4 months ago
በምዕራብ አርሲ ዞን የደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎችን ሕይወት ቀጠፈ
#ethiopia | በምዕራብ አርሲ ዞን ነሲቦ ወረዳ "አመሽቃ" ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በ35 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
የአደጋው ዝርዝር፦
* ቀን፦ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ከሰዓት በኋላ)
* መነሻና መድረሻ፦ ከደላ ከተማ ወደ ወረቃ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ
* የተሽከርካሪ ዓይነት፦ 40 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ
* ምክንያት፦ ተሽከርካሪው በገጠመው ድንገተኛ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መገልበጡ ተገልጿል።
የተጎጂዎች ሁኔታ፦
በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 35 ተጓዦች በአሁኑ ወቅት በሻሸመኔ እና በነሲቦ ሆስፒታሎች አስፈላጊው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
የተሽከርካሪ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች መሰል አደጋዎችን ለመከላከል የቴክኒክ ምርመራን በወቅቱ እንዲያደርጉና ጥንቃቄ እንዲጨምሩ መልዕክት ተላልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ብስራትሬዲዮ #ኢትዮጵያ #ትራፊክአደጋ #ምዕራብአርሲ #ነሲቦ #ዜና #ethiopia #trafficaccident

Comments