22 days ago
በአለም በየአመቱ 134 ሚሊዮን የሕክምና ስህተቶች ይፈፀማሉ!
#ethiopia | ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም የሕሙማን ደኅንነት ቀን እየተከበረ ይገኛል።
እለቱን አስመልክቶ የአለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 134 ሚሊዮን የሕክምና ስህተቶች እንደሚፈጸሙና ይህም ለ2.6 ሚሊዮን ዜጎች ሕይወት ህልፈት ምክንያት መሆኑን ጠቅሷል።
ዛሬ መስከረም 7 ቀን የሚከበረውን የዓለም የሕሙማን ደኅንነት ቀን ምክንያት በማድረግ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ችግሩ በተለይም በታዳጊና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ አመላክቷል።
ድርጅቱ ጥንቃቄ በጎደለውና ጥራቱን ባልጠበቀ የሕክምና ምርመራ መድኃኒት አሰጣጥ እንዲሁም የአገልግሎት ግድፈት ምክንያት ነው የሚከሰተው ብሏል።
ይህ ችግር በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ላይ በየዓመቱ 1.6 ትሪሊዮን ዶላር የምርታማነት መጓደልና የኢኮኖሚ ኪሳራ እያስከተለ እንደሆነ የዓለም ባንክና የሕክምና ተቋማት ጥናቶች ጠቁመዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለፀው አብዛኞቹ የሕክምና ስህተቶች በቅድመ ጥንቃቄና በዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶች ሊቀነሱ የሚችሉ ናቸው ብሏል።
በመሆኑም በዘርፉ ላይ የሚደርሰውን የሰውና የኢኮኖሚ ኪሳራ ለማስቀረት የሕሙማንን ደኅንነት መጠበቅ የጤና አገልግሎት ዋነኛ አካል ማድረግ ይገባል ሲል ገልጿል።
የሕክምና ተቋማትን በዲጂታልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማደራጀት ያስፈልጋል ነው ያለው።
እንዲሁም የሕክምና ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበትና ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ተጠቅሷል።
የአለም ጤና ድርጅት ሀገራት የጤና ዘርፋቸውን በማዘመን የዜጎችን የማምረት አቅም እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል።
ስምንተኛው የዓለም የህሙማን ደህንነት ቀን በሀገራችን ኢትዮጵያም በዛሬው እለት በዘውዲቱ መታሰብያ ሆስፒታል በተለያዩ መርሀግብሮች ተከብሮ ውሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #worldpatientsafetyday #who #patientsafety #healthnews

25 days ago
አዲሱ የትምህርት ዘመን እና የትምህርት ጥራት ጉዞ በነገዋ ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ
******************
በኢትዮጵያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአዳዲስ ተስፋዎችና እቅዶች ተማሪዎችን ተቀብለው የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር-ማስተማር ሂደቱን በዛሬው ዕለት በይፋ ጀምረዋል።
የትምህርት ዘመኑ መጀመር የተማሪዎችንና የወላጆችን ስሜት ከማነቃቃቱም በላይ፣ የሀገራችን የትምህርት ዘርፍ አጠቃላይ ሁኔታ፣ የትምህርት ጥራትን እና የወደፊት የትውልድ እጣ ፈንታን በድጋሚ እንድንፈትሽ ትልቅ እድል ይፈጥራል።
ትምህርት የአንድ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት ከመሆኑ አንጻር፣ በትምህርት ጥራት ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩት በነገዋ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ ነው።
በቅርብ ዓመታት የተካሄዱ ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል እና የሌሎች ደረጃዎች ፈተና ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ የተማሪዎች የትምህርት አቀባበልና የውጤት ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ነው። የተማሪዎች ውጤት ዝቅ ማለት በቀጣይ የከፍተኛ ትምህርትና የሙያ ሥልጠና ብቃታቸው ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።
መሰረታዊ የጽሑፍ፣ የንባብ እና የሒሳብ ስሌት ብቃት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በበቂ ሁኔታ አለመገንባቱ ለከፍተኛ ክፍል ውጤት ማነስ እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳል።
መምህራን የትምህርት ጥራት ዋና አሸጋጋሪዎች ናቸው። የመምህራን የሙያ ማሻሻያ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና የትምህርት ዝግጅት ጥራት በቀጥታ ከተማሪዎች ስኬት ጋር የተያያዘ ነው።
የትምህርት ቤቶች ደረጃ፣ የቤተ-ሙከራዎችና ቤተ-መጻሕፍት መሟላት፣ የመማሪያ መጻሕፍት ከተማሪዎች ቁጥር ጋር ያለው ተመጣጣኝነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅርቦት ለጥራት ወሳኝ ናቸው።
ከትምህርት ሚኒስቴር እስከ ትምህርት ቤት ባለው መዋቅር ውስጥ የሚከናወን የነፃና ገለልተኛ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት ወሳኝ ነው። የትምህርት አመራሮች በሙያ ብቃትና በትምህርት አስተዳደር የበሰሉ መሆናቸው፣ አሰራርን ግልጽና ተጠያቂነት ያለው በማድረግ የትምህርት ጥራትን ያረጋግጣል።
ትምህርት የቤትና የትምህርት ቤት ጥምር ውጤት ነው። የወላጅ እና መምህራን ሕብረት ካልተጠናከረ፣ ወላጆች የተማሪዎችን የቤት ሥራና ክትትል ካላደረጉ እና ማህበረሰቡ ትምህርት ቤቶችን የራሱ አድርጎ በሀብትና በክትትል ካልደገፈ የትምህርት ጥራትን በሙሉ አቅም ማረጋገጥ አይቻልም።
በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለመመለስ በቅርብ ዓመታት ጉልህ የሪፎርም እርምጃዎች ተወስደዋል። በዚሁም የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ መደረጉ የኩረጃ እና የማጭበርበር ባህልን በማስቀረት፣ ትክክለኛውን የተማሪዎች ብቃትና የትምህርት ቤቶችን እውነተኛ ደረጃ ለማየት አስችሏል።
የዘመኑን የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ሁኔታ ያገናዘበ አዲስ ሥርዓተ-ትምህርት ተቀርጾ ወደ ተግባር ገብቷል። ሕብረተሰቡንና ባለሀብቱን ያሳተፉ የትምህርት ቤት ግንባታና የግብዓት ማሟላት ዘመቻዎች በማካሄድ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ተችሏል።
የ2019 የትምህርት ዘመን ሲጀመር፣ ከተማሪዎች የደብተርና የዩኒፎርም ዝግጅት ባሻገር የጠቅላላ ትምህርት ሥርዓታችን የጥራት ዝግጅት የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የወላጆች፣ የመምህራን፣ የባለሀብቶችና አጠቃላይ የማህበረሰቡ የጋራ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል።
አሁን የሚደረግ ማንኛውም አስተማማኝ የትምህርት ኢንቨስትመንት፣ የነገዋን ብቁና ተወዳዳሪ ኢትዮጵያን የመገንባት መሰረት ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #ebc #ethiopianeducation #educationreform #qualityeducation

1 month ago
33.26 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የምግብ ምርቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እያከናወነ ነው።
መድረኩ በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ መሪነት እየተካሄደ ሲሆን፣ በ2018 ዓ.ም በምግብ፣ በመድኃኒት፣ በሕክምና መሣሪያዎች፣ በመዋቢያ፣ በትምባሆና በአልኮል ዘርፎች የተከናወኑ የቁጥጥር ሥራዎች በዝርዝር እየተገመገሙ ይገኛል።
በግምገማው የቁጥጥር ሥራዎች አፈጻጸም፣ የላብራቶሪ ምርመራዎች፣ የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ፣ የድህረ-ገበያ ክትትልና ቁጥጥር፣ እንዲሁም በሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ባልተጠበቁ ምርቶች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
ባለሥልጣኑ በበጀት ዓመቱ 33.26 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የምግብ ምርቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
በመድኃኒትና በሕክምና ግብዓቶችም ያልተመዘገቡና ሕገ-ወጥ ምርቶች ተይዘው እርምጃ መወሰዱ ተመልክቷል።
የግምገማ መድረኩ የተከናወኑ ሥራዎችን ከመገምገም ባለፈ፣ በቀጣይ የሚከናወኑ የቁጥጥር ሥራዎችን የበለጠ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው ለማድረግ ትኩረት የሚደረግባቸውን አቅጣጫዎችም ለመለየት ያግዛል።
አዲስ አበባ፤ በ2018 በጀት ዓመት በምግብ፣ መድኃኒት፣ የሕክምና መሣሪያዎች፣ መዋቢያ፣ ትምባሆና አልኮል ዘርፎች የሸማቾችን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ ሰፊ የቁጥጥር፣ የምርመራና የሕግ አፈጻጸም ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ።
በምግብ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 4,356 የምግብ ምርቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ለ147 የምግብ አምራችና ለ1,547 አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት የቅድመ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን ተካሂዶ የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል።
በተጨማሪም በ554 አምራቾችና በ1,509 አስመጪና አከፋፋዮች ላይ ስጋት ተኮር ድህረ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን ተከናውኗል።
በሕገ-ወጥና ደህንነታቸው ባልተጠበቁ የምግብ ምርቶች ላይ በተደረጉ 8 ዙር ሰርቪላንስና 8 ኦፕሬሽኖች በአጠቃላይ 33.26 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከእነዚህም መካከል 10,600 ኪ.ግ ቅቤ፣ 6,925 ኪ.ግ ማር፣ 4,680 ኪ.ግ የታሸገ የአትክልት ቅቤ፣ 700 ኩንታል ጥራቱን ያልጠበቀ ጨው፣ የተቀላቀለና ሐሰተኛ በርበሬ እና ሌሎች ምርቶች ይገኙበታል።
በመድኃኒት ዘርፍ ደግሞ 1,939 መድኃኒቶች የገበያ ፈቃድ ያገኙ ሲሆን፣ 634 የመድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት የቅድመ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን ተደርጎላቸዋል።
በተጨማሪም 12 የሀገር ውስጥ አምራቾች፣ 1,226 አስመጪና አከፋፋዮች እና 8 የሜዲካል ኦክስጅን አምራቾች ላይ ስጋት ተኮር ኦዲት ተካሂዷል።
በቁጥጥር ሥራው በአዲስ አበባ 2 ኮንቴነሮች የሚሆኑ 32 ዓይነት ያልተመዘገቡ የሕክምና መሣሪያዎችና ሪኤጀንቶች ተይዘዋል።
በተጨማሪም በከፋ ዞን ወደ 1 ሚሊዮን ብር፣ በጅማ 1,040,078 ብር እና በበደሌ 511,596 ብር የሚገመቱ ያልተመዘገቡና ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በሕክምና መሣሪያዎች ዘርፍም 293 SRA እውቅና ያገኙ መሣሪያዎች፣ 583 አዳዲስ NIVD እና 360 አዳዲስ IVD መሣሪያዎች የገበያ ፈቃድ አግኝተዋል።
በገቢ የሕክምና መሣሪያዎች ላይ በተደረገው የጥራት ቁጥጥርም 126.47 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ መሣሪያዎች የመልቀቂያ ፈቃድ አግኝተዋል።
በላቦራቶሪ ምርመራ በምግብ ዘርፍ 4,371 የምግብ ናሙናዎች በባዕድ ነገር መቀላቀል ጥናት ተመርምረዋል፤ በምግብ ደህንነትና ንጽህና ደግሞ 588 ናሙናዎች ተመርምረዋል።
በሕክምና መሣሪያዎች ምርመራ ደግሞ 273 የኮንዶም፣ 315 የሲሪንጅ፣ 169 የግላቭ እና 229 የIVD ናሙናዎች ተመርምረዋል።
በትምባሆ ቁጥጥር ረገድ 107,240 ተቋማት ላይ የቁጥጥር ሥራ ተከናውኗል፤ በአልኮል ማስታወቂያ፣ ማስተዋወቅ፣ ስፖንሰርሺፕና በተከለከሉ ቦታዎች ሽያጭን ለመቀነስ የታቀዱ የቁጥጥር ዕቅዶችም 100 በመቶ መፈጸማቸው ተገልጿል።
በሕግ አፈጻጸም በኩልም 56 የወንጀል ጉዳዮች ክትትል የተደረገባቸው ሲሆን፣ በ23 ጉዳዮች ላይ ክስ ቀርቧል።
በተጨማሪም 20 ኬዞች ላይ ለፖሊስና ለፍርድ ቤት ምላሽና ማስረጃ ተሰጥቷል። ከሕገ-ወጥ መድኃኒት ዝውውር ጋር በተያያዘም 33 መዝገቦች ተጣርተው ለፍትሕ አካላት ተልከዋል።
4,356 የምግብ ምርቶች ተመዝግበዋል
33.26 ሚሊዮን ብር የምግብ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል
1,939 መድኃኒቶች የገበያ ፈቃድ አግኝተዋል
126.47 ቢሊዮን ብር የሕክምና መሣሪያዎች የመልቀቂያ ፈቃድ አግኝተዋል
107,240 ተቋማት በትምባሆ ቁጥጥር ተመርምረዋል
56 የወንጀል ጉዳዮች ክትትል ተደርጎባቸዋል
4,371 የምግብ ናሙናዎች በባዕድ ነገር መቀላቀል ምርመራ ተደርጎባቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #የጋዜጣዊመግለጫ #የምግብደህንነት #መድኃኒት #የሕክምናመሣሪያ #ቁጥጥር #የምግብጥራት #healthandsafety #foodsafety #medicinesafety #ethiopia #addisababa #getutemesgen #ጌጡተመስገን

5 months ago
የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀ፤ ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተባለ
#fastmereja I በአዲስ አበባ ከተማ ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም ያለው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ተመርቋል። የከተማዋን የኢኮኖሚ መዋቅር ያዘምናል የተባለውና ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀው ይህ ግዙፍ ፓርክ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይፋ እንዳደረጉት፣ ፓርኩ በ93.9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን 116 የማምረቻ ቦታዎችን፣ 356 ቢሮዎችን እና 248 ሱቆችን በውስጡ ይዟል። ከዚህም በተጨማሪ በአንድ ጊዜ ከ400 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ስፍራ፣ የ4 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ፣ 25 የሰዎችና ዕቃዎች ማጓጓዣ ሊፍቶች እንዲሁም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት የሚሰጡ 10 ትራንስፎርመሮችና ዘመናዊ ጀነሬተሮች ተገጥመውለታል።
ይህ ሁለገብ የኢንዱስትሪ መንደር ከማምረቻ ዘርፉ ባሻገር ሆቴል፣ ካፌቴሪያ፣ የጥራት ቁጥጥር ማዕከል፣ ራሱን የቻለ የውኃ ጉድጓድ እና ዘመናዊ የቆሻሻ ማጣሪያ ሥርዓት ተሟልቶለታል። በተጨማሪም የሕፃናት ማቆያ፣ የስፖርት ሜዳዎችና ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራዎች እንደተካተቱበት ተገልጿል። ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት ጊዜ፣ ጥራትና በጀት መጠናቀቁን የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ ለግንባታው ስኬት ሌት ተቀን ለደከሙ የሥራ ተቋራጮች፣ አመራሮችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ የሥራ ባህል እየገነባ ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ሰብዕና እና የሥራ ባህል እየገነባ ነው አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
አገልግሎቱ የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አስመልክቶ ባወጣው መረጃ፤ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች ዓለም አቀፍ የጥራት ቁጥጥር ስታንዳርዶችን፣ ጥብቅ የጊዜ አጠቃቀምንና ስልታዊ የአመራር ክህሎትን በመላበስ ላይ ናቸው ብሏል።
ከታችኛው የሥራ እርከን ተነስተው በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ እስከ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ደረጃ የደረሱ ወጣቶች፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው "ምርጥ ምርት" የሰው ሀብቷ መሆኑን እያስመሰከሩ ነው ሲልም ገልጿል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ‘በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምርትን ከማሳደግና የውጭ ምንዛሬን ከመታደግ ባሻገር ዕውቀትንና ክህሎትን ለዓለም የምናበረክትበት አዲስ የኢንዱስትሪ ምዕራፍ ተጀምሯል!’ በሚል ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፤ 830 ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ስራ በማስገባት፣ 4.85 ቢሊየን ዶላር ገቢ ምርትን በመተካት እና 433 ሚሊየን ዶላር ከኤክስፖርት በማስገኘት አስደናቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ውጤት አስመዝግቧል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ሀገራዊ ንቅናቄ ሲጀምር፣ ግቡ ምርትን ማሳደግና የውጭ ምንዛሬን መታደግ ብቻ አልነበረም።
ከእነዚህ ኢኮኖሚያዊ ስሌቶች ባሻገር፣ ትልቁና ስትራቴጂካዊው ስኬታችን የተመዘገበው ኢትዮጵያን የዕውቀትና የክህሎት ምንጭ በሚያደርገው የሰው ሀብት ልማት ላይ ነው። ዛሬ ላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የፋብሪካዎች ስብስብ መሆኑ ቀርቶ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚገነቡ ብቁ ባለሙያዎችና መሪዎች የሚፈሩበት ታላቅ የተግባር ትምህርት ቤት መሆን ችሏል። ይህ ሽግግር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተወዳዳሪነት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቴክኖሎጂ ላኪነትና ክህሎት አቅራቢነት ከፍ የሚያደርግ ለነገዋ ኢትዮጵያዊ መሠረት የሚጥል የታሪካችን እጥፋት ነው።
በታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በግዙፍ ፋብሪካዎች ውስጥ የታየው ተጨባጭ ለውጥ የመንግሥትን የፖሊሲ ጥንካሬ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው። ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ክፍያ በሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች ብቻ ይተዳደሩ የነበሩ ውስብስብ የቴክኖሎጂ ሲስተሞች፣ ዘመናዊ የምርት መስመሮችና የሶፍትዌር መሠረተ-ልማቶች ዛሬ ላይ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ወጣት መሐንዲሶችና ቴክኒሻኖች እየተመሩ ይገኛሉ። ይህ ስኬታማ የዕውቀት ሽግግር፣ መንግሥት ጥራት ያለው ፖሊሲ የመቅረጽ ብቻ ሳይሆን ፖሊሲን በተጨባጭ ወደ ተግባር የመለወጥና የማስፈጸም አቅም እንዳለው ትልቅ ማሳያ ነው።
በዘረፉ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም የተፈጠረላቸውን ምቹ ዐውድ ተጠቀመው ቴክኖሎጂን የመቀበል ብቻ ሳይሆን፣ የመግራትና የማላመድ ብቃታቸውን በተግባር በማሳየት፣ ሀገራችን ለዘመናት የነበረባትን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት በፈጠራ አቅማቸው እያስቀሩና አዳዲስ የሥራ ባሕልና የታሪክ ምዕራፍ እየጻፉ ይገኛሉ።
የ "ኢትዮጵያ ታምርት"ንቅናቄ ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር፣ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ሰብዕና እና የሥራ ባህል እየገነባ ነው ። በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎች ዓለም አቀፍ የጥራት ቁጥጥር ስታንዳርዶችን፣ ጥብቅ የጊዜ አጠቃቀምንና ስልታዊ የአመራር ክህሎትን በመላበስ ላይ ናቸው። ከታችኛው የሥራ እርከን ተነስተው በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ እስከ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ደረጃ የደረሱ ወጣቶቻች፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው "ምርጥ ምርት" የሰው ሀብቷ መሆኑን እያስመሰከሩ ነው።
መንግሥት የኢንዱስትሪ ሽግግሩን ትክክለኛ ፍሬ የሚለካው በወጪ ንግድ ስሌቶች ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የደረጀና በዕውቀት የበለጸገ አምራች ዜጋ መፈጠሩ ነው። በመሆኑም ይህን የክህሎት አብዮት ይበልጥ በማፋጠንና ዘርፉን የቴክኖሎጂ ምንጭ በማድረግ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች በቁርጠኝነት ይቀጥላሉ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

7 months ago
⚠️ "OK በረኪና" የተሰኘውን ምርት ከመጠቀም ይቆጠቡ!
#ethiopia | የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባደረገው ጥብቅ የጥራት ፍተሻ እና የላቦራቶሪ ምርመራ፤ "OK በረኪና" የተሰኘው የጽዳት ምርት አስገዳጅ የሆነውን የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርት የማያሟላ ሆኖ በመገኘቱ፣ ህብረተሰቡ ምርቱን ከመጠቀም እንዲቆጠብ አስቸኳይ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
🔍 ለምን ታገደ?
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በገበያ ላይ ባደረገው የኢንስፔክሽን ስራ እና በወሰደው ወካይ ናሙና መሰረት የሚከተሉት ከፍተኛ የጥራት ጉድለቶች ተገኝተውበታል፡
* የመለያ መረጃ አለመኖር፦ በምርቱ ላይ የአምራች ስም፣ አድራሻ እና የብሄራዊ የደረጃ ምልክት (Quality Mark) የለውም።
* የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት፦ በምርቱ ውስጥ ያለው የሶዲየም ሃይድሮክሳይድ ይዘት (Sodium hydroxide content) እና የጥንካሬ መጠኑ (Stability) የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ (CES 234:2023) የደነገገውን መስፈርት አያሟላም።
* ምንጩ የማይታወቅ፦ ምርቱ የት እንደሚመረትና ማን እንደሚያመርተው የማይታወቅ በመሆኑ ለጤና እና ለደህንነት አስጊ ነው።
🚫 የተወሰዱ እርምጃዎች
የህብረተሰቡን ጤና እና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ሚኒስቴሩ የሚከተሉትን መመሪያዎች አስተላልፏል፡
* ለተጠቃሚዎች፦ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይህንን ምርት ከመግዛትም ሆነ ከመጠቀም እንዲቆጠብ።
* ለነጋዴዎች፦ በሱቆች፣ በሱፐርማርኬቶች እና በማንኛውም የንግድ ስፍራ ይህንን ምርት መሸጥ የተከለከለ ሲሆን፣ በሚሸጡ አካላት ላይ ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።
* ለተቆጣጣሪዎች፦ በየደረጃው የሚገኙ የክልልና የከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮዎች ምርቱ ከገበያ እንዲሰበሰብ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ ታዟል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መሰል የጥራት ጉድለት ያለባቸውንና የህብረተሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ምርቶችን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የጤና_ጥንቃቄ #የጥራት_ቁጥጥር #ኢትዮጵያ #የንግድና_ቀጣናዊ_ትስስር_ሚኒስቴር #ok_በረኪና #የተጠቃሚዎች_መብት

በአዲስ አበባ የመምህራን የሙያ ብቃት የሙከራ ፈተና በበይነ መረብ ሊሰጥ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት የሙከራ ፈተና በመጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በበይነ መረብ (Online) እንደሚሰጥ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት፣ ለሙከራ ፈተናው 11 ሺህ 103 ተመዛኞች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ይህም መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚሰጠው ዋና ምዘና ዝግጅት ነው።
ለሂደቱ ስኬታማነት የኮምፒውተርና የኢንተርኔት መሠረተ ልማቶች የተሟሉ ሲሆን፣ የቴክኒክ ኮሚቴም ተዋቅሮ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።
የጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢዘዲን ሚስባህ በበኩላቸው፣ ሁሉም ተመዛኞች በሙከራ ፈተናው ላይ እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል። ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና የአይሲቲ ባለሙያዎችም አስፈላጊው የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

8 months ago
የመንጃ ፈቃድ የሕክምና ምርመራ በአንድ ማዕከል ተጀመረ—ከእንግልት ነፃ ወይስ ተጨማሪ መጨናነቅ?
በአዲስ አበባ ከተማ ለዓመታት ተገልጋዮችን ሲያማርር የቆየውና በየጤና ጣቢያው ሲንከራተቱበት የነበረው የመንጃ ፈቃድ የሕክምና (ሜዲካል) ምርመራ፣ ከአሁን በኋላ በባለስልጣኑ ቅርንጫፎች ውስጥ "በአንድ ማዕከል" እንዲሰጥ መደረጉ ተበሰረ።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረጉት ስምምነት መሰረት፦
በ11ዱም ክፍለ ከተማ በሚገኙ የባለስልጣኑ ቅርንጫፎች።
በአንድ መሶብ የአገልግሎት ማዕከላት ውስጥ የጤና ባለሙያዎች በቋሚነት ተመድበዋል።
አገልግሎቱ አዲስ መንጃ ፈቃድ ለማውጣትም ሆነ ለማደስ የሚመጡ ተገልጋዮችን ያካትታል።
የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ እና የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደሳለኝ ተረፈ እንደገለጹት፤ አሰራሩ "የተገልጋዮችን እንግልት ይቀንሳል፣ አገልግሎቱንም ወደ ህዝቡ ያቀርባል" ብለዋል።
ሂሳዊ ትችት
ይህ ጅምር በቴክኒክ ደረጃ "አንድ መስኮት አገልግሎት" (One-Stop Service) ለመዘርጋት የሚደረግ መልካም እርምጃ ቢሆንም፣ የሚከተሉት ነጥቦች ግን ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፦
የመሠረተ ልማት ዝግጅት፡ ባለስልጣኑ በሰው ኃይል እጥረትና በሲስተም መቆራረጥ ቅሬታ የሚቀርብበት ተቋም ነው። አሁን ደግሞ የሕክምና ምርመራ ክፍልን በቢሮዎቹ ውስጥ መጨመሩ ያለውን መጨናነቅ (Congestion) እንዳያባብሰው ስጋት አለ።
የምርመራው ጥራት፡ ቀደም ሲል በጤና ጣቢያዎች ሲደረግ የነበረው ምርመራ በላቦራቶሪና በተሟላ መሣሪያ የታገዘ ነበር። በአንድ ማዕከል በሚሰጡ ጠባብ ክፍሎች ውስጥ የሚደረግ ምርመራ "ለአሰራር እንዲመች" ተብሎ የጥራት ደረጃውን (ለምሳሌ የአይንና የጤና ሁኔታን በጥልቀት ማረጋገጥ) እንዳያጓድል ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
የሙስና ስጋት፡ ምርመራውና ፈቃዱ በአንድ ጣራ ስር መሆኑ ቁጥጥር ካልተደረገበት፣ "ያለ ምርመራ ክፍያ በመፈጸም ብቻ" ወረቀት የመያዝ አዝማሚያን ሊያበረታታ ይችላል። ይህ ደግሞ በመንገድ ደህንነት ላይ ቀጥተኛ አደጋ አለው።
የዲጂታል ትስስር ጥያቄ፡ የሕክምና ውጤቱ በቀጥታ ወደ ሲስተም የማይገባ ከሆነና አሁንም በወረቀት ንክኪ የሚቀጥል ከሆነ ለውጡ ከቦታ መቀየር ያለፈ ትርጉም አይኖረውም።
ማጠቃለያ፡ አሰራሩ ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ ትልቅ ፋይዳ ቢኖረውም፣ ተቋማቱ ከህንፃ ማጋራት ባለፈ የቴክኖሎጂና የጥራት ቁጥጥር ስራቸውን ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል።

9 months ago
ኢትዮጵያ ከውጭ እቃ እያስመጣቹ ንግድ ላይ መሰማራት ለምትፈልጉ ማወቅ ያለባቹ ጠቃሚ መረጃዎች
በኢትዮጵያ አስመጪ መሆን ትልቅ አቅም ያለው ቢሆንም፣ ውስብስብ ህጎችን እና ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ማለፍን ይጠይቃል። ይህ ጽሑፍ በስድስት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፍሎ ስኬታማ የሚያደርጉህን ነጥቦች ይዘረዝራል።
ምዕራፍ 1፡ የገበያ ጥናትና የዕቃ ምርጫ
ብዙዎች የሚከስሩት "ሰው ስለሰራው" ብቻ ወደ ዘርፉ ስለሚገቡ ነው። የተሳካ አስመጪ ለመሆን፡-
ፍላጎትን መለየት፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛው ምርት ነው እጥረት ያለበት? (ለምሳሌ፡ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃዎች፣ የፀሐይ ብርሃን ኃይል መሣሪያዎች፣ ወይም የቴክኖሎጂ ውጤቶች)።
የቀረጥ ተመን (HS Code) ጥናት፡ እያንዳንዱ ዕቃ የራሱ የቀረጥ መጠን አለው። አንዳንድ ዕቃዎች (ለምሳሌ ኮምፒውተሮች ወይም የግብርና መሣሪያዎች) ከቀረጥ ነፃ ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ እስከ 100% በላይ ቀረጥ ሊኖራቸው ይችላል። ይህንን አስቀድሞ ማወቅ ትርፍህን ለመወሰን ይረዳሃል።
ወቅታዊነትን ማጤን፡ እንደ አልባሳት ያሉ ዕቃዎች በፋሽንና በወቅት ስለሚቀያየሩ ፈጣን ሽያጭ ይፈልጋሉ።
ምዕራፍ 2፡ ህጋዊ ሰውነትና የመሠረት ድንጋይ
ማንኛውም የንግድ ጉዞ የሚጀምረው በህጋዊ ሰነዶች ነው። ኢትዮጵያ አሁን ላይ የ "E-Trade" ስርዓትን ስለምትከተል አብዛኞቹ ስራዎች በኦንላይን ይከናወናሉ።
የንግድ ስም ማረጋገጫና ምዝገባ፡ መጀመሪያ የምትፈልገው የንግድ ስም በሌላ ሰው አለመያዙን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ታረጋግጣለህ።
የመመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ፡ ንግዱን በግል (Sole Proprietorship) ወይም በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) መልክ ልታቋቁመው ትችላለህ። PLC መሆኑ ለወደፊት ዕድገትና ለባንክ ብድር የተሻለ ተአማኒነት ይሰጥሃል።
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፡ ይህ ቁጥር የንግድህ "መታወቂያ" ነው። ያለ TIN ቁጥር የባንክ አካውንት መክፈትም ሆነ ዕቃ ማስገባት አይቻልም።
የንግድ ፈቃድ (Import License)፡ የምታስመጣቸውን የዕቃ ዓይነቶች (ለምሳሌ፡- የግንባታ እቃዎች፣ አልባሳት፣ ኬሚካሎች) ለይተህ ፈቃድ ታወጣለህ። አንድ ድርጅት ከአንድ በላይ ዘርፍ ላይ መሰማራት ይችላል
ምዕራፍ 3፡ የውጭ ምንዛሬና የባንክ ስልቶች
በኢትዮጵያ አስመጪነት ውስጥ ትልቁ "እንቅፋት" የውጭ ምንዛሬ እጥረት ነው። ይህንን ለማለፍ፡-
የባንክ ግንኙነት፡ ታማኝና ቀልጣፋ ባንክ ምረጥ። የውጭ ምንዛሬ ተራ (Forex Queue) ረጅም ሊሆን ስለሚችል ቀድሞ ማመልከት ያስፈልጋል።
የክፍያ መንገዶች፡
L/C (Letter of Credit)፦ ባንክህ ለአቅራቢው ክፍያ ዋስትና የሚሰጥበት አስተማማኝ መንገድ።
CAD (Cash Against Documents)፦ ሰነዶች ባንክ ሲደርሱ ክፍያ የሚፈጸምበት መንገድ።
ፕሮፎርማ (Proforma Invoice)፦ ከአቅራቢህ የምታገኘው ይህ ሰነድ የዕቃውን ዝርዝር፣ ዋጋ፣ የመክፈያ መንገድ እና የመጫኛ ጊዜን መያዝ አለበት።
ምዕራፍ 4፡ አስተማማኝ አቅራቢና የጥራት ቁጥጥር
ከማታውቀው የውጭ ኩባንያ ጋር ስትሠራ ጥንቃቄ ማድረግ አለብህ፦
አቅራቢን ማረጋገጥ፡ በአሊባባ (Alibaba) ወይም መሰል ገጾች ስትጠቀም "Verified Supplier" እና "Trade Assurance" ያላቸውን ምረጥ።
የቅድመ-ጭነት ምርመራ (Pre-Shipment Inspection)፡ ዕቃው ተጭኖ ከመውጣቱ በፊት በገለልተኛ ድርጅት (እንደ SGS ወይም Bureau Veritas) ጥራቱና ብዛቱ እንዲረጋገጥ አድርግ። ይህ አገር ውስጥ ከገባህ በኋላ ለሚመጣ ኪሳራ መከላከያ ነው።
የኢንሹራንስ ዋስትና፡ ለምታስመጣው ዕቃ የባህር ወይም የአየር ላይ ዋስትና (Marine Insurance) ከአገር ውስጥ ኢንሹራንስ ኩባንያ መግዛት ግዴታ ነው።
ምዕራፍ 5፡ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓትና ሎጂስቲክስ
ዕቃህ ጅቡቲ ወደብ ሲደርስ የሚጀምረው ሂደት የንግድህ "የመጨረሻ ፈተና" ነው፡-
የመድረሻ ዋጋ (Landed Cost) ስሌት፡
የዕቃው መግዣ + የባህር ጭነት (Freight) + ኢንሹራንስ + የጉምሩክ ቀረጥ + የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) + የትራንስፖርት + የወደብ መቆያ (Demurrage)። እነዚህን ሁሉ ደምረህ በአንድ ዕቃ ላይ ያለውን ዋጋ በትክክል ማስላት አለብህ።
የጉምሩክ አስተላላፊ (Transit/Clearing Agent)፡ ፈቃድ ያለውና ታማኝ አስተላላፊ መቅጠር ስራህን ያቀልልሃል። ሰነዶች በትክክል ካልተዘጋጁ ለቀናት ወይም ለሳምንታት በወደብ ላይ ዕቃህ ሊታገትና ከፍተኛ ቅጣት ሊጠየቅ ይችላል።
ምዕራፍ 6፡ ሽያጭ፣ ስርጭትና የገንዘብ ዝውውር (Cash Flow)
ዕቃው መጋዘንህ ከገባ በኋላ ያለው ስራ፡-
ቅድመ-ሽያጭ (Pre-sale)፦ ዕቃው ገና ሳይመጣ ለደንበኞችህ ናሙና በማሳየት ትዕዛዝ ተቀበል። ይህ ዕቃው ሲመጣ በፍጥነት ገንዘብህ እንዲመለስ ያደርጋል።
የገንዘብ ዝውውር አያያዝ፡ በብድር ከመሸጥ ይልቅ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ለቀጣዩ ዙር አስመጪነት የውጭ ምንዛሬ ቶሎ እንድታመለክት ይረዳሃል።
የኤክስፖርት ትስስር፡ የውጭ ምንዛሬ ተራ ላለመጠበቅ፣ የሀገር ውስጥ ምርቶችን (እንደ ቡና፣ ሰሊጥ፣ ቅመማ ቅመም) ወደ ውጭ በመላክ በምታገኘው ምንዛሬ (Retention Account) የራስህን ዕቃ በቀጥታ ማስመጣት ትችላለህ። ይህ የ "ብልጥ" አስመጪዎች መንገድ ነው።
🌟 ማጠቃለያ ምክር
በኢትዮጵያ አስመጪነት "በትንሽ ጀምሮ በትልቅ ማሰብ" ወርቃማ ህግ ነው። የመጀመሪያው ዙር ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን ሂደቱን (ከባንክ እስከ ጉምሩክ) ለመማር እንደሆነ አስብ። አንዴ ሰንሰለቱን ካወቅከውና አስተማማኝ አቅራቢና ገዢ ካገኘህ፣ ዘርፉ እጅግ ትርፋማና ተከታታይነት ያለው ንግድ ነው።
seledadotio

የኢትዮጵያ የችርቻሮ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ፡ ሚድሮክ 17 አዳዲስ የካርፎር ሀይፐርማርኬቶችን በኢትዮጵያ ሊከፍት ነው
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መቀመጫውን ፈረንሳይ ካደረገውና በዓለም አቀፍ የችርቻሮ ንግድ ዘርፍ ግዙፍ ከሆነው ካርፎር ግሩፕ (Carrefour Group) ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ታሪካዊ ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።
ይህ ለ10 ዓመታት የሚቆየው ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ የኢትዮጵያን ዘመናዊ የችርቻሮ መልክዓ ምድር ለማጠናከርና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ነው።
የሚድሮክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ እንደገለጹት፣ ስምምነቱ የካርፎርን ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ከሚድሮክ ሰፊ የምርት መሰረት ጋር በማጣመር ሀገራዊ ተፅእኖ ያለው የንግድ ስርአት ለመዘርጋት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህም የኢትዮጵያን ምርቶች እሴት በመጨመር እና ዘመናዊ የአቅርቦት ሰንሰለት በመፍጠር ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል።
በስምምነቱ መሰረት ሚድሮክ 17 አዳዲስ የካርፎር ሱቆችን በዋነኛነት በ"ሀይፐርማርኬት" ፎርማት ለመክፈት የወሰነ ሲሆን፣ እነዚህም በአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ድሬዳዋ፣ ደሴ፣ ባሕር ዳር እና ጎንደር ይገነባሉ።
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ያሉት 13 የኩዊንስ ሱፐርማርኬቶች በካርፎር ብራንዲንግ እና የጥራት ቁጥጥር ስርአት እንዲመሩ ይደረጋል።
ይህ አጋርነት ሁለት ዋና ዋና የንግድ ትስስሮችን የያዘ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የካርፎርን ዓለም አቀፍ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የሸማቾችን ምርጫ ማስፋት ነው።
ሁለተኛው ደግሞ ሚድሮክ እንደ ቡና፣ ሻይ እና ቅመማቅመም ያሉ ያለቀላቸው የኢትዮጵያ ምርቶችን ለካርፎር ዓለም አቀፍ የችርቻሮ መረብ የሚያቀርብበት ስትራቴጂካዊ የኤክስፖርት ስምምነት ነው።
በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ የምግብ አቅራቢዎች አንዱ የሆነው ካርፎር፣ በምግብ ጥራትና ደህንነት ላይ ባለው ጥብቅ መመሪያ ይታወቃል።
ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን ምርቶች ለዓለም ገበያ የሚያስተዋውቅና የሀገር ውስጥ የችርቻሮ አገልግሎትን ወደ ላቀ የጥራት ደረጃ የሚያሸጋግር በመሆኑ ለዘርፉ አዲስ ተስፋ ይዞ የመጣ መሆኑ ተገልጿል።

11 months ago
በሰንበት ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ከመደበኛ የገበያ ሽያጭ ዋጋ አንፃር ልዩነት እንደሌላቸውና የጥራት ጉድለት እንዳለባቸው ሸማቾች ቅሬታቸውን ገለጹ
በአዲስ አበባ ከተማ በሰንበት ገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና ምርቶች ከመደበኛ ገበያ የሽያጭ ዋጋ አንፃር ምንም አይነት ልዩነት እንደሌላቸውና ምርቶቹ ጥራታቸውን የጠበቁ ባለመሆናቸው ምክንያት ለተጨማሪ ወጪ ተዳርገናል ሲሉ ሸማቾች ቅሬታቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።
በተቋቋሙ ገበያ ማዕከላት ውስጥ ምርቶችን የሚሸጡ ነጋዴዎች የሚያቀርቧቸው ግብዓቶች፤ በተለጠፈው ዋጋ አማካኝነት እንደማይሸጡላቸውና በተለይ የግብርና ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዳልሆኑ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
አንዳንድ ምርቶች ከመደበኛ ገበያ ዋጋ አንፃር ከፍ እንደሚሉ የገለጹም ሲሆን፤ በተለጠፉ የዋጋ ተመን ነጋዴዎች እንደማይሸጡላቸው አክለዋል።
በተጨማሪም ምርቶችን ከገዟቸው በኋላ በጥራት ጉድለት ምክንያት እንደሚጥሏቸው ተናግረዋል።
መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማጣጣም እና የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር ታቅደው እንዲሁም ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ አምራች ና ሸማችን በቀጥታ እንዲያስችለው ታስበው የተቋቋሙ ማዕከላቱ ውስጥ ሕገ-ወጥ ተግባራት እንደሚያጋጥሟቸው ነዋሪዎች አሳስበዋል። በዚህም ምክንያት ለተጨማሪ ወጪ ተዳርገናል ብለዋል።
አሐዱም የነዋሪዎቹን ቅሬታ በመያዝ፤ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮን አነጋግሯል።
የቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ብርሀኑ በምላሻቸውም፤ በሰንበት ገበያ ማዕከላት ከተለጠፈው ዋጋ ውጭ ምርቶችን በሸጡ ከ13 በላይ ነጋዴዎች አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ የሰንበት ገበያ ማዕከላት መቋቋም አላማን ሲያስረዱ፤ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና የዜጎችን የምርቶች ፍላጎትን ከአቅርቦት ጋር ለማጣጣም እንደሆነ ነው።
ከጥራት አኳያ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና ምርቶች የግብይት የጥራት ፕሮሞሽን የዋጋ የምርት ጥናት ይካሄዳል ያሉም ሲሆን በጥናቱ መሰረት ግብይት እንደሚደርግ ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የዋጋና የጥራት ቁጥጥር ሥራዎች በምርቶች ላይ ይካሄዳል ብለዋል። የተወሰዱ እርምጃዎች የጹሑፍ እና የማስጠንቀቂያ እንደሆነም ነግረውናል።
ከሰንበት የገበያ ማዕከላት ጋር በተገናኘ ነዋሪዎች የሚቀርቡላቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዳልሆኑ በተደጋጋሚ አቤቱታዎችን ሲያሰሙ ይደመጣል።
#አሐዱ

1 year ago
በ2018 ዓ.ም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀመር ታውቋል።
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ በመጪው አመት 2018 ዓ.ም በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ በአሁን ወቅት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እየተካወነ ያለው ዳግም ምዝገባና ምዘና ስራ ሲጠናቀቅ ይኸው እንቅስቃሴ በመንግስት ኮሌጆች፣ የማሰልጠኛ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ላይም በቀጣዩ አመት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
አቶ ውብሸት ታደለ በዝርዝር ምን አሉ ?
" አሁን እየተከናወነ ያለውን የመጀመሪያው ዙር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ምዝገባና ግምገማ እንደጨረስን፣ በሁለተኛውና በሶስተኛው ዙር የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን እንመዘግባለን፣ እንገመግማለን፡፡ በፌደራልና በክልሎች የተከፈቱ ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማት አሉ፡፡ መጀመሪያ የምናየው እነሱን ነው፡፡ ቀጥለን ደግሞ ሁሉንም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን እናያለን፡፡
እስካሁን የግል ተቋማት ላይ ያተኮርነው፣ እዚህ ዘርፍ ላይ የነበረው ችግር ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ያለንን የሰው ሀይልና ሀብት ወደዚህ ዘርፍ በማዞር ቅድሚያ ሰጥተናል፡፡ ሁሉንም አንድ ላይ ማየት አንችልም፡፡ አሁን የግሎቹን ተቋማት ካጠናቀቅን በኋላ፣ ወደ መንግስት ትምህርት ተቋማት ግምገማ እንገባለን፡፡
የመንግስት የትምህርት ተቋማት በመሰረተልማት በኩል ችግር የለባቸውም፡፡ የራሳቸው ህንፃና ግቢ አላቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ ጋ ትኩረት የምናደርገው ጥራት ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ፕሮግራሞቹ/ትምህርቱ በበቂ መምህራንና አኳሀን መሰጠቱን እናያለን፡፡ አካዳሚያዊ የድርጊት መርሀግብራቸው ትክክል መሆኑን እንፈትሻለን፡፡
የተገቢነትና አስፈላጊነት ጥያቄ የሚነሳባቸው፣ ዝም ብለው ያለ በቂ ጥናት የሚከፈቱ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የትምህርት ግብአት እና የላቦራቶሪ ቁሳቁሶች፣ እንዲሁም የዳታ ማዕከላቸው ይታያል፡፡ ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች የሚቀርቡት አገልግሎቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ወይ የሚለውን እናያለን፡፡
ቀደም ብለው የተቋቋሙት ነባሮቹ ዩኒቨርሲቲዎች የዚህ አይነት ችግር ላይኖርባቸው ይችላል፡፡ አዳዲሶቹ ዩኒቨርሲቲዎች ግን በነዚህ መስፈርቶች በኩል ክፍተት ይኖሩባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ ግን ጥራትን እናምጣ ካልን፣ ሁሉንም የመንግስት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎችን መፈተሽ አለብን፡፡ በዳግመ ምዝገባችን፣ በተቋማቱ የሚሰጡትን ሁሉንም ፕሮግራሞቻቸውን እናያለን፡፡ ፋይሎቻቸውን እንዲያስገቡ አድርገን እያንዳንዱን ፕሮግራም እንመዝናለን፡፡ አያስፈልጉም የምንላቸውን ፕሮግራሞች እንዲዘጉ፣ ያስኬዳሉ የምንላቸውን ደግሞ እንዲያስቀጥሉ እናደርጋለን፡፡
የመንግስት ተቋማትን ከግሎቹ በበለጠ ጠንከር ያለ ምዘና እናደርጋለን፡፡ ጠበቅ አድርገን ለማየት እንሞክራለን፡፡ የግሎቹን እንደጨረስን፣ በየክልሉ ያሉትንና በፌደራል ደረጃም ያሉትን ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማትን እናያለን፡፡ ከዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንሔዳለን፡፡ ይህ ስራ በ 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይመስለኛል " ብለዋል።
@tikvahethiopia

Comments