18 days ago
ኢትዮጵያን በልባቸው ያነገቡት የቱሪዝም አምባሳደር፤ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ የምግብ ትራክ
#ethiopia | ታላላቅ ታሪኮች ብዙ ጊዜ የሚጀምሩት ባልታሰቡ አጋጣሚዎች ነው። የአቶ አበራ ዋሲሁን የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነበር።
በ12 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ተክለሃይማኖት አካባቢ መንገድ የጠፉ ሁለት ጣሊያናውያን ቱሪስቶችን በመርዳት እና የኢትዮጵያን ታሪክ በማስተዋወቅ የመጀመሪያውን የአስጎብኚነት ጉዞ ጀመሩ።
በዚያን ቀን የተቀበሉት 20 ብር ሽልማት ከገንዘብ በላይ የሀገር ፍቅርና የቱሪዝም አገልግሎት መንፈስን በልባቸው አስርጎ አስቀመጠ።
ከዚያ ጀምሮ ለአራት አስርት ዓመታት በቱሪዝም ዘርፍ ያሳለፉት ጉዞ በብዙ ስኬቶች የተሞላ ነው። ከአስጎብኚነትና ከሹፌርነት ተነስተው የራሳቸውን "አበራ አስጎብኚ ድርጅት" በመመስረት የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሯዊ ውበት ለዓለም ማስተዋወቅ ችለዋል።
ለቢቢሲ ጋዜጠኞች፣ ለአውሮፓ ኅብረትና ለአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢዎች ያበረከቱት አገልግሎትም በሙያቸው ያላቸውን ብቃት ያሳያል።
በ2012 በአሜሪካ "Ethio USA Tours" የተሰኘውን ድርጅታቸውን በመመስረት የኢትዮጵያን ታሪክና የቱሪዝም ሀብት ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ማስተዋወቅ ቀጠሉ። ኮቪድ-19 የቱሪዝም ዘርፉን ቢያዳክምም፣ የሀገር ማስተዋወቅ ተልዕኳቸው አልቆመም።
በአዲስ አቅጣጫ "MULU FEST LLC" የተሰኘ የምግብ ትራክ በመጀመር በዋሽንግተን ዲሲ፣ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ፣ ባህልና እንግዳ ተቀባይነት ለብዙዎች እያስተዋወቁ ይገኛሉ።
ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች የጀመረው ሕልማቸው ዛሬ በዓለም ሌላ ጫፍ የኢትዮጵያን ስም በክብር እያስጠራ ይገኛል። አቶ አበራ ዋሲሁን በሥራቸው የኢትዮጵያ ባህል፣ ቱሪዝምና ምግብ እውነተኛ አምባሳደሮች መሆን የቻሉ ተምሳሌት ናቸው።
#ethiopia #tourism #culture #ethiopiancuisine #ethiopiantourism #diaspora #getutemesgen #ኢትዮጵያ #ቱሪዝም #ባህል #አበራዋሲሁን #ጌጡተመስገን

Comments