2 months ago
አኮቦ ሚኒራልስ በሦስት ወራት ውስጥ 23 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረቱን አስታወቀ
#ethiopia | መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገውና በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልልን በማዕድን ልማት ላይ የተሰማራው አኮቦ ሚኒራልስ (Akobo Minerals) ፣ ባለፉት ሦስት ወራት 23 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረት መቻሉን ይፋ አደረገ።
ኩባንያው ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ካመረተው አጠቃላይ የወርቅ መጠን ውስጥ 7.5 ኪሎ ግራም የሚሆነው በመጋቢት ወር ብቻ የተመረተ ነው። አኮቦ ሚኒራልስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅን በቀጥታ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ፣ በአሁኑ ወቅት ምርቱን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ሆኖም ኩባንያው በሥራው ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን በሚመለከት የሚከተሉትን ነጥቦች አንስቷል፡-
በመካከለኛው ምሥራቅ ካለው ወቅታዊ ጦርነት ጋር ተያይዞ የነዳጅ እጥረት ከተባባሰ፣ በማዕድን ማውጣት ሥራው ላይ መስተጓጎል ሊፈጠር እንደሚችል አመልክቷል።
ኩባንያው ተግዳሮቶች ቢኖሩም ምርቱን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን አጠናክሮ ለመቀጠል እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
አኮቦ ሚኒራልስ በጋምቤላ ክልል በሚያከናውነው የቁፋሮና የማምረት ተግባር ከፍተኛ ጥራት ያለው ወርቅ በማግኘት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #mining #gold #akobominerals #gambella #economy #businessnews #ኢትዮጵያ #ማዕድን #ወርቅ #ኢኮኖሚ #አኮቦሚኒራልስ