3 months ago
ያልተዘመረለት ጀግና!
* በኢትዮጵያ 30 ትምህርት ቤት አስገንብቷል
***
የአቶ አዲስ ገሠሠ አጭር የሕይወት ታሪክ
#ethiopia | አቶ አዲስ ገሰሰ ከአባታቸው ከግራዝማች ገሰሰ መንገሻ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አስናቀች መልሴ ጥር 8 ቀን 1945 ዓ.ም. በቀድሞው ኢሊባቦር ጠቅላይ ግዛት ጎሬ ከተማ ተወለዱ፡፡
እስከ 9ነኛ ክፍል በጎሬ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ት/ቤት ከተማሩ በኋላ፤ የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረው፤ ወደ ጅማ በመሄድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሚያዝያ 27 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በህይወታቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጡትና “ ስብዕናዬን በዲሲፕሊን ገንብቶታል” የሚሉትን የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በ1961 ዓ.ም. በመቀላቀል ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በበረራ ቴክኒሻንነት ተመርቀዋል፡፡
በሙያቸው አንድ ዓመት ካገለገሉ በኋላ፤ በ1964 ዓ.ም. ነፃ የትምህርት እድል በማግኘታቸው ወደ አሜሪካ ሀገር ሺካጎ ከተማ በማቅናት በራንቱል ኤርፎርስ ቤዝ፤ እና በቴክሳስ ላክላንድ ኤርፎርስ ቤዝ ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በወጣትነት ዘመናቸው ያን ጊዜ ሉፕ ኮሌጅ በሚባለው ሃሮልድ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በመቀጠልም በኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ወንድሞቻቸውን ሙሉጌታ ገሰሰን፤ ዘለቀ ገሰሰንና ጓደኞቻቸውን እነ መላኩ ረታን ወደ ሺካጎ ካመጡ በኋላ ዳሎል ባንድን መስርተዋል፡፡ አቶ አዲስ ገሰሰ በሚማሩበት ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር ታሪክ ወር /Black History Month/ በሚል መጠሪያ በየዓመቱ የካቲት ወር ላይ በተለያየ መዘክር በሚከበር በዓል ላይ፤ ዳሎል ባንድ ሙዚቃ እንዲያቀርብ በማስቻል የሙዚቃ ማኔጅመንት የህይወት ጉዟቸውን ሀ ብለው ጀመሩ፡፡
በመቀጠልም ዳሎል ባንድን ይዘው በዋሺንግተን፤ በሎስ አንጀለስ እና በመላው አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን-በኢትዮጵያ ባንድ የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ ፈር ቀዳጅ እና ውጤታማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ሙዚቃን ማኔጅ በማድረግ ጉዟቸው የእውቁን የሬጌ ሙዚቃ ንጉስ የቦብ ማርሌን ቤተሰብ ሃብትና ንብረቱን በማስተዳደር ብቻ ሳይሆን፤ የቦብን ልጆች በስነ ምግባር ኮትኮቶ ለማሳደግ ከአሜሪካ ኒውዮርክ -ጃማይካ ኪንግስተን እየተመላለሱ በትጋትና በታማኝነት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡
በዚያን ጊዜም ዘመን አይሽሬውን የቦብ ማርሌይ “ሌጀንድ አልበም" እንዲሰራ ባቀረቡት ንድፈ-ሃሳብ መሰረት ከአይላንድ ሪከርዲንግ ጋር በመፈራረም ውጤማ ስራ ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በቦብ ማርሌይ ቤተሰቦች የተዘጋጁትንና ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ የተደረጉትን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ኮንሰርቶች ሃሳብ ከመጠንሰስ ጀምሮ ለሃያ ሁለት ዓመታት ያክል ስራውን በሃላፊነት መርተዋል፡፡ አስተዳድረዋል፡፡
በዚሁ የአስተዳደር ዘመናቸው በዘረጉት መንገድ እስካሁን ድረስ በየዓመቱ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል በማይናወጥ መሰረት ላይ አፅንተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ዚጊ ማርሌይን ከጃማይካ… የነዘለቀን ገሰሰን ዳሎል ባንድ ደግሞ ከሺካጎ ወደኒዮርክ በማምጣት ካጣመሩ በኋላ ፤ ከሲግማ ስቱዲዮ እና ከቨርጂኒያ ሪከርድስ ጋር ውል በመፈራረም በአሜሪካ ምድር ቁጥር አንድ ተደማጭ የነበረውን ኮንሺየስ ፓርቲ አልበም እንዲለቀቅ አድርገዋል፡፡
በአልበሙ ከተካተቱት ስራዎች መካከል ቱሞሮ ፒውፕል የተሰኘው ሙዚቃ በዓለም ላይ እጅግ ከመወደዱ የተነሳ ብዙዎች እንደ ብሔራዊ መዝሙር ያዜሙት ነበር፡፡
በአቶ አዲስ ገሰሰ ማናጀርነት በተመራው በዚሁ የሙዚቃ አልበም ዚጊ ማርሌይ የአሜሪካንን ትልቁን ግራሚ አዋርድ ሽልማት ሲያገኝ፤ የኢትዮጵያው ዳሎል ባንድ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ባንድ የግራሚ ሽልማት እንዲወስድ በማስቻል ታሪክ የማይረሳውን ስራ ሰርተዋል፡፡
ለሀገራቸው ኢትዮጵያ የተለየ ፍቅር የነበራቸው አቶ አዲስ ገሰሰ ከወንድማቸው ከአርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊ 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ለመዘከር የሚዘጋጀውን “አፍሪካ ዩናይት” ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያን መዳረሻ በማድረግና አንድ አመት የፈጀ የዘመቻ /ካምፔይን/ በመስራት ፤ በ1997 ዓ.ም. መስቀል አደባባይ የተካሄደውን የሙዚቃ ፌስቲቫል ስኬታማ እንዲሆን አስችለዋል፡፡ በዚሁ ፌስቲቫል ላይ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ሪታ ማርሌይና አምስቱ የቦብ ልጆች ተገኝተዋል፡፡
ይኸው ፌስቲቫል በፈጠረው መልካም አጋጣሚም ሀገራችንን በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ፤ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና ኢንቨስመንት ለመሳብ በማለም ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጋብዘው የራሳቸውን የዜግነት ድርሻ ተወጥተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት የሕይወት ጉዟቸው ያካበቱትን እውቀትና ልምድ ተጠቅመው ተሰጥዎ ያላቸውን ልጆች በመቃኘት ሀገራቸውን በሙዚቃው ኢንደስትሪ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው፡፡ ለዚህም ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮን/ከመጀመሪያው አልበሙ ጀምሮ ማኔጅመንቱን በመያዝ ፤ እንዲሁም እጅጋየው ሽባባው /ጂጂን/ ከአጋራቸው ፓልም ሪከርዲንግ ጋር በመሆን ተወዳጅ የሆነ አልበሟን እንድተሰራ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን ጃኖ ባንድን በመመስረት ለልጆቹ ውጤታማነት አቶ አዲስ ገሰሰ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ አቶ አዲስ “ጃናናይት” የተባለ ተሰጥዎ ያላቸውን ሴቶች የያዘ ባንድ መስርተው ስኬታማ ለማድረግ ያደረጉት ጥረትም የሚወሳ ነው፡፡
በሙዚቃ ኢንዱስትሪው- እጅግ ገዝፈው፤ በተለያየ የአድናቆት ቃል የሚጠሩት አቶ አዲስ ገሰሰ ከሀገራችን ውጪ እንደ ዚጊ ማርሌ፤ ስቴፈን ማርሌ፤ ሎረን ሂል፣ ፊል ኮሊንስ፣ ኧርዝ ዊንድ ኤንድ ፋየር እና ሌሎችንም በርካታ የሙዚቃ ከዋክብትን በማግኘትና በማስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙ ታላላቅ የሙዚቃ ሰዎች ስራን መስመር አሲዘዋል።
አቶ አዲስ ገሰሰ መደበኛ መኖሪያቸውን ወደ ኢትዮጵያ ካዞሩ በኋላ በሆቴሊንግ ዘርፍ በመሰማራት ላየንስ ዴን ሆቴልን፤ በማእድን ዘርፍም ዩኒቨርሳል ማይኒንግን፤ በግብርና መስክ አድሶጌት ኩባንያን በማቋቋም ለሀገራቸው እድገት ቀን ከሌት ያለእረፍት ሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንትና በኢንቨስትመንት ስራቸው ብቻ ሳይሆን በበጎ አድራጎታቸውም አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል፡፡ በግል ከደገፏቸው ግለሰቦች በተጨማሪ በሀገራችን በተለያዩ ወቅቶች በተፈጠሩ ሰብአዊ ችግሮች ቀድመው በመድረስ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
በዋናነትም ከወንድማቸው ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን በተለያዩ ገጠራማ አካባቢዎች 30 ትምህርት ቤቶችን አሰርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ስለእነኚሁ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ስላሰሯቸው 30 ትምህርት ቤቶች ሲናገሩ “ተስፋ ሳልቆርጥ በፅናት የታገልኩበት በጎ ተግባር በመሆኑ ያስደስተኛል” ይሉ ነበር፡፡
ቤተ-ክርስቲያን በጠራቻቸው ጊዜ ሁሉ እየተገኙም በመላው ኢትዮጵያ አዳዲስ ቤተክርስቲያኖችን በማሰራት ፤ የተጎዱ ገዳማትንና ቤተክርስቲያኖችን በማደስ ፤ የተዘጉ ቤተክርስቲያኖችን በማስከፈት፤ የቤተክርስቲያኖችን ንዋየ ቅዱሳን በማሟላትና የካህናት ደሞዝን በመክፈል እስከ ህይወት ፍፃሜያቸው ድረስ ድምፃቸውን አጥፍተው አገልግለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በማህበራዊ ህይወታቸው ቀልድ አዋቂ፤ ተጫዋች እና በቀላሉ ከሰዎች ጋር ተግባብተው የመኖር ፀጋ የነበራቸው ሲሆን ከሁሉም ግን ሰው አካባሪ እና ስነ-ምግባር ያለው ቀረቤታቸው ተወዳጅና በሰው ልብ አይረሴ አድርጓቸዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ከወ/ሮ ሶስና ሽፈራው ጋር በነበራቸው የፀና ትዳር አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጅ አፍርተዋል፡፡
አቶ አዲስ ገሰሰ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ፤ በአሜሪካ ሀገር ኒውጄርሲ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡
የቀብር ሥነ ስርዓቱ ዛሬ፣ ሰኔ 20 ቀን 2018ዓ.ም በ6:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
አቶ አዲስ ገሰሰን ከአጠገቡ ሳትለዩ ላስታመማችሁትና ለጠየቃችሁት ወዳጅ ዘመዶች ልዑል እግዚአብሔር ብድራችሁን ይከፈላችሁ፡፡
የአቶ አዲስ ገሰሰን ነፍስ ልዑል እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ከደጋጎቹ አብርሃም ይስሐቅ እና ያቆብ ጎን ያሳርፍልን፡፡
ለቤተሰቡ፤ ለወዳጆቹ፤ ለዘመዶቹ፤ ለሙያ አጋሮቹ፤ ለአድናቂዎቹ ሁሉ መፅናናቱን ይስጣቸው፡፡

4 months ago
የሀዘን መግለጫ
#ethiopia | ዓለም አቀፍ እውቅናን የነበረቻው እውቁ የሙዚቃ ማናጀር አቶ አዲሱ ገሰሰ ባደረባቸው ህመም በአሜሪካ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ73 ዓመታቸው ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
በሙዚቃ ኢንዱስትሪው "የነፍስ አባት" (Godfather) በመባል የሚታወቁት አቶ አዲሱ ገሰሰ የህይወት ፔንዱለም ወደ ሙዚቃ ማናጀርነት ከማዞሯ በፊት በዲሲፕሊን አንፆኛል በሚሉት ዝነኛው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በግራንድ ቴክኒሳንነት ለአንድ አመት እንዳገለገሉ የትምህርት እድል በማግኘታቸው ወደ አሜሪካ ሺካጎ በማቅናት ራንቱል ኤርፎርስ ቤዝ እና ቴክሳስ ላክላንድ ኤርፎርስ ቤዝ ትምህርታቸውን ተከታትለው ተመርቀዋል፡፡
በመቀጠልም ሃሮልድ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ በዛን ስያሜው ሉፕ ኮሌጅ በሚባለው ሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ ይማሩበት በነበረው ኖርዝ ኢስተርን ኢሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር ታሪክ ወር /Black History Month/ ተብሎ በየዓመቱ የካቲት ወር ላይ በተለያየ መዘክር ወንሞቻቸው ዘለቀ ገሰሰ፤ ሙሉጌታ ገሰሰ፤ እና ጓደኞቻቸውን እነ መላኩ ረታ በዳሎል ባንድ ሙዚቃ እንዲያቀርቡ በማስቻል የማናጅመንቱን ስራ በመስራት የሙዚቃ ህይወት ጉዟቸውን ሀ ብለው ጀመሩ፡፡
በዋሺንግተን፤ በሎስ አንጀለስ በአሜሪካ መድር በኢትዮጵያን ለኢትዪጵያን የመጀመሪያውን የሙዚቃ መድረክ በዳሎል ባንድ ውጤታማ ስራ መስራት ችለዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ የማርሌን ቤተሰብ ከነሃብት ንብረቱ በሚያስተዳድሩበት ጊዜ ዘመን አይሽሬውን ኤክሶደስ ሌጀንድ አልበም ከአይስ ላንድ ሪከርዲንግ ጋር እነዲሰራ ማድረግ የቻሉ ሲሆን አቶ አዲሱ ገሰሰ በማርሌ ቤተሰቦች በሚዘጋጀው አለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ መድረክ ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ለተደረጉት የሙዚቃ መድረኮች የሙዚቃ ጉዞ ሃሳቡን ከመጠንሰስ ጀምሮ ከሁለት አስር ዐመታት በላይ ስራውን በማኔጅመንትነት በመምራት እና በማስተዳደር የዘረጉት መንገድ እስካሁን ድረስ በየዓመቱ የሚደረግን ዓለም አቀፍ የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል የማይናወፅ የማእዘን ድንጋይ ተክለዋል፡፡
በየሀገሩ እና ሙዚቃ በተደረገበት መድረክ ሁሉ አቶ አዲስ ፕሮግራሙን የሚያስጀምሩት አባታችን ሆይ በሚለው ቡራኬና ፀሎት በመሆኑ ፌስቲቫሉን የተለየ ድባብ መፍጠራቸውም የሚዘነጋ አይደለም፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ ዚጊን ከጃማይካ የነዘለቀን ዳሎል ባንድ ከሺካጎ ወደኒዮርክ በማምጣት ካጣመሩ በኋላ ከሲግማ ስቱዲዮ ጋር፤ እና ከቨርጂኒያ ሪከርድስ ጋር ውል በማድረግ በአሜሪካ ምድር ቁጥር አንድ አልበም የሆነውን ኮንሺየስ ፓርቲ ማኔጅ በማድረግ ዚጊ ማርሌ የሜሪካንን ትልቁን ግራሚ አዋርድ ሽልማት ሲያገኝ፤ የኢትዮጵያ ዳሎል ባንድ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ባንድ የግራሚ ሽልማቱን እንዲወስዱ በማስቻል ታሪክ የማይረሳው ስራ ሰርተው አልፈዋል፡፡
ለሀገራቸው ኢትዮጵያ የተለየ ፍቅር የነበራቸው አቶ አዲሱ ገሰሰ ከወንድማቸው አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊ 60 ዓመት የልደት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያን መዳረሻ በማድረግ አንድ አመት የፈጀ የዘመቻ /ካምፔይን/ በመስራት በ1997 ዓ.ም. መስቀል አደባባይ የተካሄደውን የሙዚቃ ፌስቲቫል ስኬታማ እንዲሆን በማስቻል መልካም አጋጣሚ በመፍጠር፤ ሀገራችንን በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ፤ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ፤ እና ኢንቨስመንት ለመሳብ በማለም ዓለም አቀፍ የሆኑ ከ50 በላይ ሚዲያዎችን በመጋብዝ ድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት የሕይወት ጉዟቸው ያካበቱትን እውቀትና ልምድ በመላ ተጠቅመው ተሰጥዎ ያላቸውን ልጆች በመቃኘት ሀገራቸውን በሙዚቃው ኢንደስትሪ ዓለም አቀፍ ተወዳዳዳሪ ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው፡፡ በዚህም እጅጋየው ሽባባውን /ጂጂ/ ከአጋራቸው ፓልም ሪከርዲንግ ጋር በመሆን ተወዳጅ የሆነ አልበሟን እንድተሰራ ያደረጉ ሲሆን፤ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በሚሰራው ሙዚቃም ማኔጅምቱን በመያዝ ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ነው፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን ጃኖ ባንድን በመመስረት እና ለፍሬ እንዲበቁ የአቶ አዲስ ገሰሰ ድጋፍ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ተግባር ነበር፡፡ አቶ አዲስ ጃናናይት የተባለ ተሰጥዎ ያላቸውን ሴቶች የያዘም ባንድ መስርተው ለመጓዝ ያደረጉትንም ጥረት የሚወሳ ነው፡፡ በሙዚቃ ኢንዱስትሪው "የነፍስ አባት" (Godfather) በመባል የሚታወቁ አቶ አዲሱ ገሰሰ ከሀገራችን ውጪ እንደ ዚጊ ማርሌ፤ ስቴፈን ማርሌ፤ ሎሪን ሂል፣ ፊል ኮሊንስ፣ አርዝ ዊንድ ኤንድ ፋየር (Earth, Wind, & Fire) እና ሌሎችንም በርካታ የሙዚቃ ከዋክብትን በማግኘትና በማስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዙዎችን የሙዚቃ ስራ መስመር አሲዘዋል።
አቶ አዲሱ ገሰሰ በሙዚቃ ማኔጅመንት ስራቸው ብቻ ሳይሆን በበጎ ስራ ተግባራቸው የተወደደ አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል፡፡ ከነዚህም መሃከል በግል ከደገፏቸው ግለሰቦች በተጨማሪ በሀገራችን በተለያያ ጊዜ የተፈጠሩ ሰብአዊ ችግሮችን ለመድረስ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚጠቀስ ሲሆን በዋናነት ከወንድማቸው ዘለቀ ገሰሰ ጋር በመሆን በተለያዩ ገጠረማ አካባቢዎች 30 ትምህርት ቤቶችን በማሰራት ያደረጉት በጎ ተግባር በታሪክ የሚወሳ አርአያነት ያለው ተግባር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ መደበኛ መኖሪያቸውን ወደ ኢትዮጵያ ካዞሩ በኋላ በሆቴሊንግ ዘርፍ በመሰማራት ላየንስ ዴን ሆቴልን፤ በማእድን ዘርፍ ዩኒቨርሳል ማይኒንግን፤ በግብርና መስክ አድሶጌት ኩባንያን በማቋቋም የራሳቸውን ጡብ ለማስቀመጥ ቀን ከሌት ያለእረፍት ጥረዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ በማህበራዊ ህይወታቸው ቀልድ አዋቂ፤ ተጫዋች እና በቀላሉ ከሰዎች ጋር ተግባብተው የመኖር ፀጋ የነበራቸው ሲሆን ከሁሉም ግን ሰው አካባሪ እና ስነ ምግባር ያለው ቀረቤታቸው ተወዳጅ እና በሰው ልብ አይረሴ አድርጓቸዋል፡፡
አቶ አዲሱ ገሰሰ ከወ/ሮ ሶስና ሽፈራው ጋር በነበረው የፀና ትዳር አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ለማፍራት ችለዋል፡፡
የአቶ አዲሱ ገሰሰ የአስክሪን ሽኝትና ስርዓተ ቀብር አፈጻጸም ስንነስርዓት በቅርቡ እናሳውቃለን ፡፡

8 months ago
"የትግራይ ሕዝብ ሀገሩን ከሚወጉት ጋር ተሰልፎ የመዋጋት ጥቁር ታሪክ የለውም"
- ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም
የትግራይ ሕዝብ ሀገሩን ከሚወጉት ጋር ተሰልፎ የመዋጋት ጥቁር ታሪክ የለውም ሲሉ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬርያ ኢብራሂም ገለጹ፡፡
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬርያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የሕወሓት ቡድን ግን የተሰለፈው ከትግራይ ሕዝብና ከሀገሪቱ ጠላት ጋር ነው።
የትግራይ ሕዝብ ሀገሩን የሚወድ እንጅ ከሕዝብና ከሀገሩ ጋር ተቃራኒ ሆኖ የሚሰለፍበት ምንም ዓይነት ሁኔታ የለም፤ እንደዚህ ዓይነት ታሪክም የለውም ብለዋል።
እንደ ወይዘሮ ኬርያ ገለጻ፤ የትግራይ ሕዝብና የትግራይ ምድር የጦር ሜዳ እንዳይሆን ህዝቡ ሊጠነቀቅ ይባል፡፡
ይህ እንዳይከሰት አሰላለፋችንን ማስተካከል እና ከጥፋት ኃይሎች በተቃራኒ መቆም አለብን ሲሉ መክረዋል።
ለትግራይ ሕዝብ ሲባል የጦርነት በር መዘጋት አለበት ያሉት ወይዘሮ ኬርያ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ለሰላም ግፊት ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች መመለስ የሚቻለው ከፌዴራል መንግሥት ጎን በመሰለፍ በሰላማዊ እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጅ በጦርነት አይፈታም ሲሉም አስረድተዋል።
@ጋዜጣ-ፕላስ

9 months ago
ታዋቂው ዩቲዩበር I Show Speed ግብፅን በጎበኘበት ወቅት የጠየቀው ጥያቄ አሁንም መነጋገሪያነቱ አልበረደም
ለምንድነው አብዛኞቹ የግብፅ ሃውልቶች አፍንጫቸው የተቆረጠው?
ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች ከታሪክ፣ ከፖለቲካና ከዘር ማንነት ጋር የተያያዙ ናቸው።
1️⃣ "ጥቁርነታቸውን ለመደበቅ የተደረገ ሴራ"
ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎችና የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ አጥኚዎች (Afrocentrists) እንደሚከራከሩት የሃውልቶቹ አፍንጫ እንዲሰበር የተደረገው የጥንት ግብፃውያን ጥቁር አፍሪካውያን መሆናቸውን ለመደበቅ ነው።
* የአፍንጫ ቅርጽ ምስክርነት፦
የአፍሪካውያን መለያ የሆነው ሰፋ ያለ አፍንጫ (Afroid features) በሃውልቶቹ ላይ በግልጽ ይታይ ነበር ይህንን የዘር ምልክት በማጥፋት ስልጣኔው የጥቁሮች አለመሆኑን ለማሳየት ሆን ተብሎ የተደረገ የጥፋት ስራ ነው ይላሉ።
* የፈርኦኖች የፀጉር አሠራር፦
የጥንት ፈርኦኖችና ንግሥቶች ምስል ሲታይ ፀጉራቸው ዛሬ በአፍሪካውያን ዘንድ እንደሚታየው ሹሩባ (Braids)፣ ቁንጮ (Locs) እና አፍሮ (Afro) ስታይል ነው ይህ የፀጉር አሠራር ከዛሬዎቹ ነጭ ግብፃውያን ይልቅ ከጥቁር አፍሪካውያን ባህል ጋር ቀጥታ ይገናኛል።
2️⃣ "አሁንም ድረስ ያሉት ጥቁር ግብፃውያን"
የጥንት ግብፃውያን የዘር ግንድ ዛሬም አልጠፋም በደቡባዊ ግብፅ (በአስዋንና አካባቢው) የሚኖሩት ኑቢያውያን (Nubians) የጥንቶቹ ፈርኦኖች ቀጥተኛ ወራሾችና ጥቁር ቆዳ ያላቸው ግብፃውያን ናቸው ዛሬም ድረስ በግብፅ ውስጥ ጥቁር ቆዳ ያላቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኑቢያውያን መኖራቸው "ጥንታዊቷ ግብፅ የጥቁሮች አልነበረችም" የሚለውን የተሳሳተ ትርክት ውድቅ ያደርገዋል።
3️⃣ "የመንፈሳዊ ኃይል መግደያ"
(የምዕራባውያን ምሁራን እይታ)
በሌላ በኩል ደግሞ አርኪኦሎጂስቶች የሚከተለውን ምክንያት ያቀርባሉ
* ትንፋሽ መከልከል - ጥንታውያን ግብፃውያን ሃውልቶች "ካ" (Ka) የተባለ መንፈስ አላቸው ብለው ያምኑ ነበር።
የአንድን ሃውልት አፍንጫ መስበር ማለት መንፈሱ እንዳይተነፍስና ኃይል እንዳይኖረው ማድረግ እንደሆነ ይታመን ነበር።
* የፖለቲካ በቀል - አዳዲስ ነገሥታት የቀደሙትን ዝና ለማጥፋትና መንፈሳቸውን ለመግደል አፍንጫቸውን ያስሰብሩ ነበር።
የ"I Show Speed" ጥያቄ አለም በግብፅ ታሪክ ላይ የነበረውን የተዛባ አመለካከት እንዲመረምር በር ከፍቷል የፈርኦኖቹ የፀጉር አሠራር፣ የፊታቸው ቅርጽና ዛሬም ድረስ ያሉት ጥቁር ኑቢያውያን ምስክሮች ናቸው።
የግብፅ ስልጣኔ የአፍሪካውያን ስልጣኔ መሆኑንና አፍንጫዎቹ የተሰበሩትም ይህን እውነት ለመሸፈን ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ።
የእናንተስ አስተያየት ምንድነው?
ታሪኩን ለመቀየር የታቀደ የዘር ጥቃት ነው? ወይስ የጥንቶቹ ግብፃውያን መንፈሳዊ እምነት ውጤት?
አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇🏾
Comments