2 days ago
አርሰን ቬንገር ለእግር ኳስ ካበረከቱት አንፃር ምን ቃል ይገልፃቸዋል?
ቬንገር ገንዘብ አይፈልጉም፣ ደግፉኝ አይፈልጉም፣ አልተሳካም ብሎ ምናገባኝን አይፈልጉም……… አንድ ነገር ግን ይፈልጋሉ የኳስ ትክክለኛ አላማ እንዲታወቅ ይፈልጋሉ ኳስ በደጋፊዎች ፈገግታ እንጂ በአሰልጣኞች ውስብስብ ታክቲክ እንዳይለካ ይፈልጋሉ።
እኚህን ፕሮፌሰር እስቲ በአንድ ቃል ግለጿቸው፣ ሚቻል ግን አይመስለኝም!
@Bisrat_Sport_433et

4 days ago
አዲስ ሕይወት ጄኔራል ሆስፒታል ለላንቃ እና ከንፈር መሰንጠቅ የሚሰጠውን ነፃ ህክምና ወደ ሙሉ ማዕቀፍ አሳደገ
አዲስ ሕይወት ጄኔራል ሆስፒታል ከዓለም አቀፉ 'ስማይል ትሬን' እና 'ሪስቶሪንግ ስማይል' ጋር በመተባበር የላንቃ እና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው ህፃናት ሲሰጥ የነበረውን ነፃ የቀዶ ጥገና አገልግሎት በማስፋት ሙሉ የሕክምና ማዕቀፍ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
የዓለም የፈገግታ ቀንን አስመልክቶ ማዕከሉ ከቀዶ ሕክምናው በተጨማሪ የስነ-ምግብ፣ የአነጋገር ማስተካከያ፣ የጥርስ እና የአፍ ንፅህና እንዲሁም የስነ-ልቦና ድጋፍን ያካተተ ነፃ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል ።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሚካኤል ተስፋዬ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት፤ በተያዘው በጀት ዓመት ከ130 በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የቀዶ ሕክምና እንዲሁም ለሌሎች በርካታ ህፃናት ተያያዥ የቴራፒ ህክምናዎችን ለመስጠት ታቅዷል።
ሪስቶሪንግ ስማይል' በበኩሉ በዘንድሮው ዓመት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ 175 ህፃናትን ለይቶ ወደ ህክምና ለማምጣት እየሰራ መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም መኮንን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
የታካሚዎች እና የአጋዥ ቤተሰቦቻቸው ትራንስፖርት፣ ምግብ፣ ማረፊያ እና ሙሉ የሕክምና ወጪ በዓለም አቀፉ 'ስማይል ትሬን' ድርጅት ሙሉ በሙሉ የሚሸፈን መሆኑን የተናገሩት አቶ ቢኒያም፣ የላንቃ እና ከንፈር መሰንጠቅ ሙሉ በሙሉ በህክምና የሚስተካከል እንጂ እርግማን ባለመሆኑ፤ ህብረተሰቡ ችግሩ ያለባቸውን ህፃናት በመደበቅ ፈንታ ወደ ጤና ተቋማት በመውሰድ የነፃ ህክምናው ተጠቃሚ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በሚኪያስ ፀሐዬ
#ዳጉ_ጆርናል

15 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዕይታ) የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና የሰርከስ ጅምናስቲክ ባለሙያዎች አንድ የሚያመሳስላቸው ድንቅ ጠባይ አለ፤ ሁለቱም አየር ላይ ይገለበጣሉ፣ ግን መሬት ላይ ሲያርፉ እግራቸው አይሰበርም። ልዩነቱ የሰርከስ ባለሙያው ሲገለበጥ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ሲጥል፣ ፖለቲከኛው ግን ሲገለበጥ የህዝብን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉ ነው።
ዛሬ በኒውዮርክ ከተማ፣ በ81ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA) ደጃፍ ላይ የታየው ትዕይንት ይህንኑ የፖለቲካችንን የሰርከስ ትርዒት በሚገባ ያሳያል። አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከአስር ዓመታት በኋላ ተገናኝተው ተቃቅፈዋል። አቶ ጌታቸውም በምስሉ ላይ እንደሚታየው፣ ጥርሳቸው እስከ መንጋጋቸው እስኪታይ በደስታ ተሞልተው፣ "ወንድሜን ዶ/ር ቴድሮስን ከአስር ዓመት ገደማ በኋላ በኒውዮርክ ማግኘቴ ትልቅ ደስታ ነው" ብለው ጻፉልን።
አስር ዓመት! ለፖለቲከኛ አስር ዓመት ማለት አንዲት የቡና እረፍት ያህል አጭር ናት። ለኢትዮጵያ ምስኪን እናቶች ግን አስር ዓመት ማለት... አያሌ የጦርነት፣ የምጥ፣ የረሃብ እና የስደት ዘመን ነው። ምስኪኑ የትግራይ ወጣት "አንተም ሙት፣ እኔም ልሙት" ተብሎ እንደ ደረቅ ቅጠል በጦርነት እሳት ሲማገድ፣ መንደሩ ሲፈርስ እና ሚሊዮኖች ሲራቡ፣ የጦርነቱ ጠባሳ ገና ሳይሽር፣ መሪዎቹ ግን በኒውዮርክ ንጹህ አየር እየተነፈሱ፣ ሙሉ ሱፍ ለብሰው ለካሜራ "ቺዝ" ይላሉ። አቤት የሰማይ እና የምድር ርቀት! አቤት የህዝብ እውነታ እና የልሂቃን ቅንጦት!
የፖለቲካችንን ነገር ይበልጥ አስቂኝ የሚያደርገው የአቶ ጌታቸው የትናንት እና የዛሬ ሚና ነው። ትናንት የፌደራል መንግስቱን በጠላትነት ፈርጀው፣ ህዝብን ወደ ጦርነት ሲያመሩ አልነበረም? ዛሬ ደግሞ የዚያኑ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ሹመት ተቀብለው ዲፕሎማሲ ሲሰሩ ማየት፣ ፖለቲካችን ምን ያህል የልብስ ቅያሪ እንጂ የልብ ቅያሪ እንደሌለው ያሳያል። ዶ/ር ቴድሮስም ቢሆኑ፣ በጄኔቫ ሆነው የኢትዮጵያን መንግስት አጥብቀው ሲተቹ እና ሲያወግዙ አልነበሩም? ዛሬ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀኝ እጅ ከሆኑት አቶ ጌታቸው ጋር ሞቅ ያለ የናፍቆት ሰላምታ ሲለዋወጡ፣ "እስስትም የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች ቢያይ ቀለሙን መቀየር ያቆማል" ያሰኛል።
ከዚህ ፎቶግራፍ ተራው ዜጋ የሚማረው አንድ መራራ ሀቅ አለ... የፖለቲካ ልሂቃን ደማቸው አይቃባም፤ ጥቅማቸው ሲነካ ይጣላሉ፣ አቋራጭ ሲያገኙ ደግሞ ይተቃቀፋሉ። እሳቱን የሚያቀጣጥሉት እነሱ፣ ማገዶው ደግሞ በስሜት የሚነዳው ምስኪኑ ህዝብ ነው። ጦርነቱ ሲያልቅ ማገዶው አመድ ይሆናል፤ አቀጣጣዮቹ ግን ኒውዮርክ ሄደው ይተቃቀፋሉ። ስለዚህ የኒውዮርኩ ፈገግታ የትግራይን ብሎም የኢትዮጵያን እናቶች እንባ የሚያብስ አይደለም፤ የልሂቃኑን ምቾት እና ግድየለሽነት በታሪክ መዝገብ ላይ የሚያሰፍር አሳዛኝ የካሜራ ብልጭታ እንጂ።
ከአበጀ በለው

17 days ago
ማስታወቂያ
*******
የአዲስ ዓመት የብርሃን ስጦታ፦ የአይን ብሌንዎን ለመለገስ ቃል ይግቡ!
አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ጅምርና አዲስ ብርሃን ይዞ ይመጣል። በዚህ አዲስ ዓመት ከምናበረክታቸው ስጦታዎች ሁሉ የሚበልጠውና ዘላለማዊ ህያውነት ያለው ስጦታ አንዱን ሰው ከጨለማ ወደ ብርሃን ማውጣት ነው።
በሃገራችን በርካታ ወገኖቻችን በአይን ብሌን ሕመም ምክንያት የቀኑን ብርሃን፣ የወዳጆቻቸውን ፈገግታና የአለምን ውበት ማየት ተስኗቸዋል። ለእነሱ ትልቁ የአዲስ ዓመት ምኞትና ስጦታ ደግሞ ማየት ነው!
በዚህ አዲስ ዓመት የእርስዎን የአይን ብሌን ለመለገስ ቃል በመግባት ለአንድ ወገን የማይጠፋ የብርሃን ስጦታ ያበርክቱ።
ዛሬውኑ ይመዝገቡ፤ የሌሎች ብርሃን ይሁኑ!
መልካም አዲስ ዓመት!

19 days ago
ምስጋና #አርቲስት
አዲስ ከተማ ነው ተወልዶ ያደገው። ለሰፈሩም ሰፈሩ ላበቀለውም «የኛ አዲስ ከቴ እግርኳስ ክለብ» ልዩ ፍቅር አለው፤ የአራዳ ልጅ ምልክት እየተባለ የሚጠራው ለኔ ደሞ ክላስ ሜቴ የነበረው አርቲስት አብረሃም ፀጋዬ — በ«ቤቶች»፣ «ሲስተርሊ ብራዘርሊ» እና «ልጄስን» በተሰኙ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎቹ እንዲሁም በ«ሌዲስ ፈርስት X»፣ «ጥቁር እና ነጭ»፣ «ፈላሺያው» እና «የሰማይ ፈገግታ» ፊልሞቹ የሚታወቅ የጥበብ ሰው ነው። አንባቢ ትውልድን ለማፍራትና ንባብን ለማበረታታት አምስት መጽሐፍትን በአምስት ሺህ ብር ገዝቶ አርአያ ሆኗል፤ እናመሰግናለን!
መፅሀፉን ማግኘት ለምትፈልጉ 0930363882
CBE 1000115018845
Abyssinia 31362587
tele bir 0930363882
(Ahenafi Malet)

25 days ago
ለመላው ውድ የGunners ቤተሰብ…
አንዳንድ ነገሮች በቃላት ብቻ አይገለጹም።
አንዳንድ ፍቅሮች በጊዜ አይለኩም።
አንዳንድ ቤተሰቦችም በደም ብቻ አይገናኙም፤ በአንድ ልብ፣ በአንድ ፍቅር፣ በአንድ ስሜት ይገናኛሉ።
እኛም እንደዚህ ነን።
ከተለያዩ ከተሞች፣ ከተለያዩ ሙያዎች፣ ከተለያዩ የሕይወት መንገዶች መጥተን አንድ ነገር አገናኘን—Arsenal!
ግን ዛሬ የሚያገናኘን ከእግር ኳስ በላይ ሆኗል።
እኛ Arsenalawiyan ተመሳሳይ ልብ አለን፤
ተመሳሳይ ጽናት አለን፤
ተመሳሳይ ታማኝነት አለን፤
ተመሳሳይ ፍቅር አለን።
ድል ሲኖር አብረን እንደሰታለን፤
ፈተና ሲመጣ አብረን እንጸናለን፤
ተስፋ ሲርቅ እንኳን እንደገና እናምናለን።
ምክንያቱም Arsenal ለእኛ 90 ደቂቃ ብቻ አይደለም።
ፍቅር ነው። ጽናት ነው። ታማኝነት ነው። ቤተሰብነት ነው።
ይህን አዲስ ዓመትም በአንድ ቃል ጀምረነዋል፦
“አንድ ሆነን!” 🤝
አንድ ሆነን እንደጋገፋለን።
አንድ ሆነን ደስታችንን እንካፈላለን።
አንድ ሆነን በፈተና ጊዜ እንቆማለን።
አንድ ሆነን ለሚፈልጉን እጃችንን እንዘረጋለን።
አንድ ሆነን ለወጣቶች ዕድል እንፈጥራለን።
አንድ ሆነን ለማህበረሰባችን የሚቀር መልካም ነገር እንሠራለን።
የGunners ቤተሰብነት ጀርሲ በመልበስ ብቻ አይለካም።
አንዱ ለአንዱ በሚዘረጋው እጅ፣
በምንጋራው ፍቅር፣
በምንፈጥረው ዕድል፣
በምንሰጠው ተስፋ፣
እና በምንተወው መልካም አሻራ ይለካል።
Gunners Media ይህን ፍቅር ከስታዲየምና ከ90 ደቂቃ በላይ የሚያደርስ የሁላችንም ቤት ነው።
የምንገናኝበት፣
የምንደጋገፍበት፣
ዕድሎችን የምንፈጥርበት፣
ደስታችንንና ፈተናችንን የምንካፈልበት፣
ከArsenal ፍቅራችን ተነስተን ለማህበረሰባችን መልካም ነገር የምንሠራበት ቤት።
Gunners Media የእናንተ ነው።
የሁላችንም ነው።
ለእናንተም ሁሌም አለ!
ይህ አዲስ ዓመት ለእኛ ቀን መቀየር ብቻ አይደለም።
አዲስ ጉዞ ነው። አዲስ ተስፋ ነው። አዲስ ታሪክ ነው።
በዚህ ዓመት ብዙ እንሠራለን።
ብዙ ሰዎችን እናገናኛለን።
ብዙ ዕድሎችን እንፈጥራለን።
ብዙ ፈገግታዎችን እናያለን።
ብዙ ልቦችን እናስደስታለን።
ብዙ ሕልሞችን እንደግፋለን።
ከሁሉም በላይ ግን—አብረን እንሆናለን።
ምክንያቱም አንድ ሰው ሕልም ማለም ይችላል፤
አንድ ቤተሰብ ግን ሕልምን እውን ማድረግ ይችላል።
ዘንድሮ ተመልካቾች ብቻ አንሆንም—ታሪኩን አብረን እንጽፋለን።
በደስታ ጊዜ አብረን።
በፈተና ጊዜ አብረን።
በድል ጊዜ አብረን።
በሕልማችን ጉዞ ላይ አብረን።
አንድ ሆነን ጀምረናል፤
አንድ ሆነን እንጓዛለን፤
አንድ ሆነን እናሸንፋለን። 🔥
ይህ ዓመት የፍቅር ዓመት ይሁን።
የአብሮነት ዓመት ይሁን።
የመደጋገፍ ዓመት ይሁን።
የስኬት ዓመት ይሁን።
የGunners ቤተሰብ ዓመት ይሁን! 🤍
🔥 ይህ ዓመት የእኛ ነው!
አንድ ሆነን ዓመቱን ጀምረናል… አንድ ሆነን ታሪክ እንሠራለን!
Once a Gunner, Always a Gunner.

Sponsored by
Surafel
25 days ago
“የጉዞዎን ልምድ ከመደበኛ ወደ ልዩ ያሻሽሉ!” የኢትዮጵያ አየር መንገድ CIP Lounge & Terminal Service
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አዲሱን CIP (Commercially Important Person) Lounge & Terminal Service በግል ተሞክሮ ለማየት እድሉን አግኝቻለሁ።
ይህ የኤርፖርት ጉዞ ከመግቢያ እስከ አውሮፕላን በር ድረስ በተቀናጀ አገልግሎት፣ በምቾትና በግላዊ ትኩረት የሚያልፍ የጉዞ ልምድ ነው።
እናንት ያገሬ ልጆች፣ ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
CIP Service ምን ያካትታል?
* የግል ቼክ-ኢን እገዛ — ረጅም ሰልፎችን በማስቀረት ፈጣንና የተቀናጀ አገልግሎት።
* የሻንጣ አስተዳደር ድጋፍ — ከሻንጣ ማስተናገድ ጀምሮ በሂደቱ ሁሉ የሚደረግ እገዛ።
* የጉምሩክና ኢሚግሬሽን ድጋፍ — የተቀናጀና ፈጣን የሰነድ ሂደት።
* CIP Lounge — ምቹና ጸጥተኛ ማረፊያ፣ የምግብና መጠጥ አገልግሎት፣ የባህላዊ ቡና ሥነ-ሥርዓት፣ Quiet Room፣ የስብሰባ ክፍል፣ የጸሎት ክፍሎችና የሻወር አገልግሎት።
* የግል የመሳፈሪያ እገዛ — ከላውንጁ እስከ አውሮፕላኑ በር ድረስ በልዩ መኪና የሚደረግ ሽኝት።
ኢትዮጵያዊ ሆስፒታሊቲ በCIP Lounge
በላውንጁ ውስጥ ከአገርኛና ከዓለም አቀፍ ምግቦች በተጨማሪ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥነ-ሥርዓትና ቆሎ መቅረቡ የጉዞውን ልምድ የበለጠ ልዩ ያደርገዋል።
በዚህ ሁሉ ውስጥ የሚታየው የሰራተኞች ትጋትና ፈገግታ ደግሞ የአገልግሎቱ ዋነኛ ማራኪነት ነው።
ሮዛ ወንደወሰን — Lounge Attendant በትህትናና በትጋት ያደረገችልኝ አገልግሎት ከምቾቱ በላይ የሰው ልጅ እንክብካቤ ምን ያህል የጉዞ ልምድን እንደሚቀይር አሳይቶኛል።
በመጨረሻም በሎሪ እስከ አውሮፕላኑ ድረስ ሸኝተውኝ፣ “መልካም ጉዞ” ብለው በመመኘት ተመልሰዋል።
የCIP Service ዋጋ
መደበኛ ዋጋ፦ $150
የቅናሽ ዋጋ፦ $120
በተጠቀሰው የማስተዋወቂያ ጊዜ ውስጥ
ከኢኮኖሚ እስከ ቢዝነስ ክላስ ድረስ የትኬት ዓይነትዎ ሳይወሰን፣ አገልግሎቱን ለመጠቀም ከበረራዎ በፊት በቂ ጊዜ ማሳወቅ ያስፈልጋል።
በአጠቃላይ፣ CIP Lounge & Terminal Service ለእኔ የተለየ የኤርፖርት ተሞክሮ ነበር። ከረጅም ሰልፍና ከተለመደው የጉዞ ግርግር ርቆ፣ ጊዜን በመቆጠብ፣ በምቾት በመቀመጥና በግላዊ እንክብካቤ ጉዞን መጀመር የሚያስችል አገልግሎት ነው።
የጉዞዎን ልምድ ከመደበኛ ወደ ልዩ ያሻሽሉ።
Ethiopian Airlines CIP Lounge & Terminal Service
በአጠቃላይ፣ CIP Lounge & Terminal Service ለእኔ የተለየ የኤርፖርት ተሞክሮ ነበር። ከተለመደው የጉዞ ሂደት ለየት ያለ ፣ ጊዜን በመቆጠብ፣ በምቾት እና በግላዊ እንክብካቤ ጉዞን መጀመር የሚያስችል ቀልጣፋ አገልግሎት ነው።
ለበለጠ መረጃ
https://www.ethiopianairli...
በአቅራቢያ የሚገኘው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ቢሮ ጎራ ይበሉ
ወይንም
6787 - ይደውሉ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopianairlines #cipservice #ciplounge #flyethiopian #premiumtravel #travelexperience #ethiopia #ethiopianairlines #cipservice #ciplounge #flyethiopian #premiumtravel #ethiopianhospitality #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

27 days ago
የእናቶች እንባ ታበሰ፤ የብዙዎች ቤት በአዲሱ ዓመት በማዕድ ደመቀ!
#ethiopia | «አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት» የበጎ አድራጎት ማህበር በ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት ዋዜማ ያቀደውን ታላቅ የበጎ ሥራ በስኬት አጠናቋል።
በብዙ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ ከ90 በላይ አቅመ ደካማ እናቶች የአዲስ ዓመት ማዕዳቸውን እንዲያሰናዱ ድጋፍ ተደርጓል።
ለእያንዳንዳቸውም፦
3 ሊትር የምግብ ዘይት
5 ኪሎ ጥራት ያለው ዱቄት
በእጃቸው በማድረስ የአዲስ ዓመት ደስታቸውንና ተስፋቸውን ማደስ ተችሏል።
በባዶ ማዕድ ሊያሳልፉ የነበሩ እናቶች ዛሬ ፊታቸው በፈገግታ ተሞልቷል፤ እጆቻቸውንም ወደ ፈጣሪ ዘርግተው ለረዷቸው ሁሉ በረከት ተመኝተዋል።
ውድ አጋሮችና ደጋፊዎቻችን፣
ይህ ታላቅ ስኬት የእናንተ ርኅራኄ፣ ደግነት፣ ሰብአዊነትና ወገናዊ አለኝታነት ውጤት ነው።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ሆናችሁ፣ በገንዘባችሁ፣ በሃሳባችሁና በጸሎታችሁ ከጎናችን ለቆማችሁ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ በእናቶቻችን ስም ከልብ እናመሰግናለን!
ፈጣሪ አብዝቶ ይተካላችሁ!
ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ!
❤️
እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
#አንድ_እንጀራ_ለአንዲት_እናት #ethiopia

28 days ago
በፋንታ መኪና እየተሸለሙ በነፃ ይጓዙ! የት እንምጣ?
🎉 አዲስ አበባ በአዲስ ዓመት ከፋንታ ጋር እየደመቀች ነው! 🎉
ተወዳጁ ፋንታ እንደተለመደው አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በጳጉሜ ወር በሙሉ በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚገኙ ተሳፋሪዎች የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል!
በጉዞው ወቅት ምን ይጠብቅዎታል?
🚌 ነፃ ጉዞ: ከፒያሳ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮ፣ መርካቶ፣ ኮዬ፣ አያት፣ ሱሉልታ፣ ጣፎ፣ ጀሞ፣ ቃሊቲ እና ወደ ሌሎችም አካባቢዎች የሚደረጉ ጉዞዎች ሙሉ በሙሉ ነፃ ናቸው!
🐔 የበዓል ሽልማቶች: በአውቶቡስ ውስጥ በሚደረጉ አዝናኝ ጨዋታዎች ለሚሳተፉ መንገደኞች ዶሮዎች፣ እንቁላሎች እና ሌሎች የበዓል ስጦታዎች ይበረከታሉ።
🎭 መዝናኛ: ከታዋቂ ቲክቶከሮች እና ኮሜዲያኖች ጋር በሚደረጉ ጨዋታዎች፣ ጥያቄዎች እና ቀልዶች ከመነሻ እስከ መድረሻዎ ፈገግታ እንደበራ ይጓዛሉ።
👇 ፋንታ አሁንም “የት እንምጣ?” እያለዎት ነው!
የፋንታ አውቶቡስ ወደ እርስዎ ሰፈር እንዲመጣ ይፈልጋሉ? ያሉበትን አካባቢ አሁኑኑ ኮመንት ላይ ጻፉልን፤ እኛ ወደ እርስዎ እንመጣለን!
መልካም አዲስ ዓመት! ከፋንታ ጋር በነፃ ይጓዙ፣ ይጫወቱ፣ ይሸለሙ!
#fantaethiopia #addisababa #fantafreetransportaddis #enkutatash2019 #fantabusactivation #ethiopiannewyear #fantagiveaway

(ዘ-ሐበሻ መዝናኛ ዜና) ዓለምን ጉድ ያሰኘው የ2022ቱ የዊል ስሚዝ እና የክሪስ ሮክ የኦስካር መድረክ ላይ ግጭት አሁንም የብዙዎች ትውስታ ነው። ሆኖም፣ ዝነኛው ኮሜዲያን አሁን ላይ ትኩረቱን አዲስ ዳይሬክት ወዳደረገው ፊልም እና "ይቅርታ" ወደ ማድረግ አዙሯል።
ዝነኛው ኮሜዲያን እና ተዋናይ ክሪስ ሮክ፣ አራተኛውን የዳይሬክተርነት ሥራውን "Misty Green" የተሰኘ አዲስ ፊልም በቶሮንቶ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ለማስተዋወቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል። በአጋጣሚ ሆኖ የዚህ ፊልም ታሪክ የሚያጠነጥነው አንዲት ሴት የሥራ ባልደረባዋን በጥፊ በምትመታበት ክስተት ዙሪያ ነው፤ ይህም የ2022ቱን የኦስካር መድረክ ጥፊ የብዙዎችን ትውስታ ዳግም ቀስቅሷል።
ፊልሙን በማስተዋወቅ ላይ እያለ ከቫሪየቲ መጽሔት ጋር በነበረው ቆይታ፣ "ወደ ኦስካር መድረክ አቅራቢነት ዳግም ትመለሳለህ ወይ?" የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ክሪስ ሮክ በሰጠው ምላሽ "በፍጹም አልመለስም አልልም፤ ነገር ግን የእኔ ጊዜ ያለፈ ይመስለኛል" በማለት፣ እንደ ኮናን ኦብራያን ያሉ ምርጥ አቅራቢዎች መኖራቸውን አድንቋል። አክሎም ለሽልማት እስካልታጨ ድረስ በስነ-ስርዓቱ ላይ በታዳሚነት እንደማይገኝ እና የመታጨት እድሉም ጠባብ መሆኑን በፈገግታ ገልጿል።
ስለ ዊል ስሚዝ እና ስለተፈጠረው ክስተት አሁን ምን እንደሚሰማው ሲጠየቅ፣ ጉዳዩን ማራዘም እንዳልፈለገ አመላክቷል። "አሁንም ምንም ነገር ባልተፈጠረ ብዬ እመኛለሁ" ያለው ሮክ፣ አሁን ላይ ትኩረቱ በፊልሙ እና በዋና ተዋናይቷ ሮዛሊንድ ኤሌዛር ላይ መሆኑን ተናግሯል። "ዓለማችን በብዙ ችግሮች ተተብትባለች፤ እኛ በመንገዳችን ላይ ቤት አልባ ሰዎችን አልፈን እንሄዳለን። ስለዚህ እኔ ያሳለፍኩት አንድ መጥፎ ቀን ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ችግሮች አኳያ ሲታይ ያን ያህል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው አይደለም" በማለት ሀሳቡን አጠቃልሏል።
ከዚህ ቀደም በ2023ቱ የኔትፍሊክስ ዝግጅቱ ላይ እሱ "ተጎጅ" እንዳልሆነና ጥፊውን በጀግንነት እንደተቀበለው በስፋት አውርቶ የነበረው ሮክ፣ በቅርቡ በማርች 2026 በነበረ አንድ የኦስካር ድህረ-ዝግጅት ላይ ግን ለየት ያለ ሀሳብ አንጸባርቋል። "በይቅርታ ውስጥ ነው የምኖረው፤ እውነተኛ ፍቅር የሚጀምረው ከይቅርታ ነው" ሲል ለኢ ኒውስ ተናግሯል። ይቅርታ ማድረግ የማይችሉ ሰዎች በምድር ላይ እጅግ ምስኪን መሆናቸውንም አክሏል።

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልድ ትራፎርድ ኢፕስዊች ታውንን 5-2 በሆነ አስገራሚ ውጤት ካሸነፈ በኋላ፣ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ስለ ኮቢ ማይኖ ያቀረበው አድናቆት የብዙዎችን የዩናይትድ ደጋፊዎች ልብ የነካ ነበር። ካሪክ የወጣቱን አማካይ ብቃት "እጅግ አስደናቂ" ሲል በከፍተኛ ስሜት አወድሶታል።
በዓለም ዋንጫው ላይ አንድም ደቂቃ ሳይጫወት መቅረቱ ብዙዎችን ቢያስገርምም፣ ከዚያ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ ቋሚ ሆኖ የጀመረው ማይኖ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። አምበሉ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሃት-ትሪክ በሰራበት በዚህ ድንቅ ምሽት፣ ካሪክ የ21 ዓመቱ ወጣት ብቃት እንዳይደበቅ አድርጓል። ይሁን እንጂ፣ ቀድሞው የዩናይትድ ግብ ጠባቂ ቤን ፎስተር የተለየ አመለካከት ነበረው። ፎስተር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዲህ ሲል አስነብቧል፦ "ኮቢን እወደዋለሁ፤ እርሱ የክለቡ የወደፊት ተስፋ ነው፣ ግን ገና እዚያ አልደረሰም። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ በመጀመሪያዎቹ አራት እና አምስት ቋሚ ተሰላፊዎች ዝርዝር ውስጥ እንደማይገባ ግልጽ ነው። ለውሰት ተሰጥቶ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የሚሆንበት፣ በየጨዋታው የሚፈለግበት እና ሀላፊነት የሚወስድበት አንድ ዓመት ቢያሳልፍ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ሊያገኝ የማይችለውን ልምድ ያካብታል።"
ይህ የፎስተር አስተያየት ግን በማህበራዊ ሚዲያ የዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ ጠንካራ ተቃውሞን አስተናግዷል። በርካቶች ማይኖ በእርግጥም በካሪክ ስብስብ ውስጥ "ከመጀመሪያዎቹ አራት ወይም አምስት" ተመራጮች ውስጥ ያለ ጥርጥር መካተት እንዳለበት ያምናሉ። ነገር ግን ይህ እውነት ከሆነ፣ ዩናይትድ በዚህ ክረምት የአማካይ ክፍሉን ለማጠናከር ሲል ከ150 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያፈሰሰባቸው ሦስት ዓለም አቀፍ አማካዮች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ነው? የሚለው ጥያቄ የካሪክ ዋነኛ የቤት ስራ ሆኗል።
ዩናይትድ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ መመለሱ የሚያስከትለውን ጫና ማይክል ካሪክ በቅርቡ በተግባር ማየት ይጀምራል። ቡድኑ ከኤቨርተኑ ጨዋታ ጀምሮ ከመጀመሪያው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እረፍት በፊት በ16 ቀናት ውስጥ 5 ከባድ ጨዋታዎችን ያደርጋል። በካራባኦ ዋንጫ ጉዞውን ከቀጠለ ደግሞ፣ እስከ ገና በዓል ድረስ አንዳችም የመሀል ሳምንት የእረፍት ጊዜ አይኖረውም። በዚህም ምክንያት በተገነባው አዲስ የአማካይ ክፍል ውስጥ የተጫዋቾች ሮቴሽን (ፈረቃ) ማድረግ ግድ ነው።
ካሪክ የቡድኑን አዳዲስ ፈራሚዎች አስመልክቶ ሲናገር ሚዛን (ባላንስ) ወሳኝ መሆኑን ያነሳል። ብራዚላዊው ካሴሚሮ ኮንትራቱ አልቆ ሲለቅ፣ ጉዳት ያስተናገደው ማኑኤል ኡጋርቴ ደግሞ እስከ ቀጣዩ ዓመት ከሜዳ ይርቃል። ማይኖ፣ ፈርናንዴዝ እና ሜሰን ማውንት ብቻቸውን ሲቀሩ ዩናይትድ ወደ ገበያ ወጥቶ ብራዚላዊውን አንድሬ ሳንቶስን ከቼልሲ በ48 ሚሊዮን ፓውንድ፣ በማግስቱ ደግሞ የ29 ዓመቱን ቤልጄማዊ ዩሪ ቴሌማንስን ከአስቶን ቪላ በ35 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈረመ።
ካሪክ በአየርላንድ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ ሳንቶስን ሲያሞካሽ፣ "አንድሬ ገና ወጣት ቢሆንም ያለው ስብዕና እና ብስለት እጅግ አስደናቂ ነው። ቶሎ ለመማር ዝግጁ ነው፤ አብረውት ያሉትን ተጫዋቾች ይረዳል፣ በሜዳ ላይም በሚገባ ያወራል። ዩሪ ደግሞ በፕሪሚየር ሊጉ በደንብ የምናውቀው እና ልምድ ያለው ተጫዋች ነው። ሁለቱ አማካዮች ወደፊት ብዙ አቅም ይፈጥሩልናል" ብሏል።
በዚህ የኮከቦች ስብስብ ውስጥ ሌላኛው ከባድ ፈራሚ ካርሎስ ባሌባ ተቀላቅሏል። በ70 ሚሊዮን ፓውንድ የተዘዋወረው ካሜሩናዊው፣ በክለቡ ታሪክ ውድ ከሚባሉ ፈራሚዎች ተርታ ተሰልፏል። ይሄን ያህል ዋጋ የወጣበት ተጫዋች ቋሚ ተሰላፊ መሆን አለበት ተብሎ ይታሰባል።
እያንዳንዱ አማካይ ለቡድኑ የተለየ ኃይል ይዞ ይመጣል። ባሌባ ፍጥነት፣ ጉልበት እና የተከላካይነት ንቃት ሲሰጥ፤ ቴሌማንስ ኳስን በማረጋጋት፣ በማቀበል እና ሜዳን በማንበብ ወደር የለውም። ሳንቶስ በግል ግንኙነቶች (duels) እና ኳስን በማቋረጥ ሲጎላ፤ ማይኖ ደግሞ በጠባብ ቦታዎች ኳስን ተቆጣጥሮ ቡድኑን ወደ ፊት በማስኬድ ልዩ ችሎታ አለው። ይሁንና እነዚህ ሁሉ በአንድ ጊዜ በሜዳ ላይ ሊሰለፉ አይችሉም።
ከኤቨርተኑ ጨዋታ በፊት ይህን ፈተና በተመለከተ የተጠየቀው ካሪክ በፈገግታ እንዲህ ሲል አብራርቷል፦ "ልክ የአሰልጣኞች ክፍል ገብታችሁ ቋሚ አሰላለፍ እየመረጣችሁ ያለ ይመስላል! እኛ ቡድን የምንገነባው ለአንዱ እሁድ ጨዋታ ብቻ አይደለም፤ ሙሉውን የውድድር ዓመት የሚያሻግረን ጠንካራ ስብስብ ነው የሚያስፈልገን። ጨዋታዎች በየሦስት እና አራት ቀናት ሲመጡ አሰላለፍ መቀየር ግድ ነው። በጉዳትም ሆነ በቅጣት የሚመጣውን ክፍተት ለመድፈን እና የተሟላ ጥምረት ለመፍጠር ማንኛውም ወደ ሜዳ የሚገባ ተጫዋች የራሱ የሆነ ወሳኝ ሚና አለው።"

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ዝነኛዋ የካንትሪ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ ፓርተን በሰማንያ ዓመቷ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፏን ተከትሎ፣ ድምፃዊት ቢዮንሴ ጥልቅ ሐዘኗን በስሜት ገልጻለች። የሁለቱ የጥበብ ከዋክብት ቁርኝት እ.ኤ.አ. በሁለት ሺህ ሃያ አራት በወጣውና የቢዮንሴ የሙዚቃ አብዮት ማሳያ በሆነው "ካውቦይ ካርተር" የተሰኘ አልበም ላይ በደመቀ ሁኔታ ተንጸባርቋል። በዚህ አልበም የፓርተን የሺ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት የማይጠወልግ የጥበብ ፍሬ የሆነው "ጆሊን" የተሰኘው ሙዚቃ በአዲስ ዜማና አቀራረብ ዳግም ሕይወት ዘርቶ ቀርቧል።
ቢዮንሴ በድረገጿ ላይ ባሰፈረችው ልብ የሚነካ መልእክት፣ "ዶሊ ሆይ፣ አንቺ ለሁላችንም የልቀት መለኪያና የሰሜን ኮከባችን ነበርሽ" በማለት የጥበብ እናቷን አሞግሳለች። አክላም "አንቺ ደፋርና ድንቅ፣ ተሰጥኦ የተረፈሽና ወደኋላ የማትዪ ጀግና ነሽ። ማንነትን በልዩ ሁኔታ እንዴት መግለጽ እንደሚቻል ለብዙዎቻችን አብነት ሆነሻል። ለጥበብሽ፣ ለሰፊው ልብሽ፣ ለለጋስነትሽ፣ ለፈገግታሽና ለስራ ፈጣሪነትሽ ምንጊዜም ዕዳ አለብኝ" ስትል የልቧን አውጥታለች።
ድምፃዊቷ አብረው ያሳለፉትን ወርቃማ ጊዜ ወደኋላ መለስ ብላ በማስታወስ፣ የፓርተንን የዘመን ተሻጋሪ አሻራ በክብር አንስታለች። "ካንቺ ጋር አብሮ የመስራት ጸጋን በማግኘቴ እጅግ እኮራለሁ፤ ይህንንም ትዝታ በልቤ ጓዳ ለዘላለም በክብር አኖረዋለሁ" ስትል ገልጻለች። በመቀጠልም "በዚህች ዓለም ላይ ላሳረፍሽው ጥልቅና በጎ ተጽእኖ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስሽ። በሚያፈነድቀው ጥበብሽ ይህችን ምድር የተሻለችና የደመቀች ስፍራ ያደረግሽ የሰላም መልአክ ነሽ። አንቺ በእውነት በምትክ የማይገኝልሽ ልዩ ፈጠራ ነሽ፤ ነፍስሽ በሰላም ትረፍ" በማለት የመጨረሻ ስንብቷን አድርጋለች።
በአልበሙ ውስጥ በአዲስ መልክ ከተቀነቀነው "ጆሊን" ባሻገር፣ ዶሊ ፓርተን በ"ካውቦይ ካርተር" አልበም ላይ የማይረሱ የድምጽ አሻራዎቿን አኑራለች። በዘጠነኛው ትራክ ላይ "ዶሊ ፒ" በሚለው አጭር ትረካ፣ እንዲሁም በሃያ አምስተኛው ትራክ መጀመሪያ ላይ ልዩ በሆነውና ማራኪ አንደበቷ የራሷን ድምቀት ፈጥራለች።
ቢዮንሴ "ቴክሳስ ሆልድ ኤም" በተሰኘው ሙዚቃዋ የቢልቦርድ የካንትሪ ሙዚቃ ሰንጠረዥን በመምራት በዘመናዊው የካንትሪ ሙዚቃ ታሪክ ይህን ክብር ያገኘች የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ሆና ታሪክ ስትሰራ፣ አልበሙ ገና ለዕይታ ከመብቃቱ በፊት ፓርተን አድናቆቷን ችራላት ነበር። በወቅቱም የቢዮንሴ ትልቅ አድናቂ መሆኗንና የካንትሪ ሙዚቃ አልበም በመስራቷ እጅግ መደሰቷን በመግለጽ፣ ሙሉ አልበሙን ለማድመጥ በጉጉት እንደምትጠብቅ ስሜቷን አጋርታ እንደነበር ይታወሳል።

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ፊላደልፊያ ከተማ እምብርት ውስጥ ከ130 ዓመታት በላይ ዕድሜ ባስቆጠረው እና የዓለም ሀገራት የምግብ አማራጮች በሚቀርቡበት ታዋቂው ሪዲንግ ተርሚናል ገበያ፣ የመጀመሪያው አፍሪካዊ እና የኢትዮጵያ ምግብ ቤት የሆነው "ሰከላ ኪችን" ሐሙስ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኦገስት 20 ቀን 2026) በይፋ ተከፍቷል። የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት በድምቀት የተመረቀው ይህ ተቋም፣ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ ለዓለም ለማስተዋወቅ ለሚሹ ሁሉ ትልቅ የኩራት ምንጭ እና መነቃቃትን የሚፈጥር ስኬት ሆኗል።
ለባለቤቷ ማርታ (ሜሮን) ከበደ ይህ ስኬት በአንድ ጀምበር የመጣ አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ በእናቷ ምግብ ቤት ማዕድ ቤት ውስጥ አድጋ የሙያውን ጥበብ የቀሰመችው ማርታ፣ በ2007 ወደ አሜሪካ ከመጣች በኋላ ሪዲንግ ተርሚናል ማርኬት አካባቢ (አሁን ፋሽን ዲስትሪክት በሚባለው ስፍራ) ለዓመታት ሠርታለች። በተጨማሪም በፊላደልፊያ ብሪወሪታውን አካባቢ በሚገኘው "ኢራ" የተሰኘ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ውስጥ በስራ አስኪያጅነት አገልግላለች። በ2017 እዚሁ ታሪካዊ ስፍራ ላይ የራሷን የንግድ ተቋም ለመክፈት ራዕይ ሰንቃ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያመጣባትን መጓተት እና የፋይናንስ ዝግጅት ፈተናዎችን ሁሉ በፅናት ተቋቁማ ዛሬ ያንን ትልቅ ህልሟን እውን ለማድረግ በቅታለች።
በዚህ ውብ ማዕከል ውስጥ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ለአመጋገብ እና ለአቀራረብ በተመቸ እና በቀለለ ፈጣን ዘመናዊ መልኩ ይቀርባሉ። ደንበኞች እንደ ዶሮ ወጥ፣ እንጀራ እና ሳምቡሳ ያሉትን ትክክለኛ የኢትዮጵያ ምግቦች እንደምርጫቸው በሳህን ላይ እያዋሃዱ ለቁርስ፣ ለምሳ እና ለእራት መመገብ ይችላሉ። ማርታ እንደምትገልጸው፣ በዚች ታሪካዊ ከተማ ውስጥ ብቸኛው አፍሪካዊ ሬስቶራንት የሆነው ሰከላ ኪችን፣ የኢትዮጵያን ልዩ ጣዕም ከምንጩ ከማቅረብም ባሻገር፤ የሀገሪቱን ታሪክ፣ ድንቅ ባህል እና እንግዳ ተቀባይነት ለፊላደልፊያ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች የማስተዋወቅ የላቀ ዓላማን አንግቧል።
የኢትዮጵያን ጣዕም እና ባህላዊ ሞገስ በአሜሪካ ምድር የሚያንፀባርቀውን ይህንን ተቋም መጎብኘት ለምትፈልጉ አድራሻው 1136 አርች ጎዳና፣ ሪዲንግ ተርሚናል ማርኬት፣ ፊላደልፊያ፣ ፔንሲልቬንያ 19107 ሲሆን፣ ማዕከሉ በየቀኑ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ክፍት ሆኖ ደንበኞቹን በኢትዮጵያዊ ፈገግታ ያስተናግዳል።

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) የኢትዮጵያ ምግብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ድንቅ ተወዳጅነት እና ማራኪ ጣዕም ዳግም በሚያረጋግጥ መልኩ፣ ታዋቂዋ የሆሊውድ እና ቦሊውድ ኮከብ ፕሪያንካ ቾፕራ ለኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች፣ በተለይም ለእንጀራ ያላትን ጥልቅ ፍቅር አሳውቃለች።
ፕሪያንካ በቅርቡ ‘Hey Jonas!’ በተሰኘው የፖድካስት ዝግጅት ላይ በነበራት አስደሳች ቆይታ፣ የዕለቱ ምግቧ የኢትዮጵያ ምግብ እንደነበር በኩራት አጋርታለች። ኮከቧ ዝግጅቱን በሳቅ በማጀብ፣ ታዋቂው ድምጻዊ የሆነው ባለቤቷ ኒክ ጆናስ እንደ እሷ የኢትዮጵያን ምግብ በየቀኑ የመመገብ አቅም እንደሌለው ገልጻ "በየቀኑ እንጀራ መብላት ለእሱ ይከብደዋል" በማለት በፈገግታ ተናግራለች። እሷ ግን እንጀራን አዘውትራ ብትመገብ እንደማይሰለቻትና ልዩ የጣዕም ፍቅር እንዳላት አሳይታለች።
ይህ የፕሪያንካ አድናቆት ዝም ብሎ የተነገረ ቃል ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በዘመናት ውስጥ የተፈተነውን እና ከአያት ቅድመ አያቶቻችን ሲወራረስ የመጣውን የሀገራችንን የማዕድ ጥበብ ከፍታ የሚያሳይ ነው። ከጤፍ የሚዘጋጀው፣ ጤናማውና ከግሉተን ነፃ የሆነው ልዩው የኢትዮጵያ እንጀራ፣ በጣዕሙ ብቻ ሳይሆን በማዕድ ዙሪያ ሰዎችን በማሰባሰብ የፍቅር እና የአንድነት ተምሳሌት በመሆን በዓለም ዙሪያ እውቅናን እያተረፈ ይገኛል። ዓለም አቀፍ ከዋክብት የሀገራችንን ባህል እና ጣዕም እንደዚህ ከፍ አድርገው ሲያደንቁ መስማት፣ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትልቅ የኩራት ምንጭ ነው።
የኮከቧን አስተያየት ተከትሎ የቪዲዮው ቅንጭብጭብ በቲክቶክ እና ኢንስታግራምን በመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተዘዋወረ (ቫይራል ሆኖ) ይገኛል። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም፣ ፕሪያንካ ቀደም ሲልም የኢትዮጵያን ባህል እንደምታደንቅ በማስታወስ ደስታቸውን እና ኩራታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። በእርግጥም የኢትዮጵያ ጣዕም አንዴ ከቀመሱት የልብን የሚያማልል፣ ድንበር ተሻጋሪ ልዩ ሚስጥር አለው!
ከኢትዮጵያ ምግቦች ዓይነት ውስጥ፣ የእርስዎ 1ኛ ምርጫ ምንድን ነው?

(ዘ-ሐበሻ ዜና) መቼም በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የምትኖሩ ወገኖች ዛሬ ማለዳ በትራፊኩ መጨናነቅ እና መስተጓጎል የተነሳ 'ምን ተፈጥሮ ይሆን?' ብላችሁ መጠየቃችሁ አልቀረም። ምክንያቱ ግን እጅግ አስገራሚ፣ አልፎ ተርፎም ፈገግ የሚያሰኝ ሆኖ ተገኝቷል።
ዛሬ ማለዳ (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ትናንት) 1፡00 ሰዓት አካባቢ፣ በሰሜን ምዕራብ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ታሪካዊው የቴንሊታውን ሰፈር ያልተጠበቀ ክስተት ተፈጠረ። በአንድ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ አቅራቢያ የተተወ አጠራጣሪ እቃ፣ የጸጥታ ኃይሎችን እግር በእሳት አስጠብቆ የጠዋቱን የተጨናነቀ የትራፊክ ፍሰት ለሁለት ሰዓታት ያህል ሙሉ በሙሉ አስቁሞት አርፍዷል።
የአካባቢው የጸጥታ አካላት እና የዋሽንግተን ዲሲ የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍል ይህንን "አጠራጣሪ እሽግ" እንደ ትልቅ የጸጥታ ስጋት በመቁጠር በአፋጣኝ ወደ ስፍራው አቀኑ። ዘ-ሐበሻ ያገኘው የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ አንድ ግለሰብ ወደ ጣቢያው ጀርባ በመምጣት የኤሌክትሪክ ገመዶቹ ወደ ውጭ የወጡበትን ይህን እቃ ጥሎት መሄዱ ታውቋል። የገመዶቹ ወደ ውጭ መውጣት ደግሞ እቃው አደገኛ ፈንጂ ወይም ቦምብ ሊሆን ይችላል የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬን ፈጥሮ ነበር።
ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የቦምብ አምካኝ ባለሙያዎች እና ልዩ አፋሽ የፖሊስ ውሾች (K-9 Units) አካባቢውን አጥረው ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ፍተሻቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ሆኖም ከከፍተኛ ጥንቃቄ እና ፍርሃት በኋላ፣ ይህ መላውን ሰፈር ያሸበረው እና መንገዶችን ያስዘጋው ቁሳቁስ ምንም ዓይነት አደጋ የማያስከትል "ሰማያዊ እና ጥቁር ቀለም ያለው ኤሌክትሮኒክ ተንቀሳቃሽ የሴክስ (የወሲብ) መጫወቻ" ሆኖ ተገኝቷል።
ፖሊስ እቃውን ከስፍራው በማንሳት የትራፊክ ፍሰቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ያደረገ ሲሆን፣ በክስተቱ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱ ተረጋግጧል። ጉዳዩን የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት ተጨማሪ ምርመራ እያደረገበት ይገኛል። በርግጥም የዛሬው የዲሲ የትራፊክ መጨናነቅ ሰበብ፣ በነዋሪው ዘንድ ግርምትን የፈጠረና በፈገግታ የሚታወስ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትምህርት መድረክን በስኬት ተሻግራ የነገዋን ብሩህ የሕክምና ዓለም በዓይነ ህሊናዋ ስትስል የነበረችው ወጣት፣ ህልሟ በአንድ የጭለማ ምሽት የጥይት ድምጽ በአሳዛኝ ሁኔታ ተቋጭቷል። ቅዳሜ ነሐሴ 8 ቀን 2026 ዓ.ም. ምሽት በፍሬዝኖ ከተማ በተዘጋጀ የቤት ውስጥ ድግስ ላይ በተፈጠረ ድንገተኛ ጸብ፣ በሕክምናው ዘርፍ ትልቅ ተስፋ የተጣለባት የ26 ዓመቷ ማሪዮን ፀጋይ በግፍ ተገድላለች።
በፍሬዝኖ ፖሊስ መርማሪዎች ማረጋገጫ መሠረት፣ አሳዛኙ ክስተት የተፈጠረው ማሪዮን ከተጠርጣሪዋ የ24 ዓመቷ ኔማዲያ ነክልስ ጋር ኃይለኛ የቃላት ምልልስ ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው። ጭቅጭቁ ወዲያውኑ ወደ አሰቃቂ የጥይት ድምጽ ተቀየረ። ማሪዮን በጥይት መመታቷን ያዩ የድግሱ ታዳሚዎች፣ ህይወቷን ለማትረፍ ባደረጉት የሞት ሽረት ትግል በመኪና ወደ ሆስፒታል ይዘዋት ሲበረሩ፣ ከምሽቱ 3፡20 ገደማ ፍሩት እና ሺልድስ አቬኑ አካባቢ በድንገት ከእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪ እና ከድንገተኛ አደጋ ሠራተኞች ጋር ተገናኙ። የድንገተኛ አደጋ ባለሙያዎች ወጣቷን በፍጥነት ወደ 'ኮሚዩኒቲ ሪጅናል ሜዲካል ሴንተር' ወስደው ህይወቷን ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም፣ ማሪዮን የደረሰባት የጥይት ቁስለት እጅግ ከባድ በመሆኑ ህይወቷ አልፏል።
ማሪዮን ፀጋይ በነገዋ ላይ ብሩህ ተስፋ የነበራት፣ ለስኬት የምትተጋ እና ቤተሰቦቿን የምታኮራ ወጣት ነበረች። እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2023 ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (ፍሬዝኖ) በኪኔዚዮሎጂ እና የአካል ብቃት ሳይንስ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ሲሆን፣ በምረቃዋ ዕለትም በቤተሰቧ ታሪክ የመጀመሪያዋ የምረቃ ካባ ለባሽ መሆኗን የሚገልጽ "First Generation" የሚል ጽሑፍ በኩራት አጥልቃ ነበር።
ማሪዮን ከዩኒቨርሲቲ ትምህርቷ ጎን ለጎን በማክዶናልድስ ምግብ ቤት ውስጥ ለዓመታት ሠርታ እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅነት እርከን የደረሰች ጠንካራ ሠራተኛ ነበረች። ህይወቷ ባለፈበት ወቅት ደግሞ በፍሬዝኖ የልብ እና የቀዶ ጥገና ሆስፒታል ውስጥ የአካል ብቃት ሕክምና ረዳት በመሆን ሙያዊ ህልሟን እያሳደደች ትገኝ ነበር።
የማሪዮን ድንገተኛ ሞት ወዳጅ ዘመዶቿን በከባድ ሀዘን ውስጥ ጥሏል። አንዲት የማሪዮን ጓደኛ በማህበራዊ ሚዲያ ገጿ ላይ ባሰፈረችው የልብ ሰባሪ ስንብት፣ "ማሪዮን፣ ህይወትሽ ትርጉም ነበረው። ስኬትሽ፣ ህልሞችሽ፣ እና ፈገግታሽ ትርጉም ነበራቸው። አሁን ደግሞ መለየትሽ የከፋ ትርጉም አለው። የኖርሽው አጭር ህይወት፣ እኛ በህይወት ያለነው ሰዎችን አጥብቀን እንድንወድ፣ ቶሎ ይቅር እንድንል እና ማንኛውንም ቀን እንደ ቀላል እንዳንቆጥር ትልቅ ትምህርት ትቶልን አልፏል" ስትል ሀዘኗን ገልጻለች። ሌላኛዋ ጓደኛዋ ቪክቶሪያ ክሪነር በበኩሏ፣ "በአካል በተገናኘንባቸው ጊዜያት ሁሉ ከካንቺ ያገኘሁት ደግነትን ብቻ ነው፤ አንቺ ሁልጊዜም ብሩህ ብርሃን ነበርሽ" በማለት ሸኝታታለች።
የፍሬዝኖ ፖሊስ ግድያው በተፈጸመ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ፣ ቅዳሜ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ገደማ ብላክስቶን እና ዌልደን አቬኑ አቅራቢያ በሚገኝ ዌንዲስ (Wendy's) ምግብ ቤት ውስጥ የ24 ዓመቷን ተጠርጣሪ ኔማዲያ ነክልስን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ተጠርጣሪዋ በግድያ ወንጀል ተከሳ በፍሬዝኖ ካውንቲ እስር ቤት የምትገኝ ሲሆን፣ የዋስትና መብቷም በ1 ሚሊዮን ዶላር ተተምኗል።
የፍሬዝኖ ፖሊስ ግድያውን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው፣ የነፍስ ግድያ መርማሪ ለሆኑት ኤ. ባራጋን አሊያም አር. ጋሌጎስ መረጃ በመስጠት የፍትህ ሂደቱን እንዲያግዝ ጥሪውን አስተላልፏል። በአንድ ምሽት የቃላት ምልልስ የተቀጨው የማሪዮን ብሩህ የህይወት ጉዞ፣ የከተማዋን ማህበረሰብ በሀዘን ከማስመጡም ባሻገር፣ የጠመንጃ ሁከት በአሜሪካ ከተሞች ውስጥ የሚፈጥረውን የማይሽር ጠባሳ በድጋሚ አስታውሷል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ታዋቂው የፊልም እና የቴሌቪዥን ዥረት አገልግሎት አቅራቢ ኔትፍሊክስ ተቋሙን ዳግም ለኦስካር የሽልማት ፉክክር ተፎካካሪ ሊያደርጉ የሚችሉ ሁለት ሽልማት ያገኙ አጫጭር ዘጋቢ ፊልሞችን መግዛቱን አስታውቋል። ወደ ኔትፍሊክስ መድረክ ከሚቀላቀሉት ፊልሞች መካከል፣ በ2025ቱ የዓለም አቀፍ የዘጋቢ ፊልም ፌስቲቫል የምርጥ አጭር ዘጋቢ ፊልም አሸናፊ የሆነው 'አን ኦፕን ፊልድ' እና በ2026ቱ የአስፐን ሾርትስፌስት በርካታ ሽልማቶችን የሰበሰበው 'ዋን ላስት ኦርደር' ይገኙበታል።
'አን ኦፕን ፊልድ' የተሰኘው ዘጋቢ ፊልም ዳይሬክተር ተቦሆ ኤድኪንስ፣ እ.ኤ.አ. በ2019 በኢትዮጵያ በተከሰተው አሳዛኙ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ወንድሙን ማክስ ታቢሶ ኤድኪንስን አጥቷል። በቦይንግ የኤም.ሲ.ኤ.ኤስ (MCAS) አውቶማቲክ የበረራ ሶፍትዌር ብልሽት ምክንያት የተከሰተው ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 አደጋ፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትን 157 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ይታወሳል። አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በኦሮሚያ ክልል፣ ጊምቢቹ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ክፍት የእርሻ ማሳ ላይ ነበር።
ይህ ዘጋቢ ፊልም፣ አደጋው እንደተከሰተ የአካባቢው ነዋሪዎች እርዳታ ለማድረግ ወዲያውኑ ወደ ስፍራው መትመማቸውን፣ እንዲሁም የተወሰኑት የአደጋውን ስፍራ ለመጠበቅ እና ለማቆየት ለአንድ ወር ያህል ዘብ መቆማቸውን ያሳያል። ፊልሙ፣ ቦይንግ አደጋውን ተከትሎ የሰጠውን እና በብዙዎች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ የተተቸበትን ምላሽ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ካሳየው ጥልቅ ርህራሄ ጋር በማነፃፀር ያቀርበዋል።
ዳይሬክተር ተቦሆ ኤድኪንስ ስለ ፊልሙ ሲናገር "ይህ ስስ እና ግላዊ የሆነ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ መሰረታዊ ተፈጥሮን የሚያሳይ ስራ ነው። ኔትፍሊክስ ፊልሙን ለዓለም አቀፍ ተመልካቾች ማቅረቡ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው፤ ድጋፋቸውንም እጅግ አደንቃለሁ" ብሏል።
በሌላ በኩል በሎረን ዴፊሊፖ እና ሳም ሶኮ ዳይሬክት የተደረገው 'ዋን ላስት ኦርደር' የተሰኘው ፊልም፣ በፍሎሪዳ ግዛት ጌይንስቪል ከተማ ውስጥ የተፈጸመን አንድ ልብ የሚነካ ታሪክ ይተርካል። ሺላ ዊሊያምስ የተባለች ሴት፣ በማክስ ድራይቭ-ትሩ የፈጣን ምግብ ማቅረቢያ ውስጥ ለ37 ዓመታት ማህበረሰቡን በፍቅር እና በፈገግታ ስታገለግል ከቆየች በኋላ የመጨረሻ የስራ ቀኗን ስታሳልፍ ፊልሙ ያሳያል።
የምግብ ቤቱ ባለቤት በዕለቱ የሚገኘው ሙሉ የሽያጭ ገቢ ለሺላ እንደሚሰጥ ሲያስታውቅ፣ ከተማዋ ውለታዋን ለመመለስ በመኪና ረዥም ሰልፍ በመፍጠር እስከ ሶስት ሰዓታት ድረስ ስትጠብቅ የሚያሳይ ስሜት ቀስቃሽ ፊልም ነው። ዳይሬክተሮቹ እንዳሉት፣ ይህ ፊልም የዕለት ተዕለት ደግነትን ለሚያሳዩ እና ተራ ቦታዎችን ልዩ ለሚያደርጉ ሰዎች የተጻፈ የፍቅር ደብዳቤ ነው።
ኔትፍሊክስ ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት (በ2025 እና 2026) በምርጥ አጭር ዘጋቢ ፊልም ዘርፍ የኦስካር ሽልማቶችን ማሸነፉ ይታወሳል። አሁንም ከእነዚህ ሁለት ፊልሞች በተጨማሪ፣ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርን ታሪካዊ "I Have a Dream" ንግግር በማዘጋጀት ትልቅ ሚና በነበራቸው ክላረንስ ቢ. ጆንስ ላይ ያተኮረውን እና 'The Baddest Speechwriter of All' የተሰኘውን ሌላ ጠንካራ የኦስካር ተፎካካሪ ፊልም ከሰንዳንስ የፊልም ፌስቲቫል መግዛቱን ተቋሙ አስታውቋል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የሊቨርፑል ደጋፊዎች አዲሱን አሰልጣኛቸውን አንዶኒ ኢራኦላን እና ስብስባቸውን በአንፊልድ ለመቀበል ስታዲየሙን በሞሉበት የሞናኮው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ፣ በክለቡ አዲስ ዘመን የመጀመሩ የጉጉት ስሜት ደምቆ ይታይ ነበር። ሆኖም ኢራኦላ ተጫዋቾችን ከቀየሩ በኋላ፣ ሊቨርፑል በተከታታይ ለሁለተኛ ጨዋታ የነበረውን የሁለት ግብ መሪነት አሳልፎ ሰጥቷል። ይህ ደግሞ በቡድኑ የስብስብ ጥልቀት ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን አመላካች ሆኗል።
ከጨዋታው በኋላ ኢራኦላ ለኤል.ኤፍ.ሲ ቲቪ በሰጡት አስተያየት የነበራቸውን ብስጭት አልሸሸጉም። "ከሊድስ ጋር ካደረግነው ጨዋታ ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው" ያሉት አሰልጣኙ፣ "በመጀመሪያው አጋማሽ፣ በተለይም በመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ምርጥ ነበርን። ነገር ግን ይህንን ደረጃ ጠብቆ ለመጫወት የሚያስችል በቂ አቅም አሁን ላይ የለንም። ሞናኮዎች ጨዋታውን መቀልበስ ይገባቸዋል" ብለዋል።
አክለውም፣ "የመጀመሪያዎቹን ሁለት የቅድመ-ውድድር ዘመን ጨዋታዎች አሸንፈናል፤ በነዚህ የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ግን የምንፈልገውን የጨዋታ ፍጥነት ሙሉ ሰዓት ማስቀጠል አልቻልንም። ለውጦችን እንዳደረግን ተጫዋቾች መድከም ጀመሩ። ስለዚህ ገና ብዙ የምንሰራቸው ስራዎች አሉን" በማለት ተናግረዋል።
ሊቨርፑል የፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት ነሐሴ 10 ከኮሞ ጋር ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ያደርጋል። ከሁለት ሳምንት በኋላ ከኒውካስል ጋር ለሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ግን ከቪርጅል ቫን ዳይክ ጋር በማዕከላዊ ተከላካይነት ማን ይሰለፋል የሚለው ጥያቄ አሁንም ምላሽ አላገኘም።
ቫን ዳይክ ከዓለም ዋንጫ ዕረፍት በኋላ አሊሰን እና ኮዲ ጋክፖን በመቀላቀል በሞናኮው ጨዋታ ላይ ተመልሷል። ጨዋታውን የጀመረው ከ18 ዓመቱ ድንቅ ታዳጊ ኢፌአንዪ ንዱክዌ ጋር ቢሆንም፣ ታዳጊው በስራ ፈቃድ ችግር ምክንያት በዚህ የውድድር ዘመን በውሰት ሊሰጥ ይችላል። ጨዋታው ሲጠናቀቅ ሊቨርፑል በመሃል ተከላካይነት ሉክ ቻምበርስን እና ዋታሩ ኤንዶን ለመጠቀም መገደዱ የቡድኑን ክፍተት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
በሌላ በኩል የተከላካይ ክፍሉን ለማጠናከር፣ የ27 ዓመቱ ሮናልድ አራውሆ ከባርሴሎና በውሰት ለመዘዋወር (በ47.2 ሚሊዮን ፓውንድ በቋሚነት የመግዛት አማራጭን ጨምሮ) እሁድ ዕለት የህክምና ምርመራውን አድርጓል። ከሬንስ የመጣው የ21 ዓመቱ ጀረሚ ጃኬት በጉዳት ምክንያት ሙሉ ልምምድ ባይጀምርም፣ በቀጣዩ የኮሞ ጨዋታ ላይ ሊሰለፍ እንደሚችል ተስፋ ተጥሏል።
ባለፈው ክረምት በ225 ሚሊዮን ፓውንድ የጋራ ዋጋ ወደ ሊቨርፑል ያመሩት ፍሎሪያን ቨርትዝ እና አሌክሳንደር ኢሳክ በሞናኮው ጨዋታ ያሳዩት ጥምረት ለደጋፊዎች ትልቅ ተስፋን ሰጥቷል። ቨርትዝ ከኢሳክ ጀርባ በ10 ቁጥር ሚና የተጫወተ ሲሆን፣ ኢሳክ ምርጥ በሆነ የውጪ እግር አጨራረስ የመጀመሪያዋን ግብ አስቆጥሯል።
የሜዳው ምርጥ ተጫዋች የነበረው ቨርትዝ የሊቨርፑልን ሁለተኛ ግብ ያስቆጠረ ቢመስልም፣ ከጨዋታው በኋላ ኢሳክ የመጨረሻውን ንክኪ ማን እንዳደረገው እርግጠኛ እንዳልሆነ ተናግሯል። "እኔም ሆንኩ ፍሎ ኳሷን ነክተናታል፣ ግን የመጨረሻውን ንክኪ ማን እንዳደረገ አላውቅም" ሲል በፈገግታ ገልጿል።
ኢሳክ በአዲሱ አሰልጣኝ ስር ስላለው ቆይታ ሲናገር፣ "በጣም ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው። በቡድኑ ውስጥ ያለው መንፈስ አስደሳች ነው፤ ሁሉም ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል። ለውድድር ዘመኑ ጅማሮ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን" ብሏል።

"ትልቅ ነገር ማድረግ ካልቻላችሁ ትንሽ ነገር በትልቅ ፍቅር አድርጉ"
#ethiopia |በአለም ታሪክ ውስጥ ብዙ ሀያላን መሪዎች ፈላስፎች እና ታላላቅ ሰዎች ንግግር አድርገዋል።
ነገር ግን እንደ ማዘር ትሬዛ በለሰለሰ ድምፅ የዓለምን ልብ የነካ የታበዩትን ያሳፈረ እና ለተቸገሩት ተስፋ የሰጠ ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ጥቂት ነው።
ማዘር ቴሬዛ በሰሩት ወደር የሌለው የመልካምነት እና የርህራሄ አገልግሎታቸው በ1979 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸንፈዋል።
ሽልማቱን ባሸነፉበት ወቅት ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር ዛሬም ድረስ በሰው ልጅ ህሊና ውስጥ አዲስ ሆኖ ይደመጣል።
"ትልቅ ነገር ማድረግ ካልቻላችሁ ትንሽ ነገር በትልቅ ፍቅር አድርጉ" የሚል ታሪካዊ ንግግር አደረጉ።
የመልካምነትን እውነተኛ ትርጉም ለአለም ሁሉ አበሰሩ።
የዓለም ሰላም እንዲሰፍን እና መልካምነት እንዲኖር ምን እናድርግ ብሎ የጠየቃቸውን ሰው ሲመልሱ ወደ
ቤትህ ተመለስና ቤተሰብህን ውደድ ሲሉ ነበር የመለሱለት።
መልካምነት ከሩቅ ሳይሆን ከራሳችን
ከጎረቤታችን እና ከቅርብ ወዳጆቻችን ፈገግታ እንደሚጀምር በፅኑ አሳስበዋል።
ዛሬ የምታደርጉት መልካም ነገር ነገ ሊረሳ ይችላል ቢሆንም ግን መልካም ማድረጋችሁን ቀጥሉ።
የማዘር ቴሬዛ ይህ ታሪካዊ ንግግር የቃላት ስብስብ ብቻ ሳይሆን የተግባር ውጤት ነበር።
ህይወታቸውን በሙሉ በኮልካታ ጎዳናዎች ለወደቁት፣ ለታመሙት እና ለተረሱት አሳልፈው የሰጡት እናት ናቸው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #nobelprize #religion #mothorteresa #charity

ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት፡ ስልክ ላይ የማቀርቀርን አዚም የሰበረው ባለታክሲ
********************
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚንቀሳቀሱ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች አብዛኛውን ጊዜ በሙዚቃ ጩኸት፣ በትራፊክ ጫጫታና በጉዞ ድካም አዙሪት ውስጥ በመቆየት ይታወቃሉ።
ተሳፋሪውም ታክሲ ውስጥ እንደገባ አንገቱን ደፍቶ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ መንሸራሸር የዘመናችን የተለመደ እውነታ ሆኗል። ወጣት ሰሎሞን አማረ ግን፣ የራሱን ሜትር ታክሲ ከዚህ አሰልቺ እና የተለመደ ምህዋር በማውጣት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወደ የሚሽከረከር "ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት" ቀይሮታል።
በንግድና በጥድፊያ በሚታወቀው የመርካቶ ሰባተኛ ሰፈር ተወልዶ ያደገው ሰሎሞን፣ ከቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ከዲጂታል ሚዲያው መስፋፋት ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ፣ በተለይም ወጣቱ፣ ከመጽሐፍት እየራቀ መምጣቱ በእጅጉ አሳስቦታል። በዚህም የተነሳ፣ ላለፉት ጥቂት ወራት ታክሲውን የዕውቀት ማዕከል በማድረግ ልዩ ልዩ የአማርኛና የእንግሊዝኛ መጻሕፍትን ለተሳፋሪዎቹ እንደ አዲስ አማራጭ ማቅረብ ጀምሯል።
ሁሉም ሰው ስልኩ ላይ ባቀረቀረበት በዚህ ዘመን፣ ሰሎሞን የታክሲው ውስጥ መደርደሪያዎች ላይ መጽሐፍትን በማስቀመጥ የሰዎችን ትኩረት ወደ ንባብ ለመመለስ የራሱን የትግል ስልት ነድፏል።
ሰለሞን ወደ ታክሲው ለሚገቡ መንገደኞች የሚያቀርበው ሞቅ ያለ ፈገግታና ሰላምታን ብቻ አይደለም፤ በስርዓት የተደረደሩ የዕውቀት ማህደሮችንም ጭምር እንጂ። የትራፊክ መጨናነቅን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ተሳፋሪዎች በጉዞ ወቅት መጽሐፍትን እንዲያነቡ ይጋብዛል።
የጀመሩት መጽሐፍ ልባቸውን ከሰረቀው ደግሞ፣ እዚያው ታክሲ ውስጥ ገዝተውት መንገዳቸውን ያለመሰልቸት በዕውቀት ታጅበው ያጠናቅቃሉ። ይህ አሰራር ከማህበራዊ ሚዲያ ጩኸት ለተወሰኑ ደቂቃዎችም ቢሆን አእምሮን የሚያሳርፉበት ልዩ የጉዞ ተሞክሮ ሆኗል።
የሰሎሞን አካሄድ የንባብ ባህልን ከማበረታታት ባለፈ፣ የገበያ ጥናትን (Marketing Management) ከተግባር ጋር ያዋሃደ አዲስ የስራ ፈጠራ ነው።
ጊዜን ወደ እሴት መቀየር፡ የታክሲ ተሳፋሪን የትራፊክ ውስጥ የባከነ ጊዜ ወደ ምርታማ የገበያ ሰዓት ቀይሮታል።
ድርብ ገቢ፡ ከትራንስፖርት አገልግሎቱ ባሻገር፣ መጽሐፍትን በመሸጥ የራሱን የገቢ ምንጭ አሳድጓል።
ማህበራዊ ካፒታል፡ "ተሳፋሪዎች የሚሰጡት አዎንታዊ ምላሽና አስደናቂ ስሜት ለስራዬ ትልቅ መነቃቃት ይፈጥርልኛል" የሚለው ሰሎሞን፣ በየቀኑ ከሚያገኛቸው አዳዲስ ሰዎች ጋር የሚያደርገው ገንቢ ውይይት ከገንዘብ በላይ የሆነ ትልቅ የህይወት ስንቅ እንደሆነለት ይናገራል።
የሰሎሞን አስገራሚው ጎን የዲጂታል ዓለሙን ሙሉ በሙሉ መሸሹ ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለራሱ ዓላማ ማዋሉ ነው። "Sol Books" በሚል ስያሜ በቲክቶክና በሌሎች ማኅበራዊ ገጾች መጻሕፍትን በማስተዋወቅ፣ ዲጂታል ትውልዱን በዲጂታል መድረክ እየቀሰቀሰ ይገኛል።
የዚህ አብዮተኛ ወጣት መልዕክት አጭር እና ግልጽ ነው፦ የተለመደውን አሰራር በመስበር ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም ይህን መሰል በጎ ተግባር ቢያራምዱ፣ ታክሲዎቻችንን ከትራፊክ ጫና ማምለጫነት አልፈው የዕውቀት፣ የሰላምና የፈጠራ ማዕከል ማድረግ ይቻላል።
በሊያ ተስፋዬ
Ethiopian Broadcasting Corporation FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/ #መጽሀፍ #ንባብ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ኦስቲን ከተማ በታዋቂው የአማዞን ኩባንያ ውስጥ በሶፍትዌር ኢንጂነርነት ሲሰራ የነበረው (ከዚህ ቀደም በኢንሳ ሰርቷል) ኢትዮጵያዊው ወጣት ያዴሳ እምሩ አጋ በኔቫዳ ግዛት በሚገኘው ታዋቂው 'ሌክ ታሆ' ሐይቅ ውስጥ ሰምጦ አሳዛኝ ህልፈተ ህይወት እንዳጋጠመው ትናንት በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል። የካሊፎርኒያ ጋዜጦች ዛሬ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘው ወጥተዋል። የሰላሳ ሁለት ዓመቱ ወጣት ያዴሳ ወደ ስፍራው ያቀናው ከቅርብ ጓደኞቹ ጋር በመሆን መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን ኮንፈረንስ ላይ ለመካፈል እንደነበር የቅርብ ሰዎቹ እና ቤተሰቦቹ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆነው ገልጸዋል።
አደጋው የደረሰው ሰኞ ምሽት አካባቢ ሲሆን፣ የዋሾ ካውንቲ የሸሪፍ ጽህፈት ቤት ፖሊሶች እንደገለጹት ወጣቱ ድንጋያማ ወደሆኑት የሐይቁ ክፍሎች እየዋኘ ከሄደ በኋላ በድንገት ከውሃው ወለል በታች ጠፍቶ ሊሰምጥ ችሏል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በፍጥነት ወደ ውሃው በመግባት ያዴሳን አውጥተው የመጀመሪያ እርዳታ (CPR) ያደረጉለት ቢሆንም፣ እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ህክምና ባለሙያዎች ቦታው ላይ ደርሰው ህይወቱን ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም በዚያው በስፍራው ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ፖሊስ አረጋግጧል።
የያዴሳ ጓደኞች፣ ቤተሰቦች እና የቤተክርስቲያን አባላት ለቀብር ማስፈጸሚያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ያዘጋጁ ሲሆን፣ ወጣቱ እጅግ ትሁት፣ ፊቱ ሁልጊዜ በፈገግታ የተሞላ እና ለሰዎች አሳቢ እንደነበር መሰክረውለታል። እምነቱ በህይወቱ ውስጥ ትልቁን ስፍራ እንደሚይዝና ተፈጥሮን ማድነቅ እንዲሁም መጎብኘት ይወድ እንደነበር አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት አስከሬኑን ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ለመላክ እና በአሜሪካም ሆነ በሀገር ቤት ለሚደረገው የቀብር ስነ-ስርዓት የሚወጣውን ወጪ ለመሸፈን ማህበረሰቡ ርብርብ እያደረገ ይገኛል። ቀጣሪው የአማዞን ኩባንያም የተወሰነውን ወጪ ለመሸፈን ከቤተሰቦቹ ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።
የአካባቢው ፖሊስ አደጋውን ድንገተኛ የመስመጥ አደጋ ብሎ የመዘገበው ቢሆንም፣ የዋሾ ካውንቲ የህክምና መርማሪዎች ቢሮ ምርመራው ገና ስላላለቀ ትክክለኛውን የሞት መንስኤ ይፋ አለማድረጉን አሳውቋል። የባለሙያዎቹ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለመውጣት ከአስር እስከ አስራ ሁለት ሳምንታት ሊፈጅ እንደሚችል ተገልጿል። ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረው፣ በዚሁ ተመሳሳይ ሐይቅ ውስጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሌላ ሰው በውሃ ውስጥ አደጋ አጋጥሞት ህይወቱ ማለፉ ከተሰማ በኋላ መሆኑ ታውቋል።
የጎ ፈንድ ሚ ሊንኩን ኮመንት ላይ አስቀምጠናል።

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ይህን ዘገባ ትናንት በቪዲዮ አቅርበነው ነበር፤ ብዙዎቻችሁ፣ 'ኢንተርኔት ፍጥነት በሌለባቸው አካባቢዎች ቪድዮ ለማየት ስለሚቸገሩ' በጽሑፍ ይቅረብልን ባላችሁን መሠረት እንደሚከተለው ቀርቧል | ወዳጅነት... ከለላና መሸሸጊያ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፤ ለዲዛይነር ቅድሳን ይርጋለም ግን ወዳጅነት የሞት ወጥመድ ሆኖ አረፈው። የ2026ቱ የ"ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" የውበት ንግሥት የሩት ይርጋለም ታላቅ እህት የሆነችው ቅድሳን፣ በሞዴሊንግ ዓለም ውስጥ ስኬትን ከምትመኘውና ከእህቷ ጋርም የትምህርት ቤት ትውውቅ ከነበራት ቅድስት ሙሉቀን ጋር የጠበቀ ጓደኝነት ነበራት። ሆኖም ከዚህ ጓደኝነት ጀርባ፣ ጥልቅ የሆነ ምቀኝነት እና አደገኛ ሴራ ተሸሽጎ ነበር።
ሁሉም ነገር የተጀመረው አርብ ዕለት በተደረገ አንድ የስልክ ጥሪ ነው። ለአንድ ዓመት ያህል ተጠፋፍታ የነበረችው ቅድስት፣ የናፍቆት በሚመስል የጓደኝነት መንፈስ ለቅድሳን ደወለች። "አዲስ ኮንዶሚኒየም ተከራይቻለሁ፤ መጥተሽ ቤቴን እዪልኝ። ደግሞም የማገናኝሽ አዲስ የስራ እድል አለ" በማለት የጓደኛዋን ልብ አባበለች። በጓደኛዋ ላይ አንዳችም ክፋት ያልጠረጠረችው ቅድሳን፣ ሜክሲኮ አካባቢ ተገናኝተው አብረው ወደ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም አመሩ። ቅድሳን የጓደኛዋን አዲስ ሕይወት ለማየት በደስታ ስትጓዝ፣ እየሄደች ያለችው ግን ወደራሷ የሞት ቀጠሮ ነበር።
አዲሱ ቤት ደጃፍ ላይ ደርሰው ወደ ውስጥ ሲገቡ፣ የነበረው ወዳጃዊ ድባብ ቅጽበታዊ በሆነ ሽብር ተተካ። ቤት ውስጥ አድፍጦ ይጠብቅ የነበረው የቅድስት ፍቅረኛ ደሳለኝ፣ ቅድሳን ድምጿን አውጥታ እንኳ ርዳታ እንዳትጠራ አፍኖ አሰራት። ያመነቻት ጓደኛዋ እጅ ከፍንጅ ለሞት አሳልፋ ሰጠቻት።
አጋቾቹ ወዲያውኑ የሟች ቤተሰቦች ጋር በመደወል የሁለት ሚሊዮን ብር ቤዛ ጠየቁ። የቤተሰብ ልብ በጭንቀት እየመታ የድርድር ሀሳቦች ሲለዋወጡ፣ አጋቾቹ አንድ ዘግናኝ እውነት ተገነዘቡ። የጠየቁትን ገንዘብ ቢያገኙ እንኳ፣ ሟች በቅርበት ስለምታውቃቸው ነገ ሚስጥራቸውን አሳልፋ እንደምትሰጣቸው አሰቡ። ፍርሃት እና ምቀኝነት ያደነደነው ልባቸው፣ እዚያው አርብ ዕለት ጭካኔ የተሞላበት ውሳኔ ላይ ደረሰ። የቅድሳንን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አጠፉ። አስከሬኗንም ማንም እንዳያገኘው በሚል እዚያው አካባቢ በተከራዩት ሌላ ተጨማሪ ቤት ውስጥ ደበቁት።
ይሁን እንጂ...የፈጸሙት ግፍ በጨለማ ሊቀበር አልቻለም። ፖሊስ ባደረገው አፋጣኝ እና የተቀናጀ ክትትል፣ ዋነኛ ተጠርጣሪዋ ቅድስት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ጎተራ አካባቢ በቁጥጥር ስር ዋለች። የወንጀሉ ተባባሪ የነበረው ደሳለኝ ደግሞ፣ ሁኔታው ሲከፋበት ለማምለጥ ሞክሮ አዳማ ከተማ ውስጥ ተደብቆ እያለ በፖሊስ መረብ ውስጥ ወደቀ። በአጠቃላይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ስምንት ሰዎች ታሰሩ። ዋነኛ ተጠርጣሪዎቹም ወንጀሉን መፈጸማቸውን አምነው፣ እንዴት እንዳከናወኑት በቦታው ተገኝተው ለፖሊስ አሳይተዋል።
ይህ ክስተት የ2026ቷን የውበት ንግሥት ሩትን ብቻ ሳይሆን፣ መላውን ማኅበረሰብ በሐዘን እና በስጋት ውስጥ ጥሏል። ሩት በልብ ስብራት "ከጠላቴ እኔ እጠነቀቃለሁ፤ ከወዳጄ አንተ ጠብቀኝ" ብላ ያሰፈረችው መልእክት፣ የዚህን ትረካ አሳዛኝ ማጠቃለያ ይወክላል፦ ጠላት ፊቱን አውቆ ሲመጣ፣ ክህደት ግን በወዳጅ ፈገግታ ታጅቦ ይመጣል።

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ፈገግታው፣ ቅርበቱ፣ የጓደኝነት ድባቡ... ዛሬ ላይ ቆሞ ለሚያየው በእጅጉ ልብ ይሰብራል። በዚህ ምስል ላይ የምትመለከቷት የ2026ቷ "ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ" ሩት ይርጋለም ስትሆን፣ አጠገቧ የቆመችው ደግሞ የሩትን ታላቅ እህት (ዲዛይነር ቅድሳን ይርጋለምን) ከፍቅረኛዋ እና ከተባባሪዎቿ ጋር አሳግታ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድላለች ተብላ በፖሊስ የተያዘችው ዋና ተጠርጣሪ ቅድስት ሙሉቀን ናት።
ከ5 ዓመታት በፊት የገናን በዓል በፍቅር እና በጓደኝነት መንፈስ አብረው ሲያከብሩ፣ ከዓመታት በኋላ ይህችው "ጓደኛ" በምቀኝነት ታውራ የእህቷን ሕይወት በጭካኔ ትቀጥፋለች ብሎ ማን ያስብ ነበር? የሰው ልጅ ልብ እንዴት አይታወቅም! ያኔ አብራ እየሳቀች፣ በውስጧ ግን ጥቁር ጥላቻን እና አደገኛ ሴራን ትፈትል ነበር።
ሩት በልብ ስብራት "ከጠላቴ እኔ እጠነቀቃለሁ፤ ከወዳጄ አንተ ጠብቀኝ" ስትል ያስተላለፈችው መልእክት ምንኛ እውነት መሆኑን ይህ ፎቶ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። ጠላት ፊቱን አውቆ ሲመጣ መጠንቀቅ ይቻላል፤ ክህደት ግን በወዳጅ ፈገግታ እና በናፍቆት ስም ተጀቡኖ ሲመጣ ማምለጫ የለውም።
እባካችሁ ጓደኛ ስትመርጡ ወደ ውስጣችሁ የምታስገቡትን ሰው ማንነት በሚገባ መርምሩ። ፈገግ ላለላችሁ ሁሉ ልባችሁን አትስጡ!
ፍትህ ለቅድሳን ይርጋለም! 🕊️

በ108 ዓመታቸው የመኪና መሪ አልለቅም ያሉት የእድሜ ባለፀጋዋ ሜሪ
መሪ በቀላሉ የምንደሰት ከሆነ የማይቻል ነገር የለም ይላሉ
#ethiopia | በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ108 አመት ባለፀጋዋ መሪ በሰሞኑ የመንጃ ፍቃዳቸውን እስከ ፈረንጆቹ 2033 ድረስ አሳድሰዋል።
108 ዓመታቸው ላይ የሚገኙት መሪ በራሳቸው መኖሪያ ቤት ብቻቸው ከመኖራቸውም በላይ መኪናቸውንም እያሽከረከሩ ይገኛሉ።
ሜሪ ፍሊፕ የተባሉት እኚህ ባለታሪክ ለረጅም እድሜ የበቁበትና ጤናማ የሆኑበትን ምስጢር አካፍለዋል።
በቅርብ ጊዜ የመንጃ ፈቃዳቸውን እስከ ፈረንጆቹ 2033 ድረስ ያደሱት ሜሪ ሙሉ በሙሉ ነፃነታቸውን ጠብቀው በራሳቸው መኖር እንደሚወዱ ይናገራሉ።
ራሴን ሙሉ በሙሉ በራሴ ነው የምንከባከበው የሚሉት ሜሪ በየቀኑ ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን መስራት እንደሚያዘወትሩ ይናገራሉ።
ሜሪ እረጅም ዕድሜ የመኖራቸው ምክንያት ሲናገሩ በሕይወታችን ውስጥ ከባድ ችግሮች ሲገጥሙን አዎንታዊ ጎኑን ማየትና ሁልጊዜም ፈገግታን ማብዛት ጤናማ ህይወት መኖር ይቻላል ብለዋል።
በሰው ላይ አለመደገፍ እና የራስን የቤት ውስጥ ስራዎች በተቻለ መጠን በራስ መወጣት ያስፈልጋልም ሲሉ ተናግረዋል።
በቀላሉ ልንደሰትባቸው በሚያስችሉን አነስተኛ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እና ጭንቀትን ማስወገድ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #centenarian #drives #longlife #merryfelipe

"ታሪክ ይፈርዳል ሕዝብ ይመሰክራል እውነት ለዘላለም ይኖራል!"
#ethiopia | እኔ ለኢትዮጵያ የተወለድሁ በኢትዮጵያ ያደግሁ ለኢትዮጵያም ሕይወቴን ለመስጠት በቃልኪዳን የቆምኩ ኩሩ ወታደር ነበርኩ ።
ወታደርነት ዩኒፎርም መልበስ ወይም መሣሪያ መታጠቅ ብቻ አይደለም ። ወታደርነት ማለት የሀገርን ክብር በነፍስ መጠበቅ የሕዝብን ተስፋ በደም ማቆየት የነፃነትን አደራ በትውልድ ላይ ማስቀጠል ነው።
ወታደር ማለት ሀገር ነው።
ሀገር ደግሞ በካርታ ላይ የተሳለ ድንበር ወይም ዝም ያለ መሬት አይደለችም።
ሀገር ማለት የአባቶች አደራ የእናቶች እንባ የጀግኖች መስዋዕትነት የሕፃናት ፈገግታ የወጣቶች ሕልም የአረጋውያን ተስፋ እና የመጪው ትውልድ እጣ ፈንታ ናት።
ሀገር ማለት
• የሕዝቧ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት
• የሕፃናት ያልተቋረጠ የነፃነት ሳቅ
• የእናቶች የልብ እፎይታ
• የወጣቶች ብሩህ ተስፋ
• በነፃነት የሚተነፈስ አየርና በፍትሕ የሚገነባ ነገ ናት።
እነዚህን ሁሉ ክቡር እሴቶች በደሙና በሕይወቱ ዋጋ የሚጠብቀው ወታደር ነው። ለእያንዳንዱ የሰላም ሰከንድ የማይታይ መስዋዕትነት አለ ከእያንዳንዱ የነፃነት ቀን ጀርባም የብዙ ጀግኖች ደምና ታሪክ ተጽፎበታል።
ዛሬም ሀገሬ ኢትዮጵያ በጠራችኝ ጊዜ ሁሉ ከፊት የመቆም ግዴታዬን እየተወጣሁ እገኛለሁ። በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ስለ ሰላም ስለ አብሮነት ስለ ሀገራችን ቀጣይነት ስለ ፍትሕና ልማት ስለ ትውልድ የሚተርፍ አንድነት ከወገኖቼ ጋር በኃላፊነትና በቅንነት እየተመካከርኩ ነው።
ዛሬ ሁላችንም በታሪክ ፊት ቆመናል።
በዚህ ወሳኝ ወቅት የምንናገረው ቃል የምንወስነው ውሳኔ የምንፈፅመው ተግባር በዘመናት መዝገብ ላይ ይቀረፃል።
ስለዚህ ከልዩነታችን በላይ የሚያስተሳስረንን ሀገራችንን እናስቀድማለን ።
ከጊዜያዊ ክርክር በላይ ዘላቂ ሰላምን እንመርጣለን ከመከፋፈል ይልቅ መተባበርን እናከብራለን።
የሕዝብን ተስፋ ለማደናቀፍ የመግባባትን መንፈስ ለማዳከም የሚሞክሩ ድምፆች ሊኖሩ ይችላሉ
ነገር ግን እውነት ከአሉባልታ ይበልጣል አንድነት ከመከፋፈል ይበረታል የሕዝብ ፍቅር ከጥላቻ ይልቃል።
እኛ ኢትዮጵያውያን ነን።
የልዩነታችን ውበት አንድነታችንን አያጠፋም ይልቁን ያጎለብተዋል።
ሰላምን በጽናት ፍትሕን በብልህነት ሀገርን በፍቅር እንገነባለን።
ለኢትዮጵያ የሕይወት ቃልኪዳን
"ሀገሬ ኢትዮጵያ ሆይ!
ለአንቺ የማልከፍለው ዋጋ የማልሰጥሽ ጥረት የማልከብርሽ ክብር የለም።
በጠራሽኝ ጊዜ ሁሉ በየትኛውም ስፍራና በየትኛውም ዘመን ለነፃነትሽ ለሰላምሽ ለአንድነትሽ እና ለክብርሽ እቆማለሁ።
ይህ የፖለቲካ ቃል አይደለም ።
የሕይወቴ ቃልኪዳን ነው።
ይህ የዛሬ ውሳኔ ብቻ አይደለም ። ለመጪው ትውልድ የተቀመጠ አደራ ነው።
አሉባልታ ይጠፋል
ውሸት ይደበዝዛል
ጊዜ ያልፋል
ነገር ግን የታሪክ እውነት የሕዝብ ፍቅር የሀገር ክብር እና የጀግኖች መስዋዕትነት ለዘላለም ይኖራሉ ።
ታሪክ በቃላት አይገነባም በመስዋዕትነት ይጻፋል።
ሀገር በምኞት አትፀናም በአንድነት ትቆማለች።
ሕዝብ በፍርሃት አያድግም በተስፋ ያብባል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ፍቅር በልጆቿ ጥረት በልጆቿ አንድነት ለዘላለም ፀንታ ትኑር !
ለሐገሬና ለሕዝቤ የተገባ የሕይወት ቃልኪዳን ።
አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ኢትዮጵያ)

3 months ago
ኢትዮጵያ የአፍሪካን አዲስ የቱሪዝም ካርታ በጥበብ እየሳለች ነው
******************
"ኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ናት" የሚለው የቆየ አስተሳሰብ ከጊዜ ጋር በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ ይገኛል። ዛሬ ኢትዮጵያ የሺህ ዓመታት ጥንታዊ ቅርሶቿን ከዘመናዊ የቱሪዝም ልማቶች ጋር በስምምነት እያጣመረች፣ ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች አዲስና ተመራጭ የጉዞ መስመር እየሆነች ነው።
ኢትዮጵያ ታሪክን፣ ተፈጥሮን፣ ባህልን እና ዘመናዊ መሠረተ-ልማትን በአንድ ወጥ የጉዞ ተሞክሮ ውስጥ አጣምራ የምታቀርብበት አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።
ዛሬ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ታሪኳን ብቻ አትተርክም፤ ይልቁንም አዲስ የቱሪዝም ታሪክ በተግባር እየጻፈች ትገኛለች። ለምሳሌ ያህል፣ በቅርቡ ተገንብተው ለፍሬ የበቁት የ"ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ታላላቅ ፕሮጀክቶች፣ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት፣ ዘመናዊ መናፈሻዎች፣ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች እና አረንጓዴ ስፍራዎች ኢትዮጵያን ከባህላዊ መዳረሻነት ወደ ዘመናዊ የጉዞ ልምድ እየቀየሯት ይገኛሉ።
በጎርጎራ የጣና ሐይቅ ዳርቻ ላይ የተገነቡት ዘመናዊ የመስተንግዶ ማዕከላት፣ በወንጪ የተራራ ሐይቅን የሚያቅፉት አስደናቂ የእይታ መድረኮች፣ እንዲሁም በሀላላ ኬላ የተፈጥሮንና የታሪክን ውበት የሚያሳዩት መዝናኛዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም ገጽታ በአዲስ መልክ የሳሉት ትልልቅ ስኬቶች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም የአንድነት ፓርክ፣ የወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ተፈጥሮ ፓርክ፣ የሳይንስ ሙዚየም እና የአዲስ አበባ አዳዲስ አረንጓዴ መናፈሻዎች የከተማ ቱሪዝምን ወደ ላቀ የደረጃ ማማ አሸጋግረውታል።
ነገር ግን ሀገራችን የዘመናዊ ቱሪዝም ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ስታስፋፋ የትናንት ታሪኳንና ማንነቷን ከቶም አልዘነጋችም። እንደ ላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የፋሲል ግቢ፣ የሰሜንና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮች፣ እሳተ-ገሞራማው የዳናኪል ምድር እና የአንትሮፖሎጂ መገኛ የሆነው የኦሞ ሸለቆ ያሉ ዓለም አቀፍ ቅርሶች ከአዳዲሶቹ መዳረሻዎች ጋር ተደምረው ለጎብኚዎች ልዩና ድንቅ የጉዞ ተሞክሮ እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ዓለም ዛሬ መዝናናትንና መጎብኘትን ብቻ ሳይሆን፣ የማይረሳ ሕያው ተሞክሮን አጥብቆ በሚሻበት በዚህ ዘመን፤ ኢትዮጵያ ያንን ፍላጎት በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በሕዝቦቿ ሞቅ ያለ ፈገግታና በዘመናዊ ልማቶቿ በአንድ ላይ አሟልታ ታቀርባለች። ዛሬ ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የምትጋብዝበት ምክንያት ትናንቷ ብቻ አይደለም፤ ብሩህ የሆነው ነገዋም ጭምር ነው። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ታሪኳን በአግባቡ ጠብቃ፣ የወደፊቱን የአፍሪካ የቱሪዝም ካርታ በበላይነት እየሳለች ያለች ታላቅ ሀገር መሆኗን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች።
በልዩ እሸቱ
#ebc #ethiopia #tourism #landoforigins #visitethiopia

(ዘ-ሐበሻ የመዝናኛ ዜና) በአምስተርዳም ጆሃን ክራይፍ አሬና በተካሄደው የሙዚቃ ድግስ ላይ፣ ቀይ የሚያበሩ ዓይኖች ያሉትና የሚያንጸባርቅ ጥቁር አቦሸማኔ የሚመስል ጭንብል አጥልቆ ወደ መድረክ ብቅ ሲል የተመልካቹ ጩኸት አዳራሹን አናጋው። ካናዳዊው-ትውልደ ኢትዮጵያዊ የዓለም ኮከብ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ)፣ እጁን ጭንብሉ ላይ አድርጎ ለጥቂት ሴኮንዶች ከቆመ በኋላ ፊቱን ሲገልጥ፤ ሰፊና ደማቅ ፈገግታው ታየ። በዚህን ጊዜ የአሬናው ድባብ በከፍተኛ ደስታ ሲሞላ፣ አቤልም "አምስተርዳም... ይህ እጅግ አስገራሚ አቀባበል ነው" በማለት በፈገግታ ሰላምታውን አቀረበ።
መድረኩ እጅግ አስገራሚ በሆኑና አይንን በሚማርኩ ትዕይንቶች የታጀበ ነበር። ዘ ዊክንድ በቀይ ካባ እና ሚስጥራዊ ጭንብል በተሸፈኑ ዳንሰኛ 'መነኮሳት' ታጅቦ ነበር መድረኩን የረገጠው። እነዚህ ዳንሰኞች፣ ሌዘር ከዓይኗ በሚፈነጥቅ እና የጥንቷን ግሪክ አፈ-ታሪክ ሜዱሳን በምትመስል ግዙፍ የወርቅ ሐውልት ዙሪያ እየዞሩ ያሳዩት ትዕይንት የሙዚቃ ዝግጅቱን ግርማ ሞገስ ልዩ አድርጎት ነበር።
ከአቤል መግባት በፊት አዳራሹን በከባድ የባዝ ድምጾች ሲያሞቅ የነበረው ፕሌይቦይ ካርቲ የተባለው አቀንቃኝ፣ ከዘ ዊክንድ የመጀመሪያ የሙዚቃ ዘመናት ጋር የሚመሳሰል ሚስጥራዊ እና ጥቁር የሙዚቃ ድባብን ፈጥሮ ነበር። ሆኖም በዚህኛው ምሽት ዘ ዊክንድ ይዞት የመጣው ድባብ፣ ዓለምን ያንቀጠቀጠበትን ደማቅ የሬትሮ-ፖፕ የሙዚቃ ስልቱን ነው።
የቆዳ ጃኬት ለብሶ እና ትልቅ የአልማዝ መስቀል በአንገቱ አስሮ መድረክ ላይ የወጣው አቤል፣ ፊቱ ላይ የነበረውን ጭንብል እንዳወለቀ ምንም ዓይነት ማቅማማት ሳይታይበት ማይኩን ተቆጣጠረው። ታዋቂዎቹን 'Starboy' እና 'Take My Breath' የተሰኙ ስራዎቹን ሲያዜም፣ ድምጹ እጅግ ጥርት ያለ እና ማራኪ ነበር። ዘና ብሎ የቅንጦት መነጽሩን አድርጎ ሲያቀነቅን አድናቂዎቹ በከፍተኛ ስሜት አብረውት ይዘምሩ ነበር። የተመልካቹን የደስታ ጩኸት ሲሰማም በአድናቆት "አምላኬ ሆይ... ዛሬ እኮ ድምጻችሁ አዳራሹን እያናጋው ነው!" በማለት ጥልቅ ስሜቱን አጋርቷል።
በመቀጠልም 'Call Out My Name' እና 'Save Your Tears' የተሰኙትን ልብ የሚነኩ ስራዎቹን በቀይ የብርሃን ድባብ ታጅቦ ሲያቀርብ፣ ወጣቶች ተቃቅፈው አብረውት ቃል በቃል ሲዘምሩ ታይተዋል። ከዝግጅቱ መጀመሪያ ላይ የነበረው ፕሌይቦይ ካርቲ 'Timeless' ለተሰኘው የጋራ ስራቸው በድጋሚ ወደ መድረክ ብቅ ብሎ ታዳሚውን አዝናንቷል።
በመጨረሻም፣ በስፖቲፋይ የዓለማችን የምንግዜም ከፍተኛ ማዳመጫ በማግኘት ክብረ-ወሰን የያዘው ታዋቂው 'Blinding Lights' የሙዚቃ ድግሱን በከፍተኛ ድምቀት ቋጭቶታል። አቤል ተስፋዬ ከዓመታት በፊት በቶሮንቶ ጎዳናዎች ማንነቱ ሳይታወቅ በድብቅ ይለቃቸው ከነበሩት ስራዎች ተነስቶ፣ ዛሬ ላይ የዓለማችንን ትላልቅ መድረኮች በሚሊዮን ከሚቆጠሩ አድናቂዎቹ ጋር በአንድነት እያንቀጠቀጠ መሆኑን በዚህ አስደናቂ ምሽት በተግባር አስመስክሯል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የዘመናችን ታላቁ የእግር ኳስ ጠበብት እና በባርሴሎና የቀኝ መስመር ላይ የክብሩ ወራሽ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ድንቁ ወጣት... እሁድ ዕለት አርጀንቲና ከስፔን በሚያደርጉት የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ይፋጠጣሉ። ሊዮኔል ሜሲ በ39 ዓመቱ፣ ላሚን ያማል ደግሞ ገና በ19 ዓመቱ በዚህ ታላቅ የእግር ኳስ መድረክ ላይ መገናኘታቸው፣ የሜሲን አስደናቂ ጽናት እና የያማልን ልዩ የተፈጥሮ ተሰጥኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው።
ይሁን እንጂ የሁለቱ ተጫዋቾች መንገድ ሲገናኝ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ጊዜው እ.ኤ.አ 2007 ነበር፤ የ20 ዓመቱ ወጣት ሊዮኔል ሜሲ በባርሴሎና ዋናው ቡድን ውስጥ ቋሚ ተሰላፊ መሆን በጀመረበት በዚያን ወቅት፣ ላሚን ያማል ገና የ5 ወር ጡት ጠባቂ ሕፃን ነበር። ይህን አስገራሚ ታሪካዊ አጋጣሚ በካሜራው ሌንስ ያስቀረው ፎቶግራፍ አንሺ ጆአን ሞንፎርት ነው። ፎቶግራፎቹ ከሁለት ዓመት በፊት ያማል ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ዩሮ 2024ን ሲያነሳ፣ አባቱ «የሁለት ጀግኖች ጅማሮ» በሚል ጽሑፍ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እስካጋራው ጊዜ ድረስ ተዘንግተው ቆይተው ነበር። በምስሉ ላይ ፊቱ በፈገግታ የተሞላው ሜሲ፣ ከዓመታት በኋላ የእሱን የእግር ኳስ ፈለግ በጥብቅ የሚከተለውን አንድ ትንሽ ሕፃን በውሃ ገንዳ ውስጥ እያጠበና እያጫወተ ይታያል።
ፎቶግራፍ አንሺው ጆአን ሞንፎርትሲናገር "...ይህ እውነተኛ የዕጣ ፈንታ ተአምር ነው" ይለዋል። "ይህን ታሪክ ለፊልም ጽሑፍ ብታቀርበው እንኳን አሳማኝ አይሆንም። ከምትገምተው በላይ እጅግ ልዩ የሆነ ነገር ስታገኝ የሚሰማህ ስሜት ነው" በማለት ይገልጸዋል።
የፎቶግራፍ መነሳቱ መርሃ ግብር የተከናወነው በባርሴሎናው ካምፕ ኑ ስታዲየም የመልበሻ ክፍል ውስጥ ነበር። የያማል ቤተሰቦች በወቅቱ እዚያ ሊገኙ የቻሉት በእጣ አሸናፊነት ነው። ትውልደ ሞሮኳዊው አባቱ ሙኒር ናስራውይ እና ኢኳቶሪያል ጊኒያዊቷ እናቱ ሺላ ኢባና፣ በልጅነታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ካታሎንያ ከመጡ በኋላ ነበር የተዋወቁት። ላሚን ያማል የመጀመሪያ ልጃቸው ሲሆን፣ እሱ በተወለደበት ወቅት የካታላኑ ስፖርት ጋዜጣ ከባርሴሎና ማሊያ ስፖንሰር ዩኒሴፍ (Unicef) ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የእጣ ውድድር ላይ ተሳትፈው አሸናፊ ሆኑ። የውድድሩ አሸናፊዎች ከባርሴሎና ዋናው ቡድን ተጫዋች ጋር የልጃቸውን ፎቶግራፍ በሙያዊ መንገድ የማንሳት ዕድል ያገኛሉ። የያማል ቤተሰቦች በዕለቱ ስታዲየም ሲደርሱ፣ በዕጣ ፈንታ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር እንዲነሱ ተመደቡ።
ፎቶግራፍ አንሺው ሞንፎርት ያንን ቀን ሲያስታውስ፣ "ሜሲ በጣም አይን አፋር እና ዝምተኛ ልጅ ነው። ወደ መልበሻ ክፍሉ ገብቶ በድንገት ከዚህ ሕፃን ጋር ፎቶ መነሳት እንዳለበት ሲነገረው፣ ሕፃኑን ምን እንደሚያደርገው ግራ ገብቶት ፊቱ ተለዋውጦ ነበር" ይላል። "ለአንድ ወጣት ልጅ ከባድ ቢሆንም፣ ላሚን ግን በጣም ደስተኛ እና ፈገግታ የማያጣ ሕፃን ነበር። እናቱ ሺላም ታግዘን ነበር፤ በጣም ደሀ ቤተሰቦች ቢሆኑም አብሮ ለመስራት እጅግ ጥሩ ሰዎች ነበሩ። ሜሲ እንዲህ ባሉ ነገሮች ላይ ሁልጊዜም ፕሮፌሽናል ስለሆነ፣ ከሁኔታው ጋር ቶሎ ተላመደ።"
ላሚን ያማል ሰኞ ዕለት 19ኛ ዓመቱን ሲያከብር፣ አስገራሚ የእግር ኳስ ጉዞን አስመዝግቧል። ሜሲ 19 ዓመት ሲሞላው 11 የክለብ ግቦችን አስቆጥሮ አንድ የላሊጋ እና አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፎ ነበር። ያማል ግን በአንጻሩ 56 ግቦችን ከመረብ አሳርፎ፣ ሦስት የላሊጋ ዋንጫዎችን፣ አንድ የኮፓ ዴል ሬይ እና የዩሮ 2024 ዋንጫን ማንሳት ችሏል።
የሚገርመው ነገር «ያማል» የልጁ የአባት ስም ሳይሆን፣ ሁለተኛው መጠሪያ ስሙ መሆኑ ነው። ሙሉ ስሙ ላሚን ያማል ናስራውይ ኢባና ሲሆን፣ በማሊያው ጀርባ ላይ የሚጠቀመው የመጀመሪያዎቹን ሁለት ስሞቹን ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ፣ እሱ በሚወለድበት ወቅት ቤተሰቡ በከፍተኛ የገንዘብ ችግር ውስጥ ወድቆ በነበረበት ሰዓት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉላቸው ሁለት የቅርብ ወዳጆቻቸው ክብር ሲሉ አባቱ ቃል በገባው መሠረት የተሰየመ ነው።
በአረብኛ «ላሚን» ማለት ታማኝ ማለት ሲሆን፣ «ያማል» ደግሞ የጀማል ሌላኛው አጠራር ሆኖ ውበት ወይም ግርማ ሞገስ ማለት ነው። ያማል ባስቆጠራቸው ግቦች ላይ በጣቶቹ «3-0-4» የሚል ምልክት በማሳየት ደስታውን ይገልጻል፤ ይህ ደግሞ ያደገበትንና ከባርሴሎና 20 ማይል ርቃ የምትገኘውን የሮካፎንዳ ሰፈር የፖስታ ኮድ የሚያመላክት ነው። ያማል ስለ ቤተሰቦቹ ሲናገር... "ወላጆቼ ያደረጉልኝን ነገር እኔ ልጄ ላልሆነ ሰው ማድረግ አልችልም። ገንዘብ ከሌለህ ልጅህ እግር ኳስ እንዲጫወት መርዳት በጣም ከባድ ነው፤ ወላጆቼ ግን ይህን ሁሉ አሳክተዋል። ውለታቸውን መቼም ልመልስላቸው አልችልም" ብሏል።
ለካታላኑ እና የባርሴሎና ደጋፊ ለሆነው ፎቶግራፍ አንሺ ሞንፎርት፣ የሁለቱ ተጫዋቾች በዓለም ዋንጫ የፍጻሜ መድረክ ላይ መገናኘት ከሁለት አሥርት ዓመታት በፊት ለጀመረው ታሪክ ፍጹም ማሳረጊያ ነው። የ58 ዓመቱ ሞንፎርት፣ "የታሪካቸውን ዑደት እየዘጋን ይመስለኛል፤ አስደሳች ፍጻሜ ነው። እኔ የባርሴሎና ደጋፊ ነኝ፤ ለሜሲ የእግር ኳስ ህይወቱን ሁለተኛውን የዓለም ዋንጫ በማንሳት ቢያጠናቅቅ ፍጹም ይገባዋል እላለሁ። ላሚን ደግሞ ገና ወደፊት የዓለም ዋንጫን የሚያነሳበት ብዙ ጊዜ አለው። ነገር ግን ስፔን እና ላሚን አሁን በጥሩ ሞራል ላይ ይገኛሉ፤ ይህንን ዋንጫ ቢያነሳ ከሌሎች ክብሮቹ ሁሉ የላቀ ይሆናል። ስለዚህ ምርጫው ለእኔ በጣም ከባድ ነው፤ ልቤ ለሁለት እየተሰነጠቀ ነው" በማለት ስሜቱን ገልጿል።

ዶናልድ ትራምፕን የምትመስለው ስፔናዊቷ ገበሬ የመገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ ሆናለች!
በሰሜን ምዕራብ ስፔን ገጠራማ ስፍራ (ጋሊሲያ) የምትኖረው ዶሎሬስ ሌይስ አንቴሎ የተባለችው አዛውንት፣ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባላት አስገራሚ መመሳሰል የተነሳ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በድጋሚ ከፍተኛ ትኩረት እየሳበች ትገኛለች።
እ.ኤ.አ. በ2018 ስለ ገጠር ህይወት የሚዘግብ አንድ ጋዜጠኛ የዕድሜ ባለጸጋዋን ዶሎሬስን በፈረንቃ (አካፋ) ተደግፋ በፎቶ ካሜራው አስቀርቷት ነበር። በፎቶው ላይ ያላት የፀጉር ቀለም፣ የፊት አወቃቀር እና አስተያየት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ፍጹም አንድ አይነት በመሆኑ በወቅቱ ዓለምን አስገርሞ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ምስል አሁን በ2026 በድጋሚ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት እየተጋራ ይገኛል።
የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የሁለቱን ምስሎች ጎን ለጎን በማነፃፀር "መንትዮች ናቸው" እስከማለት ደርሰዋል።
ዶሎሬስ ይህንን አጋጣሚ በጣም በሚያስቅ ሁኔታ የተቀበለችው ሲሆን፣ በወቅቱ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ በሰጠችው አስተያየት፦ "ምስሌ በጣም ሩቅ ቦታ የተጓዘ ይመስላል፤ እኔ እንደማስበው ግን ይህ የሆነው በፀጉሬ ቀለም ምክንያት ነው" ስትል በፈገግታ ተናግራለች።
ይህ ድንገተኛ ዝና በገጠሯ ስፔን የምትመራውን ቀለል ያለ የግብርና ህይወት አላስተጓጎላትም፤ ይልቁንም አሁንም ድረስ በደስታ ስራዋን እየቀጠለች ትገኛለች ነው የተባለው።
Seledadotio

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ከተማ በሆነችው ሲያትል ውስጥ የምትኖረው ሰላም... የ25ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ለማክበር በከፍተኛ ጉጉትና ደስታ ላይ ነበረች። በስደት ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው እርስ በእርስ መደጋገፋቸው የተለመደ እንደመሆኑ፣ ሰላምም ከልጅነቷ ጀምሮ አብራት ካደገችውና አሁን በሎስ አንጀለስ ከምትኖረው የልብ ጓደኛዋ ሄለን ጋር የማይነጥቅ ወዳጅነት ነበራት። ሄለን ለሰላም ልደት ልትመጣ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተዋታል። ሰላም የሀገር ቤት ባህላዊ ምግቦችን እያዘጋጀችና ቤቷን በጉጉት እያስተካከለች የልብ ጓደኛዋን ትጠብቅ ነበር።
በዚህ መሃል በስራዋ ኮምፒውተር ላይ የኢሜል መልዕክት መድረሱን የሚጠቁም ድምጽ ተሰማ። የላከችው ሄለን ነበረች። ሰላም የበረራዋን መረጃ ወይም ሰዓት የላከችላት መስሏት በፈገግታ ከፈተችው። ነገር ግን ኢሜሉ ሄለን ከአክስቷ ጋር ስታደርገው የነበረው ረጅም የኢሜይል ልውውጥ በስህተት ለሰላም 'Forward' የተደረገ ነበር። ሰላም መጀመሪያ ላይ በቸልተኝነት ማንበብ የጀመረች ቢሆንም፣ ወደ ታች በወረደች ቁጥር ግን ያነበበችው ነገር ልቧን እንደ መስታወት ሰባበረው፤ መተንፈስም አሳጣት።
ሄለን ለአክስቷ በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንዲህ የሚል አስደንጋጭ አረፍተ ነገር ሰፍሮ ነበር... "ሰላም ፊቷ በጣም ማራኪና ቆንጆ ነው፣ ነገር ግን ያን ያህልወፍራም ሆና ከልቡ የሚወዳትን ወንድ ፈጽሞ ልታገኝ አትችልም" የሚል። ህመሙ እና ክህደቱ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ሄለን በመቀጠል ሰላም በጋራ የሚያውቋቸውን ጓደኞቻቸውን እንደምትበድል፣ እንዲሁም ከተለያዩ ወንዶች ጋር እንደምታድር የሚገልጹ፣ ፈጽሞ ከእውነት የራቁና ስሟን የሚያጠፉ የፈጠራ ወሬዎችን በዝርዝር አስፍራለች። ሰላም ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ "አንጀትና አንገት" ሆነው የኖሩት ጓደኛዋ፣ ከጀርባዋ እንዲህ ያለ የክፋት ምላስ ይዛ መገኘቷን ስታይ ሆዷን አገላበጣትና የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰማት።
ገና የኢሜሉን አስከፊ ውሸቶች አንብባ ሳትጨርስ...በቢሮ ስልኳ ላይ የሄለን ስም ብልጭ አለ። ስልኩን ስታነሳው ሄለን በከፍተኛ ድንጋጤና በመንተባተብ "ሰላሜ... በስህተት የላክሁት ኢሜል አለ! እባክሽ ዝም ብለሽ አጥፊው፣ እንዳታነቢው!" ስትል ተማጸነች። ነገር ግን ሁሉም ነገር ረፍዶ ነበር። ጭምብሉ ተገፏል፤ እውነተኛው ማንነትም በግልጽ ወጥቷል። ሰላም በስልኩ ላይ ምንም ሳትናገር፣ የውስጧን ከባድ እንባ አምና ስልኩን ዘጋችው። በመቀጠልም ሄለንን "እንዳትመጪ፣ የበረራ ትኬትሽን ሰርዢ" የሚል አጭርና ግልጽ መልዕክት ሰደደችላት።
ያ ምሽት ለሰላም የለቅሶ ምሽት ቢሆንም... የ25ኛ ዓመት ልደቷ ግን በህይወቷ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተላት ትልቅ የብርሃን ቀን ሆነ። ሰላም የሰው ልጅ ዋጋ በሰውነቱ ቅርጽ፣ በክብደቱ ወይም ሌሎች ስለ እሱ በሚያወሩት አሉባልታ እንደማይለካ በተግባር የተረዳችበት አጋጣሚ ሆነ። በስደት ህይወት ውስጥ "ጓደኛ" መስለው ከጀርባ ምላጭ የሚሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅና ራስን ማክበር ትልቅ የህይወት ብስለት መሆኑን ተገነዘበች። ከራሷ ጋር ሰላም አውርዳ፣ በራሷ ተማምና እና ይቅርታ አድርጋ መኖር የጀመረች ሲሆን፣ ይህ ታሪክ በስደት ላሉት ለእነዚህ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሴቶች እውነተኛውን የጓደኝነት ትርጉም ያስተማረ ትልቅ የህይወት መማሪያ ሆኗል።

Comments