1 month ago
አርቲስት ነፃነት አንበርብር የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ማዕከል አምባሳደር ሆነች
#ethiopia | ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እያከናወነ ያለውን ሰብአዊ ተግባር ይበልጥ ለማሳደግ ታዋቂዋን ተዋናይት ነፃነት አንበርብርን የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መርጧታል።
ላለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት በጤና፣ በትምህርት እና በተለያዩ ማህበራዊ ድጋፎች ላይ በስፋት ሲሳተፍ የቆየው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፣ አርቲስቷን አምባሳደር አድርጎ የሾመው ተቋሙ በኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ የጀመረውን እንቅስቃሴ ለህዝብ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በማለም ነው።
ማዕከሉ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የኩላሊት ህሙማን የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ የሚለውን መሪ ቃል በመጠቀም የሚንቀሳቀሰው ሜሪ ጆይ፣ ይህ አዲስ አጋርነት የኩላሊት እጥበት አገልግሎቱን ለማስፋፋት እና ግንዛቤ ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይጠበቃል።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
#ሜሪጆይ #ጤና #ነፃነትአንበርብር #ኩላሊትእጥበት #ሰብአዊነት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments