለቀጣይ 3 አመታት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ዳይሬክተሮች ቦርድና 7 አባላት ምርጫ ተከናውኗል።
በቦርድ አባላት በተደረገ የስራ ኃላፊነት ክፍፍል
የመቻል ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ብ/ጄ ኑሩ ሙዘይን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ አቶ መንግስቱ ታደሰ ከኢትዮጵያ ቡና የዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል።
👉ሰባቱ የሊግ ካምፓኒው አመራሮች
🔴 ብ/ጄ ኑሩ ሙዘይን(መቻል)
🔴 አቶ መንግስቱ ታደሰ(ኢትዮጵያ ቡና)
🔴አቶ ልዑል ፍቃዱ(ባህር ዳር ከተማ)
🔴 አቶ ተስፉ ተክሌ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
🔴 አቶ መንግስቱ አባይነህ(ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
🔴አቶ ታገል ጌታቸው(ሀላባ ከተማ)
🔴 ወ/ሮ ከነዓን በለጠ(ሲዳማ ቡና) በመሆን ተመርጠዋል።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

የሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ጥቆማ!
ስታዲየሞችን በስቱዲዮዋችን!
ዛሬ ከአመሻሽ ⏱ 12:00 ጀምሮ ዞላ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር 'በሞዛይክ ስፖርት' ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ ወደ እናንተ ይደርሳል።
የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ👇
🥅 ክራቨን ኮቴጅ
⚪️ፉልሃም ከ ማንቸስተር ዩናይትድ 🔴
✍ሀሳብ አስተያየት እና ግምታችሁን አጋሩን!

20 days ago
ወርኃዊ 120 ጊ.ባ የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል ገዝተው፤ በነጻ በሚያገኙት የ1 ዓመት ሜዳ ጥቅል የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ዘና ብለው ይመልከቱ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_Su... በመጫን አሁኑኑ ይመዝገቡ!
ቴሌብር - እጅግ ፈጣን፣ ቀላል፣ ምቹ እና አስተማማኝ
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነንየሻሞ

ቼልሲ በብሬንትፎርድ 3 ለ 0 ተሸነፈ
**************
በአምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ጂቴክ ኮሚዩኒቲ ስታዲየም አቅንቶ ብሬንትፎርድን የገጠመው ቼልሲ 3 ለ 0 ተሸንፏል።
ቼልሲ በውድድር ዓመቱ ለ2ኛ ጊዜ በተረታበት ጨዋታ የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች ጄደን አንቶኒ፣ ኢጎር ቲያጎ እና ፋቢዮ ካርቫዮ አስቆጥረዋል።
ቼልሲ ከአምስቱ ጨዋታዎች ለሁለተኛ ጊዜ መሸነፉን ተከትሎ በሰባት ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ፣ ሁለተኛ ድሉን ያሳካው ብሬንትፎርድ በዘጠኝ ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
#epl #premierleague #chelsea #brentford #football #sports #ebc

21 days ago
21 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ማክሰኞ ዕለት ማንቸስተር ዩናይትድን ለመልቀቅ በይፋ ደብዳቤ ያስገባው የጄጄ ገብርኤል ውሳኔ፣ በእግር ኳሱ ዓለም ያልታሰበ ማዕበል ፈጥሯል። ገና በ15 ዓመቱ በአውሮፓ ከሚገኙ እጅግ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች አንዱ ተብሎ የሚታሰበው ይህ ድንቅ አጥቂ፣ ከዘጠኝ ዓመቱ ጀምሮ ያሳለፈበትን ክለብ ለመሰናበት ቋምጧል፤ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦችም እሱን ለመጥለፍ አሰፍስፈዋል።
ሪያል ማድሪድ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ በጥሩ ቁመና ላይ ሲገኝ፣ ባርሴሎና፣ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን እና ባየር ሙኒክም ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ነው። ዩናይትዶች ልጁን ለማቆየት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ ነገሮች ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ይመስላሉ። ገብርኤል ባለፈው ሀሙስ በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ከ19 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር በዩኤፋ የወጣቶች ሊግ ሀትሪክ ከሰራ በኋላ ወደ ስፍራው ድርሽ አላለም፤ አሁን ባለው ሁኔታም ይመለሳል ተብሎ አይጠበቅም። በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ዩናይትድ ወደፊት 100 ሚሊዮን ፓውንድ ሊያወጣ የሚችልን አልማዝ በገዛ እጁ እያጣ መሆኑን ይገምታሉ።
ይህ ውሳኔ ድንገት የመጣ አይደለም። የችግሩ ጭላንጭል የታየው ባለፈው ሀሙስ ነበር። ገብርኤል በኦልድ ትራፎርድ በሻምፒዮንስ ሊግ ከሚጫወተው ዋናው ቡድን ጋር ከመሰለፍ ይልቅ፣ ከአዘርባጃኑ ሳባህ ጋር ለሚጫወተው የ19 ዓመት በታች ቡድን እንዲሰለፍ ተደረገ። በጨዋታው ሶስት ግቦችን ቢያስቆጥርም፣ እሱና ቤተሰቡ ግን የሻምፒዮንስ ሊግ ድባብን በዋናው ቡድን ውስጥ ሆኖ እንዲቀምስ ፈልገው ነበር። ይህ ክስተት ትልቅ ስብራት ፈጠረ፤ ውሳኔውም ወዲያውኑ ለክለቡ ተነገረ። ቅዳሜ ዕለት ከዋናው ቡድን አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ጋር ልምምድ ማድረግ ሲገባው፣ ከካሪንግተን በመቅረት ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደወል አቃጨለ። ወዲያውም ከኢንስታግራም ገጹ ላይ ስለ ዩናይትድ የሚገልጹ መረጃዎችን በሙሉ አጠፋ። ሰኞ ዕለት ደግሞ ምዝገባው እንዲሰረዝለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለክለቡ አስገባ። የማንቸስተር ዩናይትድ ኃላፊዎች፣ በተለይም ዋና ስራ አስፈፃሚው ኦማር ቤራዳ እና አብሮ ባለቤቱ ሰር ጂም ራትክሊፍ በጉዳዩ ክፉኛ ተደናግጠዋል።
ሪያል ማድሪድ ይህንን ታዳጊ ለማስፈረም በስውር ሲሰራ ወራት አልፈውታል። ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ፣ የፊፋን ጥብቅ ህጎች ላለመጣስ ሲባል ክለቡ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓል። የማድሪድ እቅድ ልጁን መጀመሪያ ለካስቲላ (የማድሪድ ሁለተኛ ቡድን) እና ከ19 ዓመት በታች ቡድን እንዲጫወት አድርጎ፣ ቀስ በቀስ ወደ ዋናው ቡድን ማሳደግ ነው። ይህ ከዚህ ቀደም በአያክሱ የ17 ዓመት ታዳጊ አብደላ ኦዋዛኔ ላይ ሊሞክሩት ያሰቡት ዓይነት ስልት ነው። የማድሪድ ሰዎች የገብርኤልን የሀሙስ ዕለት ሀትሪክ በቅርበት ሲከታተሉና ሲያከብሩ ነበር።
በህግ አግባብ ዩናይትድ የልጁን ውል የመቀደድ ፍላጎት የለውም። ነገር ግን ገብርኤል የአውሮፓ ህብረት ፓስፖርት ካገኘ፣ ልክ ጥቅምት 6 ቀን 16 ዓመት ሲሞላው ወደ ሌላ የአውሮፓ ክለብ መዘዋወር ይችላል። አባቱ ጆ ኦኬሩይል የተወለደው ለንደን ቢሆንም ለአየርላንድ ብሄራዊ ቡድን ተጫውቷል፤ እናቱም የሳይፕረስ ትውልድ አላት። ይህ ደግሞ ፓስፖርቱን በቀላሉ እንዲያገኝ በር ይከፍትለታል። ከዚህም ባሻገር፣ ገብርኤል መደበኛ የትምህርት ቤት ትምህርቱን በቤት ውስጥ የሚከታተል በመሆኑ፣ በዩናይትድ ሙሉ ጊዜ አካዳሚ ስር አይወድቅም፤ ይህም ክለቡ በልጁ ላይ ያለውን ሙሉ ቁጥጥር ያላላዋል። ገብርኤል ዩናይትድን የሚለቅ ከሆነ፣ ፊፋ ባስቀመጠው የካሳ ስሌት መሰረት ዩናይትድ ከ100,000 ፓውንድ በላይ የማሳደጊያ ካሳ ሊያገኝ ይችላል።
ገብርኤል ገና በዘጠኝ ዓመቱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ላይ ሲወጣ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ይነጻጸር ነበር። ነገር ግን የእሱ ተወዳጅ ተጫዋች ኔይማር ሲሆን፣ ኳስን አጣብቆ የመያዝ፣ ፈጣን እንቅስቃሴ የማድረግ እና በሁለቱም እግሮቹ ግሩም አጨራረስ ያለው በመሆኑ የጨዋታ ስታይሉ ከብራዚላዊው ኮከብ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። በዩናይትድ የዋናው ቡድን ልምምዶች ላይ በተደጋጋሚ በመሳተፍ፣ አንጋፋ ተጫዋቾችን ሳይቀር በቴክኒክ ብቃቱ አስገርሟል። በአካላዊ ጥንካሬ ከእሱ በሚበልጡ ተጫዋቾች ቢገፋም፣ በተፈጥሮ ያገኘው ክህሎት ወደፊት ከዓለማችን ምርጥ ተጫዋቾች ተርታ እንደሚያሰልፈው ብዙዎች ይስማሙበታል። ባለፈው ታህሳስ በኤፍኤ የወጣቶች ዋንጫ ለዩናይትድ በመሰለፍ እና ግብ በማስቆጠር ታሪካዊ ሪከርድ ሰብሯል፤ በወጣቶች ሊግ ባደረጋቸው 34 ጨዋታዎችም 31 ግቦችን እና 6 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ዩናይትድ ታዳጊዎችን ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ ታላቅ ታሪክ አለው። "በቂ ብቃት ካለህ፣ በቂ ዕድሜ አለህ" የሚለው የሰር ማት ባስቢ ብሂል ክለቡን ለዘመናት መርቶታል። ገብርኤልም የዚህ ታሪክ ቀጣይ አካል ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ነገር ግን በቅርብ ጊዜ የተፈጠሩ ክስተቶች ጥርጣሬን አጭረዋል። በክረምቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ በቂ የመጫወት ዕድል አላገኘም፤ በአትሌቲኮ ማድሪዱ ጨዋታ ከተፈጥሮ ቦታው ውጪ እንዲጫወት ሲደረግ፣ አዲሱ ፈራሚ የ18 ዓመቱ ታይናን ቶምሰን ግን በገብርኤል ተወዳጅ ቦታ በግራ ክንፍ ላይ የመሰለፍ ዕድል አግኝቷል። በሻምፒዮንስ ሊግ የ'ኤ' ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት መቅረቱም ሌላው ቅር ያሰኘው ጉዳይ ነው። አርሰናል የ15 ዓመቱን ማክስ ዶውማንን በዝርዝሩ ውስጥ አካቶ ክብረ ወሰን ሲሰብር፣ የገብርኤል ስም ግን አልነበረም። አላማው በቋሚነት መሰለፍ ሳይሆን፣ ክለቡ በእሱ ላይ ያለውን እምነት በተጨባጭ ማየት ነበር።
ባለፈው ክረምት ማንቸስተር ሲቲ ገብርኤልን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ የዩናይትድ የስፖርት ዳይሬክተር ጄሰን ዊልኮክስ እና የድርድር ዳይሬክተሩ ማት ሀርግሪቭስ ጣልቃ ገብተው አክሽፈውት ነበር። ወደ ሌላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ማምራቱ በህግ አግባብ እጅግ ፈታኝ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ዩናይትድ ልጁን ለማሳመን ከቀድሞው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እና ከታላቁ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር ጭምር አገናኝቶታል። ማይክል ካሪክ በቅርበት ያሰለጠነው ሲሆን፣ የዋናው ቡድን ማሊያ ቁጥር 77ም ተሰጥቶታል።
አሁን ላይ ዩናይትዶች በቀጣዩ ወር 16ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ሲያከብር የማበረታቻ የትምህርት ኮንትራት እና በ17 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ውል ለማቅረብ እየተዘጋጁ ነበር። በፋይናንስ አቅርቦት ማንም ክለብ እንደማይበልጣቸው ያምናሉ። ነገር ግን የገብርኤል ውሳኔ የተቆረጠ ይመስላል፤ ስለዚህ ዩናይትድ ውጤቱን በትዕግስት ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም። አርብ ዕለትም ክለቡ ለቀረበው የምዝገባ ስረዛ ደብዳቤ ይፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

23 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በእግር ኳሱ ዓለም ገና በለጋ እድሜያቸው የኮከብነት ብርሃን ከሚፈነጥቁ ታዳጊዎች መሀል፣ የ15 ዓመቱ ጄጄ ገብርኤል በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ሆኖም ማንቸስተር ዩናይትድ ይህንን የነገ ተስፋውን በእጁ ለማቆየት እጅግ ፈታኝ በሆነ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ገና የ14 ዓመት ታዳጊ እያለ ያለፈውን የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊግ ከ18 ዓመት በታች ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን የጠራረገው ይህ ድንቅ ታዳጊ፣ በአሁኑ ሰዓት ከክለቡ ጋር ያለውን ውል በአስቸኳይ ለማቋረጥ ይፋዊ ጥያቄ አቅርቧል።
ክለቡን ይህን ያህል እንቅልፍ ያሳጣው የዚህ ታዳጊ የእግር ኳስ ተሰጥኦ ቀላል አይደለም። ዩናይትዶች ገብርኤልን በእጃቸው ለማቆየት ሲሉ በክብር እንግዶች ስፍራ ከቤተሰቦቹ ጋር ጨዋታ እንዲያይ ከማድረግ ባለፈ፣ ከታላቁ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር ጭምር አገናኝተውታል። አንድ የዩናይትድ የውስጥ አዋቂ ታዳጊውን "በአውሮፓ ምርጡ የ15 ዓመት ታዳጊ" ሲል የገለጸው ሲሆን፣ የቀድሞው ጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር ደግሞ ዓለም በእጁ ላይ እንዳለች በመግለጽ አሞካሽቶታል። ምንም እንኳን በሰውነት አቋሙ ገና ያልጎለበተ ቢሆንም፣ ፈጣን እግሮቹ፣ አስገራሚ ቴክኒኩ እና ተከላካዮችን ፊት ለፊት ተጋፍጦ የማለፍ ድፍረቱ ከእድሜው በላይ ልዩ ያደርገዋል። ባለፈው ሳምንት በዩኤፋ የወጣቶች ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታው ላይ ሀትሪክ የሰራ ሲሆን፣ የክለቡን የፕሪሚየር ሊግ 2 ቡድን ከተቀላቀለም በኋላ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች እጅግ ማራኪ ጎሎችን አስቆጥሯል።
ነገር ግን ነገሮች እንዴት ወደዚህ ውድቀት አመሩ የሚለው ጉዳይ አከራካሪ ሆኗል። ዋና ስራ አስፈፃሚው ኦማር ቤራዳ እና የእግር ኳስ ዳይሬክተሩ ጄሰን ዊልኮክስ ከታዳጊው ቤተሰቦች ጋር ቀጥተኛ ድርድር ውስጥ ቢገቡም፣ የገብርኤል እና የዩናይትድ ግንኙነት የሻከረው በተከታታይ በተፈጠሩ ክፍተቶች ነው። ታዳጊው በቅድመ-ውድድር ዝግጅት ወቅት የተጫወተው በአትሌቲኮ ማድሪድ ጨዋታ ላይ ለ8 ደቂቃዎች ብቻ ነበር። በዚህም ጨዋታ በኡራጓያዊው ሆሴ ማሪያ ሂሜኔዝ ጠንካራ ታክል የተደረገበት ሲሆን፣ ሌሎች የአካዳሚ አጋሮቹ እና በቅርቡ ከቶተንሃም የመጣው ታይናን ቶምፕሰን የተሻለ የመሰለፍ እድል ማግኘታቸው ቅሬታን ፈጥሯል። ከዚህም በላይ በቻምፒየንስ ሊግ ዩናይትድ ሳባህ ኤፍኬን ሲረታ ገብርኤል በካሜራው አልነበረም፤ ከ16 ዓመት በታች በመሆኑ በ'A' ሊስት ውስጥ ባለመመዛገቡ በ1956 ዴቪድ ጋስኬል ያስመዘገበውን "የዩናይትድ የምንግዜም ወጣት ተጫዋች" ክብረ ወሰን የመስበር ታሪካዊ ዕድል አምልጦታል።
ይህ ሁሉ ውዝግብ የዩናይትድን ደጋፊዎች ወደ 2012 የፖል ፖግባ ትዝታ እየወሰዳቸው ነው። በወቅቱ የ19 ዓመት ታዳጊ የነበረው ፖግባ በቂ የመሰለፍ ዕድል ባለማግኘቱ ክለቡን ለቆ ወደ ጁቬንቱስ ማምራቱ እና ዩናይትድ ከዓመታት በኋላ የራሱን ታዳጊ መልሶ ለማምጣት 89 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ለማድረግ መገደዱ ይታወሳል። አሁንም ገብርኤል በጥቅምት 6 የ16ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ሲያከብር ውሉን ለማቋረጥ ከተፈቀደለት፣ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች እሱን ለመጥለፍ ወረፋ መያዛቸው አይቀርም። ማንቸስተር ዩናይትድ ይህንን ድንቅ ታዳጊ ቢያጣው፣ በድጋሚ እንደ ፖግባ ዘመን በከፍተኛ ዋጋ ተጫዋቹን መልሶ ለመግዛት የሚገደድ እና በጸጸት የሚኖር ታሪክ ዳግም ሊደገም ይችላል።

አርሰናል ወደ ካራባዎ ካፕ 4ኛ ዙር ተሸጋገረ
የ16 ዓመቱ ማክስ ዳውማን አንፀባራቂ ብቃት — ድንቅ ምሽት!
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ — ኢትዮጵያ
#ethiopia | በፖርትማን ሮድ ስታዲየም በተደረገው የካራባዎ ካፕ 3ኛ ዙር ጨዋታ አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን 4–2 በማሸነፍ ወደ 4ኛው ዙር ተሸጋግሯል። በጨዋታው የተለየ ትኩረት የሳበው ግን 16 ዓመቱ የአርሰናል ወጣት ኮከብ ማክስ ዳውማን ነበር።
ዳውማን በ7ኛው ደቂቃ ከግማሽ ሜዳ አካባቢ ኳሱን ይዞ በፍጥነት ወደ ኢፕስዊች የግብ ክልል በመግባት ተከላካዮችን አልፎ በማስደነቅ የአርሰናልን የመጀመሪያ ግብ አስቆጠረ። ከዚያም በ47ኛው ደቂቃ ሁለተኛ ግቡን በማስቆጠር የራሱን የመጀመሪያ የሁለት ግብ ጨዋታ አሳክቷል።
ይህም ዳውማንን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በአንድ ጨዋታ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረ ሁለተኛው 16 ዓመት ተጫዋች እንዲሆን አድርጎታል፤ ከእርሱ በፊት ይህን ያደረገው ዌይን ሩኒ እ.ኤ.አ. በ2002 ነበር።
አርሰናል ከዳውማን ሁለት ግቦች በተጨማሪ በኖኒ ማዱዌኬ እና ሚኬል ሜሪኖ ግቦች የ4–0 መሪነት አግኝቶ ነበር። ማዱዌኬ በ16ኛው ደቂቃ ሁለተኛውን ግብ ሲያስቆጥር፣ ሜሪኖ ደግሞ በ58ኛው ደቂቃ አራተኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ኢፕስዊች ታውን ግን በቀላሉ እጅ አልሰጠም። አኒስ መህሜቲ በ62ኛው ደቂቃ አንድ ግብ ሲያስቆጥር፣ የቀድሞ የአርሰናል የአካዳሚ ተጫዋች ቹባ አክፖም በተጨማሪ ጊዜ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሮ የውጤቱን ልዩነት ወደ 2–4 አጥብቧል።
የአርቴታ የወጣቶች ዕድል
ሚካኤል አርቴታ ከሳምንቱ መጨረሻ የሱንደርላንድ 2–0 ድል ጋር ሲነፃፀር 9 ለውጦችን በማድረግ በኢፕስዊች ላይ የተለየ ስብስብ አሰልፏል። በዚህም በርካታ ወጣት ተጫዋቾች የመድረኩን ዕድል አግኝተዋል።
በተለይ 17 ዓመቱ ማርሊ ሳልሞን በመከላከያ ክፍል ጎልቶ የታየ ሲሆን፣ የወጣቱ ተጫዋች የመድረክ መዳመጥ እና የኳስ ቁጥጥር ትኩረት ስቧል።
አርቴታም ስለ ዳውማን ብቃት ሲናገር የወጣቱ ተጫዋች በሜዳ ላይ የሚያሳየውን ችሎታ እንደሚያስደስተው ገልጾ፣ እድገቱ በጥንቃቄ መመራት እንዳለበት አመልክቷል።
በመጨረሻም የፖርትማን ሮድ ምሽት ለአርሰናል ከውድድሩ ቀጣዩን ዙር ከማለፍ በላይ የቡድኑን የስብስብ ጥልቀት እና የአካዳሚውን የወጣት ተጫዋቾች አቅም ያሳየ ሆኗል።
በተለይ የ16 ዓመቱ ማክስ ዳውማን ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ያሳየው አንፀባራቂ ብቃት የምሽቱ ዋና ትዝታ ሆኖ ቀርቷል።
አበቃሁ!

24 days ago
ሁለቱም ዳኞች ከፕሪሚየር ሊጉ ታገዱ!
#ethiopia | በማንቸስተር ደርቢ የቪዲዮ ረዳት ዳኛ የነበሩት ማት ዶኖሁ እና ብሌክ አንትሮቡስ በጊዜያዊነት ከፕሪሚየር ሊጉ ታግደዋል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ ባደረጉት የደርቢ ጨዋታ ላይ በተፈጠረ የዳኝነት ውሳኔ ስህተት ምክንያት በዕለቱ የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) የነበሩት ማት ዶኖሁ እና ረዳታቸው ብሌክ አንትሮቡስ በጊዜያዊነት ከሊጉ ጨዋታዎች መታገዳቸው ታወቀ።
ይህ ከባድ ውሳኔ የተላለፈው የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማህበር ዋና ኃላፊ ሃዋርድ ዌብ እና በስራ አመራር ቦርዱ በተደረገ አስቸኳይ ግምገማ መሆኑ ተገልጿል።
የእገዳው ዋና ምክንያት በማንቸስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድ ያስቆጠረው የማሸነፊያ ግብ ዙሪያ የተወሰነው ውሳኔ ነው።
ግቡ ከመቆጠሩ በፊት ወይም በሂደቱ ውስጥ የነበረውን ጥፋት ቫር ሳያርመው እንዲጸድቅ ማድረጉ ትልቅ የውሳኔ ስህተት መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።
ረዳት ዳኞቹ አጠራጣሪ መሆኑን እያወቁ ጎሉ እንዲጸድቅ ከማድረጋቸው በፊት ዋናው ዳኛ ስክሪኑን እንዲመለከቱ ማድረግ ነበረባቸው ሲል የዳኞች ማህበር ተናግሯል።
ሁለቱ የቫር ዳኞች ለቀጣይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በዋና ዳኝነትም ሆነ በቫር ክፍል እንዳይመደቡ እግድ አውጥቷል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #manchesterderby #premierleague #epl #var #mancity #manutd #erlinghaaland #pgmol #footballnews

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ መካከል በተደረገው የዘንድሮው የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ የቪዲዮ ረዳት ዳኛ በመሆን የመሩት ማት ዶኖሁ እና ረዳታቸው ብሌክ አንትሮቡስ፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ከሚካሄዱት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መታገዳቸው ተገለጸ። ይህ ውሳኔ የተላለፈው የፕሪሚየር ሊጉ የዳኞች ተቋም ዋና ኃላፊ በሆኑት ሃዋርድ ዌብ እና በአመራር ቦርዳቸው ሲሆን፣ ተቋሙ በጨዋታው ላይ ኤርሊንግ ሃላንድ ለማንቸስተር ሲቲ ያስቆጠረውን የማሸነፊያ ግብ በማጽደቅ "የውሳኔ ስህተት" መፈጸሙን አምኖ መቀበሉን ተከትሎ የተወሰነ ነው።
በኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ፣ አጥቂው ሃላንድ በ60ኛው ደቂቃ ከጆስኮ ግቫርዲዮል የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ነበር። ግቡ በመጀመሪያ በሜዳ ላይ ባለው ዳኛ ከጨዋታ ውጭ በሚል ቢሻርም፣ የቫር ዳኞች የዩናይትዱ ፓትሪክ ዶርጉ ጫማ ሃላንድን ከጨዋታ ውጪ እንዳይሆን አድርጎታል ማለት ግቡን አጽድቀውታል። ይሁንና ዋነኛው ውዝግብ የተነሳው፣ በወቅቱ ከጨዋታ ውጪ በነበረ አቋም ላይ የነበረው የሲቲው አማካይ ኤንዞ ፈርናንዴዝ ኳሱን በጭንቅላቱ ለመግጨት ዘሎ በመሞከሩ በጨዋታው ላይ ተጽዕኖ ፈጥሯል ወይስ አልፈጠረም በሚለው ላይ ነው።
የዳኞች ተቋሙ ባወጣው መግለጫ፣ "ኤንዞ ፈርናንዴዝ ኳሱን አለመንካቱ የከጨዋታ ውጭ ህጉን አተረጓጎም በዳኛው ግላዊ እይታ ላይ የሚተው ቢያደርገውም፣ በዚህ አጋጣሚ ግን የቫር ዳኛው የተጫዋቹን የቦታ አቀማመጥ ተጽዕኖ ባለመረዳቱ ዋናው ዳኛ በሜዳ ላይ ባለው ስክሪን ሄዶ እንዲያየው ሊመክረው ይገባ ነበር" ብሏል። ጨዋታውን ማንቸስተር ሲቲዎች በ23ኛው ደቂቃ ፊል ፎደን በቀይ ካርድ ከሜዳ ቢወጣባቸውም አሸንፈው፣ በሊጉ ያደረጓቸውን አራቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ የ100 በመቶ የድል ጉዟቸውን አስጠብቀዋል።
ምንም እንኳን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቴክኖሎጂ (VAR) አጠቃቀምን ቢያዘምንም፣ የመጨረሻው ውሳኔ አሁንም በሰው ልጅ ግላዊ እይታ እና ትርጓሜ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ውዝግቦች ሊወገዱ አልቻሉም። በተለይም እንደ ማንቸስተር ደርቢ ባሉ ትልልቅ ጨዋታዎች ላይ የሚፈጠሩ እንዲህ ዓይነት የዳኝነት ስህተቶች፣ የሊጉን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ከመክተታቸውም ባለፈ ቴክኖሎጂው የጨዋታውን መንፈስ እያበላሸው ነው የሚለውን የደጋፊዎች ትችት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

25 days ago
አርሰናል ጥያቄ አለው
#ethiopia | የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መሪው አርሰናል በሰንደርላንዱ ጨዋታ የተሰጠበትን አወዛጋቢ ፍፁም ቅጣት ምት ተከትሎ ከሊጉ የዳኞች ማህበር ጋር ወደ ውዝግብ ገብቷል።
የክሉቡ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት የዳኛውን ውሳኔ “ተቀባይነት የለውም” ሲሉ በፅኑ የኮነኑ ሲሆን አሁን ላይ መድፈኞቹ የዳኞች ማህበር ሃላፊውን ሀዋርድ ዌብ አግኝተው ስለ ውሳኔው ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።
በጨዋታው ላይ የተሰጠውን ያንን ፍፁም ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ በጥሩ ብቃት ያከሸፈው ቢሆንም የውሳኔው ትክክለኛነት ግን ክለቡን እስከ ከፍተኛ አመራሮችን ጭምር አሳስቧል።
አርሰናል የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ለመቀጠል በሚያደርገው ጉዞ ላይ መሰል የዳኝነት ውሳኔዎች ተፅዕኖ እንዳያሳድሩበት ያለው ስጋት አሁንም በስፖርቱ ዓለም ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቀጥሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ts

Comments