7 days ago
የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ቁጥጥር ይደረጋል!
- የሚዲያ ተቋማትና አስተዋዋቂዎች ተጠያቂዎች ናቸው
#ethiopia | አዳማ — የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና ጤና አገልግሎት ቁጥጥር ባለሥልጣን የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ለሕዝብ ከመሰራጨቱ በፊት በሕግና በሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ፣ እውነተኛና አሳሳች ያልሆነ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የማስታወቂያ ቁጥጥር መመሪያ መኖሩን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ በአዳማ ክሎቨርዴል ሆቴል ዛሬ ባዘጋጀው የሚዲያ ግንዛቤ መድረክ፣ የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ቁጥጥርን በተመለከተ ለሚዲያ አካላት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የምግብ ምዝገባና ፈቃድ ባለሙያዋ ዳግማዊት ንጋቱ እንዳብራሩት፣ የማስታወቂያ አሰራጮች ከአስተዋዋቂዎች የሚቀበሉት መረጃ ትክክለኛነትና ማስታወቂያው የቁጥጥር መመሪያውን ማሟላቱን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው።
በመመሪያው መሠረት የማስታወቂያ አሰራጭ ድርጅቶች በባለሥልጣኑ የተሰጠ ሕጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸው እንደሚገባና ባለሥልጣኑ በሚጠይቅበት ጊዜ ያስተላለፏቸውን ማስታወቂያዎች ቅጂና አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ያልተረጋገጡና የተጋነኑ የጤና ጥቅም ጥያቄዎች አይፈቀዱም
የምግብ ማስታወቂያዎች በተገቢ ሳይንሳዊ ማስረጃ ያልተደገፉ የጤና ጥቅም ወይም የፈውስ ተግባር እንዳላቸው አድርገው ማቅረብ እንደማይችሉ ተመላክቷል።
እንዲሁም “ብቸኛ”፣ “ለመጀመሪያ ጊዜ”፣ “ከዚህ ቀደም ያልነበረ”፣ “የሁሉም ምርጫ”፣ “ልዩ” እና “አንደኛ” የመሳሰሉ የተጋነኑ መግለጫዎች በተገቢው ማስረጃ ሳይደገፉ መጠቀም እንደማይፈቀድ ተገልጿል።
የአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ ላይ ገደቦች
መመሪያው የአልኮል መጠጦች ለጤና ተስማሚ፣ ለማህበራዊ ስኬት ወይም ለአካላዊ ብቃት ጠቃሚ እንደሆኑ አድርጎ ማስታወቅን ይከለክላል።
በተጨማሪም ከ12 በመቶ በላይ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦችን ከቤት ውጭ ማስታወቂያ በስተቀር በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች ማስታወቅ ላይ ገደቦች መኖራቸው ተጠቁሟል።
ከዚህ ባለፈ አካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናትን በአልኮል ማስታወቂያ ላይ መጠቀም፣ በሕፃናት ፕሮግራሞች ላይ የአልኮል ማስታወቂያ ማስተላለፍና ከ12 በመቶ በላይ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦች አምራቾች ወይም ነጋዴዎች ፕሮግራሞችን ስፖንሰር ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል።
የጨቅላ ሕፃናት ምግብ ማስታወቂያ
የጨቅላ ሕፃናት ምግብን በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በጋዜጣና በኢንተርኔት ጨምሮ በማንኛውም የሚዲያ መድረክ ማስታወቅ እንደተከለከለ ተብራርቷል።
በምርቶቹ ማሸጊያ ላይም ከእናት ጡት ወተት ጋር ማወዳደር ወይም “የማይተካ” የሚሉ መግለጫዎችን መጠቀም እንደማይፈቀድ ተጠቁሟል። በሽያጭ ቦታዎች ናሙና መስጠትና የዋጋ ቅናሽ ማስታወቂያ መለጠፍም ከተገደቡት ተግባራት መካከል ናቸው።
ሕፃናትን ያማከሉ ማስታወቂያዎች
ሕፃናትን ያማከሉ ማስታወቂያዎች የልጆችን ዕድሜና የማስተዋል ደረጃ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው ተገልጿል።
አንድ ምግብ የተጠቀመ ልጅ ካልተጠቀመ ልጅ በላይ የማህበራዊ ወይም የአእምሮ ብልጫ እንዳለው ማሳየትና ሕፃናት ፈጣን ምግቦችን ከመጠን በላይ እንዲወስዱ ማበረታታት እንደማይፈቀድ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የግለሰቦችን ምስክርነት ወይም የግል ልምድ በመጠቀም ስለ አንድ ምግብ ጣዕም፣ ይዘት ወይም ጥቅም ማስታወቅ በመመሪያው የተገደበ መሆኑ ተብራርቷል።
ለሚዲያ ተቋማት የተሰጠው መልዕክት
የምግብ ምርት ማስታወቂያን ከማስተላለፍ በፊት ይዘቱ ከተደነገጉት የሕግና የቁጥጥር መስፈርቶች ጋር መጣጣሙን ማረጋገጥ የሚዲያና የማስታወቂያ አሰራጭ ተቋማት ኃላፊነት መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
መመሪያው ከነሐሴ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና መሆኑን የገለጸው ማብራሪያው፣ መመሪያውን በመጣስ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ለሚያስተላልፉ አካላት ሕጋዊ ተጠያቂነት ሊያስከትል እንደሚችል አመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#adama #media #foodregulation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

9 days ago
የወባ መድኃኒቶችን ጨምሮ 15 ህገ ወጥ የመድኃኒት አይነቶች ተከማችተው መገኘታቸው ተገለጸ
👉🏼ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተቆጣጣሪ አካላት ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ በአርባ ምንጭ ከተማ ከፖሊስ ጋር በመተባበር ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የወባ መድኃኒቶችን ጨምሮ 15 ህገ ወጥ መድኃኒት አይነቶች በአንድ ቦታ ተከማችተው መያዛቸውን አስታውቋል፡፡
በባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ የመድኃኒት ጥራት እና ደህንነት ክትትል ክፍል አማካሪ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደማርያም ይህ የተገኘው ተቋሙ ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል።
መድኃኒቶቹ በተለያየ ህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ መሆናቸው አንስተው ተከማችተው ከተገኙ ህገ ወጥ መድኃኒቶች ውስጥ አርቴሱኔት እና ክሎሮኪን የተባሉ የወባ ህክምና መድኃኒቶች ይገኙበታል ብለዋል።
መንግስት ከሚያቀርበው የወባ መድኃኒት ውጪ እንደዚህ አይነት ያልተረጋገጡ መድኃኒቶች ወደ ገበያ መግባታቸው ታካሚዎች ፈውስ እንዳያገኙ ከማድረጉም በላይ ለከፋ አደጋ እንደሚያጋልጣቸው ገልጸዋል።
ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ጥራታቸው እና ፈዋሽነታቸው በላብራቶሪ ተረጋግጦ እውቅና የተሰጣቸው መድኃኒቶች የሚመዘገቡበት መረጃ ቋት ያለው ቢሆንም በአርባ ምንጭ ከተማ የተያዙት እነዚህ 15 መድኃኒቶች አይነቶች ሲፈተሹ ግን የተፈቀዱ የመድኃኒት ዝርዝር ውስጥ ያልተመዘገቡ ናቸው ብለዋል።
በአርባ ምንጭ ከተማ የተያዙት መሰል ህገ ወጥ መድኃኒቶች በባህር ዳር ፣ ድሬዳዋ ፣ መቀሌ እና በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ መድኃኒቶችን ሲገዛ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እንዲሁም የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ስርጭት እና አጠቃቀማቸውን እንዲቆጣጠሩ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

10 days ago
በማንቸስተር ዩናይትድ «ኦልድ ትራፎርድ» ስታዲየም ጸሎት ተደረገ
#ethiopia | በማንቸስተር ዩናይትድ «ኦልድ ትራፎርድ» ስታዲየም በናይጄሪያዊው ፓስተር ጄሪ ኢዜ በተመራው ታላቅ የጸሎት ጉባኤ ላይ በ75 ሺ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች መሳተፋቸው ተገለጸ።
«ስትሪምስ ኦፍ ጆይ ኢንተርናሽናል» በተሰኘው አገልግሎት የተዘጋጀው ይህ «NSPPD UK Prayer Conference» የተሰኘው ጉባኤ፤ ከመላው እንግሊዝ እና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወጣጡ ክርስቲያኖችን ለአንድ ቀን የጸሎት፣ የምስጋና እና የአምልኮ ጊዜ አንድ ላይ አሰባስቧል።
በቅድሚያ ምዝገባ ይጠይቅ የነበረው ይህ መርሃ ግብር፣ እስከ 74 ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለውን ታሪካዊውን ስታዲየም ሙሉ በሙሉ በምእመናን አጥለቅልቋል።
በጉባኤው ላይ እንደ መርሲ ቺንዎ ፣ ደንሲን ኦየካን ፣ ሰንሚሶላ አግቤቢ እና ኬስትሪንግስ ያሉ የወንጌል ዘማሪዎች አምልኮን መርተዋል።
ፓስተር ጄሪ ኢዜ በየዕለቱ በኢንተርኔት አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚስበው «ኒው ሲዝን ፕሮፌቲክ ፕሬየርስ ኤንድ ዲክላሬሽንስ» (NSPPD) የተሰኘው ታዋቂ የጸሎት መድረክ መስራች ሲሆን፤ በናይጄሪያ፣ በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በካናዳ ቅርንጫፎች ያሉት «ስትሪምስ ኦፍ ጆይ» ቤተክርስቲያን መሪ ነው።
የዘንድሮው የማንቸስተር ጉባኤ ቀደም ሲል በለንደን ከተማ ከተካሄዱት ተመሳሳይ ታላላቅ የጸሎት መርሃ ግብሮች ቀጥሎ የተደረገ ሲሆን፣ያለፈውጰሁለት ዓመት በትዊከንሃም ስታዲየም በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መሳተፋቸው ይታወሳል።
የNSPPD ተከታዮች በየዕለቱ በሚደረጉት እነዚህ የጸሎት ፕሮግራሞች ላይ የተለዩ ተአምራት እና የፈውስ ምስክርነቶች እንደሚስተናገዱ ይናገራሉ።
ከመርሃ ግብሩ ፍጻሜ በኋላ ፓስተር ጄሪ ኢዜ በኢንስታግራም ገጹ ባሰፈረው ስሜታዊ መልእክት «ይህንን ሁሉ ያደረግኸው አንተ እንደሆንክ እኔና አንተ እናውቃለን፤ ልቤ በደስታ ተሞልቷል... እኔን ሁልጊዜ የምትረዳው ጌታ» ሲል የጸሎት ጉባኤው ስኬት ከአቅም በላይ እና በቃላት የማይገለጽ እንደነበር አስታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

14 days ago
የመደመር አንቀጽ
የመደመር ዕሳቤ ደግሞ መፈራረስና መጠፋፋትን ሳይሆን መገንባትንና አብሮነትን፤ ሥርዓት አልበኝነትንና ዝብርቅርቅነትን ሳይሆን ሥርዓታዊ መያያዝን፤ ብሎም ወደ ጋራ ግብ አብሮ መፍሰስንና መገሥገሥን የሚያስተምር ነው።
በቀውስ መሐል ፈውስ፣ በመፈራረስ ውስጥ መታደስ፣ ተበታትኖ በመጥፋት መካከል ተሰባስቦና ተጣምሮ በአዲስ ጉልበት መነሣት የመደመር መንገድ ነው።
ሀገራችንም በዚህ የመደመር መንገድ እንድትጓዝና ከገባንበት አፍራሽና በታታኝ አካሄድ ነጻ እንድትወጣ ያስፈልጋል።
ከዚህ ተላቅቃ ወዳለምንላት የብልጽግና ማማ እንድትወጣ ወደ አዎንታዊ ተጓዳኝነትና ብዝኃነትን ወደማይጨፈልቅ አንድነት መሻገር ይገባናል።
የመደመር መንግስት
ገፅ 66
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስት

Sponsored by
Surafel
15 days ago
ቅዱስ ሩፋኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ !
ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ🙏
ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ስሙም ከሚካኤልና ከገብርኤል ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ ይቀመጣል፡፡ በመጽሐፈ ጦቢት 12÷15 “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” ይላል፡፡ ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል፡፡ ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡ በሉቃስ 13÷6-9፣ ዘካርያስ 1÷12 እንደተጻፈው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቋረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነው፡፡ ፈዋሴ ዱያን፡ ሕሙማንን የሚፈውስ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ምድር ላይ እየተመላለሰ ሲያስተምር ድውያነ ሥጋን በተአምራት ድውያነ ነፍስን ደግሞ በትምህርቱ ይፈውስ ነበር፡፡ መድኃኒትነት ለእርሱ የባህሪው ነው፡፡ የማዳንን ጸጋ ለቅዱሳን ሰጥቷል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ድውያንን ይፈውሱ ነበር፡፡
ከቅዱሳን መላእክትም ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኃጢአት ቍስልና በሰውነታችን ላይ ከሚወጣው ደዌም ሆነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የሚረዳ መልአክ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክ 10÷13 “በበሽታ ዅሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ለቆሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው መልአክ ነው፡፡ ዛሬም ሁላችንን በአማላጅነቱ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ይፈውሰናል፣ ይጠብቀናልም፡፡ እግዚአብሔር የመካኒቱን ማኅፀን ፈትቶ የተባረከ ልጅን የሚሰጥ አምላክ ነው፡፡ ይህ ስልጣን ከተሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው፡፡ በብሉያና በአዲስ ኪዳን ብዙ እናቶች ከመካንነት የተነሳ ሀዘን ጸንቶባቸው ቢቆይም ምንም የማይሳነው አምላክ እጅግ ድንቅን ያደረጉ የተባረኩ ልጆችን ሰጥቷቸዋል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ የይስሐቅ እናት ሣራ፣ የያዕቆብ እናት ርብቃ፣ የዮሴፍ እናት ራሄል፣ የሶምሶን እናት እንትኩን፣ የነቢዩ ሳሙኤል እናት ሐና፣ የመጥምቀ መለኮት የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ፣ የድንግል ማርያም እናት ቅድስት ሐና ይገኙበታል፡፡ አዋላጅ ብትኖር ባትኖርም ሐኪም ቅዱስ ሩፋኤል አይታጣም፡፡ በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ ሴቶች ሁሉ የመልአኩን መልክ አንግተው ማርያም ማርያም ይላሉ ማየ ጸሎቱን ጠጥተው ፈጥነው ይወልዳሉ፡፡ ሕፃናት በማኅፀን ሳሉ በሥላሴ አርአያ መልካቸው መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለዱበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃው አይለያቸውም፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ጭንቀታቸውን ያቀልላቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በተሰጠው ስልጣን አጋንንትን የሚያሳድድ መልአክ ነው፡፡
በራዕይ 8÷2 እንደተጻፈው ቅዱሳን መላእክት የሰውን ልጅን ጸሎት ከምድር ወደ ሰማይ የእግዚአብሔርን ምህረት ደግሞ ከሰማይ ወደ ምድር ያደርሳሉ፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሩፋኤል መዝገበ ጸሎትና አቃቤ ኆኅት ይባላል፡፡ “ሩፋኤል” የሚለው የስሙ ትርጓሜ “ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ” ማለት ነው፡፡ በሌላም መልኩ ይህ የከበረ ታላቅ መልአክ ሰሙ የዕብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት ውጤት ነው፡፡ “ሩፋ” ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን “ኤል” ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጠል ስመ አምላክ ነው:: “ሩፋኤል” የሚለው በጥምረት “ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ” የሚለውን ይተካል፡፡ በየዓመቱ ጳጉሜ ሦስትም በዓለ ሲመቱ ይከበራል፡፡ በዚህ ዕለትም ሰማይ ደጆች ተከፍተው የምህረት ዝናብ ይወርድልናልና አዝመራው ከክፉ ሁሉ ይጠበቃ፡፡ ገዳማውያንም ቅዱስ ሩፋኤል የተዘራውን እንዲባርክ በጸሎት ይጠይቁታል፡፡ ገዳማቸው እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

23 days ago
የመደመር አንቀጽ
የመደመር ዕሳቤ ደግሞ መፈራረስና መጠፋፋትን ሳይሆን መገንባትንና አብሮነትን፤ ሥርዓት አልበኝነትንና ዝብርቅርቅነትን ሳይሆን ሥርዓታዊ መያያዝን፤ ብሎም ወደ ጋራ ግብ አብሮ መፍሰስንና መገሥገሥን የሚያስተምር ነው።
በቀውስ መሐል ፈውስ፣ በመፈራረስ ውስጥ መታደስ፣ ተበታትኖ በመጥፋት መካከል ተሰባስቦና ተጣምሮ በአዲስ ጉልበት መነሣት የመደመር መንገድ ነው። ሀገራችንም በዚህ የመደመር መንገድ እንድትጓዝና ከገባንበት አፍራሽና በታታኝ አካሄድ ነጻ እንድትወጣ ያስፈልጋል።
ከዚህ ተላቅቃ ወዳለምንላት የብልጽግና ማማ እንድትወጣ ወደ አዎንታዊ ተጓዳኝነትና ብዝኃነትን ወደማይጨፈልቅ አንድነት መሻገር ይገባናል።
የመደመር መንግስት
ገፅ 66
#ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስ #ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስት Ethiopian Broadcasting Corporation

26 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት| የአምናዋ ሚስ ወርልድ አፍሪካ ሐሤት ደረጀ የአዲስ ዓመት መልዕክቷ እንዲህ ይነበባል፦ "በራሳችን የዘመን ቀመር አዲስ ምዕራፍን ዳግም መጀመር ልዩ የሆነ የውበት ስሜት አለው። አዲሱን ዓመት በደስታ ስንቀበል፣ ለምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለኝ ትልቅ ምኞት፤ ሰላም፣ እውነተኛ ፈውስ እና በአንድነት የምንፈነድቅባቸው በርካታ ምክንያቶች እንዲበዙላት ነው።
"አዲሱ 2019 ዓ.ም ሩህሩህ ቀናትን፣ ለወጣቶቻችን ሰፊ ዕድሎችን፣ እንዲሁም እያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ብሩህ ተስፋን ይዞልን ይምጣ።
ይህንን መልእክቴን ለምታነቡት ደግሞ፤ ለሰዎች የምታካፍሉት ጣፋጭ የምሥራች፣ አብረዋችሁ ደስታችሁን የሚያከብሩ ቅን ሰዎች፣ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ ስታልሙት የነበረውን ህልም እውን ለማድረግ የሚያስችል ወኔና ድፍረት ይስጣችሁ። ቆም ብላችሁ፣ "አምላኬ ሆይ... ለዚህች ቀን እኮ ነበር ስጸልይ የነበረው" ብላችሁ በደስታ የምታመሰግኑባቸው ልዩ አጋጣሚዎች በዓመቱ ውስጥ ይብዙላችሁ።
ከብዙ ፍቅር ጋር፣ መልካም የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት!
መልካም አዲስ ዓመት! 🤍🌼 እንቁጣጣሽ!

ይሄ ምን የሚሉት አገልግሎት ነው?
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ ሊምፖፖ ግዛት የሚገኘው የሴቨንፎልድ ሆሊ ስፒሪት ሚኒስትሪ መሪ ፓስተር ክሪስት ፔኔሎፔ በምዕመኖቻቸው ላይ አየር በመልቀቅ (ፈስ በመፍሳት) የፈውስ አገልግሎት ይሰጣሉ በሚል የቀረበባቸው ክስ ከፍተኛ አጀንዳ ሆኗል።
ይሁን እንጂ መጋቢው የቀረበባቸውን ወቀሳ ሙሉ በሙሉ በማስተባበል ድርጊቱ ተራ ድርጊት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ኃይል ለማሳየት የሚደረግና ከእምነት ጋር የተያያዘ ልዩ የፈውስ ሥነ-ሥርዓት እንደሆነ ይከራከራሉ።
ፓስተርዬ!! መጽሐፍ ቅዱስ ተገልብጦ ቢነበብ እንኳን የእግዚአብሔር ኃይል እንዲህ ያለ ትርጉም የለውም።
የአዕምሮ እክል ያለባቸው እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ህዝብ እየቀለዱ ነው።
ስለሆነም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ ትምህርትቶች መመለስ የሚበልጠው መፍትሄ ነው።
በእኛም ሀገር የሚስተዋሉ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዋ ልምምዶች እንቢ እንድንለው የሚያስፈልግ ነው።ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ክብር ፤ ለሰውም ጥቅም የላቸውምና።
“አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤” — ገላትያ 6፥7
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

28 days ago
የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት እና ምልጃቸው አይለየን🙏
ታላቅ ጻድቅ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ትውልዳቸው ግብጽ ንሒሳ ውስጥ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ሠላሳ ሦስት ዓመት በትዳር ሲቆዩ በሩካቤ ስጋ የተዋወቁት ለሦስት ቀናት ብቻ ነው፡፡ ይህም ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን እየለመኑ ነው፡፡ አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን “ክብሩና ሥልጣኑ ከሰማይ ከፍታ ከፍ የሚል ንጽሕናው ከሚካኤል ከገብርኤል የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነቢዩ ኤልያስ የሆነ ልጅ እንቺ ተቀበይ” የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ መጋቢት 29 ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ደም ግባቱ እጅግ ያማረ ዓይናችን በገለጽንበት ቅጽበት ከሚታይ ነገር ላይ እንደሚያርፈው ሁሉ በተወለደበት ቅጽበት አንደበቱ ሲያመሰግን የተገኘ፣ ወንድ ልጅ ወለደች። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ “የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን” አላት፡፡
ወዲያውም ሕፃኑ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገዶ “ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን” አለ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ባረከችው ቅዱሳን መላዕክት ዘወትር ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን አባ ዘመደ ብርሃን የተባሉ አባት ላሉበት ገዳም ሰጣቸው፡፡ እሳቸውም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማሩ አሳድገው ሲጨርስ ዲቁና ሰጡት ፍጹም የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታልና ሥራው ሁሉ በዕውቀት የተመላና የተቃና ሲሆን እንደ ቅዱስ እንጦንስም አስኬማ ሰጥተው አመንኮሱት፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀብለው በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡
እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ ወደ ሰማያት አርገው በረከትና ጸጋ የተቀበሉ፣ አጋንንትን የሚያሳድዱበት፣ ታላቅ ጸጋ ተሰጣቸው፡፡ ሰውነታቸው አንድ ክንድ ከስንዝር በሚረዝም ጠጉር የተሸፈነው አባታችን ወደ ሀገራችን መጥተው ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡
ከሰው ተለይተው ወደ ዱር ገብተው ከስድሳ አንበሶችና ከስድሳ ነብሮች ጋር የሚኖሩት አባታችን፣ እንስሳቱ እርሳቸውን የረገጡትን መሬት ልሰው ጠግበው ይኖራሉ። በሀገራች ያለውን የኃጢአት ስራ ባዩ ጊዜ በዝቋላ ሐይቅ አንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው መላው ኢትዮጵያን እንዲምርካቸው ጸልየው ቃል ኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው ዓለምን ንቀው ለጌታችን ተገዝተዋል፤ ገዳማቱን እንርዳ በዓታችውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

1 month ago
የ፴፻ ዓመታት ታሪክን ከፍልሰት እንታደግ!
“ዓይኖች ሁሉ ወደ ጣና ቂርቆስ ይሆናሉ!”
ለሦስት ሺህ ዓመታት ያህል የአባቶቻችንን እምነት፣ ታሪክና ቅርስ ጠብቆ ለትውልድ ያስተላለፈው ጥንታዊው ጣና ቂርቆስ ገዳም አሁን በገጠመው ችግር ምክንያት የሁላችንንም አስቸኳይ ድጋፍ ይሻል።
ይህን ታሪካዊ ቅርስና ቅዱስ ስፍራ ለመታደግ እንረባረብ!
በተዘጋጀው የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፍ፣ የበኩልዎን አሻራ ያኑሩ።
የቀጥታ ስርጭቱ በፈውስ መንፈሳዊ እና በሌሎች ሚዲያዎች ይተላለፋል።
ገዳሙን ለመርዳት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000016689843 (1527)
አሐዱ ባንክ
0085165811801 (1521)
አቢሲኒያ ባንክ
260616412 (1505)
ዳሸን ባንክ
5442102261011 (2115)
አባይ ባንክ
4491113090983013 (1521)
ታሪክ የሚኖረው በትውልድ እጅ ነው። ዛሬ የምናደርገው ድጋፍ የነገውን ቅርስ ይታደጋል!
ጣና ቂርቆስን እንታደግ!
ታሪካችንን እንጠብቅ!
ቅርሳችንን ለትውልድ እናስቀምጥ!
#ጣናቂርቆስ #ቅርሳችን #ታሪካችን #ኢትዮጵያ #የቅርስጥበቃ #ትውልድ

☦️ የ፴፻ (ሦስት ሽህ) ዓመታት ታሪክን ከፍልሰት እንታደግ! ☦️
“ዓይኖች ሁሉ ወደ ጣና ቂርቆስ ይሆናሉ”
ለሦስት ሺህ ዓመታት ያህል የአባቶቻችንን እምነት፣ ታሪክ እና ቅርስ ጠብቆ ለትውልድ ያቆየው ጥንታዊው ገዳማችን አሁን ላይ በገጠመው ችግር ምክንያት የእያንዳንዳችንን አስቸኳይ ድጋፍ ይሻል።
ይህንን ታሪካዊ ቅርስ እና ቅዱስ ስፍራ ለመታደግ በተዘጋጀው የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በመገኘት የበኩልዎ አሻራ እንዲያኖሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የቀጥታ ስርጭት መርሐግብሩ በፈውስ መንፈሳዊና በሌሎች ሚዲያዎች ይተላለፋል።
ገዳሙን ለመርዳት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000016689843(1527)
አሐዱ ባንክ 0085165811801(1521)
አቢሲኒያ ባንክ 260616412 (1505)
ዳሸን ባንክ 5442102261011 (2115)
አባይ ባንክ 4491113090983013 (1521)

''የአደይ አበባ ምንጣፍ..."
መስከረም ሲጠባ፣ ሰማዩ ከዳመናው ተላቆ ፊቱን ሲያጠራ፣ ምድሪቱ በአደይ አበባ ወርቃማ ቀሚስ ስታጌጥ፤ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ አዲስ ተስፋ ይፈነጥቃል።
በባህላችን አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፣ የይቅርታ፣ የእርቅ እና የዕድሳት ምዕራፍ ነው። "ያምናውን በአምና ትተን፣ አዲሱን በደስታ እንቀበል" እንደሚባለው፣ የቆየውን ቂምና ቁርሾ አሮጌው ዓመት ይዞት እንዲሄድ በማድረግ፣ አዲሱን ዘመን በንጹሕ ልብ የምንቀበልበት የብሩህ ተስፋ መግለጫ ነው። ይህ የተፈጥሮ ዑደት እና የአዲስ ዓመት ብርሃን፣ ዛሬ ላይ ሀገራችን ከደረሰችበት ሁለንተናዊ የከፍታ ምዕራፍ ጋር በጥልቅ ይስተጋባል።
እናም፣ ምድር በክረምት ዝናብ ታጥባ፣ አረንጓዴ ምንጣፏን ዘርግታ በቢጫው አደይ አበባ ስትደምቅ፣ በተፈጥሮ ላይ የሚታየው ይህ መታደስ ለሀገራችን የፖለቲካዊ ዕድሳት ተምሳሌት ጭምር ነው።
ልክ እንደ አደይ አበባው መፈካት ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ከረጅም የፖለቲካ ክረምትና ስብራት በኋላ ፊቷን ወደ መስከረም ብርሃን ሀገራዊ ምክክሯን አሳክታ ተመልሳለች።
ምድሪቱ በአደይ አበባ እንደምታጌጠው ሁሉ፣ የፖለቲካ ምኅዳራችንም በውይይት፣ በመቻቻል እና በጋራ መግባባት ማበብ ጀምሯል። ይህ ሀገራዊ ምክክር የትናንቱን ቁስል አድርቀን የነገውን ተስፋ የምንዘራበት የፈውስ ጉዞ ነው ። ክረምቱ የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን መስከረምን እንደማያስቀር ሁሉ፣ የፖለቲካ ፈተናዎቻችንም በሕዝቦች የጋራ ውይይትና መግባባት ተፈትተው ብሩህ ዘመን መቷል።
ደግሞ ...
ልክ የፖለቲካ ምኅዳራችን በሀገራዊ ምክክሩ አዲስ ተስፋ እንደፈነጠቀ ሁሉ፣ የኢኮኖሚውም መስክ ከክረምቱ ፈተና ወጥቶ የፍሬ ዘመኑን ማብሰር ጀምሯል። ይህ የዕድሳት መንፈስ በጉባ ብስራት ግዙፍ ፕሮጀክቶች የልማት ዜና ታጅቦ መምጣቱ አዲሱን ዘመን ይበልጥ ልዩ ያደርገዋል።
ክረምት የዘር፣ የድካም፣ የጭቃ እና የፈተና ጊዜ ነው፤ መስከረም ደግሞ የፍሬ፣ የብርሃንና የስኬት መገለጫ ነው። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያሳለፈቻቸው መዋቅራዊ ማነቆዎች ልክ እንደ ክረምት የትግል ጊዜ ነበሩ። አሁን ግን ሀገሪቱ እየተገበረች ያለው የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ማነቆዎችን በመፍታት እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በመቋቋም ኢትዮጵያ እንደምታከናውን በተግባር ወዳጅም ጠላትም በአይኑ አረጋግጧል።
ይህ የማከናወን አቅም በጉባ ብስራቶች በኩል በተጨባጭ የሚታይ ሲሆን፣ አገሪቱ በኃይል፣ በኢንዱስትሪ፣ በአቪዬሽን፣ በማዕድንና በከተማ ልማት ዘርፍ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍታለች ።
የቢሾፍቱ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ110 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን ለማስተናገድ የተነደፈው ፕሮጀክት፣ አገሪቱን የአፍሪካ ዋና የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ መገናኛ ኮሪደር በማድረግ የንግድ የበላይነታችንን ሲያስቀጥል ፤ የወደፊት የኃይል ፍላጎትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተጀመረው የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ እንዲሁም በጎዴ እየተገነባ ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካ ስኬት ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የኢንዱስትሪ ምዕራፍ ያሸጋግራታል።
የግብርና ምርታማነትን የሚያረጋግጠው ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና የውጭ ምንዛሪ ጫናን የሚያቃልለው የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት፣ አገሪቱን ከውጭ ጥገኝነት የሚያላቅቁ ስትራቴጂካዊ ርምጃዎች ናቸው።
ከቀናት በፊት በተግባር እንደ አዲስ አመት ስጦታ ገቢርነቱ የተሰማው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶችን ለመገንባት የተጀመረው ፕሮጀክት ፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር በቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር እርግጥ ነው ።
እነዚህ እርስ በርስ የተሰናሰኑ ግዙፍ የልማት ርምጃዎች በአጋጣሚ የመጡ ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያ በራሷ የመደመር መንገድ እና በረጅም ጊዜ አርቆ አሳቢነት የተመዘገቡ ድሎች ናቸው። የመደመር ጽንሰ-ሐሳብ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው በሀገራዊ ምክክሩ እንዲፈወሱ ከማድረግ ባለፈ፤ የውስጥ አቅምን አጠናክሮ የውጭ ተግዳሮቶችን የመመከት አቅማችንን በተግባር ያረጋገጠ መሠረት ነው።
በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለምን ስናስተናግድ፣ በኒውክሌርና በተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካው ኃይላችንን ስናጎለብት፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ አንገቷን ቀና አድርጋ ትራመዳለች። ይህም ብሔራዊ ጥቅሟን በክብር የምታስጠብቅበት የከፍታ ዘመን ማሳያ ነው።
ከተፈጥሮ መታደስ እስከ ፖለቲካዊ እርቅ፣ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እስከ ግዙፍ የጉባ ብስራት ፕሮጀክቶች ድረስ የምናየው እውነት አንድ ነው፤ ኢትዮጵያ የብልጽግና እና የኢኮኖሚ ነፃነት ታሪካዊ መሠረቷን በጽኑ ጥላለች።
አዲሱ ዓመት ልክ እንደ ፈካው የአደይ አበባ፣ እነዚህን ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አፍክተን የድካማችንን ፍሬ የምንበላበት ዘመን ይሆናል። እንግዲህ የትናንቱን የክረምት ፈተና፣ ድህነት እና መከፋፈል ከኋላችን ትተን፤ በአዲሱ ዓመት አንድነታችንን አጠናክረን ወደ ብልጽግናው ማማ በአደይ አበባ ምንጣፍ እንረማመድ።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

ጳጉሜ - የጊዜ ድልድይ፣ የትዝታና የተስፋ መገናኛ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሮጌው ዓመት መጨረሻና በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ መካከል ቆማ፣ ያለፈውን በትዝታ እያሰናበተች የሚመጣውን በተስፋ የምትቀበል አንዲት ልዩ ወር አለች፣ እርሷም ኢትዮጵያዊቷ ጳጉሜ ናት።
ጳጉሜ ቀናቷ አምስት ወይም ስድስት ብቻ ቢሆኑም የምትሸከመው ጥልቅ ትርጉም ግን ከቀናት ቁጥር ይረዝማል።
እሷ ያለፈውን ዘመን በአንድ ገጽ ላይ አጠናቃ ለአዲሱ ብሩህ ምዕራፍ መንገድ የምትከፍት፣ የትናንትና የነገ መገናኛ ድልድይ ናት። ወደ ኋላ ለመቅረት ሳይሆን ለጥቂት ጊዜ ቆሞ ይበልጥ ለመፍጠን እና ነገን አርቆ ለማየት የሚደረግ ውብ የመንፈስ ጉዞ ማሳያ ናት፣ ጳጉሜ፡፡
በኢትዮጵያዊያን ህሊና ውስጥ ይህች አጭር ወር የታሪክ ማጠፊያና የይቅርታ ወር ናት። ያለፈውን ዓመት ድካም፣ ጭንቅና ቅሬታ አራግፋ እና አጽድታ፣ በአዲስ መንፈስ ለአዲሱ ዘመን ንጹህ ልብና አዲስ መንፈስ ታዘጋጃለች።
በጳጉሜ ሰዎች ከተጣሉት ጋር የሚታረቁበት፣ የፈጣሪን ምህረት በጸሎት የሚያስቡበት ቅዱስ ጊዜ በመሆኑ በማህበረሰባችን ዘንድ ልዩ የክብር ስፍራ አላት።
ይህ የመታደስ መንፈስ በተግባርም ይገለጣል። ጳጉሜ ሲመጣ ህፃናት፣ ወጣቶችና አዋቂዎች ጎህ ሳይቀድ ተነስተው ወደ ወንዝ ያመራሉ። በወሩ የሚዘንበው ዝናብና የሚፈሰው ውሃ ፈውስና በረከት አለው ተብሎ ስለሚታመን፣ ያለፈው ዓመት ደካማነትና ህመም በሙሉ ታጥቦ ይሄዳል ተብሎ ይታመናል።
በየቤቱም አዲስ አመትን ለመቀበል የሚደረገው ጉድጉድም በነዚህ ቀናት ነው የሚካሄደው፡፡
እናቶች የቤታቸውን ውበት እያደሱ ለአዲሱ ዓመት የእንቁጣጣሽ በዓል ሲሰናዱ፣ ህፃናት በየደጃፉ በቅኔና በጨዋታ ድምፃቸው መንደሩን ያደምቁታል። ይህም ልዩ የመታደስ የሽግግር መንፈስ እና የበዓል ድባብ ያላብሳል፡፡
ጎረቤት ከጎረቤቱ ጋር የሚጠያየቅበት፣ አረጋውያን የሚጎበኙበትና ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ የሚበላበት ይህ ወቅት የኢትዮጵያዊነትን የመደጋገፍና የፍቅር እሴት በጉልህ ያሳያል።
በዚህም ጳጉሜ አንድ ትልቅ እውነት ታስተምረናለች፡፡ ይህም የአንድ ነገር መጨረሻ የሕይወት መጨረሻ ሳይሆን የአዲስ ጅምር መነሻ ሊሆን እንደሚችል ነው ።
ያለፈውን አስተውለን፣ ከስህተታችን ተምረን፣ ወደ አዲሱ ዓመት በተስፋ እንድንሻገር ጳጉሜ የተስፋ ድልድይ ሆና ታገለግላለች።
በአመለወርቅ ደምሰው

የ፴፻ (ሦስት ሽህ) ዓመታት ታሪክን ከፍልሰት እንታደግ!
ለሦስት ሺህ ዓመታት ያህል የአባቶቻችንን እምነት፣ ታሪክ እና ቅርስ ጠብቆ ለትውልድ ያቆየው ጥንታዊው ገዳማችን ርዕሰ ገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም አሁን ላይ በገጠመው ችግር ምክንያት የእያንዳንዳችንን አስቸኳይ ድጋፍ ይሻል።
ይህንን ታሪካዊ ቅርስ እና ቅዱስ ስፍራ ለመታደግ የፊታችን ጳጉሜን 1፣2፣3እና 4 በተዘጋጀው የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ በመገኘት የበኩልዎ አሻራ እንዲያኖሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የቀጥታ ስርጭት መርሐግብሩ በፈውስ መንፈሳዊና በሌሎች ሚዲያዎች ይተላለፋል።
ገዳሙን ለመርዳት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000016689843
አሐዱ ባንክ 0085165811801
አቢሲኒያ ባንክ 260616412 (1505)
ዳሸን ባንክ 5442102261011 (2115)
አባይ ባንክ 4491113090983013 (1521)
ጣና ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም
ስልክ
0949174444
0949624444
0948974444
1 month ago
የመደመር አንቀጽ
የመደመር ዕሳቤ ደግሞ መፈራረስና መጠፋፋትን ሳይሆን መገንባትንና አብሮነትን፤ ሥርዓት አልበኝነትንና ዝብርቅርቅነትን ሳይሆን ሥርዓታዊ መያያዝን፤ ብሎም ወደ ጋራ ግብ አብሮ መፍሰስንና መገሥገሥን የሚያስተምር ነው።
በቀውስ መሐል ፈውስ፣ በመፈራረስ ውስጥ መታደስ፣ ተበታትኖ በመጥፋት መካከል ተሰባስቦና ተጣምሮ በአዲስ ጉልበት መነሣት የመደመር መንገድ ነው። ሀገራችንም በዚህ የመደመር መንገድ እንድትጓዝና ከገባንበት አፍራሽና በታታኝ አካሄድ ነጻ እንድትወጣ ያስፈልጋል።
ከዚህ ተላቅቃ ወዳለምንላት የብልጽግና ማማ እንድትወጣ ወደ አዎንታዊ ተጓዳኝነትና ብዝኃነትን ወደማይጨፈልቅ አንድነት መሻገር ይገባናል።
የመደመር መንግስት
ገፅ 66
#ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስ #ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስት Ethiopian Broadcasting Corporation
የመደመር ዕሳቤ ደግሞ መፈራረስና መጠፋፋትን ሳይሆን መገንባትንና አብሮነትን፤ ሥርዓት አልበኝነትንና ዝብርቅርቅነትን ሳይሆን ሥርዓታዊ መያያዝን፤ ብሎም ወደ ጋራ ግብ አብሮ መፍሰስንና መገሥገሥን የሚያስተምር ነው።
በቀውስ መሐል ፈውስ፣ በመፈራረስ ውስጥ መታደስ፣ ተበታትኖ በመጥፋት መካከል ተሰባስቦና ተጣምሮ በአዲስ ጉልበት መነሣት የመደመር መንገድ ነው። ሀገራችንም በዚህ የመደመር መንገድ እንድትጓዝና ከገባንበት አፍራሽና በታታኝ አካሄድ ነጻ እንድትወጣ ያስፈልጋል።
ከዚህ ተላቅቃ ወዳለምንላት የብልጽግና ማማ እንድትወጣ ወደ አዎንታዊ ተጓዳኝነትና ብዝኃነትን ወደማይጨፈልቅ አንድነት መሻገር ይገባናል።
የመደመር መንግስት
ገፅ 66
#ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስ #ኢትዮጵያ #መደመር #ebc #ethiopia #መንግስት Ethiopian Broadcasting Corporation
1 month ago
ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ግን ይቻላል!
#ethiopia | የሀኪሞች ''አብቅቷል'' የሚለው ቃል በሸርሊ ህይወት ላይ ታላቅ ድንጋጤን ፈጥሮ ነበር። ህመሙ ወደ ጡቷ፣ አጥንቶቿና የሰውነት ክፍሎቿ በመስፋፋቱ በአራተኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ሊታከም እንደማይችል የገለጹላት ሀኪሞቿ በምድር ላይ ለመኖር ያላትን እድል የ90 ቀናት ገደብ ብቻ ሰጧት።
ህመሙ እየበረታና መራመድ እንኳ እየከበዳት በመጣበት በዚያ አስጨናቂ ወቅት በፍርሃት ለመዋጥ ብትቃረብም እሷና ባለቤቷ ማርክ ግን ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ በእምነታቸው ለመጽናት ወሰኑ። ባለቤቷ ማርክ በየቀኑ በጸሎትና በመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት በመደገፍ ለባለቤቱ ፈውስ ይጸልይ ነበር።
በሂደቱም ከተሰጣት ከባድ የላብ አወጣጥና የሰውነት ማፅዳት ህክምና፣ እንቅስቃሴ እና ጥብቅ የአመጋገብ ስርዓት ጎን ለጎን ወዳጅ ዘመዶቿ እና የቤተክርስቲያን አባላት በጾምና በጸሎት ይደግፏት ነበር።
ከህመሟ ምርመራ ሶስት ሳምንታት በኋላ ከተመለከተችው ህልም እና ከፈጣሪዋ ከተቀበለችው የተስፋ ቃል በመነሳት ውስጣዊ ብርታትን ያገኘችው ሸርሊ ከቀን ወደ ቀን ጥንካሬዋ እየተመለሰ መጣ።
የ90 ቀናት ገደቧ ተጠናቆ ለምርመራ ወደ ሀኪሞች ዘንድ ስትመለስ ግን የህክምና ባለሙያዎቹን በከፍተኛ ሁኔታ ያስደነቀ ተአምር ተከሰተ።
የተደረገላት የስካን ምርመራ በሰውነቷ ውስጥ ምንም አይነት የካንሰር ህዋስ አለመኖሩንና ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ነፃ መሆኗን አበሰራት። የህክምና ባለሙያዋም "አራተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ካንሰር ሙሉ በሙሉ ሲጠፋ ይህ በእርግጥም ተአምር ነው" ሲሉ ተደመጡ።
ይኸው ክስተት ከተፈጸመ ከአስር ዓመታት በላይ ያለፉ ቢሆንም፣ ሸርሊ ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ ከካንሰር ነፃ ሆና በደስታና በጤና በመኖር ላይ ትገኛለች።

2 months ago
“ከኢትዮጵያ ወዴት ይሸሻል?” የፕሮፌሰሩ ምላሽ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር ከስሜት፣ ከደም እና ከሥነ ልቦናዊ ቅኝት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ሕያው ማንነት ነው።
የሰው ልጅ ከሀገሩ ጋር ያለው ትስስር የእምነትና የሕልውና ያህል የጠነከረ ነው። ለዚህ ነው ለብዙዎቻችን ነገራችንና ጉዳያችን የምትሆነው፡፡
ኢትዮጵያ ታዲያ የሥነ ልቦናችን ስሪት የተገነባበት፣ የማንነታችን የተቀረጸበት፣ በዕውቀት የታነጽንበት፣ የተዳርን፣ የተኳልንባት ታላቅ የእናት እቅፍ ናት።
ሀገራችን ሲከፋን የምንተዋት፣ ሲደላን የምናጌጥባት ሳትሆን በጥብቅ ቃል ኪዳን የተሳሰርናት የማንነታችን ማህተም ናት፡፡ ለችግሯ ጊዜ ስትፈልገን አለሁልሽ አለማለት የእኛ መልካችንም ልካችንም አይደለም።
ትናንት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያውን ታሪካዊ የምክክር ምዕራፍ በስኬት ባጠቃለለበት ታላቅ መድረክ ላይ፣ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ያነሱት ሀሳብ የብዙዎችን ስሜት ኮርኩሯል፤ የሀገርንም ፍቅር ጥልቅነት ዳግም አበስሯል።
ኮሚሽነሩ በቤተሰብ ሐዘን ምክንያት ለጥቂት ቀናት ወደ ውጭ ሀገር ባቀኑበት ወቅት፣ «ምክክሩን ጥለው ጠፉ፤ ከሀገር ኮበለሉ» የሚሉ ሀሰተኛ ዘገባዎች ተሰራጭተውባቸው ነበር። መቼም ለሐሰተኛ መረጃ አሰራጮቹ "በሬ ወለደ" ብርቃቸው አይደልም። “ወደቀ” ሲባል “ተሰበረ” እንጀራቸው ነው።
መስፍን አርዓያ(ፕ/ር) ትናንት በልዩ ሕዝባዊ ኃላፊነት ወደ መድረኩ ተመለሱ፡፡ የተነዛውን ሀሰተኛ መረጃ በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜት ሲገልጹ፣ «ከሀገሬ አልሸሸሁም፤ ከሀገሬ ምንጊዜም አልሸሽም፤ ከሀገሬ ምንጊዜም አልኮበልልም! እንኳን በዚህ ዕድሜ፣ የዛሬ አርባ ዓመት ጉልበት በነበረኝ ጊዜ፣ መውጣት በምችልበት ወቅትና እህት ወንድሞቼ ውጭ ባሉበት ጊዜም ቢሆን ከሀገሬ አልወጣሁም። የቀረችኝን ዕድሜ እዚሁ ነው የማሳልፈው!» ብለዋል፡፡
ይህ ተራ ንግግር አይደለም። ይልቁንም ዕድሜያቸውን ሙሉ ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን ያገለገሉ፣ ከታመመው ጋር የታመሙ፣ አያሌዎችን ተስፋ ያለመለሙ፣ ከመከረው ጋር የመከሩ ልብ የሚነካ የሀገር ፍቅር የተግባር ቃል እንጂ።
እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ እንጠይቅ፣ በእርግጥስ ከኢትዮጵያ ወዴት ይጠፋል? እንደ መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ያሉ አባቶች የሚያስተምሩን ትልቅ እውነት ቢኖር፡ ሀገር ችግር ሲገጥማት ጥሎ አይሸሽም፤ ይልቁንም ፈውስ ለመሆን በጽናት ይቆማል። ፕሮፌሰሩና ባልደረቦቻቸው ኢትዮጵያ እንድትፀና አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍተዋል፤
ይህንን ጥብቅ ሀገራዊ ትስስርና የፍቅር ዕዳ የከበደውን የቆራጥነት ስሜት ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ «ሀገሬ» በሚለው ዘመን ተሻጋሪ ግጥሙ ተቀኝቶበታል፣
«ብሞት እሄዳለሁ እመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ የእማማ የአባባ፤
ስሳብ እሄዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ ሀገሬ።»
ከትውልድ ሀገር ጋር ያለ ቀጠሮ በምንም ዓይነት ወሬና ውሸት የሚበጠስ አይደለም። ሐሰተኛ መረጃዎችና የሰዎች አሉባልታ በየቀኑ ቢነፍሱም፣ ለሀገር የሚደረግ እውነተኛ አገልግሎት ግን በቆራጥነትና በተግባር የሚታይ ነው።
ዋና ኮሚሽነሩ በሐዘን ላይ ሆነውም ቢሆን ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የምክክር ኮሚሽኑን ታሪካዊ ፍጻሜ በውጤታማነት እንዲደመደም ማድረጋቸው፣ ለወሬኞች የተሰጠ ከባድና ተግባራዊ ምላሽ ነው።
ይህ የቁርጠኞችና የባለአደራዎች መንገድ ነው። የትኛውም ትውልድ ቢሆን ከዚች ሀገር ሕመም ጋር ተጋምዶ መፍትሔ ከመፈለግ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም።
የመስፍን አርዓያ(ፕ/ር) አባባል የሚያስገነዝበን፣ የቀረችውንም ዕድሜ ቢሆን ለሀገር መኖሪያ ማድረግ ትልቅ የታሪክ ባለአደራነትና የስብዕና መሰረት ነው። በእርግጥም ከኢትዮጵያ ወዴት ይሸሻል?
በአፈወርቅ እያዩ

ኢትዮጵያ፣ ትንቢተ-ውድቀትን ያከሰመች ታላቅ ሀገር
የሽንፈት ነጋሪዎችና የውድቀት ነቢያት «አይሳካላትም» አሉ። ኢትዮጵያውያን በጋራ ቋንቋቸው ተነጋግረው ችግራቸውን የመፍታት ጥበብ የላቸውም ሲሉ ደመደሙ።
ብዙ ተነበዩ፤ ብዙ ታዘቡ፤ አፍራሽ ውሳኔዎችንም ያለ አግባብ አስተላለፉ። ኢትዮጵያ ግን ለነዚህ ሁለተኛ ደረጃ ትንቢቶችና የተስፋ መቁረጥ ጩኸቶች ጆሮ አልሰጠችም።
በምትኩ፣ በታላቅ አስተዋይነትና ፀጥታ የታጀበ ታሪካዊ እርምጃ ወሰደች፤ወንበር ስባ ተቀመጠች። የዘመናት ቁስሏን፣ ውስብስብ ፈተናዎቿን፣ ስጋቷንና ተስፋዋን ይዛ ልጆቿን በአንድ የሰላም ጠረጴዛ ዙሪያ ሰበሰበች። ተነጋገሩ፤ በጽኑ ተከራከሩ፤ እውነቱንም ተጋፈጡ።
ውድቀቷን በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ኃይሎች በሙሉ ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በመክፈት ምላሽ ሰጠች። ዘላቂ ችግርን በጥይት ሳይሆን በሰለጠነ ውይይት፤ በመከፋፈል ሳይሆን በላቀ የመደማመጥ ባህል መፍታት እንደምትችል አረጋገጠች። ይህም በሀገሪቱ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አዲስና ብሩህ መንገድ የሚቀይስ ክስተት ሆነ።
ጠላቶቿ በሽንፈቷ ሊደሰቱ ሲደግሱ፣ እርሷ ስኬትን አበሰረች፤ ተቺዎቿ መበታተኗን ሲተነብዩ፣ እርሷ ጠንካራ አንድነትን ገነባች። ይህ አንፀባራቂ ድል በሆነ አጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን በጽናት፣ በትዕግስትና በጋራ ህልውና ላይ በተገነባ ፅኑ ፍላጎት የተረጋገጠ ነው።
ዛሬ የአፍራሽ ትንቢት ነጋሪዎች ድምፅ ጭጭ ብሏል፤ እውነታው ተስፋ አስቆራጭ ስጋቶችን ሙሉ በሙሉ አክስሟቸዋል።
ኢትዮጵያ በተግባር አረጋገጠች፦ ልዩነት ቢኖርም የጋራ ቅን ልብ ካለ መፍትሔ አይጠፋም። የቆየ ቁስል ቢኖርም በትዕግስትና በይቅርታ ፈውስ ይመጣል።
ጨለማ ቢጋርድም የተስፋ ጭላንጭል ካልጠፋ ብርሃን ይወጣል።
ልጆቿ ተስፋ ባልቆረጡ ቁጥር ይህች ሀገር ልትሸነፍ አትችልም። በተግባር የተረጋገጠው ስኬታማ ምክክር ለነገው ትውልድ አዲስና የማይናጋ እውነትን ይተክላል፡፡
«ኢትዮጵያ ታላቅ ናት፤ ታሸንፋለችም!» የተጠራጣሪዎች ጩኸት ባዶ ሆኖ ቀርቷል፤ የኢትዮጵያ ድል ግን በታሪክ መዝገብ ላይ ለዘላለም ተቀርፆ ይኖራል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ደቡብ አፍሪካዊው ፓስተር በኢትዮጵያ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ወደ2030 ማራዘማቸውን አስታወቁ፡፡ ደቡብ አፍሪካዊው ታዋቂ ፓስተር ጆን አኖሲኬ በኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹ሀዋሪያዊ›› ጉብኝት እንደሚያደርጉ በሰፊው ሲያስተዋውቁ ቆይተዋል፡፡ በተለያዩ አገራት ተመሳሳይ ጉብኝት በማድረግ የሚታወቁት እኚህ ፓስተር በማስታወቂያቸው ላይ ‹‹ኢትዮጵያ አሁን የአንቺ ጊዜ ደርሷል›› በማለትም ገልፀዋል፡፡ ለኢትዮጵያ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለመጮህ መዘጋጀታቸውንና የፈውስና መዳን ኮንፈረንስ እንደሚያቀርቡም በስፋት አስታውቀዋል፡፡ በማስታወቂያቸው ላይ በኮንፈረንሳቸው ላይ ለመሳተፍ መግቢያው በነፃ ቢሆንም አስቀድሞ መመዝገብና የኪውአር ኮድ መያዝ ግዴታ መሆኑንም ሲገልፁ ነበር፡፡
ይህ ኮንፈረንስ ኦገስት 20 እና 21 ወይንም በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው ‹‹ሊቪንግ ሆፕ ሚራክል ሚኒስትሪ›› እንደሚከናወን አስታውቀው የነበረ ቢሆንም ዛሬ ባወጡት መግለጫ ፕሮግራሙ መራዘሙን ገልፀዋል፡፡ ፓስተር አኖሲኬ በመግለጫቸው ‹‹ለኢትዮጵያ የምንጮህበት ቀን ወደ2030 ተራዝሟል›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ከኦገስት 20 እስከ 21 በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የታቀደው የፈውስና የመዳን ኮንፈረንስ መራዘሙን ለምንወዳቸው አጋሮቻችንን፣ ቅዱሳንና ጓደኞቻችን በደግነት ማሳወቅ እንደወዳለን፡፡
ይህ ፕሮግራም የተራዘመው የወደፊት እቅዳችን አካል በመሆኑ ነው›› ካሉ በኋላ ኮንፈረንሱን በጉጉት ሲጠብቁ ለነበሩት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በመግለጫቸው ማጠቃለያም ‹‹ይህንን ኮንፈረንስ ለመታደም ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ወደኢትዮጵያ ለመጓዝ ያሰባችሁ በሙሉ ዝግጅቱ ስለማይካሄድ የጉዞ ዝግጅታችሁን እንድትሰርዙ ወይንም እንድታስተካክሉ በአክብሮት እጠይቃለሁ›› ብለዋል፡፡

የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና አረንጓዴ ውበት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቀናት የስራ ድካም አረፍ ለማለት፤ ከተፈጥሮ ጋር ለማውጋት የእያንዳንዱ ሰው ነፍስ የሳምንቱን ማክተሚያ ቀናት በናፍቆት ትጠብቃለች።
እነዚህ ቀናት ከአድካሚው የኑሮ እሽቅድምድም በኋላ አካልና አዕምሮን የሚያድሱበት፣ የህይወትን ትንፋሽ አድሰው የሚቀጥሉበት ወርቃማ ገፆች ናቸው።
በእነዚህ ቀናቶች የሰዎች ነፍስ አብዝታ ወደ ተፈጥሮ መጠጋትን ትሻለች፤ እረፍትና አረንጓዴነት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በተከታታይነት በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሰዎች የዕረፍት ጊዜያቸውን በሚያጣጥሙባቸው ቀናት አዲስ የህይወት ቀለም ጨምሯል።
የሰው ልጅ ከቤቱ ወጥቶ መዝናናትን ሲፈልግ በለመለሙ ስፍራዎችና በለስላሳ ነፋስ የሚወዘወዙ ዛፎች ስር አረፍ ብሎ የሰላምን አየር መማግ ቀዳሚ ምርጫው ያደርጋል፡፡
ከትርምስምሱ ገለል ብሎ በተፈጥሮ እቅፍ ውስጥ መሆን ለአእምሮ ሰላም የሚሰጠው ፈውስ ወደር የለውም።
በአረንጓዴ ዐሻራ እጆች የተደገፉና ዳግም ያገገሙ ስፍራዎች አሁን ላይ በተለይም በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የነዋሪዎች ዋነኛ የመዝናኛ ስፍራ ሆነዋል።
ለአብነትም እንደ አንድነትና እንጦጦ ፓርክ ያሉ ማራኪ የከተማ መናፈሻዎች ሰዎችን በሰፊው እቅፋቸው በመቀበል ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ የአረንጓዴነት ምልክቶች ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠብቁ ውብ መድረኮችም ናቸው።
ቤተሰቦችና ወዳጆች እጅ ለእጅ ተያይዘው ያልተበከለ አየር እየሳቡ ረጅም የእግር ጉዞዎችን ያደርጋሉ።
ንፁህ አየር እየማጉ፣ በደስታ እየተጨዋወቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከተፈጥሮ ውበት ጋር አዋህደው ያጣጥማሉ።
ይህ አይነቱ ውብ መስተጋብር በሰዎች መካከል ያለውን ፍቅር ከማጠናከሩም በላይ፤ ተፈጥሮን የመንከባከብን ጥልቅ ባህል በየቀኑ ህይወታችን ውስጥ በሂደት እንዲሰርፅ እያደረገ ይገኛል።
የዕረፍት ቀናትና የአረንጓዴ ዐሻራ ቁርኝት በመዝናናት ብቻ የሚገደብ አይደለም።
ንቁ ዜጎች፣ ወጣቶችና ቤተሰቦች የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትን ወደ በጎ ተግባር በመቀየር በጥላ ስር ይሰበሰባሉ፤ እረፍታቸውን አዳዲስ ችግኞችን በመትከልና ለነገው ህይወት አሻራቸውን በማኖር ያሳልፋሉ።
ዛሬ የትናንቶቹን ዛፎች ጥላ ተጠልለን እንደምንዝናናው ሁሉ፤ እኛም በእረፍታችን የምንተክላቸው ችግኞች ለነገው ትውልድ ምቹ የመዝናኛና የህይወት ዋስትና ሆነው ያገለግላሉ።
የሰዎች የእረፍት ቀናት ምርጫና የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት ፈትል በጥብቅ የተሳሰሩ ናቸው።
በእመቤት ሲሳይ

የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚያሰራውን ቤተሰሊሆም አጠቃላይ ሆስፒታል ህንፃ ግንባታን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡
ከሁሉ አሰቀድመን እግዚአብሔር አምላካችን ለ2018 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሁላችንንም በሰላም በጤና ስላደረሰን እናመሰግነዋለን፡፡የተከበራችሁ አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት እና ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ምዕመናን እና ወጣቶች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንዲሁም ይህን መልእክት ለመላው ዓለም ለማስተላለፍ የተገኛችሁ የሚድያ አካላት በሙሉ በእግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችንን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከሆነው ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እናቀርባለን፡፡
“በኂሩተ ጻድቃን ትረትዕ ሀገር”
“በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል”
ምሳ 11፥10
እግዚአብሔር በንጉሱ ሰሎሞን ላይ አድሮ የተናገረውን መነሻ በማድረግ ልማት ለቤተከርስቲያን ፣ልማት ለሀገር፣ልማት ለማኅበረ ስብእ አስፈላጊ መሆኑን በማሰብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሚገነባው ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል የህንፃ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ የእግዚአበሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን።
1. ታሪካዊ ዳራ እና የልማት መነሻ
ከአክሱም ዘመነ መንግሥት (በአባ ሰላማ ዘመን) የጀመረውና ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና የአዲስ አበባን ከተማ አመሰራረት የሚተርክ ህያው ቅርስ ነው።ይህ ታሪካዊ ደብር በአብርሃ ወአጽብሃ፣ በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በንግሥት ጣይቱ፣ እንዲሁም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በርካታ የታሪክና የፈተና ምዕራፎችን አልፎ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ደብሩ ከሃይማኖታዊ አገልግሎቱ ባሻገር፣ የአዲስ አበባ የመጀመሪያው የቀብር ቦታ በመሆን የሊቃውንቱና የካህናቱ እንዲሁም የታላቁ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴን፣ የኢትዮጵያ ታላላቅ ጄነራሎችና ፊት አውራሪዎችን ዓጽም በክበር ማረፊያ ሆኗል፡፡ የጸሎትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም ለአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መመስረት ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይታወቃል። ዛሬ ይህ ታሪካዊ ደብር ጥንታዊ ታሪኩንና መንፈሳዊ ታላቅነቱን በዘመናዊ ማህበራዊ ልማት ለመድገም፣አካላዊ ፈውስን በሳይንሳዊ ሕክምና የመንፈሳዊ ፈውስን በፀሎትና በጠበል የሚያዋህድ ታላቅ የልማት ፕሮጀክት ይፋአድርጓል።
2. የሆስፒታሉ ይዘት፣ ራዕይና ሰብዓዊ ተልዕኮ
ቤተክርስቲያኑ ባለ 15 ወለል ማለትም (2 Basement+G+ 12ወለል) የሆነውን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል» ህንፃ ግንባታ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።
3. የግንባታ ወጪ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዝርዝር፦
• ቀን፦ ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም
• ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ
የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አማራጮች፦
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277
• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227
• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA
• ወገን ፈንድ 👉 ሊንክ ኮመንት ላይ አለ
ለተጨማሪ መረጃ፦
• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
• Email፦ Seyoumwgebrielgmail .com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

• ወገን ፈንድ 👉 https://www.wegenfund.com/...

ምክክር ለዘላቂ ሠላም
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጥንታዊ ነጻ ሀገረ መንግሥታት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በበርካታ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና እሴቶች የተዋቀረች ኅብረብሔራዊት ሀገር ናት፡፡
ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው ሀገራችን ህልውናዋን አጽንታ ዘመናትን መሻገር የቻለችው በልጆቿ የተባበረ ክንድ ስለመሆኑ ታሪክ ህያው ምስክር ነው።
በእነዚያ ጊዜያት ውስጥ ሰላሟንና ልማቷን ሲፈታተኑ የዘለቁ ቅራኔዎችን በሰላማዊ ውይይት በመፍታት ነገዋን የተሻለ ለማድረግ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ትገኛለች፡፡
ዜጎቿ ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ የጋራ መግባባት ላይ የሚያደርስ መፍትሄ እንዲያበጁ በገለልተኛ የምክክር ኮሚሽን የሚመራ አሳታፊና አካታች ሀገራዊ መድረክ አበጅታለች፡፡
ይህ አሳታፊነት ምክከሩ በሀገሪቱ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከታዩ እጅግ ሰፊና ለውጥ አምጪ እንቅስቃሴዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡
ለብዙ ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ አለመግባባቶች ዛሬም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚቀሰቀሱ ግጭቶችና የሰላም እጦት በምክንያትነት ሲቀርቡ ይስተዋላል፡፡
ሀገር በቀል እውቀቶችንና ባህላዊ የውይይት እሴቶችን ማዕከል በማድረግ እየተካሄደ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር እነዚህን የቆዩ ቁርሾዎች በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል፡፡
የጋራ ሀገራዊ ራዕይ እውን የሚሆንበት ይህ መድረክ ከጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥቅም በላይ የሀገሪቱን የዘላቂ ሰላም ጉዞ የሚያሳልጥ ታሪካዊ እድል ነው፡፡
የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፅ እኩል የሚሰማበት ይህ ሀገራዊ ምክክር የአሸናፊና ተሸናፊ ትርክትን በጋራ መግባባት ላይ በተመሠረተ ባህል የሚተካ ወሳኝ መድረክ ነው።
አንዲት ሀገር ለትናንት ቅራኔዎች ሕዝብን ባሳተፈ መንገድ እውነተኛ መፍትሄ ሳትሰጥ ሰላማዊ ነገን መገንባት አትችልም።
በዚህ መንፈስ በእኩልነት ላይ በተመሰረተ፣ ግልጽ፣ ነጻ እና አሳታፊ ሂደት እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፥ ሀገሪቱን ወደ ብልጽግና የሚያሸጋግር ድልድይ እንዲሁም ከውርስ ህመሟ የሚፈውስ ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡
ግጭትና የሕዝቦች መለያየት የሀገርን ሀብት የሚያወድሙና ልማትን የሚያደናቅፉ በመሆናቸው፤ የሀገርን ጥቅም ባስቀደመ የጋራ መግባባት የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታን በመፍጠር ብሔራዊ ምክክሩ ለጠንካራ ኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ይጥላል።
የዜጎችን የጋራ መግባባት ጽኑ መሰረት አድርጋ የምትገነባው ሰላማዊት ኢትዮጵያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂና ሌሎች የመሠረተ ልማት ዘርፎች ያላትን አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም የዜጎቿን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትችላለች፡፡
ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ማዕከል እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ እንደመሆኗ፤ አለመግባባትን በውይይት ለመፍታት የጀመረችው ጉዞ አፍሪካውያን ችግሮችን በራሳቸው ለመፍታት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም አርአያ ነው።
የተዋሃደችና ደህንነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድን በማረጋጋት የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር፣ ንግድና የጋራ ደህንነት ማረጋገጥ ይቻላታል፡፡
ምክክሩ የአንድ ጊዜ ሁነት ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ ተቆርቋሪነት የሚጠይቅ የታሰበበት ረጅም ጉዞ ነው።
አለመግባባቶች የማህበረሰብ ተፈጥሯዊ አካል ቢሆኑም ጠንካራ ሀገር የሚገነባው ግን እነዚህን ልዩነቶች ባስተናገዱበት ጤናማ መንገድ እንደሆነ ይታመናል፡፡
ኢትዮጵያ ከግጭት ይልቅ ውይይትን በማስቀደም እያከናወነች የምትገኘው ሀገራዊ ምክክር አንድነት፣ የተቋማት ጥንካሬና ዘላቂ ሰላም የሚጸናበት አዲስ ምዕራፍ ነው፡፡
ከምንጊዜውም በላይ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በመጠቀም ለወደፊቱ ትውልድ ምቹ ሀገር ለመገንባት ጊዜው አሁን ነው።
በምሕረት ደምሴ

ብሩስ ዊሊስ ባለቤት የባለቤቷን ህመም (FTD) ለመከታተል የሚያስችል ህግ እንዲፀድቅ ግፊት አደረገች
የታዋቂው የፊልም ኮከብ ብሩስ ዊሊስ ባለቤት የሆነችው ኤማ ሄሚንግ ዊሊስ፣ ባለቤቷ የተጠቃበትን 'የፊት ለፊት የጭንቅላት ክፍል መጎዳት' (Frontotemporal Degeneration - FTD) የተሰኘውን የመርሳት ህመም የሚከታተል ህግ እንዲፀድቅ ሰኞ ዕለት በካሊፎርኒያ ካፒቶል ከሚገኙ ህግ አውጪዎች ጋር በመሆን ግፊት አድርጋለች።
በሴናተር ሮጀር ኒየሎ የተዘጋጀው እና ኤማ ሄሚንግ ዊሊስ ድጋፏን የሰጠችለት ይህ ረቂቅ ህግ፣ የካሊፎርኒያ የህዝብ ጤና መምሪያ ስለ FTD ህመም መረጃዎችን እንዲሰበስብ የሚያስገድድ ነው። መምሪያው በአሁኑ ወቅት የሃንቲንግተን፣ የፓርኪንሰንስ፣ የአልዛይመርስ እና የማልቲፕል ስክለሮሲስ በሽታዎችን መረጃዎች በመሰብሰብ ላይ ይገኛል። የህጉን ሂደት በተመለከተ፣ ረቂቅ ህጉ ሀምሌ 1 ቀን የህግ አውጪው ምክር ቤት የአንድ ወር የክረምት እረፍት ከመውጣቱ በፊት በምክር ቤቱ ተጠባባቂ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ነበር። ምክር ቤቱ ሰኞ ዕለት ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ ረቂቅ ህጎችን ለማጽደቅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ቀርቶታል። ይህ የህግ ማዕቀፍ እስከ ጥር 1፣ 2032 ድረስ የሚራዘም ሲሆን፣ የህጉ ትንታኔ እንደሚያሳየው ለሰራተኞች እና ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍያን ጨምሮ በዓመት 2.7 ሚሊዮን ዶላር በጀት ይጠይቃል።
ኤማ ሰኞ ዕለት በካፒቶል በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳብራራችው፣ FTDን በነርቭ መጎዳት በሽታዎች መዝገብ ውስጥ ማካተት የካሊፎርኒያ ታካሚዎችን መቁጠር ብቻ ሳይሆን፣ በካሊፎርኒያ የሚገኙ የባዮቴክ ተመራማሪዎች ህክምና እና ፈውስ ለማግኘት የሚፈልጉትን ጠቃሚ የመረጃ ቋት መገንባት ነው። ባለቤቷ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2022 በበሽታው መያዙ እንደታወቀ የጠቀሰችው ኤማ፣ አሁን ላይ ህመሙን የሚያዘገይ ወይም የሚያቆም ህክምና እንደሌለ ብታምንም፣ የህመሙን መረጃዎች መሰብሰብ ግን ለምርምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግራለች። ታዋቂው ተዋናይ ስለሚገኝበት ሁኔታ ተጠይቃ ስትመልስም፣ በዚህ እጅግ ጨካኝ በሆነ በሽታ ውስጥ ሆኖ ማድረግ የሚችለውን ያህል በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብዬ አስባለሁ ስትል ገልጻለች።
'ፒክስ ዲዚዝ' በመባልም የሚታወቀው ይህ ህመም፣ ከግንባር ጀርባ ወይም ከጆሮ አካባቢ ባሉ የጭንቅላት ክፍሎች ላይ በሚከሰት የነርቭ ሴሎች መጎዳት የሚመጣ የጭንቅላት እክል ነው። የበሽታው ምልክቶች የባህሪ እና የስብዕና ለውጥን፣ ስሜት አልባ መሆንን ፣ ውሳኔ የመስጠት፣ የመንቀሳቀስ እና የመናገር ችግርን፣ እንዲሁም ቃላትን የመረዳት አቅም ማጣትን ያካትታሉ።
የኤፍ ቲ ዲ ማህበር የጥብቅና እና የበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ ዳይሬክተር የሆኑት ሜጋን ቡዝቢ እንደገለጹት፣ የታካሚ ቤተሰቦች እነዚህ ምልክቶች ሲታዩ ከሐኪሞች ግልጽ የሆነ ምላሽ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ይቸገራሉ። ዳይሬክተሯ አክለውም፣ ይህ ሁኔታ ለብዙ የካሊፎርኒያ ቤተሰቦች የFTD ምርመራ ውጤትን ለማግኘት የሚያደርጉት ረጅም እና አድካሚ ጉዞ እውነታ መሆኑን አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት በሽታውን ለማከም የሚረዱ ህክምናዎች እጅግ ውስን ሲሆኑ፣ ፈውስም እስካሁን አልተገኘለትም።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሰኞ ዕለት በአማራ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። የፍለጋ እና የነፍስ አድን ስራው አሁንም ቀጥሎ ባለበት በዚህ ወቅት፣ እስካሁን የገቡበት ያልታወቁ እና በፍርስራሹ ስር የተቀበሩ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ተነግሯል።
አደጋው የተከሰተው በፃድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ሲሆን፣ በወቅቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ለፀበል እና ለመንፈሳዊ ፈውስ በስፍራው ተሰብስበው ነበር። የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቃ ጥበብ አባቡ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፣ "አደጋው የተከሰተው ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ፀበል ለመጠመቅ የተሰበሰቡ ነበሩ።" ስራ አስኪያጁ አክለውም፣ "ከሟቾቹ መካከል አስራ አንዱ በገዳሙ ውስጥ የተቀበሩ ሲሆን፣ የሌሎቹ አስከሬን ወደ ትውልድ ስፍራቸው ተልኳል፤ ይሁን እንጂ የአንዳንዶቹን ሟቾች ማንነት ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል" ብለዋል።
ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከገዳሙ 70 ኪሎ ሜትር (43 ማይል) ርቀት ላይ ወደምትገኘው የሰሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን ዋና ከተማ ደብረ ብርሃን ለህክምና ተወስደዋል። የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተው ከተራራ አጠገብ በመሆኑ፣ ግዙፍ አለቶች ተገንጥለው በምዕመናኑ ላይ መውደቃቸው አደጋውን ይበልጥ አባብሶታል። የአካባቢው አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የፍለጋ እና አድን ስራዎችን ለማገዝ የአካባቢው የአደጋ መከላከል ጽህፈት ቤት ባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መሰማራቱን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ከሰኔ እስከ መስከረም በሚዘልቀው የክረምት ወቅት ከባድ ዝናብ የሚያስከትለው የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለመደ መጥቷል። በሐምሌ 2024 በደቡብ ኢትዮጵያ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ አሳዛኝ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 257 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ከዚህ ቀደምም በዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ጋሞ ውስጥ በተከሰተ ተመሳሳይ የመሬት መንሸራተት ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በአፍሪካ ቀንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ የከፋ የአየር ፀባይ ክስተቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቃች ትገኛለች። በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ያለው ደካማ መሰረተ ልማት፣ በርካታ ማህበረሰቦችን ለጎርፍ፣ ለመሬት መንሸራተት እና ተደጋጋሚ ድርቅ በቀላሉ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ሲሆን፣ ለእንደዚህ አይነት አደጋዎች ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅማቸውም እጅግ ውስን ሆኖ ቆይቷል።

በሰሜን ሸዋ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም በመሬት መንሸራተት 14 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ
#ethiopia | አዲስ አበባ – በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው ታሪካዊው የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በደረሰ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ 14 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ 5 ሰዎች ደግሞ የከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እንደ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት መረጃ፣ አደጋው በክረምቱ ወቅት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የተከሰተ ሲሆን፣ በወቅቱ ለጸበል፣ ለሱባኤ እና ለንግሥ በገዳሙ የተገኙ ምዕመናን ላይ ጉዳቱ ደርሷል።
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በአደጋው ስፍራ በመገኘት ለሕይወታቸው ላለፉት የፍትሐት ጸሎት አድርገው፣ ለተጎዱትና ለተጨነቁት ምዕመናን አባታዊ ቃለ በረከትና የማጽናኛ ትምህርት ሰጥተዋል።
ሀገረ ስብከቱ በመግለጫው በአደጋው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጾ፣ ለሞቱት ዕረፍተ ነፍስ፣ ለተጎዱት ፈጣን ፈውስ፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናት ተመኝቷል።
የአደጋው መንስኤ ከከፍተኛ ዝናብ ጋር የተያያዘ የመሬት መንሸራተት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በቦታው ያሉ አስፈላጊ የድጋፍና የእርዳታ ሥራዎች መቀጠላቸው ተጠቁሟል።
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት አቡ ቀለምሲስ ሚዲያ

የሞተው ሕያው የሆነበት ማሩ ከዋሻ የሚፈስበት አስደናቂው ስፍራ
♦️ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
#ethiopia | በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ምስራቅ በለሳ ወረዳ፣ ጎጋ ቀበሌ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፤ የቀደመ ታሪኩን ፣ የተፈጥሮ ግርማውንና ታአምራት በአንድ ላይ የያዘ ድንቅ መንፈሳዊ ስፍራ ነው።
አባቶች እንደሚያስረዱት የስፍራው የቀደመ መጠሪያ "ዛጅር ማኤል" ይሰኝ ነበር። ይህ ስም "ዛጅር" ማለት ውሃ በደረቅ አለት ላይ ፈንጥቆ የሚወጣበትን አቅጣጫ ሲያመላክት፣ "ማ" ዋሻውን፣ "ኤል" ደግሞ የሰማይ አምላክን በመወከል እግዚአብሔር በድንቅ ሁኔታ በደረቅ አለት ላይ ውሃ የፈነጠቀበት ስፍራ መሆኑን ይናገራሉ።
የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የስብከተ ወንጌል ኃላፊ እና ጸኃፊ አባ ብርሃነ ሠላም እንደሚገልጹት፣ የቦታው ተአምራዊ ጉዞ በይፋ ጎልቶ መታየት የጀመረው በ2013 ዓ.ም የጸበል አገልግሎት ሲጀመር ነው።
በተለይም የስፍራውን ስም ከአዲሱ ስያሜ ጋር ያያዘው ታዓምር በዚሁ ዘመን ተከስቷል። ከገዳሙ 12 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በምትገኘው ዙ ሐሙሲት ከተማ አቅራቢያ የምትኖር አንዲት ሴት በጽኑ ታማ ወደ ህክምና ከተወሰደች በኋላ በቃሬዛ ላይ እያለች ህይወቷ ያልፋል።
በወቅቱ የጸበሉ አስተዳዳሪ የነበሩት አባት እና ሌሎች ካህናት አስከሬኑን ይዘው በመንገድ ላይ ሳሉ የእግዚአብሔርን ኃይል በማመን ቅዱስ ጸበሉን አፍሰው ረጩባት። በዚያው ቅጽበት የሞተችው ሴት ትንፋሽ ተመልሶላት ተነሳች፤ ሙሉ ፈውስ አግኝታም ድንቅ ምስክርነቷን ሰጠች።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጸበሉ "ሙት አንሳ" የሚለውን ስያሜ አገኘ። በኋላም ከዋሻው በላይ ከሚንጠበጠበው ማር ጋር ተያይዞ "ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም" ተብሎ መጠራት ጀመረ።
የገዳሙ መነኮሳት እንደሚናገሩት በዋሻው ጣሪያ ላይ ለዘመናት ሳይቆረጥ የቆየ ልዩ ማር ይገኛል። ይህ ማር በተለያዩ ጊዜያት በራዕይ "ተቆርጦ ለምእመናን ፈውስ ይሁን" የሚል መልእክት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም፣ የቦታው ገደላማና አስፈሪ አቀማመጥ ማንም እንዲደፍረው አላደረገም።
ቆየት ብሎ መነኮሳቱ በጸሎትና በምህላ ሲገቡ ንቡ ቦታውን ለቆ ይወጣል። ማሩ አሁን ላይ እየተቆረጠ ለበርካታ ድውያናትና ምእመናን ዘላቂ ፈውስን በመስጠት ላይ ይገኛል።
ዛሬ ለቁጥር በርካታ የሆኑ መነኮሳት የሚኖሩበት ይህ ታላቅ ገዳም የተመሰረተው በአንድ አባት መንፈሳዊ ታዛዥነትና ጽናት ነው። አባ ብርሃነ ሠላም እንደሚያስረዱት፣ በ2009 ዓመተ ምህረት ግንቦት 21 ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ አባ ብርሃነ ማርያም ከድዊ አንሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ተነስተው ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ በፊታቸው የተለየ ብርሃን እየመራቸው
ቦታው ይደርሳሉ።
ያን ብርሃን እየተከተሉ የሶስት ሰዓት መንገድ በእግር ተጉዘው አሁን ገዳሙ በሚገኝበት ስፍራ ሲደርሱ ብርሃኑ ተሰወረባቸው። በወቅቱ ምንም ዓይነት መኖሪያ ቤትና መጠለያ በሌለበት፣ የክረምቱ ዝናብና ቅዝቃዜ በበዛበት ወቅት አባታችን በእርጥብ ዋሻ ውስጥ ማደር ጀመሩ።
እግዚአብሔርም በቸርነቱ የሚያድሩበትን ስፍራ ደረቅ በማድረግ ጠበቃቸው፤ የዕለት ምግባቸውንም የአካባቢው ህዝብና ጸበልተኞች እያመጡ ያቀርቡላቸው ነበር።
የአባታችንን ትምህርትና ተአምራዊ ፈውሱን ያዩ በርካታ መንፈሳውያን ልጆች በየጊዜው ወደ ስፍራው በመምጣታቸው የምናኔ ሀሳብ በብዙዎች ህሊና ውስጥ ሰረፀ። አባ ብርሃነ ሠላም አያይዘው እንደሚገልጹት፣ በ2011 ዓመተ ምህረት በአካባቢው ሰበካ ጉባኤ ድጋፍ የተገዙ በሬዎችን በመጠቀም መሬት ማረስና የጋራ ኑሮ ተጀመረ። በ2013 ዓመተ ምህረት የመነኮሳቱ ቁጥር ከመቶ በላይ በመድረሱ የአካባቢው ህዝብና ካህናት ተመካክረው ቦታ በመስጠታቸው ትንሽ መቃኞ ተሠርቶ ታቦተ ሚካኤል ገባ።
በመጨረሻም በ2014 ዓመተ ምህረት መስከረም 29 ቀን በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቡጽዕ አቡነ ዮሐንስ አባታዊ ቡራኬና ውሳኔ ገዳም የመሆን ሙሉ ክብሩንና ስያሜውን አገኘ።
ይህን መንፈሳዊና ታሪካዊ ገዳም የሚገኘው ከአዲስ አበባ
በሰሜን አቅጣጫ 667 ኪሎ ሜትር፣ ከባህርዳር ከተማ 183 ኪሎ ሜትር፣ ከዞኑ ጎንደር ከተማ በአዲስ ዘመን - እብናት -ጎሃላ 192 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከጎንደር ማክሰኚት- አረባያ -ጎሃላ 119 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፤ በአባቶችና በእናቶች ጸሎትና በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ እስከ ዛሬ የቆየ፣ ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ መንፈሳዊ አደራ ነው።
ይህ ገዳም ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። ከሰሞኑን በገዳሙና በአካባቢው በመዘዋወር እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ሥራዎች ተመልክተናል፤ የተመለከትነውንም በተከታታይ ክፍሎች እናቀርብላችኋለን።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#mutansa #ethiopianmonastery #gondarethiopia #ethiopianorthodox #spiritualjourney

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ካውንስ ዋና ጸሐፊ ቄስ ጀሪ ፒላይ በአማራ ክልል በአምልኮ ቦታዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እንዲሁም የሲቪሎችን መገደል እና መቁሰል "እጅግ የሚረብሽ እና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው" ሲሉ በጽኑ አውግዘዋል። ዋና ጸሐፊው ዛሬ ባወጡት መግለጫ፣ የሃይማኖት ተቋማት እና ሲቪሎች በፍጹም ኢላማ ሊደረጉ ወይም በወታደራዊ ዘመቻዎች እንቅስቃሴ ውስጥ ሊገቡ እንደማይገባ በማሳሰብ፣ በአማራ ክልል በሲቪል ማኅበረሰብ እና በሃይማኖት ተቋማት ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
ካውንስሉ ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ ዙሪያ አስቸኳይ፣ ተዓማኒ፣ ግልጽ እና ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲካሄድና ይህንን ድርጊት የፈጸሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕግጋትን እንዲያከብሩ እንዲሁም ሲቪሎችንና የሃይማኖት ተቋማትን የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲወጡ ዋና ጸሐፊው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የጥቃት አዙሪቱን እንዲያስቆሙ፣ በንጹሃን ዜጎች ላይ መከራ የሚያስከትሉ ጥቃቶችን እንዲገቱ እና አሁን ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈልጉም አበክረው ጠይቀዋል።
መግለጫው በማጠቃለያው ለተጎጂዎች ያለውን አጋርነት በመግለጽ፣ በጥቃቱ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ጥልቅ ሀዘናቸውን ገልጸው ለቆሰሉት ፈውስን ተመኝተዋል። እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በክርስቲያናዊ አንድነት እንደሚቆሙ በማረጋገጥ፣ የሰላም አምላክ ሀዘንተኞችን እንዲያጽናና፣ ንጹሃንን እንዲጠብቅና ኢትዮጵያንም ወደ ፍትህ፣ ዕርቅ እና ዘላቂ ሰላም እንዲመራት መልካም ምኞታቸውን እና ጸሎታቸውን አስተላልፈዋል።

የቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦
እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።"
(መዝሙር ፻፪፥፮)
ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት።
በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው።
መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው።
በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ።
በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
© የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በገዳማትና በምእመናን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በማስመልከት ጥብቅ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ በደቡብ ወሎ እና በሀድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት በገዳማትና በምእመናን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በመኮነን አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ቅዱስነታቸው በደቡብ ወሎ ቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ በተፈጸመው ጥቃት የመነኮሳይያት ሕይወት ማለፉን፣ መቁሰልና የንዋያተ ቅድሳት ውድመት መድረሱን፤ እንዲሁም በሀድያና ስልጤ የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱን በከፍተኛ ሐዘን መረዳታቸውን ገልጸዋል።
በመግለጫቸውም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው መናንያን ላይ እጅ ማንሣት በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት የሚያሳፍር ድርጊት መሆኑን ያሰመሩበት ቅዱስነታቸው፣ መንግሥትና የሕግ አስከባሪ አካላት ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን ለፍትሕ እንዲያቀርቡና የገዳማትን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ በጥብቅ ጠይቀዋል። በተጨማሪም መላው ሕዝበ ክርስቲያንና ኢትዮጵያውያን ለተጎዱት ወገኖች አስፈላጊውን ሰብአዊና መንፈሳዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ አደራ ብለዋል።
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ መልእክት ሙሉ ይዘት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!**
ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦ እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።" (መዝሙር ፻፪፥፮)

በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን።

Comments