7 months ago
የጉራጌ ጦርነት 1867-1881
#ethiopia | በዘመናዊ የጉራጌ ታሪክ የቀቤና ቸሀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በመጀመሪያ የሚጠቀስ ገድል ነው ። ቀቤና በ1850ዎቹ በወልቅጤና በቸሀ መካከል “ ዘናበነር ” በሚባል ቀበሌ ከሰፈረ በኋላ ለቀበሌው የራሱን ስም የሰጠው አንድ የሀዲያ ማኅበረሰብ ነው።
#በ1860ዎቹ የቀቤናው ኢማም ሀሰን ኢንጃሞና የቸሀው ኢማም ኡመር በቅሳ የቀቤና አካባቢያዊ መንግሥት መሠረቱ ከ1860 ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1881 ድረስ የቀቤና መንግሥት መሪዎችና ተከታዮች በጊቤና በአዋሽ ወንዞች መካከል የሚገኙ የሀዲያ የጉራጌና የኦሮሞ ሕዝቦችን በአንድነት ለማደራጀት በወሰዱት ብርቱ የፖሊሲ እርምጃ ከአጐራባቹ የሸዋ አካባቢ መንግሥት ጋር የአስራ አራት (1867-1881) ዓመታት ጦርነት ተዋጉ ።
#በዚህ ረገድ በ1867 መጨረሻ የምኒልክ ጦር በራስ ጐበና አዝማችነት በሶዶ ጉራጌ የመጀመሪያ ጦርነት ከፍቶ በድል ተመለሰ ። ነገር ግን በ1869 በቀቤና ፣ በወለኔ ፤ በገዳባኖ ፤ በአክሊል ፡ በምሁር ፤ በእዣ ፤ በቸ ሀ ፤ በእነሞር ፡ በኤነር ፤ በየጨሬት ፤ በጉመር ፤ በውሪሮ ፤ በስልጤ በመስቃን ፤ በዶቢና በዱላ ላይ በንጉሥ ምኒልክ አዝማችነት ጦርነት የከፈተው ታላቅ የሸዋ ሰራዊት በየአካባቢው በእነ አበጋዝ ደርሰሞ በተመራው የጉራጌ ጦር ተሸንፎ እንደ ተመለሰ በታሪክ ጸሐፊ አጥመ ጊዮር ጊስና በጉራጌ ትውፊት ተመዝግቦአል ። “
#በጉራጌ የትውፊት መረጃ መሠረት ፤ የ1869 የምኒልክ ሠራዊት በአጋዝ ደርሰሞ በተመራው የጉራጌ ጦር የተሸነፈው በጉመር አገር በዌራና በአረቅጥ በተካሄዱ ተከታታይ ጦርነቶች ነው።በታሪክ ጸሐፊ አለቃ አጥመ ጊዮርጊስ ዘገባ መሠረት ፣ በጥቅምት 1869 ንጉሥ ምኒልክ ብዙ ጦር አስከተለው ወደ ጉራጌ ዘመቱ ። በጥቅምት 21 ቀን የንጉሡ ሠራዊት አለቀ።
#አለቃ ዘነብ የሚባል አዋቂ መጽሐፈ ጨወታ የደ ረሰ የዚያኑ ዕለት ሞተ። ብዙ መኳንንት ሞቱ። የቸሀና የጉመር ሌሎችም ጉራጌዎች ብዙን ሠራዊት ማርከው ወደ ከምባታ ወደ ወላሞ ሸጡ። ከንጉሡ ጋራ ከዘመቻው የተመለሰው ከሶስት አንድ እጅ ብቻ ነው። በዚያን ጊዜ በሸዋ ያልተለቀሰበት ቤት አልተገኘም። ንጉሡም በኃዘን ተመልሰው ልቼ ገቡ፡፡
#ከ1867 እስከ 1881 በጉራጌና በሸዋ መካከል በተካሄደው ጦርነት ዋና ዋና የሸዋ ጦር መሪዎችና አዛዦች ንጉሥ ምኒልክ ፣ ራስ ወልዴ አሻግሬ ፤ ደጃዝማች ገርማሜ ወልደ ሐዋርያት፤ባላምባራስ መኳንንት ወልደ ሚካኤል (በኋላ ራስ) ፤ ቀኛዝማች ውቤ ኤርገኖ ፤ ደጃዝማች በሻህ አቦዬ፡ ራስ ጐበና ዳጭ ፤ ፊታውራሪ ገረዶ ጐበና ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ነበሩ ።
#ከእነዚህ የጦር መሪዎችና አዛዦች ቀኛዝማች ውቤ ኤርገኖና ፊታ ውራሪ ገረዶ ጐበና በጦርነቱ ሞቱ። የራስ ጐበና ዳጭ ጦር አራት በተለያዩ ጊዜያት በኢማም ሀሰን ኤንጃሞ እጅ ተሸንፎ ተመለሰ ፤ አለቃ አጥመ ጊዮርጊስ እንደ መዘገቡት ፤ በ1877 ቀቤኖች ቀኛዝማች ውቤ ኤርገ ኖን ስለ ገደሉት በ1878 ደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ ፤ ደጃዝማች ገርማሜ ወልደ ሐዋርያትና ባላባራስ መኳንን ወልደ ሚካኤል በሌላ የቅጣት ዘመቻ ወደ ቀቤና ተላኩ። በመስከረም 1879 የደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ ወንድም በጦርነቱ እንደ ተገደለና ደጃዝማቹ 3000 ከብቶች በም ርኮ ይዞ ወደ እንጦጦ እንደ ተመለሰ በወቅቱ ሸዋ የነበረው አንድ የውጭ አገር ጸሐፊ መዝግቦአል። የተባለው ጸሐፊ በሰኔ 1880 ጉራ ጌዎች በበኩላቸው ከሸዋ ጦር 400 ጠመንጃዎችን በምርኮ እንደ ወሰዱ ጨምሮ ጽፎአል።
#በ1880 -1881 ኢጣሊያኖች ከሰሜን ጠረፍ፣ ሱዳኖች ደግሞ በምዕራብ ከወለጋና ከጐንደር ጠረፎች በአገሪቱ ላይ በአንድ ጊዜ በሶስት ግምባሮች ወረራ በከፈቱ ጊዜ ከጉራጌ ኢማም ሀሰን ኤንጃሞ አዋሽ ተሻግሮ “ ሸዋን ያቃጥላል በማለት ራስ ጐበና ዘምተው እንዲወጉት ተመ ከረ። ራስ ጐበናም ወደ ሀሰን ኢንጃሞ ዘመቱ ” ይህ የጐበና የ1880ው ዘመቻ በጉራጌዎች ላይ አምስተኛው ጦርነት ነበር።
#በመጨረሻ ራስ ጐበና የወሊሶን ተወላጅ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮር ጊስ ዲነግዴን በኢማም ሀሰን ኤንጃሞ ላይ በማዝመት ጦርነቱን በመ ጋቢት 1881 ወደ ፍጻሜው አድርሰው ራሳቸው በሰኔ 1881 በድንገት ታመው በእንጦጦ ሞቱ።
#ከታሪክ አኳያ በ1881 የጉራጌ ጦርነት በሸዋ ድል መፈጸሙ ለምኒልክ ወታደሮችና ሹማምንት በሚቀጥሉት አመታት በደቡብና በምዕራብ ኢሉባቦር ፣ ከፋ ፣ ጋሞጐፋ፣ ሲዳሞና ባሌ ጨምሮ ብዙ አካባቢዎችን በፍጥነት በማዕከላዊ መንግሥት ሥር ለማምጣት በር ከፈተ።
►የኢትዮጵያ የገባር ታሪክና ጅምር ካፒታሊዝም፤ላጲሶ ጌ.ዴሌቦ፤192-4

Comments