5 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ የቼዝ ጠረጴዛ ላይ፣ የየመኑ ጦርነት አዳዲስ እና ወሳኝ ወታደራዊ ክስተቶችን እያስተናገደ ይገኛል። የሁቲ አማፂያንን በመውጋት ላይ የሚገኘው ሳዑዲ መራሹ ጥምረት በሁዳይዳ ግዛት የባህር ኃይል ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን ሲያስታውቅ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠው የየመን መንግስት ጦር በበኩሉ፣ ከባብ አል-ማንደብ ስትሬት በስተደቡብ ካደረገው ውጊያ በኋላ የሞካ ከተማን ከሁቲዎች እጅ መልሶ መቆጣጠሩን አረጋግጧል።
ይሁን እንጂ፣ የሁቲ አማፂያን ይህንን ወታደራዊ ጫና በዝምታ አላለፉትም። የቡድኑ ወታደራዊ ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት፣ ታጣቂዎቻቸው በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው የኪንግ ካሊድ አውሮፕላን ማረፊያ እና በራቢግ ከተማ በሚገኘው ግዙፉ የአራምኮ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ይህ የሁቲዎች የድፍረት እርምጃ በሳዑዲ አረቢያ ላይ የፈጠረው የደህንነት ስጋት፣ የቀጠናውን ኃያላን አዲስ ወታደራዊ ስምሪት እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል።
ጉዳዩን ተከትሎ በተጠራ አስቸኳይ ስብሰባ፣ ቱርክ እና ፓኪስታን የሳዑዲ አረቢያን ደህንነት ለማጠናከር እና አጋርነታቸውን ለማሳየት ወታደሮቻቸውን በፍጥነት ለማሰማራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህ የቱርክ እና ፓኪስታን ፈጣን ወታደራዊ ምላሽ፣ የየመኑ ግጭት ከውስጣዊ የእርስ በርስ ጦርነት አልፎ ሰፊ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መልክ እየያዘ መምጣቱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
_____
🗣️ ይህ እየተወሳሰበ የመጣው የቀጠናው ውጥረት እና የኃያላኑ ጣልቃ ገብነት ወዴት ያመራ ይሆን? ሀሳባችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን!

22 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) በህንድ ኒው ዴልሂ ሲካሄድ የቆየው የዘንድሮው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ፣ የተለመዱትን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከሪያ እና የጋራ ፖሊሲ ቃላቶች በመለዋወጥ ተጠናቋል። ይሁንና ጉባዔው አንድ ትልቅ እና አንገብጋቢ ጉዳይን ሆን ብሎ በዝምታ አልፎታል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት አብዛኛዎቹን አሥራ አንድ የብሪክስ አባላት እና አሥር አጋር ሀገራትን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካ ቢሆንም፣ ቡድኑ ባወጣው የጋራ መግለጫ ላይ ጦርነቱን አላነሳም፤ እንዲሁም ግልጽ አጥቂ የሆነችውን አሜሪካን ከማውገዝ ተቆጥቧል። ይህ ሁኔታ ብሪክስ ያለውን ግዙፍ የኢኮኖሚ ጡንቻ ወደ ተባበረ የጂኦ-ፖለቲካዊ እርምጃ ለመቀየር ምን ያህል እንደሚቸገር ፍንትው አድርጎ አሳይቷል።
የብሪክስ ፖለቲካዊ ድክመት አሁን ብቻ የተከሰተ አይደለም። ባለፈው ግንቦት ወር በኒው ዴልሂ በተካሄደው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይም ተመሳሳይ ሽኩቻ ታይቶ ነበር። በወቅቱ ኢራን የአሜሪካ እና የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ በቡድኑ በይፋ እንዲወገዝላት ብትጠይቅም፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ግን የራሷን የደህንነት ስጋት እና የኢራንን ጥቃቶች ያላካተተ መግለጫ እንዲወጣ አልፈቀደችም። ይህ የሚያሳየው፣ የብሪክስ አባላት ቁጥር ማደግ የቡድኑን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ቢያሰፋውም፣ በተጓዳኝ ደግሞ እንደ ኢራን እና ኤምሬትስ ያሉ አደገኛ ቀጠናዊ ጠላትነቶችን ወደ ድርጅቱ ውስጥ ይዞ እንዲገባ አድርጎታል።
ብሪክስ በአሜሪካ ከሚመራው የምዕራባውያን የዓለም ሥርዓት የተለየ አማራጭ ለመፍጠር የተቋቋመ ቢሆንም፣ አባላቱ ከአሜሪካ ጋር ባላቸው የተለያየ የጥቅም ትስስር የተነሳ የጋራ አቋም መያዝ ተስኗቸዋል። ለምሳሌ ህንድ ብሪክስን የምትጠቀመው የራሷን የስትራቴጂክ ነጻነት ለማስፋት እንጂ ፀረ-አሜሪካ ጦር ለመገንባት አይደለም፤ በመሆኑም ከምዕራባውያን ጋር ያላትን ወታደራዊ እና የኢኮኖሚ ትስስር እያጠናከረች ትገኛለች። ሩሲያ የብሪክስን መድረክ የምዕራባውያንን ማዕቀብ ለማምለጫ ብትጠቀምበትም፣ ከአሜሪካ እና ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ጋር ቀጥታ ወታደራዊ ግጭት ውስጥ መግባትን አትፈልግም። ቻይናም ቢሆን ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቱን መለወጥ ብትፈልግም፣ አሜሪካ ለኤክስፖርት ምርቶቿ ትልቅ ገበያ በመሆኗ በየጉዳዩ ሁሉ ከዋሽንግተን ጋር መላተም አያዋጣትም። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል እና ኢንዶኔዥያ ያሉት ሀገራት ዋነኛ ፍላጎታቸው ፍትሃዊ የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት እንዲፈጠር እና ለታዳጊ ሀገራት የልማት ብድር እንዲስፋፋ እንጂ፣ በጂኦ-ፖለቲካዊ ፍልሚያዎች የቻይና ወይም የሩሲያ መጠቀሚያ መሆን አይደለም።
እንዳስተዋልነው ከሆነ ብሪክስ በባለብዙ-ማዕከል ወጥመድ ውስጥ ወድቋል። የስብስቡ ትልቁ ጥንካሬው ብዝሃነቱ ቢሆንም፣ ይኸው ብዝሃነቱ ደግሞ የጠራ ጂኦ-ፖለቲካዊ ርምጃዎችን በጋራ እንዳይወስድ ማነቆ ሆኖበታል። የኢራን ጦርነት ይህንን ተቃርኖ ይበልጥ አጉልቶታል። ይሁንና፣ ይህ የፖለቲካ አቋም ማነስ እንደ በረከት ሊታይ ይችላል። ብሪክስ አሜሪካን በቀጥታ ጦርነት እና ግጭት ከመውጋት ይልቅ፣ የዓለምን የፋይናንስ ሥርዓት እና ተቋማትን በማሻሻል፣ ዶላርን በሌሎች የክፍያ አማራጮች በመተካት እና ለታዳጊ ሀገራት የዲፕሎማሲ አማራጭ በመሆን ሥርዓቱን ቀስ በቀስ ለመለወጥ መገደዱ ይበልጥ ዘላቂ እና አዋጭ የሆነ ኃይል እንዲኖረው ያደርገዋል።
ብሪክስ በዚህ ልክ በውስጥ ልዩነቶች እየታመሰ እና የጋራ ፖለቲካዊ አቋም መያዝ እየተቸገረ፣ በእርግጥም የዓለምን የኃይል ሚዛን ሊቀይር እና የአሜሪካን ተጽዕኖ ሊገታ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? ወይስ የኢኮኖሚ ትብብሩ ብቻውን በቂ ነው? ሐሳብዎን እንዲያስቀምጡ ጋብዘናል።

24 days ago
ሞዲ እና የሕንድ መልክዓ ምድር
የጉዞ ማስታወሻ - ( ክፍል - 9 )
#ethiopia | ሕንድ — ተራሮች፣ ሜዳዎችና ወንዞች ይናፈቃሉ።
ሕንድ በሰፊ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር የምትታወቅ ሀገር ስትሆን፣ ከፍተኛ ተራሮች፣ ሰፊ ሜዳዎች፣ ወንዞችና ረጅም የባሕር ዳርቻዎች አሏት።
ሂማላያ (Himalayas) — በሰሜን ሕንድ የሚገኝ ሥመጥር ተራራ ነው።
ካንቸንጁንጋ (Kangchenjunga) — በሕንድና ኔፓል ድንበር አካባቢ የሚገኝ፣ በሕንድ ውስጥ ከፍተኛው ተራራ ይዟል።
ዌስተርን ጋትስ እና ኢስተርን ጋትስ — በደቡብና ምዕራብ ክፍሎች የሚገኙ የተራራ ሰንሰለቶች አይዘነጉም።
ኢንዶ–ጋንጌቲክ ሜዳ (Indo-Gangetic Plain) — በሰሜን ሕንድ የሚገኝ በጣም ሰፊና ለእርሻ ምቹ ሜዳ ሲሆን ይህ አካባቢ በወንዞች በሚመጣ ለም አፈር ምክንያት ለሩዝ፣ ስንዴና ሌሎች ሰብሎች አስፈላጊ ምድር ሆኗል።
ጋንጋ (Ganges/Ganga) — ከሕንድ ታላላቅና በባህል እጅግ አስፈላጊ ወንዞች አንዱ ነው።
ያሙና (Yamuna) — በሰሜን ሕንድ የሚፈስ፣ በአግራና ዴልሂ አካባቢ በጸጥታ፤ በዝምታ የሚጓዝ ወንዝ- እንደ ዓባይ ወንዝ አይገማሸርም።
ብራህማፑትራ (Brahmaputra) — በሰሜን-ምሥራቅ ሕንድ የሚፈስ ትልቅ ወንዛችን ነው - ይላሉ።
ጎዳቫሪ (Godavari)፣ ክሪሽና (Krishna) እና ናርማዳ (Narmada) — በሕንድ የውሃና የግብርና ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ወንዞች ናቸው።
ከወንዞቹ ግርጌ የሂማላያ ተራራ፤ ከፍታ ይታያችሁ።
ሂማላያ በሰሜን፣ ሰፊው የኢንዶ–ጋንጌቲክ ሜዳ በመካከል፣ ብዙ ትላልቅ ወንዞች ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ ተስፋፍተው ይገኛሉ።
ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሀገር፤
በለውጥ መንገድ ...
ሕንድ በዓለም ትልቁ የሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር፣ በፈጣን እድገት ላይ ካሉ ኢኮኖሚዎች አንዷ እና በእስያ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ተጽዕኖዋን እያሳደገች የምትገኝ ሀገር ናት። አዲስ ዴልሂ በአንድ በኩል የውስጥ ልማትንና ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማስፋፋት ሲሠራ፣ በሌላ በኩል ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ የአውሮፓ ሀገራትና ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስፋት ትጥራለች።
ሞዲ እና የሕንድ የፖለቲካ ገጽታ
የሕንድ ፖለቲካ በፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት ሳይሆን በፓርላማዊ ዴሞክራሲ ላይ የተመሠረተ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር መንግሥት በሕንድ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለውን ቦታ ይዟል።
በተለይም የሕንድ ፖለቲካ በልማት፣ በብሔራዊ ማንነት፣ በዲጂታል ለውጥ፣ በሥራ ዕድል እና በማኅበራዊ ፖሊሲዎች ዙሪያ የሚደረጉ ክርክሮች ይበዛባቸዋል።
ሕንድና ቻይና
ሕንድና ቻይና በአንድ በኩል ትልቅ የንግድ አጋሮች ሲሆኑ፣ በሌላ በኩል በድንበርና በጂኦፖለቲካ ጉዳዮች ውዝግብ ያላቸው ሁለት ኃያላን ሀገራት ናቸው።
በ2020 የተከሰተው የድንበር ግጭት ግንኙነታቸውን አበላሽቶ ነበር። አሁን ግን ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን በቀስታ ለማሻሻል እየሞከሩ ናቸው። የሁለቱ ሀገራት ንግድ በ2025 ወደ 155 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፣ በ2026 የመጀመሪያዎቹ ሰባት ወራትም ተጨማሪ 23% ጭማሪ ተመዝግቧል።
ይህ ለሕንድ ትልቅ የስትራቴጂ ጉዳይ ነው፤ ቻይናን እንደ ተፎካካሪ እያየች በተመሳሳይ ጊዜ ከቻይና ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት ማቋረጥ አትፈልግም።
BRICS እና የሕንድ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ
በ2026 ሕንድ የBRICS የመሪዎች ጉባኤን እያስተናገደች ነው። የ18ኛው BRICS Summit በኒው ዴልሂ ዛሬ፣ መስከረም 12 ቀን 2026 ተጀምሯል። የጉባኤው ዋና አጀንዳዎች ብዙ-ወገን ዓለም አቀፍ ሥርዓት፣ ፈጠራ፣ ዘላቂነት እና ሁሉን አካታች እድገት ናቸው።
ይህም ሕንድ ከምዕራባዊ ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት እያጠናከረች በተመሳሳይ ጊዜ ከሩሲያ፣ ቻይና እና ከGlobal South ሀገራት ጋር የራሷን የዲፕሎማሲ መንገድ እየገነባች መሆኗን ያሳያል።
ኢኮኖሚ
ከዓለም ገበያ ንዝረት ነፃ ያልሆነ
የሕንድ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች አንዱ ነው። ሀገሪቱ በማምረት፣ IT፣ ፋይናንስ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ መድኃኒት ማምረት፣ አውቶሞቢል እና አገልግሎት ዘርፎች እያደገች ነው።
ነገር ግን የዓለም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ለሕንድ ትልቅ ፈተና ነው። ዛሬ፣ መስከረም 12፣ 2026፣ Brent crude ከ100 ዶላር በላይ በመጨመሩ የሕንድ የአክሲዮን ገበያ በግፊት ውስጥ ገብቷል። Nifty 50 0.86% ወርዶ 23,431.50 ሲደርስ፣ Sensex 1.08% ቀንሶ 74,764.23 ላይ ተዘግቷል።
የሕንድ ሩፒም ወደ 94.82 ሩፒ ለ1 የአሜሪካ ዶላር ደክሟል።
ቴክኖሎጂ
ሕንድ የዲጂታል ኢኮኖሚ ኃይል
ሕንድ በIT እና በዲጂታል አገልግሎት ዘርፍ ዓለም አቀፍ ማዕከል ሆናለች። Bengaluru፣ Hyderabad፣ Mumbai፣ Delhi-NCR እና Pune የቴክኖሎጂ እና የStartup ኢኮሲስተም ዋና ማዕከላት ናቸው።
AI፣ FinTech፣ Digital Payments፣ Cloud Computing እና E-commerce በፍጥነት እያደጉ ናቸው። የUPI ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በተለይ ሕንድን ከዓለም የዲጂታል ክፍያ ምሳሌዎች አንዷ አድርጓታል።
በዚሁ ሳምንት በMumbai የሚካሄደው Global Fintech Fest 2026 የAI፣ FinTech እና የዲጂታል ፋይናንስ የወደፊት አቅጣጫ ዋና የውይይት ርዕስ ሆኗል።
መጓጓዣ እና መሠረተ ልማት
ሕንድ የባቡር፣ የአውራ ጎዳና፣ የአየር ማረፊያ እና የከተማ መጓጓዣ መሠረተ ልማትን በፍጥነት እያስፋፋች ነው።
የDelhi Airport አለም አቀፍ የመንገደኞች አቅምን ለማሳደግ እየሰራ ሲሆን፣ አዲስ የT3 አቅም ማስፋፊያ ሙሉ በሙሉ ሲሰራ ዓመታዊ የአለም አቀፍ ተጓዦች አቅሙ ወደ 31 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል።
ይህ በተለይ ሕንድ እየተቀበለች ካለችው የንግድ፣ የቱሪዝም እና የዓለም አቀፍ ስብሰባ ቁጥር ጋር ተያይዞ ወሳኝ ምዕራፍ ይዟል።
የአየር ሁኔታና የዝናብ ወቅት
የ2026 የMonsoon ወቅት በሕንድ በርካታ ክልሎች የዝናብ እና የጎርፍ ችግሮችን አስከትሏል። በተለይ በBihar 14 ወረዳዎች ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ ተጎድተዋል፣ ምንም እንኳ የወንዞች የውሃ መጠን መቀነስ ቢጀምርም።
የሕንድ የሜትሮሎጂ መምሪያም በተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ ዝናብ እንደሚጠበቅ አስታውቋል።
ባህል፣ ሃይማኖትና ቱሪዝም
ሕንድ በባህላዊ ቅርስ፣ በሃይማኖታዊ ቦታዎች፣ በተፈጥሯዊ ውበት፣ በዮጋ፣ በምግብ ባህል እና በታሪካዊ ሐውልቶች በዓለም ከሚታወቁ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዷ ናት።
የሕንድ መንግሥት ቱሪዝምን እንደ የኢኮኖሚ እድገት፣ የሥራ ዕድል እና የክልል ልማት ዋና መሣሪያ እያየው ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ሕንድ የባህል ቅርሶቿን በዲጂታል መንገድ ለመመዝገብና ለመጠበቅ እየሰራች ነው። የUNESCO የዓለም ቅርስ ቦታዎቿም ወደ 44 ደርሰዋል።
ቦሊውድ እና የመዝናኛ ኢንዱስትሪ
ሕንድ የዓለም ትልቁ የፊልም ምርት ኢንዱስትሪዎች አንዷ ናት። Bollywood ብቻ ሳይሆን Telugu፣ Tamil፣ Malayalam፣ Kannada እና ሌሎች የክልል የፊልም ኢንዱስትሪዎች በጣም ኃያላን ናቸው።
የሕንድ ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ፋሽን እና የTV ይዘት ከአገር ውስጥ ባሻገር በእስያ፣ አፍሪካ እና በዲያስፖራ ማኅበረሰቦች ዘንድ ትልቅ ተደማጭነት አለው።
ክሪኬት : ከስፖርት በላይ
በሕንድ ክሪኬት የስፖርት ጨዋታ ብቻ አይደለም፤ የሚዲያ፣ የማስታወቂያ፣ የንግድ እና የብሔራዊ ማንነት አካል ነው።
በቅርቡ የሕንድ ታዋቂ ተጫዋቾች እና በ2027 World Cup ይሳተፋሉን የሚለው ጥያቄ የስፖርት ዜናውን ተቆጣጥሮታል። ሁለቱም በዚያን ጊዜ ከፍተኛ ዕድሜ ላይ ስለሚሆኑ የተሳትፎአቸው ጉዳይ አሁንም ክፍት ነው።
ሕንድ — ቋንቋ
ሕንድ በርካታ ቋንቋዎች የሚነገሩባት አገር ናት።
ሂንዲ (Hindi) በሕንድ ማዕከላዊ መንግሥት የሕብረቱ/የUnion ኦፊሴላዊ ቋንቋ ነው። ሕገ-መንግሥቱ ሂንዲን በDevanagari ፊደል እንደ የUnion ኦፊሴላዊ ቋንቋ ይደነግጋል።
እንግሊዝኛ (English) ደግሞ ከሂንዲ ጋር በማዕከላዊ መንግሥት ኦፊሴላዊ ሥራዎች፣ ሰነዶችና ግንኙነቶች በስፋት ይጠቀማል። የOfficial Languages Act ሁለቱም ቋንቋዎች በብዙ የUnion መንግሥት ሥራዎች እንዲጠቀሙ ያስቀጥላል።
ሕንድ አንድ ብቻ የአገር አቀፍ “National Language” ያላት አገር አይደለችም። የተለያዩ ግዛቶች የራሳቸውን ኦፊሴላዊ ቋንቋ በሕግ ሊወስኑ ይችላሉ።
ሕንድ ከዓለም ትልቁ እና በፍጥነት እያደጉ ካሉ ኢኮኖሚዎች አንዷ ናት። IMF በ2026 የሕንድ Real GDP ዕድገት 6.4% እንደሚሆን ይገምታል።
ሕንድን በአንድ ሐረግ
ሕንድ የጥንታዊ ሥልጣኔን ቅርስ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ ከፈጣን ኢኮኖሚ እድገት እና ከተጽዕኖ ፈጣሪ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ጋር በማጣመር ወደ 21ኛው ክፍለ ዘመን ኃያል ሀገርነት እየተሸጋገረች ያለች ሀገር ናት።
በ2026 - የነዳጅ ዋጋ፣ የዓለም ጂኦፖለቲካዊ ግጭቶች፣ የከተማ መሠረተ ልማት፣ የሥራ ዕድል፣ የአካባቢ ለውጥ እና በፍጥነት የሚለወጠው የAI ቴክኖሎጂ እየፈተኗት፤ ከወዲሁ እጀጇን እየጠመዘዟት ነው።
ሕንድ ብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሏት ፌዴራላዊ የፓርላማ ሥርዓት ያላት አገር ናት። በብሔራዊና በግዛት ደረጃ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አሉ።
የሕንድ ፖለቲካ ፓርቲዎች
Bharatiya Janata Party (BJP) — ብሔራዊ ደረጃ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ፓርቲ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ድሮፓዲ ሙርሙ ከፓርቲው ቢመጡም የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የBJP መሪ ናቸው።
Indian National Congress (INC) — በሕንድ ታሪክ ውስጥ ረጅም ታሪክ ያለው ዋና የተቃዋሚ ፓርቲ
Aam Aadmi Party (AAP) — በተለይ በዴልሂ ፖለቲካ የታወቀ ፓርቲ
All India Trinamool Congress (AITC/TMC) — በምዕራብ ቤንጋል ጠንካራ የፖለቲካ መሠረት ያለው ፓርቲ ነው።
Dravida Munnetra Kazhagam (DMK) — በታሚል ናዱ ዋና የፖለቲካ ፓርቲ
Samajwadi Party (SP) — በኡታር ፕራዴሽ ጠንካራ ተጽዕኖ ያለው ፓርቲ
Bahujan Samaj Party (BSP) — በተለይ በኡታር ፕራዴሽ የሚታወቅ ፓርቲ
Nationalist Congress Party (NCP) — በማሃራሽትራ የተለየ ተጽዕኖ ያለው ፓርቲ
Shiv Sena — በማሃራሽትራ የተመሠረተ ታዋቂ የክልል ፓርቲ
የፖለቲካ ሥርዓቱ
ሕንድ ባለብዙ ፓርቲ የፓርላማ ዲሞክራሲ ናት። የሕንድ ፓርላማ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት፦
Lok Sabha — የሕዝብ ምክር ቤት
Rajya Sabha — የክልሎች ምክር ቤት
በአገሪቱ የሚካሄዱ ምርጫዎች በElection Commission of India ይመራሉ። የሕንድ ፖለቲካ ልዩ ባህሪው ብሔራዊ ፓርቲዎች ከክልላዊ ፓርቲዎች ጋር በጥምረት መንግሥት መመሥረታቸው ነው።
ለዘገባዎ አንድ አስፈላጊ ነጥብ፦ BJP በአሁኑ ወቅት የሕንድ ፌዴራል መንግሥትን የሚመራ ዋና ፓርቲ ሲሆን፣ ኮንግረስ ደግሞ ከዋና የተቃዋሚ ኃይሎች አንዱ ነው።
የጉዞ ማስታወሻ ( ክፍል - 10)
ይቀጥላል ....
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#india in Ethiopia (Embassy of India, Addis Ababa) #indiaethiopia #brics #financialcooperation #banking #economiccooperation #ministry of External Affairs, #government of IndiaIndia in Ethiopia (Embassy of India, #addis Ababa)Press Information Bureau - PIB, #government of IndiaDiaspora India ConnectMinistry of Information & Broadcasting, #government of #indiamygovindiaddnewsliveasian News #international (ANI)All India Radio News #india in ethiopia (embassy of india addis ababa) #manohar Lal #ethiopian Airlines #ministry of External Affairs
Government of India
# India - External Publicity & Public Diplomacy Division External Language Media Section #mr . Amit Raghav, Publicity Officer (XLM) #unesco #brics #bricssummit #india #newdelhi #diplomacy #economy #putin #modi #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ትኩረት የሚሻ ጉዳይ !
ህፃናትን አልኮል ነክ ከሆኑ መጠጦች መከልከል ለፀጥታ አካል ብቻ የሚተው ሰራ አይደለም የሁሉም ዜጋ እንጂ !
መንግስት የአልኮል መጠጦች በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያ የከለከለው ትውልዱን ለመታደግ ነው ። በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ያገኘነው ይህ ፎቶ ግራፍ በዝምታ ሊታለፍ የማይችል ሆኖ አግኘተነዋል
እነዚህ መጠጥ የያዙ ህፃናት ስንመለከት መንግስትን ወዴት ነህ ? ማለት ፈለግንና ግን እንዲህ አይነት ተግባር መንግስትን ሳይሆን የሚመለከተው ወላጅ:ቤተሰብ እንዲሁም ማህበረሰብን ነው ።
እንደዚህ አይነት ማህበራዊ መዛነፍ የሚስተካከለው ማህበረሰቡ በሚከተለው ወግና ባህል እሴት ነው።
የእያንዳንዱ ወላጅና ማህበረሰብ ልጅን በወግና በስረዓት ማሳደግ አለበት አለበለዚያ “በቅርብ ያልመለሰ እረኛ ሲሮጥ ይውላል “ እንደሚባለው ዛሬ በቅርቡ ገስፀን ያልመለስናቸው ልጆቻችን እንኳን ሀገር ተረክበው ሊያስተዳድሩ ይቅርና እራሳቸውን መምራት እማይችሉበት ደረጃ ይደርሳሉ
ትኩረት ለ ልጆቻችን

28 days ago
“መና የሚዘጋጅበት የሰማይ ቤት ከተዘጋ ቆይቷል!”
— ፖሎ ሉሙምባ
#ethiopia | የፓን አፍሪካኒዝም ተሟጋች ፕሮፌሰር ፖሎ ፓትሪክ ሉሙምባ በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ለአህጉሪቱ መሪዎችና ለሕዝቡ ጠንከር ያለና አሳሳቢ መልእክት አስተላልፈዋል።
ፕሮፌሰር ሉሙምባ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ አሁን ካለችበት አስከፊ ድህነት ኋላቀርነትና መዋቅራዊ ጭቆና ልትወጣ የምትችለው በጾምና በጸሎት ሳይሆን በተግባራዊ ሥራ በሳይንስና በጥበብ የተሞላ እርምጃ መውሰድ ስትጀምር ብቻ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
“መና የሚዘጋጅበት የሰማይ ቤት ከተዘጋ ቆይቷል!” ያሉት ፕሮፌሰሩ የችግሮች ሁሉ መፍትሔ ጸሎት ብቻ እንደሆነ ተደርጎ መወሰዱንና ለአህጉሪቱ እድገት ወሳኝ የሆኑ ተግባራዊ መፍትሔዎች ወደ ጎን መገፋታቸውን በፅኑ ኮንነዋል።
የሃይማኖት ተቋማትን ሚና በጥብቅ የነቀፉት ፕሮፌሰሩ በርካታ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች እራሳቸውን የሞራል የበላይ አድርገው ቢያቀርቡም በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመውን መዋቅራዊ ብዝበዛና ስልታዊ ሙስና ግን በዝምታ ያልፉታል ብለዋል።
አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች ከአማኞቻቸው አሥራትና ምጽዋት በሚሰበስቡበት አህጉር ሕዝቡ አሁንም ንጹህ የመጠጥ ውሃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አጥቶ በጨለማ እንዲኖር ተፈርዶበታል ነው ያሉት።
ፖሮፌሰር ፖሎ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በተግባር የተደገፈ ጥረት ሲታከልበት ብቻ መሆኑን በማስመር ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #africa #nigeria #church #plolumumba #poverty #panafricanism #economy

29 days ago
(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ሰሞኑን የብቸኝነት ቁርጥማት ሲነሳብኝ ማስታገሻዬ ዩቱብ መክፈት ሆኗል። ትናንት ማታም እንደ ልማዴ ዩቱቤን ከፍቼ ሳዳምጥ፣ ድንገት የህብስት ጥሩነህ "ወግ ነው" የሚለው የድሮ ዘፈን ተከፈተ። ዘፈኑን ሳዳምጠው ድሮም የማውቀው ቢሆንም፣ የትናንት ማታው ግን ልክ ህብስት ጓዳዬ ድረስ ገብታ የኔን ሞኝነት አይታ የዘፈነችው ነው የመሰለኝ።
ህብስት ስትዘፍን "ወግ ጥሼ መጣለሁ ይሉኝን አልፈራ..." እያለች አንጀቷን ስትጥል፣ እኔን ትዝታዬ ከነጠፈበት ጎትቶ አወጣኝ። እኛ ሀበሾች "ዝምታ ወርቅ ነው" የሚለውን ብሂል ከየት እንዳመጣነው እንጃ። እኔም ይሄንኑ ብሂል አምኜ፣ ህብስት በዘፈኗ እንደምትለው "ዝምታ ወርቅ ነው ብዬ መውደዴን ደብቄ" ስኖር፣ ኪሴ ውስጥ ወርቅ ያጠራቀምኩ መስሎኝ ነበር። ለካስ እያጠራቀምኩ የነበረው ጸጸት እና ባዶነት ነው!
ነገሩ እንዲህ ነበር... አንድ አይኔ ያረፈበት፣ አንጀቴ የፈቀደው ሸበላ ነበር። እሱ ቀድሞ ይምጣ፣ እሱ ይንገረኝ ብዬ "ከአንተው ይምጣ ብዬ" ስጠብቅ ጊዜው ነጎደ። በልቤ ውስጥ "የኔ ነህ" ብዬ በባዶ ስመካ፣ እሱ ግን የልቤን ትርታ የሚሰማበት ማይክሮስኮፕ አልነበረውም፤ "አፍ እንጂ ልብ አታይም ለካ" እንዲሉ፣ የኔው ጉድ የልቤን ዝምታ ሳይሆን፣ የሌላዋን የአፍ ጩኸት ሰምቶ ሄደ።
ህብስት ዜማዋን ቀጠል አድርጋ "ከአይን ይመነጠቃል የዘመን ሴት ጀግና" ስትል አፌን ይዤ ቀረሁ። ልክ ናታ! እኔ ገና "ዛሬ ነገ እያልኩኝ አፌ መታሰሩ" ሲያንገላታኝ፣ እና ወጉን ስጠብቅ ያቺ "የዘመን ሴት ጀግና" ከተፍ አለች። እኔ በዝምታ ወርቅ ሳጠራቅም፣ እሷ የልቤን አልማዝ ዘረፈችኝ። "ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ሲቆረጥ በሀገሩ" እንደሚባለው፣ እኔ የባስኩ ሞኝ ሆኜ ህብስት እንዳለችው "የኔስ ከጓዳዬ ሆነብኝ ነገሩ"። ምንም ሳልዘጋጅ፣ ገና በማለዳ የልቤን ንጉስ ከጓዳዬ ተነጠቅኩ!
ዘፈኑ እያለቀ ሲመጣ የህብስት ድምጽ የኔን የውስጥ ጩኸት ሆኖ አስተጋባ። "ዛሬስ ልድፈር ይወጣ ከአንደበቴ..." ስትል፣ እኔም ከራሴ ጋር ተማማልኩ። ይሉኝታ የሚባል በሽታ መድሃኒቱ መናገር ብቻ ነው። የህብስት ጥሩነህን "ወግ ነው" ዘፈን ካዳመጥኩ በኋላ አንድ ውሳኔ ላይ ደርሻለሁ። ፍቅሬ ያረፈደ ቢሆንም፣ ዳግም ዝምታ ወርቅ ነው ለሚለው ተረት አልታለልም። ወርቁን ለቀለበት ፈላጊ ትቼው፣ እኔ ግን ጮክ ብዬ "እወድሃለሁ" ለማለት ወስኛለሁ! ብቻ ምን ያደርጋል... "ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ" ሆነብኝ እንጂ።
ማርታ ከሚኒሶታ

Sponsored by
Surafel
29 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በተለይም በጃን አሞራ፣ በየዳ እና ጠለምት ወረዳዎች የተከሰተውን አሰቃቂ ድርቅ ተከትሎ ከሁለት ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ሕይወት አደጋ ላይ መውደቁን በማስታወቅ አስቸኳይ የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ። ድርጅቱ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ያለ አንዳች ድምፅ በዝምታ እያለቀ መሆኑን አጋልጧል።
በአካባቢው የተከሰተው አስከፊ ድርቅ እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ የቤት እንስሳትን ያጠፋ ሲሆን፣ የክረምት ወራት በገባበት በአሁኑ ወቅት ጭምር በየቀኑ ከ200 በላይ እንስሳት እየሞቱ መሆኑን የፓርቲው መግለጫ ያስረዳል። ለዓመታት በቀጠለው ጦርነት ከፍተኛ መከራን ሲያስተናግድ የቆየው የአካባቢው ህዝብ፣ አሁን ደግሞ በተፈጥሮ አደጋ ድርብ ስቃይ ውስጥ ወድቆ ቀያውን ጥሎ እየተሰደደ ይገኛል። መኢአድ በመግለጫው "ከበሬው የተለየ ገበሬ ከሞተ ቁጥር ነው" በማለት የችግሩን ጥልቀት እና አርሶ አደሩ የደረሰበትን የህልውና አደጋ አብራርቷል።
በዚህ ፈጣን ዘመን የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ በድርቅ ሲያልቅ ዝም ብሎ መመልከት ከገዳይነት እንደማያንስ ያስገነዘበው ፓርቲው፣ ይህን አሰቃቂ ሰብዓዊ ቀውስ ለመታደግ ሁሉም አካል የነፍስ አድን ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቋል። በዚህም መሰረት የፌዴራል እና የክልሉ የአደጋ ጊዜ ተቋማት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ የሚዲያ ተቋማት፣ ግለሰቦች እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉን አቀፍ አስቸኳይ እርዳታ በአፋጣኝ እንዲያደርሱ መኢአድ ጥሪውን አስተላልፏል።
መኢአድ በዚህ የነፍስ አድን ስራ ላይ አስቸኳይ እርዳታ ለሚያደርጉ አካላት የሚቻለውን ትብብር ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቆ፣ መላው የድርጅቱ አባላትም በዚህ የድረሱልኝ ጥሪ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

1 month ago
ለ50 ዓመታት ያህል ሚስቱ እንኳን ያላወቀችው ሚስጥር በቴሌቪዠን መስኮት ተጋለጠ!
#ethiopia | ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ በፊት በናዚ የሞት ጥላ ስር የወደቁ 669 ሕፃናትን ከሞት ታደጉ ከዚያም ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል ስለፈጸሙት አስደናቂ ጀብድ ለማንም ሳይናገሩ በዝምታ ኖሩ።
በእንግሊዝ የባንክ ባለሙያ የነበረው ዊንተን በፈረንጆቹ 1939 የናዚ ጦር ቼኮስሎቫኪያን ሲወር በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት ላይ የተደቀነውን አደጋ ቀድሞ ተመለከተ።
ጊዜ ሳይሰጥ ሰነዶችን በማዘጋጀት ባቡሮችን በማመቻቸት 669 ሕፃናት ከናዚ ጭፍጨፋ አምልጠው ወደ እንግሊዝ በሰላም እንዲገቡ አደረገ።
ይህንን ታላቅ የጀግንነት ሥራ ከሰራ በኋላ ግን ዊንተን ትምክህት አልያዘውም ለታዋቂነትም አልቸኮለም።
ላለፉት 50 ዓመታት ያህል ሚስቱ እንኳን የማታውቀው ሚስጥር አድርጎ በልቡ ይዞት ኖረ።
በ1988 ኒኮላስ ዊንተን በቢቢሲ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በታዳሚነት እንዲቀመጥ ተጋበዘ።
እርሱ ተራ የቪዲዮ ትርኢት የሚታይ መስሎት በዝግታ የተቀመጠ ቢሆንም በዙሪያው የተቀመጡትን ሰዎች ማንነት ግን ፈጽሞ አያውቅም ነበር።
በስቱዲዮው ውስጥ የነበረችው አቅራቢ በድንገት ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች።
በኒኮላስ ዊንተን መልካምነት ህይወታችሁ የተረፈ ሰዎች ካላችሁ ከተቀመጣችሁበት ተነስታችሁ ቁሙ ስትል ተናገረች።
በዚያ ቅጽበት ተአምር ተከሰተ።
በዊንተን ዙሪያ የተቀመጡት አዋቂዎች በሙሉ በቅደም ተከተል ከወንበራቸው ተነስተው ቆሙ።
በዙሪያው ያሉት ሙሉ ታዳሚዎች በሙሉ ከ50 ዓመታት በፊት በህፃንነታቸው በሱ ጥረት ከሞት አፍ የተረፉትና አሁን ትልቅ ደረጃ የደረሱት እነዚያው ሕፃናት ነበሩ።
ዊንተን በእንባ ተሞልቶ በድንጋጤና በደስታ ተመለከተ።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ በህይወት ለመኖራቸው ምክንያት የሆነው ሰው አጠገብ ቆመው በክብር ሲያበሩ አያቸው።
ከ50 ዓመታት በኋላ ሕይወታቸውን ለታደጋቸው ታላቅ ሰው አጠገብ ቆመው ምስጋናቸውን ማቅረብ ቻሉ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #england #czechoslovakia #german #worldwar #nicholaswinton #children

የሁሊያን አልቫሬዝ የመጨረሻው ቀን
ወደ አርሰናል ወይስ በይቅርታ በአትሌቲኮ ይቆያል?
በሁሊያን አልቫሬዝ የዝውውር ጉዳይ ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ እና አርሰናል ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ ዛሬ የሚያበቃ ሲሆን፣ አርጀንቲናዊው አጥቂ የአርሰናልን ጥያቄ ተቀብሎ ወደ ለንደን ማመራት ወይም ለአትሌቲኮ ማድሪድ ይቅርታ ጠይቆ በክለቡ መቆየት እንዳለበት ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት አልቫሬዝ ለአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ለአሰልጣኞች፣ ለቡድን አጋሮቹ እና ለደጋፊዎች ይቅርታ የመጠየቅ እድሉ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ይገመታል።
ተጫዋቹ ማክሰኞ ዕለት የተመከረውን ልምምድ በማቃለሉ አትሌቲኮ ማድሪድ ደስተኛ ያልነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ ነገሩን በዝምታ አልፎታል።
ነገር ግን በማክሰኞ ምሽት የታመመ መሆኑን ቤተሰቦቹ ለክለቡ ካሳወቁ በኋላ፣ ተጫዋቹ የረቡዕ፣ የሐሙስ እና የዓርብ ልምምዶችን ሙሉ በሙሉ አቃጥሏል።
በተለይም የረቡዕ ዕለት ልምምድ መቅረቱ ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ የቀየረው ሲሆን፣ አልቫሬዝ ለሚላኩለት መልእክቶች ምላሽ በመከልከሉ የክለቡ ከፍተኛ አመራር ማቴው አለማኒ ወደ ቤቱ በአካል በመሄድ መፍትሔ ለመፈለግ ተገዷል።
ይህንን ተከተሎም አልቫሬዝ ከቤተሰቦቹ፣ ከተወካዮቹ እና ከህግ አማካሪዎቹ ጋር ረጅም ስብሰባ ያደረገ ሲሆን፣ የዝውውር አማራጮቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበቡ መምጣታቸው ተጠቅሷል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቅርቡ ጅቡቲ የባብ ኤል-መንደብን ባህረ ሰላጤ ደህንነት ለማስጠበቅ ዓለም አቀፍ ኃይሎች እና የባህር መስመሩ ዋነኛ ተጠቃሚዎች ኃላፊነት እንዲጋሩ ያቀረበችው ጥሪ፣ በአፍሪካ ቀንድ የጂኦ-ፖለቲካዊ ትኩረት አቅጣጫን የሚቀይር ክስተት መሆኑን አዲስ ጥናት አመላከተ።
ሳሚያ መሐመድ የተባሉ ተመራማሪ ዛሬ ባወጡት ትንታኔ ይህ የጅቡቲ ጥሪ ሀገሪቱ ባህረ ሰላጤውን ለብቻዋ የመጠበቅ አቅም እንደሌላት በይፋ ያመነችበትና በስፍራው የሚከሰት አደጋ ከሆርሙዝ የባህር መስመር መዘጋት እጅግ ሊከፋ እንደሚችል የተሰጠ ማስጠንቀቂያ መሆኑን አስነብበዋል።
በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት መዋቅራዊ አለመመጣጠን በግልጽ የሚታይበት ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ከሞላ ጎደል በጅቡቲ ወደቦች ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ጉዳዩ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። በባብ ኤል-መንደብ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም የጸጥታ መስተጓጎል የኢትዮጵያን የገቢ ንግድ በማስተጓጎል የውጭ ምንዛሬን እና ፖለቲካዊ መረጋጋትን ክፉኛ ሊያናጋው ይችላል።
በሌላ በኩል የጅቡቲ የኢኮኖሚ ሞዴል በኢትዮጵያ የጭነት መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። ሆኖም አደጋው ሲመዘን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የህልውና ሥጋት ሲያንዣብብባት፣ ጅቡቲ ግን የሚያጋጥማት የሥራ ማስኬጃ ) ሥጋት ብቻ ነው።
ጅቡቲ እስካሁን የባህር በር ሉዓላዊነቷን በመጠቀም የተለያዩ የውጭ ሀገራት ወታደራዊ የጦር ሰፈሮችን በማስተናገድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም ስታገኝ ቆይታለች። በዚሁ ልክ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የባህር ኮሪደር ወይም የባህር ኃይል ጦር ሰፈር በጅቡቲ ለማቋቋም ስታቀርብ የነበረውን ጥያቄ ጅቡቲ በተደጋጋሚ ስትገፋው ኖራለች። ይሁን እንጂ ጅቡቲ አሁን ያቀረበችው "የጋራ ኃላፊነት" ጥሪ፣ የነበረው ነባር የአንድዮሽ የጸጥታ አደረጃጀት አቅሙ ማለቁን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው።
ጥናቱ እንደሚሞግተው ኢትዮጵያ ይህንን የጅቡቲ የትብብር ጥሪ እንደ ወሳኝ ዕድል በመጠቀም፣ ኃላፊነትን በግዴታ የመጋራት ስትራቴጂ መከተል አለባት። ኢትዮጵያ ካለባት አንገብጋቢ የህልውና አደጋ አንጻር መረጃ በመለዋወጥ፣ በጋራ የጸጥታ ጥበቃ እና አቅም ግንባታ ላይ ተመጣጣኝ ሚና የሚሰጣት መደበኛ የጋራ የጸጥታ ማዕቀፍ እንዲቋቋም በአፋጣኝ መጠየቅ ይኖርባታል።
አማራጭ ወደቦችን የማልማቱ ጉዳይ ገና ዓመታትን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ አሁን ላይ የህልውናዋ መሠረት የሆነውን የባህር መስመር ደህንነት በዝምታ መመልከት አትችልም። ተመራማሪዋ ትንታኔያቸውን ሲያጠቃልሉ "አሮጌው አሰራር እያከተመ ነው፤ አዲሱ አሰራር ደግሞ ኢትዮጵያ የራሷን ሚና እንድትወስን እና ተቋማዊ ተጽዕኖዋን እንድታሳድግ ያስገድዳታል" ሲሉ አሳስበዋል።

2 months ago
እናት ፓርቲ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን “የእነ አጼ በጉልበቱ መፈንጫ” ሲል ኮነነ ውጤቱንም እንደማይቀበል አስታወቀ
እናት ፓርቲ በቅርቡ የተካሄደውን የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ አጠቃላይ ሂደትና ፍጻሜ በማስመልከት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ ሂደቱ “በመርሕና በስክነት የተካሄደ ሳይሆን የእነ አጼ በጉልበቱ ትዕይንት ነው” ሲል በጽኑ ተቃወመ።
ፓርቲው የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ "የይምሰል ምክክር" የሚወጡ ውሳኔዎችን እንዳይቀበል ጥሪ አቅርቧል።
እናት ፓርቲ እንዳመለከተው፣ ኮሚሽኑ ራሱ ላስቀመጣቸው መመሪያዎች አልተገዛም። አብዛኛውን ተሳታፊ የወከለው ገዢው ፓርቲ እንደሆነና ሰፊው ጊዜ በዋዛ ፈዛዛ በማሳለፉ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሳል ክርክር ሳይደረግ ማለፉን ገልጻል።
በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የአብዛኛው ተመካካሪ ሀሳብ “ከተማዋ ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ ትሆናለች” የሚል ቢሆንም፣ ከገዢው ፓርቲ ፍላጎት ጋር ባለመጣጣሙ አዳራሽ ማረበሽ፣ ማስፈራራትና ሂደቱን እስከ አርብ ማራዘም እንግልት መፍጠሩን ፓርቲው ገልጿል።
አዲስ አበባ የነዋሪዎቿና የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የአንድ ቡድን ፍላጎት ማስፈጸሚያ ልትሆን አትችልም ብሏል።
ኮሚሽኑ በስራ መመሪያው ላይ በውሳኔ አሰጣጥ ወቅት 75% ድጋፍ (Consensus) ማግኘት ያስፈልጋል ብሎ ያስቀመጠ ቢሆንም፣ ያ ሳይፈጸም በዝምታና በጭብጨባ “ስምምነት ተደረሰበት” ተብሎ የተላለፉት ውሳኔዎች በሙሉ ህጋዊነት የላቸውም ሲል እናት ፓርቲ አስታውቋል።
ለምክክሩ ውጤት አልባነትና ለተፈጠረው አዲስ ውጥረት "ጠበብ ሲል የኦሮሚያ ብልጽግና፣ ሰፋ ሲል ደግሞ ገዢው ብልጽግና" ተጠያቂ ናቸው ያለው ፓርቲው፣ ለምክክሩ ውጤት ሙሉ በሙሉ እውቅና እንደማይሰጥ እና ህዝቡም በአመቸው መንገድ ሁሉ እንዲቃወመው ጥሪ አቅርቧል።
የእናት ፓርቲ ሙሉ መግለጫ በዛሬው ዕለት ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የተሰጠ ነው።

አዲስ አልበም — «በዝምታ» ተለቀቀ
🎶 90ዎቹን የሙዚቃ ዘመን በስሜት የሚያስታውስ አዲስ ድምፅ!
#ዳን_አብ ለዓመታት በጥንቃቄ ሲያዘጋጀው የቆየውን አዲስ አልበሙን «በዝምታ» ለሙዚቃ አፍቃሪያን አቀረበ።
ዳን አብን ብዙዎቻችሁ የምታውቁት በቴዲ አፍሮ ስራዎች ላይ የከቨር ሙዚቃዎችን በመስራት ሲሆን፣ አሁን ግን በራሱ ግጥም፣ ዜማ እና የሙዚቃ ቅንብር የተሰራ ሙሉ አልበም ይዞ መጥቷል።
🎼 አልበሙን በራሱ ስቱዲዮ በራሱ አቅም ያዘጋጀው ዳን አብ፣ ከዚህ በፊትም ለበርካታ ጀማሪና ታዋቂ አርቲስቶች የተለያዩ የሙዚቃ ስራዎችን በመስጠትና በማዘጋጀት ይታወቃል።
📅 ነሐሴ 15
⏰ ከቀኑ 8:00 ሰዓት
🎵 አልበሙ በዳን አብ ይፋዊ የYouTube ቻናል ተለቋል።
👇 ከአሁኑ ቻናሉን Subscribe አድርጉና የአልበሙን ሙሉ ልቀት ያጣጥሙ።
የዳን አብ ይፋዊ YouTube ቻናል
https://youtube.com/dan_a...
#በዝምታ #ዳን_አብ #danab #አዲስአልበም #ethiopianmusic #ethiopianartist #90smusic

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአክሲዮስ የዜና አውታር ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ፣ በኢራን ላይ የተጣለው የኢኮኖሚ ጫና ይበልጥ እንዲበረታ ለመፍቀድ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ምንም እንኳን ኢራን ከኦማን ጋር በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ጉዳይ ላይ እስካሁን ስምምነት ላይ ባትደርስም እና ቴህራን ቅዳሜ ዕለት አዳዲስ ቅድመ ሁኔታዎችን ብታቀርብም፣ ፕሬዝዳንቱ በዚህ አጭር ቃለ ምልልስ ላይ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ዛቻ ከመሰንዘር ተቆጥበዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የአሜሪካ የባህር ኃይል ያደረገው ማዕቀብ እና እገዳ ኢራንን "እጅግ በጣም መጥፎ ሁኔታ ውስጥ" እንደከተታት ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ወደ 75 ዶላር በማሽቆልቆሉ ምክንያት፣ የአሜሪካ ሸማቾች የኢኮኖሚ ጫናው ብዙም እንዳልተሰማቸው ተናግረዋል። ዋሽንግተን ከኢራን ጋር ስላላት ውጣ ውረድ የተሞላበት ግንኙነት ሲያብራሩም፣ "ሁሉም ነገር ይስተካከላል፤ ሁሌም መፍትሔ ያገኛል። ነገሩ ልክ እንደ ቼዝ ጨዋታ ነው" በማለት ዘይቤያዊ አገላለጽ ተጠቅመዋል።
በተጨማሪም የአሜሪካ መንግሥት በኢራን ላይ ያለውን አካሄድ አሁን ላይ "እያቀዘቀዘው" መሆኑን ትራምፕ አመልክተዋል። "ከእነሱ ጋር በከፊል-ድርድር ላይ ብቻ ነን ያለነው። ኢራን ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ሀገሪቱ ገንዘብ አልባ መሆኗን በዝምታ እየተመለከትን ነው" በማለት የዋሽንግተንን የአሁን ላይ ስትራቴጂ አብራርተዋል።

መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ
ከቢኒያም አቡራ
#ethiopia | አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን።
Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው።
ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል።
ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል?
መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም።
ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል።
መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው።
እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን?
“ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ ይገኛል።
በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል።
መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ።
“መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም።
ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው!
መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ።
auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል።
የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው።
ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል።
በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ?
ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን።
መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል።
የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው።
የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው።
“የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል።
ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል።
የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል።
ቢኒያም አቡራ
ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም

የዓድዋ ገድል በአረንጓዴ አሻራ ሲደገም
*****************
በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሀገርን የተፈጥሮ ሀብት ከመጠበቅ ባሻገር፣ ሉዓላዊነትን የማስከበር ዋነኛ ማሳያ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሉዓላዊነት በሁለት መንገዶች ሊደፈር እንደሚችል ማንሳታቸው ይታወሳል።
የመጀመሪያው በውጭ ወራሪ ሀይል በኩል ድንበር ጥሶ በመግባት የሚፈጸም ሲሆን፤ ይህንንም ኢትዮጵያውያን በዓድዋ ጦርነትና በሌሎችም አውዶች በደም መስዋዕትነት አስጠብቀዋል።
ሁለተኛውና ጸጥተኛው የሉዓላዊነት መደፈር ግን፣ እንደ አፈር ያለ ወደፊት በቀላሉ የማይተካ ውድ የተፈጥሮ ሀብት በጎርፍና በመሸርሸር ድንበር አቋርጦ ሲወጣ የሚከሰት ነው።
የሚሸረሸር አፈር፣ የሚደርቅ ሀይቅ፣ የሚጠፋ ደን፣ እንዲሁም የሚመናመን የምግብ ዋስትና በዝምታ የሚፈጸሙ የሉዓላዊነት መሸርሸር ማሳያዎች ናቸው።
ለዘመናት በውሃና በንፋስ ምክንያት ሲጠፋ የነበረው ለም አፈር የገበሬውን ምርት፣ የምግብ ዋስትናን፣ የወደፊቱን ኢኮኖሚ እንዲሁም የትውልድን ተስፋ አብሮ ይዞ የሚወጣ በመሆኑ፤ የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ይህንን ጸጥተኛ ወረራ የመቀልበስ ሀገራዊ ስትራቴጂ ሆኖ እየተተገበረ ይገኛል።
ይህ መርሃ ግብር ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን፣ ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ያላቸውን እንደ ቡና፣ አቮካዶ፣ ማካዴሚያ፣ ካካዎ እና ሮማን የመሳሰሉ ሰብሎችን በማስፋፋት ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና ለስራ እድል ፈጠራ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።
በተጨማሪም ሀይቆች ሲያገግሙ፣ አእዋፋት ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱና ደኖች ሲለሙ ለኢኮ-ቱሪዝም መስፋፋት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሲሆን ይህም በዜጎች ገቢና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ አዎንታዊ ለውጥ እንዲመጣ ያስችላል።
የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የተጀመረባት ቢሾፍቱ፣ እስከ አዋሽ ያለው ቀጠና የሀይቆች ስርዓት የአእዋፍ ብዝሃ ሕይወትና የተፈጥሮ ገጽታ ለኢኮ ቱሪዝም ትልቅ እምቅ አቅም እንዳለው ያሳያል። ተፈጥሮ ሲጠበቅ ቱሪዝም ያድጋል፤ ቱሪዝም ሲያድግ ደግሞ ለዜጎች ሥራ፣ ገቢና ኢኮኖሚያዊ እድል ይፈጥራል።
ትውልድ በታሪክ የሚታወሰው የሠራው ስራ በሚያስቀረው ውርስ ነው። የዓድዋ ትውልድ ነፃነትን አውርሶናል፤ የዛሬው ትውልድ ደግሞ አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመተው ኃላፊነት አለበት። የሚተከለው ችግኝ ዛሬ ትንሽ ቢመስልም ነገ የልጆቻችን ጥላ፣ ሀብት፣ ምግብ፣ ቱሪዝምና የአገር ክብር ይሆናል።
የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ የችግኝ ተከላ ብቻ አይደለም፤ የሉዓላዊነት ጥበቃ፣ የኢኮኖሚ ማንሰራራት፣ የምግብ ዋስትና፣ የቱሪዝም እድገት፣ የአካባቢ ጥበቃና የትውልድ ውርስ በአንድ ላይ የሚገናኙበት ሀገራዊ እንቅስቃሴ ነው።
የአባቶቻችን ገድል ነፃነትን አስጠብቆልናል፤ የዛሬው አረንጓዴ ገድል ደግሞ ያንን ነፃነት በለምለም ምድር፣ በበለጸገ ኢኮኖሚና በዘላቂ ልማት ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው።
በልዩ እሸቱ

3 months ago
በቅጠሉ ንጹህ አየርን የሚፅፍ፣ በሥሩ አፈርን የሚያፀና
ታሪክ ሁልጊዜ በብዕር ብቻ አይጻፍም፤ አንዳንዴ በእጅ የተቆፈረ ትንሽ ጉድጓድ፣ በውስጡ በተተከለ አንዲት ችግኝ እና በላዩ በተጨመረ አፈር ይጻፋል።
ዛፍ የሚተክል ሰው ለዛሬ ብቻ አይሠራም፤ ያላየውን ትውልድ እያሰበ ይተጋል። ከራሱ ዕድሜ የሚረዝም ተስፋን በምድር ውስጥ ያኖራል። ስለዚህ አንድ ችግኝ መትከል አንድ የወደፊት ምዕራፍ መጀመር ነው።
በዚህ ምክንያት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ ዘመቻ ብቻ አይደለም። አንድ ሕዝብ ከተፈጥሮው ጋር የሚያድሰው የታሪክ ውል ነው።
በዚህ ውል ላይ ፈራሚው መንግሥት ብቻ አይደለም። አርሶአደሩ፣ ተማሪው፣ መምህሩ፣ ሠራተኛው፣ ወጣቱ፣ እናት፣ አባት እና ሕፃን ጭምር ናቸው።
ምክንያቱም አካባቢን መጠበቅ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ አደራ ስለሆነ።
በዚህ ዓመት በ"ተስፋ እንትከል" መሪ ሐሳብ የወደፊት ታሪካችንን በራሳችን እጅ የምንቀርጽበት ነው። ምድር የምትለምልመው በዝናብ ብቻ አይደለም። በሰው ኃላፊነት፣ በሰው ራዕይ እና በሰው ፍቅርም ጭምር እንጂ።
ዛፍ ደግሞ ዝም ብሎ የሚቆም ፍጥረት ሳይሆን በዝምታው ብዙ ነገር ይናገራል። በቅጠሉ ንጹህ አየርን ይጽፋል፤ በሥሩ አፈርን ያጸናል፤ በጥላው ሕይወትን ያቅፋል፤ በፍሬው ተስፋን ያበቅላል። ስለዚህ አንድ ዛፍ መትከል የነገን ሕይወት መትከል ነው።
ዛሬ የዓለማችን ፈተና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የደን መመናመን፣ የመሬት መራቆትና የውኃ እጥረት ሆኗል። እነዚህን ችግሮች በንግግር ብቻ መፍታት አይቻልም፤ በተግባር የተደገፈ ኃላፊነት ይፈልጋሉ። የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴም የዚህ ኃላፊነት ሕያው መግለጫ ነው።
የዘንድሮው "ተስፋ እንትከል" መሪ ቃል በውስጡ ጥልቅ ፍልስፍና ይዟል።
ተስፋ አይዘራም፤ ይተከላል እንጂ። ምክንያቱም ሥር ማበጀት አለበት፣ በትዕግሥት ማደግ አለበት፣ ፍሬ ማፍራት አለበት። ልክ እንደ ዛፍ።
በዛፍ የሚጀምር ልማት በሀገር ዘላቂ እድገት ላይ ያለውን እምነት በተግባር ያሳያል።
የዘንድሮው ጉዞ በቁጥርም ሲገለጽ ትልቅ ራዕይን ያሳያል። በ2018 ዓ.ም 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል።
በዚህም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ቀደም ሲል የነበረውን 48 ቢሊየን ችግኞች የመትከል ግብ ወደ 56 ቢሊየን ከፍ አድርጎታል። እነዚህ ቁጥሮች የተቆጠሩ ችግኞችን ብቻ አይወክሉም። የሕዝብ ተሳትፎን፣ የሀገር ቁርጠኝነትን እና ለቀጣይ ትውልድ የሚገነባውን አረንጓዴ ተስፋ ይወክላሉ።
ዘንድሮ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የተከላ መርሃ ግብርም የዚህ ጉዞ ከፍተኛ ምዕራፍ ይሆናል። በመላ ኢትዮጵያ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአንድ ዓላማ ይሰባሰባሉ።
የመደመር መንግሥት አመራሮች፣ የልማት አጋሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተማሪዎች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች በጋራ ይሳተፋሉ።
ይህ ለሀገር አንድ የጋራ ዓላማ ሲኖር ልዩነቶች ከአንድነት ፊት እንደሚያንሱ የሚያሳይ ተጨባጭ ምሳሌ ነው። ምክንያቱም የዛሬው ችግኝ የነገው ደን ነው፤ የዛሬው አሻራ ደግሞ የኢትዮጵያ የወደፊት ታሪክ ነው።

የአርቲስት መኮንን ላዕከ የመኪና ውዝግብ
#fastmereja | ተወዳጁ አርቲስት መኮንን ላዕከ "ቃል የተገባልኝ መኪና እስካሁን አልደረሰኝም" በማለት ያቀረበው ቅሬታ በዩቶፒያ ቴክኖሎጂ በኩል ምላሽ ተሰጥቶበታል። አርቲስቱ በቅርቡ በሰይፉ በኢቢኤስ ፕሮግራም ላይ የ57 ዓመት ልደቱን ካከበረበት ጊዜ አንስቶ ቃል የተገባለትን መኪና እንዳልተረከበ በይፋ መናገሩን ተከትሎ፣ ኩባንያው ስምምነቱ ለምን እንደተቋረጠ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቷል።
የአሁኑ ውዝግብ መነሻ የሆነው ከአስራ አንድ ወራት በፊት በዝምታ ሬስቶራንትና ላውንጅ በተደረገው የልደት በዓል እና የዳግም ሙሽርነት ስነ-ስርዓት ላይ ነው። በወቅቱ የዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዶኒክ ወርቁ እና የድርጅቱ አምባሳደር አርቲስት እንግዳሰው ሀብቴ በቦታው ተገኝተው፣ መኪናውን ለአርቲስቱ እንደሚያመቻቹ ቃል ገብተው ነበር።
ይሁን እንጂ የዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ ጉዳዩ "ስጦታ" ሳይሆን በቅድመ-ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ስምምነት እንደነበር አስታውቋል። ኩባንያው እንደገለጸው፣ ስምምነቱ የአርቲስቱን የብድር ሂደት ለመጨረስ የሚያስችል ህጋዊ ውክልና ማግኘት፣ ለመኪናው የሚያስፈልገውን ቅድመ-ክፍያ መፈጸም እና አርቲስቱ ለኩባንያው የማስተዋወቂያ ስራዎችን መስራት የሚሉ ግዴታዎችን ያካተተ ነበር።
ኩባንያው አክሎም፣ መኪናው ለአራት ወራት ያህል በሾውሩማቸው ውስጥ ተይዞ ቢቆይም፣ አርቲስቱ እና አዘጋጅ ኮሚቴው በተባሉት ቅድመ-ሁኔታዎች መሰረት አስፈላጊውን ህጋዊ እና የገንዘብ ግዴታዎች ባለመወጣታቸው ስምምነቱን ለመሰረዝ መገደዳቸውን ገልጿል። በሌላ በኩል ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ አሁንም ለጥበብ ማህበረሰብ ያለውን አክብሮት በመግለጽ፣ በቀጣይ ለሚገባቸው አካላት ድጋፍ የማድረጉን ስራ እንደማያቋርጥ አስታውቋል።
ፎቶ ሲሳይ ጉዛይ

የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ለአከራዩች የሰጠዉን መብት ግምት ዉስጥ እንዲያስገባ ተጠየቀ
በተከራይ እና በአከራይ መካከል የሚኖርን ሰላማዊ ግንኙነት ታሳቢ ያደረገ ስርአት እንዲኖርም ተጠይቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከዛሬ ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደራቸውን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። ሪፖርቱን ተከትሎ የምክር ቤት አባላት ምላሽ እና ማብራሪያ ያስፈልጓቸዋል ያሏቸዉን ጥያቄዎች አንስተዋል።
የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ መኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን የተመለከተ ጥያቄ አቅርበዋል።
ዶ/ር ሲሳይ "አዋጁ ክፍተቶች ያሉት ይመስለኛል። በፍጥነት የወጣ በመሆኑ የአከራዩንም ሆነ የተከራዩን ህብረተሰቡን ፍላጎት በማገናዘብ አማካኝ የሆነ ነገር ይዞ መቷል ብዬ አላምንም" ብለዋል።
መሻሻል የነበረባቸው ጉዳዩች ያሉ ቢሆንም ስልጣኑ የፌደራል መንግስት ስለሆነ ብዙ ልንል ባንችልም ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ አፈፃፀሙ ግን በደንብ መታየት ያለበት ነገር መሆኑን ማንሳት አለብን ሲሉ ለምክር ቤቱ ገልፀዋል።
የምክር ቤት አባሉ በቀረበዉ ሪፖርት መሠረት 5 መቶ ሺህ የአከራይ ተከራይ ዉል ተደርጓል የሚለዉን በማስታወስ ይህ 5 መቶ ሺህ አባወራ አለ እንደማለት መሆኑን ይገልፃሉ።
"ይህ 5 መቶ ሺህ አባወራ በስሩ አራት ሰዉ አለ ብንል ሁለት ሚሊዮን ህዝብ ማለት ነዉ፤ እያወራን ያለነዉ ስለዚህ ህዝብ ነዉ ትኩረት ሰጥተን ማየት አለብን" ብለዋል።
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ በየአመቱ የኪራይ መጠን እየተጠና ሊጨምር እንደሚችል ያስቀምጣል።
ዶ/ር ሲሳይ ይህንን በማስታወስ" ዘንድሮ ተጠንቶ ቀረበ የተባለዉ ጭማሪ በሁለት አመቱ ነዉ፤ አዋጁ እንኳን ለአከራዩች የሰጠዉን መብት እኛ እየነፈግን ነዉ።" ሲሉ አስረድተዋል።
ይህ የሚመለከተው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ጥናቱን በየአመቱ መስራት ይገባዋል ሲሉም አክለዋል።
አሁን ለዚህ በጀት አመት ተሰራ የተባለዉ ጥናት ምን ያህል መሠረታዊ ችግርን ይፈታል ወይ? የሚል ሀሳብ አለኝ ሲሉም ጠይቀዋል።
የማዕከላዊ ስታስቲክስ አገልግሎት በየአመቱ ከኑሮ ዉድነት እና የዋጋ ጭማሪዎች ጋር አያይዞ የሚያወጣዉን ጥናት መሠረት አድርጎ ሌላ ጥናት ሳያስፈልግ ጭማሪውን መወሠን ይቻላል ያሉት ዶ/ር ሲሳይ ለሌላ ጥናት ሀብት ማባከን አያስፈልግም ይላሉ።
ከተማ አስተዳደሩ ስለ ተከራዩች ብቻ ሳይሆን የአከራዩችን መብት ግምት ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል ተብሏል።
ለምክር ቤት አባሉ "አሁን ላይ በሁለት አመት ነዉ እያሰብን ያለነዉ ፤ አንድ አመት በዝምታ ነዉ የታለፈዉ ያ ማለት የአከራዩን መብት ከአዋጁ አንፃር የሚጥስ ነዉ" ሲሉ ገልጸዋል።
በምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዩርጊስ የስታትስቲክስ አገልግሎት ጥናት የሀገር አቀፍ ጥናት በመሆኑ ለከተማዉ ቤቶች ጥናቱን ለዋጋ ጭማሪ መሠረት በማድረግ መጠቀም አንችልም ብለዋል።
የከተማዋ አስተዳደሩ በዚህ አመት ለኪራይ ዋጋ ጭማሪ ያስጠናዉ ጥናት የስታቲስቲክስ አገልግሎት ያስጠናዉንም ያካተተ መሆኑን በመግለፅ ለሁለቱም አካላት እኩል ሊጠቅም የሚችል ነዉ ብለዋል።
Seledadotio

ቁምነገር አየለ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ባልበረደበት በዚህ ወቅት፣ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማስኡድ ፔዜሽኪያን እስራኤል በቀጠናው ሀገራት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዝምታ ማለፉን በጽኑ አውግዘዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ጠንካራ ትችት ያሰሙት፣ የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን የሽኝት እና የቀብር ስነ-ስርዓት ለማሰብ በተዘጋጀው ታሪካዊ መድረክ ላይ ነው። በንግግራቸውም፣ እስራኤል በመላው የመካከለኛው ምስራቅ እያባባሰች ላለው አለመረጋጋት እና በበርካታ ሀገራት ላይ ለምትከፍተው ጥቃት፣ የዓለም ማህበረሰብ ዝምታን መምረጡን እና እርምጃ አለመውሰዱን በብርቱ ነቅፈዋል።
ፔዜሽኪያን አክለውም አዲሱ የኢራን አመራር በዚህ ወሳኝ የፈተና ወቅት ላይ ትልቅ ታሪካዊ ኃላፊነት እንደተሸከመ አብራርተዋል። ከዚህ በኋላ ዋነኛ ትኩረታቸው የእስልምናን አንድነት ይበልጥ ማጠናከር እና በሙስሊም ሀገራት መካከል ያለውን የትብብር እና የአጋርነት መንፈስ ማስፋት መሆኑን በማሳሰብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ካንሰርን ድል ያደረገች ልዕልት
#ethiopia | የካንሰር ሕክምናዋን አጠናቃ ሙሉ በሙሉ ወደ ማገገም የተመለሰችው የዌልሷ ልዕልት ኬትሪን ካጋጠማት ከባድ የሕይወት ፈተና በድል መውጣቷን በዝምታ ከማሳለፍ ይልቅ ለካንሰር ሕሙማን እንክብካቤ ድጋፍና ግንዛቤ ለመፍጠር ታላቅ ዓላማ ሰንቃ ተነስታለች።
ልዕልቷ የብሪታንያን አድካሚና ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቀውን ሦስት ታላላቅ ተራሮች የመውጣት ውድድር በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች።
በዚህም መሠረት በስኮትላንድ፣ በእንግሊዝና በዌልስ የሚገኙትን ከፍተኛ ተራሮች ማለትም ቤን ኔቪስ፣ ስካፌል ፓይክ እና ስኖውዶንን በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በመውጣትና በመውረድ፤ በረጅም ርቀት የእግር ጉዞ፣ በድንቅ ጽናት የታጀበ አስደናቂ አካላዊ ብቃቷን አስመስክራለች።
ይህ ጉዞ ከተራ አካላዊ ፈተናነት ባለፈ ለልዕልት ኬትሪን ጥልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን ከካንሰር ምርመራና ሕክምና በኋላ ሕይወትን በአዲስ መልክ ለመቃኘት እንዲሁም በሕክምናው ሂደት ከጎኗ ለነበረው የሆስፒታል ማኅበረሰብ ውለታን ለመመለስ የተጠቀመችበት ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጻለች።
ከባድ ሕመምን ተከትለው የሚመጡትን ስሜታዊ፣ አእምሯዊና ግላዊ ተግዳሮቶች ላይ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ያለመው ይህ የልዕልቷ አርአያነት ያለው ጥረት በማጠናቀቂያው ከፍታ ላይ በባለቤቷ ልዑል ዊሊያም፣ በልጆቿና በቅርብ የቤተሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ ልብ የሚነካ ታሪካዊ ወቅት ፈተናውን በስኬት ማጠናቀቋን ብቻ ሳይሆን በሂደቱ ውስጥ ያሳየችውን ጥንካሬ የማይበገር ጽናትና የምስጋና ልብ በጉልህ ያሳየ ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

ማይክል ካሪክ - የኦልድ ትራፎርድ የልብ ትርታ፣ በታላላቅ ኮከቦች ጥላ ስር ተደብቆ የኖረ ድንቅ ጥበበኛ
***********************
ስለ እርሱ ሲታሰብ አምስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችና የሻምፒዮንስ ሊጉ ድል ትዝ ሊሉን ይችላሉ። ነገር ግን እውነተኛው ማይክል ካሪክ የተገነባው በብዙዎች ዘንድ በማይታወቁ፣ ልብ በሚነኩና አስገራሚ በሆኑ ድብቅ ታሪኮች ውስጥ ነው።
ዛሬ የምናውቀው ካሪክ በኳስ ቁጥጥሩና አርቆ አሳቢነቱ የሚታወቅ የአማካይ ስፍራ ኮከብ ነው። ነገር ግን ወደ ዌስትሃም አካዳሚ በ15 ዓመቱ ሲቀላቀል ሕልሙ ሌላ ነበር፤ ያኔ የፊት መስመር አጥቂ ነበር።
ካሪክ ያደገው እንደ አላን ሺረር እና ፒተር ቤርድስሌይ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ባፈራው ታዋቂው የዎልሰንድ ቦይስ አካዳሚ ውስጥ ነው። የኒውካስል ዩናይትድ ደጋፊ የነበረ ቢሆንም፣ በ15 ዓመቱ ኒውካስልን ትቶ ወደ ዌስትሃም ዩናይትድ አቀና።
በ15 ዓመቱ ወደ ዌስትሃም አካዳሚ ሲቀላቀል የመስመር አጥቂ ነበር። በአንድ ጨዋታ ላይ ግን የመሃል አማካይ በመጥፋቱ በአጋጣሚ ቦታው ተቀይሮ የክፍለ ዘመኑ ብልህ አማካይ ሊሆን አጋጣሚው ተፈጠረ።
ካሪክ በቦታው መጀመሪያ ባይደሰትም ያለ እንቢታ ተጫወተ። ይህ አጋጣሚ ግን የእግር ኳስን ታሪኩን ቀየረች፤ አጥቂው ካሪክ ቀርቶ፣ የአውሮፓን መድረክ የሚገዛው ብልሁ አማካይ ተወለደ።
የካሪክ የጉርምስና ዕድሜ ደግሞ ሌላ አስገራሚ ፈተናን ይዞ መጣ። 17 ዓመቱ ላይ በአንድ ጊዜ 8 ኢንች ያህል ቁመት ጨመረ። በወቅቱ የነበረው ቀጭን ሰውነቱ ከቁመቱ ጋር ባለመመጣጠኑ ሜዳ ላይ መሮጥ እስኪያቅተው ተቸግሮ እንደነበር የቀድሞ አሰልጣኙ ሃሪ ሬድናፕ ያስታውሳሉ።
ብዙዎች የወደፊት መንገዱን ተስፋ ሲያጡበት፣ እርሱ ግን በትጋትና በጽናት ሰውነቱን ገነባ፤ በመጨረሻም ከሪዮ ፈርዲናንድ እና ፍራንክ ላምፓርድ ጋር የዌስትሃም ወርቃማ ትውልድ አካል ሆነ።
ካሪክ ገና በወጣትነቱ ጨዋታን የማንበብ ብቃቱ ድንቅ ነበር። ከዌስትሃም፣ ስዊንደን፣ በርሚንግሃም እና ቶተንሃም በኋላ በ2006 ታላቁን ማንችስተር ዩናይትድን ሲቀላቀል፣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በሮይ ኪን መልቀቅ የዛለውን የመሃል ሜዳ የሚያክምላቸውን የፈጠራ ሰው አገኙ።
በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ስቲቨን ጄራርድ እና ፍራንክ ላምፓርድ በችሎታ እንደማይደረስባቸው የመሀል ሜዳ ጣኦታት ይታዩ ነበር። ነገር ግን ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ልብ ውስጥ የነበረው እውነተኛው ንጉሥ ካሪክ ብቻ ነበር።
ፈርጉሰን በግል ማስታወሻቸው ላይ “...ላምፓርድና ጄራርድ ታላላቅ ስብዕና የነበራቸው ተጫዋቾች ናቸው፤ እውነተኛ ምርጥ ተጫዋቾች ግን አልነበሩም ፤ ካሪክ ግን የእግር ኳስ አዕምሮ ነበረው። የእንግሊዝ ሚዲያዎች ስለ እነርሱ አብዝተው በማወደስ ሲጮሁ፣ ካሪክ ግን በትህትናውና በአይናፋርነቱ ምክንያት በነርሱ ጥላ ስር ተደብቆ ተበደለ።” ሲሉ ነበር እንጋፋው አሰልጣኝ በብዕራችው ከትበው ስለካሪክ የመሰከሩት።
ማይክል ካሪክ ዛሬም ቢሆን ያው ነው - ዝምተኛ፣ አስተዋይና ልባም። የዩናይትድን ታላቅ ስም ለመታደግ በዋና አሰልጣኝነት ተሰይሟል። ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ዛሬም በዚያው ጥንቁቅ አዕምሮው የታላቁን ክለብ ታሪክ ለመጻፍ እየተዘጋጀ ነው።
ካሪክ እ.አ.አ በ2006 ከቶተንሃም ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ በ12 ወርቃማ ዓመታት 5 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የሻምፒዮንስ ሊግን እና የኤፍኤ ካፕን ጨምሮ በርካታ የክብር አክሊሎችን ደፍቷል።
ሆኖም ግን እንደ ፖል ስኮልስ ፣ ጄራርድ እና ላምፓርድ ባሉ ደማቅ ስሞች ጥላ ስር ተደብቆ አሳልፏል። ነገር ግን ሳይታይ የሚደምቅ የቡድኑ የጀርባ አጥንት ነበር።
በኦልድ ትራፎርድ የነበረው ስፍራ ከብዙ ተጫዋቾች የተለየ ነበር። ግቦችን ብዙ አያስቆጥርም፣ አስደናቂ ትርዒቶችንም አያሳይም፤ ነገር ግን ጨዋታው በእርሱ እግር ይጀምር፣ በእርሱም አዕምሮ ይመራ ነበር።
ከተጫዋችነት በኋላ በሞሪንሆ እና ሶልሻየር ስር በረዳትነት የሰራው ካሪክ በ2021 ለአጭር ጊዜ ዩናይትድን በጊዜያዊነት መርቶ ጥሩ ውጤት አሳይቷል።
በመቀጠል ሚድልስብሮን በዋና አሰልጣኝነት ይዞ አስደናቂ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ፣ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሩበን አሞሪም ስር የተንኮታኮተውን ማንችስተር ዩናይትድን ለመታደግ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ኦልትራፎርድ ሲደርስ ብዙዎች እምነት አልጣሉበትም ነበር።
ነገር ግን ዝምተኛው ካሪክ ፤ ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ታላቁን ክለብ ከመውረድ ውርደት ታድጎ ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ አበቃው።
ማይክል ካሪክ በተጫዋችነት ዘመኑ በማንቸስተር ዩናይትድ የቡድን አጋሮቹ "ሃቮክ" በሚል ቅጽል ስም ይጠሩት ነበር። ይህ ስም የመጣው በወቅቱ ተጫዋቾቹ በፒኤስፒ (PSP) ላይ "SOCOM US Navy SEALs: Fireteam Bravo" የተሰኘውን ታክቲካዊና ስውር የጦርነት ጨዋታ(ኮምፒዩተር ጌም) በጋራ ሲጫወቱ ከነበራቸው ትውስታ ነው።
ዌይን ሩኒ እንደተናገረው ይህ ጨዋታና የካሪክ መሪነት ቡድኑን አንድ ላይ ለማሰባሰብ ትልቅ ሚና ነበረው። ካሪክ በጨዋታው ላይ ብቻ ሳይሆን በሜዳው ላይም ያንን ስውር እና ጥንቁቅ ታክቲክ የሚተገብር መሪ ነበር።
ካሪክ ብዙ ጊዜ በሚያወሩ ኮከቦች መካከል በዝምታ የበራ ኮከብ ነበር። የጨዋታውን ስልተ-ምት በአንድ ንክኪ የሚቀይር፣ የቡድኑን ልብ በጸጥታ የሚያስመታ ረቂቅ የሙዚቃ መሪ።
እሱን የሚለየው ያሸነፋቸው ዋንጫዎች ብቻ አይደሉም፤ ያለ ጩኸት ታሪክ መፍጠር የቻለ ሰው መሆኑ ነው። አንዳንድ ኮከቦች በብርሃን ይደምቃሉ፤ ካሪክ ግን በዝምታው ታላቅ ሆነ።
ለዚህም ነው ዛሬም በኦልድ ትራፎርድ ታሪክ ውስጥ ከማይረሱ ስሞች አንዱ ሆኖ የሚጠራው፤ እየመጡ ያሉትን ብሩህ የአሰልጣኝነት ዘመናቱንም ያስናፈቀው።
በአዲስ የሺዋስ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #football

መንግሥት ያለ ምንም መዘግየት ወደ እውነተኛ ውይይት ይምጣ - ህወሓት
ህወሓት የአውሮፓ ህብረት ያወጣውን መግለጫ መቃወሙንና የሰላም ስምምነቱ አደጋ ላይ መውደቁን አስታወቀ
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን በቅርቡ በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ መሬት ላይ ያለውን እውነታ አያንጸባርቅም ሲል በጽኑ ተቃወመ።
የአውሮፓ ህብረት መግለጫ የተሳሳቱ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል በመግለጫው መሠረት ህወሓት ትይዩ ክልላዊ ምክር ቤት አቋቁሟል ተብሎ የቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓል።
ድርጅቱ በክልሉ በምርጫ የተመረጠው ብቸኛው የትግራይ ክልላዊ ምክር ቤት በቅርቡ ሥራ መጀመሩን ገልጾ ይህ ምክር ቤት ወደ ሥራ ከመመለሱ በፊት በከተሞችና በገጠር ማህበረሰቦች ዘንድ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት በነዋሪዎች በወረዳና በጣቢያ ምክር ቤቶች ሙሉ ድጋፍ ያገኘ መሆኑን አስታውቋል።
ህወሓት በጊዜያዊ አስተዳደሩ እና በፌዴራል መንግስቱ ላይ ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝሯል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የህዝቡን ጥቅም ማስጠበቅ ተስኖታል ያለው ድርጅቱ ይልቁንም እንደ ፌዴራል መንግስት አስፈጻሚ እየሰራ ነው ሲል ወቅሷል።
በተጨማሪም የሰላም ስምምነቱ (CoHA) ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ የፌዴራል መንግስት ስምምነቱን ለማዳከም እየሰራ መሆኑንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የስምምነቱን መሠረታዊ ሃሳቦች በተደጋጋሚ መካዳቸውን ገልጿል።
በዚህም ምክንያት የስምምነቱ ዋና ዋና ድንጋጌዎች ሳይፈጸሙ መቅረታቸውን በመግለጫው አመልክቷል።
ሰብአዊ ቀውስ እና የጸጥታ ስጋት
በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት መቀጠሉን የጠቀሰው መግለጫው በተለይም
* በነዳጅ እና በንግድ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ገደብ ከፍተኛ የዋጋ ንረትንና የኢኮኖሚ መገታት ማስከተሉን፣
* ተፈናቃዮች ያለ በቂ ድጋፍ የክረምቱን ዝናብ እየተጋፈጡ መሆናቸውን፣
* በክልሉ ዙሪያ እየተደረገ ያለው መጠነ-ሰፊ የወታደር ክምችት፣ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃቶችና የአየር ላይ ክትትሎች የጦርነት ስጋትን በከፍተኛ ደረጃ ማናራቸውን ዘርዝሯል።
ይህ ሁሉ እየሆነ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ በዝምታ መመረጡንና ፌዴራል መንግስቱ ግዴታውን እንዲወጣ ግፊት አላደረገም ሲል ኮንኗል።
ወታደራዊ የግዳጅ ምልመላ እና የወደፊት አቅጣጫ ላይ በሰፈረው የመግለጫው ማጠቃለያ ህወሓት አንድ ወገን ወታደራዊ ምልመላ እያካሄደ ነው ተብሎ የቀረበበትን ወቀሳ መሠረት ቢስ ነው ብሎታል።
ሆኖም የህልውና ስጋት ሲጋረጥ የትግራይ ባለስልጣናት ህዝቡን የመጠበቅና የመከላከል መብትና ኃላፊነት እንዳላቸው አስምሮበታል።
በመጨረሻም ድርጅቱ አሁንም ለሰላማዊ ውይይት ዝግጁ መሆኑንና የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ብቸኛው አማራጭ ፖለቲካዊ ውይይት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።
የአውሮፓ ህብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች የፌዴራል መንግስት ያለ ምንም መዘግየት ወደ እውነተኛ ውይይት እንዲመጣ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ጥሪ አቅርቧል።

4 months ago
"የምሁራን ዝምታ ያሳሰበኛል፤ አሁን ዳር የሚቆምበት ጊዜ አይደለም!"
- ፕ/ር መስፍን አርዓያ
#ethiopia | የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፣ አሁን ያለው የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ምሁራን ዳር ቆመው የሚመለከቱበት ጊዜ እንዳልሆነ በቁጭት ገለጹ።
የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በዋናነት የምሁራንን ዕውቀትና የሰላ ሀሳብ የሚፈልግ ቢሆንም፣ ከተወሰኑት በስተቀር አብዛኛው ምሁር በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ ከማድረግ ይልቅ "ዳር ሆኖ መመልከትን መምረጡ" በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ፣ የምሁራንን ሚና አስፈላጊነት ለማስረዳት ሲሉ ለምክክር ሂደቱ የሚያስፈልጉ 192 አማካሪዎችን ለመለየት የተጓዙበትን ፈታኝ ሂደት እንደ አብነት ጠቅሰዋል። ይህም ምሁራን ለሀገራዊ ጉዳዮች ያላቸውን ተሳትፎ ማጠናከር እንዳለባቸው ያሳያል ብለዋል።
ምሁራኑ በዝምታ ቢታቀቡም፣ በሌላ በኩል በየአካባቢው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጓቸው ጉዞዎች ግን ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎችን መመልከታቸውን ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ፦
የህዝብ አንድነት
ኢትዮጵያውያን በቋንቋና በባህል ልዩነቶች ቢኖሩም፣ በደግነት፣ በአዛኝነት እና በኢትዮጵያዊነት ስሜት የተሳሰሩ መሆናቸውን ታዝበዋል።
የህዝብ ተስፋና ቅሬታ
አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ሀገሪቱ ለገጠማት ችግር እንደ ዋነኛ ምንጭ የሚቆጥረው "ምሁራንንና የፖለቲካ ልሂቃንን" ነው። ህዝቡ መፍትሔውንም ከእነዚሁ አካላት እንደሚጠብቅ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የምክክር ሂደቱ አስፈላጊነት
ፕ/ር መስፍን አያይዘውም፣ ኢትዮጵያውያን በችግሮቻቸው ላይ በነፃነት ተወያይተው ለመፍትሔው ቀጠሮ መያዛቸው፣ ሂደቱ ለራሱ ታሪካዊና አስተማሪ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም፣ "ያለን አንድ ሀገር በመሆኑ" የምሁራኑን ዝምታ በመስበር ለዚህ ታሪካዊ ሒደት ስኬት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚገባውን አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ፕ/ር መስፍን
ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ

ዓለም በዝምታ ቢያዘግምም ኢትዮጵያ ምድርን እያከመች ነው!
********************
በዓለማችን ላይ አሳዛኝ እና ዐይን ያወጣ ኢፍትሐዊነት ቢኖር፣ ምድራችንን በበካይ ጋዝ እያፈኗት ያሉት ኃያላን ሀገራት ሲሆኑ፣ የጥፋታቸው ገፈት ቀማሽ ደግሞ ለብክለቱ ኢምንት የማያበረክቱ ደሃ ሀገራት መሆናቸው ነው።
አስቡት፤ አጠቃላይ የዓለማችንን የበካይ ጋዝ ልቀት ከ75 እስከ 80 በመቶ የሚያመነጩት ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው የቡድን 20 ሀገራት ናቸው።
በአንጻሩ፣ 54 ሀገራትን አቅፋ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት አፍሪካ ለዚህ በካይ ጋዝ ያላት አስተዋፅኦ ከ3 እስከ 4 በመቶ ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካውያን ለችግሩ ያበረከቱት አስተዋፅኦ እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም በድርቅ፣ በጎርፍ እና በሙቀት መጨመር ግንባር ቀደም ሰለባ ሆነው ዘመናትን አሳልፈዋል።
የፈረሱ ስምምነቶች እና የወረቀት ላይ ቃላት
የኢንዱስትሪ ባለቤቶች የሆኑት እነዚህ ኃያላን ሀገራት፣ ምድርን በካርቦን ጋዝ እያፈኗት መሆኑን አምነው፣ ልቀትን ለማስቀረትና ለችግሩ ሰለባ ለሆኑት ሀገራት ካሳ ለመክፈል በፓሪስ ታሪካዊ ስምምነት ፈረሙ።
ነገር ግን ዘመናት ተቆጠሩ፤ የወረቀት ላይ ቃላት ወደ ተግባር ሳይቀየሩ፣ ስምምነቶች የሚዲያ ፍጆታ ብቻ ሆነው ቀሩ። በኃያላኑ ቸልተኝነትና ቃል ማጠፍ ምክንያት ዓለማችን በድርቅ፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በበረሃማነት መስፋፋት እና ባልተጠበቀ የአየር ጸባይ መዛባት ክፉኛ መታመሷን ቀጥላለች።
ከንግግር ወደ ተግባር፤ የኢትዮጵያ አረንጓዴ አብዮት
ዓለም መፍትሔ አጥቶ በየስብሰባ አዳራሹ ሲባዝን፣ ቃሉን ሲያጥፍና ከንግግር ያለፈ አንዳች መፍትሔ ማምጣት ሲሳነው፣ ኢትዮጵያ ግን እጆቿን አጣጥፋ የኃያላኑን ምፅዋት አልጠበቀችም። ይልቁንም ተፈጥሮን እና አካባቢን ለማከም ቆርጣ በመነሳት ዓለምን ያስደመመ ተዓምራዊ የድል ትርክት መፃፍ ጀመረች።
ይህ ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዞ፣ በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በይፋ ሲበሰር፣ ገና በዕለቱ 350 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር በመትከል የህንድን የዓለም ክብረ-ወሰን በታላቅ ጀግንነት በመስበር ነበር የተጀመረው።
ዓለም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክፉኛ በተረበሸችበት በ2012 ዓ.ም እንኳን፣ ኢትዮጵያውያን ተስፋ ሳይቆርጡ 5 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ጽናታቸውን አሳይተዋል። በ2013 እና 2014 ዓ.ም ከ6 ነጥብ 8 እና 7 ነጥብ 2 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በምድሪቱ ላይ ሲያርፉ፣ እንደ ሐሮማያ ሐይቅ ያሉ ጠፍተው የነበሩ የውሃ አካላት ዳግም ህያው ሆነዋል።
የድል መዳረሻዎቻችን በዚህ አላበቁም፤ በ2015 ዓ.ም ለምግብ ዋስትና የሚሆኑ የፍራፍሬ ተክሎች ላይ በማተኮር 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተከሉ። በ2016 ዓ.ም ይህ አሃዝ ወደ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ሲሻገር፣ በአንድ ጀንበር ብቻ ከ600 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የራሳችንን ክብረ-ወሰን ደግመን ሰበርን።
በመጨረሻም በ2017 ዓ.ም ከ8 ቢሊዮን በላይ ዐሻራዎችን በማኖር፣ በሰባት ዓመታት ጉዞ ብቻ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያ በዓለም የደን ልማት መዝገብ ላይ ወደር የማይገኝለት የልዕልና ስፍራ ተቀመጠች። በየዓመቱ ከ25 እስከ 35 ሚሊዮን ዜጎች በፈቃደኝነት የሚሳተፉበት ይህ ግዙፍ ንቅናቄ፣ ብሔራዊ አንድነትን ያጠናከረ የአረንጓዴ ማዕበል ሆኗል።
ይህ የ7 ዓመታት ጉዞ ያመጣው ሥነ-ምህዳራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተዓምር ቃላት ከሚገልጹት በላይ ነው። አስቀድሞ ወደ 3 በመቶ አሽቆልቁሎ የነበረው የሀገራችን የደን ሽፋን፣ በማይታመን ፍጥነት አድጎ 23 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል።
የተተከሉት ችግኞች ከ80 እስከ 85 በመቶ በሚደርስ የፅድቀት ምጣኔ ጸድቀው፣ በአማካይ 64 ሚሊዮን በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች የሚያወጡትን በካይ ጋዝ ከከባቢ አየር ላይ በማጽዳት ዓለምን እየታደጉ ይገኛሉ።
መሬቱ ውሃን የመምጠጥ አቅሙ ከ16 ነጥብ 9 በመቶ ወደ 68 ነጥብ 9 በመቶ በከፍተኛ ደረጃ በማደጉ፣ የተፋሰስ ልማቱ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የሌሎች የኃይል ማመንጫ ግድቦችን የዕድሜ ጣሪያ ቢያንስ በ50 ዓመታት እንዲራዘም አድርጓል።
ከዚህም ባሻገር በተቋቋሙ ከ120 ሺህ በላይ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለሚበልጡ ዜጎች የስራ ዕድል ሲፈጠር፤ ተፈጥሮ በማገገሟም የሀገራችን የቡና ወጪ ንግድ ከ230 ሺህ ቶን ወደ 475 ሺህ ቶን በማደግ ትልቅ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ ነው።
በአጠቃላይ፣ ኃያላን ሀገራት ዛሬም ስለ አየር ንብረት ለውጥ ይነጋገራሉ፣ ስምምነት ያፈርሳሉ፣ ይከራከራሉ። ኢትዮጵያ ግን ንግግርን ወደ ተግባር ቀይራ፣ ቆስላ የነበረችውን ምድር በቢሊዮኖች አረንጓዴ ዐሻራ በተግባር እያከመች ነው።
አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ የመትከል ዘመቻ ብቻ ሳይሆን፣ ተፈጥሮን ማዳን፣ ማክሮ-ኢኮኖሚን መገንባት እና ትውልድን ማሻገር መሆኑን አሃዞች አፍ አውጥተው እየመሰከሩ ነው።
የዓለምን የሥነ-ምህዳር ህመም ለመፈወስ እውነተኛው እና ህያው መድኃኒት ከኢትዮጵያ ተገኝቷል፤ ወደ 50 ቢሊዮን የሚያልመው የድል ትርክታችንም በብልጽግና ጎዳና ላይ አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #climatechange #greenlegacy #climateresilience

⌚️ የሰከንድ ስሌት እና የ"ሩት ቢር" ናፍቆት ጥበብ በክንድ ላይ ስትመለክ!
በአሁኑ ዘመን የሰዓት አገልግሎት ጊዜን ማወቅ ብቻ አይደለም ጊዜውን የሚቆጥረው አካል ማንነት፣ የውበት ምርጫ እና ምናልባትም "የኪስ አቅም" ማሳያ ጭምር እንጂ።
ሰሞኑን በዲጂታሉ ዓለም የብዙዎችን አይን የሳበውና መነጋገሪያ የሆነው የስዊዘርላንዶች እጅግ ረቂቅ የእጅ ጥበብ ውጤት የሆነው Rolex GMT-Master II "Root Beer"ሰዓት ነው።
ይህ ሰዓት እንዲሁ ተራ የሰከንድ መቁጠሪያ አይደለም በስፖርታዊ ጥንካሬው እና በቅንጦት ውበቱ የብዙዎችን ልብ የሰረቀ የሰዓት አምራቾች ቁንጮ ነው።
የ"ሩት ቢር" ቀለም እና የቅንጦት ጥበብ
ይህ ሞዴል "Root Beer" የሚለውን ስም ያገኘው ከባህላዊው መጠጥ ቀለም ጋር በሚመሳሰለው ከሴራሚክ (Cerachrom) ከተሰራው ቡናማ እና ጥቁር ጠርዙ የተነሳ ነው።
ሰዓቱ የትዕግስት፣ የጥራት እና የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ውጤት ነው።
* *ሁለት ዓለም በአንድ ክንድ ላይ**
ይህ ሰዓት የተሰራው በተለይ በተደጋጋሚ ለሚጓዙ ሰዎች በመሆኑ በአንድ ጊዜ የሶስት የተለያዩ ሀገራትን የሰዓት ቀጠናዎች መቁጠር ይችላል።
የEverose ወርቅ እና የብረት ቅይጥ
ሮሌክስ የራሱን የፈጠራ መብት የተጠቀመበትን የሮዝ ወርቅ (Everose Gold) እና ልዩ ብረትን አቀናጅቶ የሰራው በመሆኑ፣ በሩቅ ሲመለከቱት እንኳ ማራኪነቱ አይን ይበላል።
ይህንን ሰዓት ልዩ የሚያደርገው ውበቱ ብቻ አይደለም ወደ ገበያው ሲመጣ የሚጠይቀው አስገራሚ የገንዘብ መጠን ጭምር ነው።
በሮሌክስ መደብሮች ውስጥ ሰዓቱን ለማግኘት እጅግ ረጅም የጥበቃ ዝርዝር (Waiting List) ያለ ሲሆን በዓለም አቀፍ የግራጫ ገበያ (Grey Market) ላይ ደግሞ ዋጋው እስከ አስር ሺዎች አሜሪካ ዶላር ድረስ ይተመናል።
የዚህን ሰዓት ዋጋ ወደ እኛ ሀገር የመግዛት አቅም እና የወርሃዊ ደሞዝ ስሌት ስንመዝነው ነገሩ ሌላ ታሪክ ይወልዳል።
በአንድ በኩል ጥበብን የሚያደንቅ አይን እንዲህ ያለውን ውድ ዕቃ በክንድ ላይ ማየቱ "የእውነትም ያምራል!" ሊያስብል ይችላል።
በሌላ በኩል ግን የኑሮው ፈተና እና የኪስ አቅሙ ሁኔታ ፈታኝ በሆነበት ምድር ላይ እንዲህ ያሉ የቅንጦት ቁንጮዎች በአደባባይ ሲታዩ "የቁጥሮቹ ስሌት እንዴት ይሆን?" የሚል የብዙዎችን የማወቅ ጉጉትና የትዝብት ጥያቄ መቀስቀሱ አልቀረም።
ታዲያ ጊዜው የቴክኖሎጂ ነውና ሰዓቱ ራሱ በአንድ ጊዜ የሶስት የተለያየ ሀገር ሰዓቶችን እንደሚቆጥረው ሁሉ ሰዓቱን የሚያዩ ሰዎችም በአንድ ጊዜ ሶስት የተለያየ ሀሳቦችን ቢያሰላስሉ አይገርምም አንደኛው የሰዓቱን ውበት ያደንቃል፣ ሁለተኛው ዋጋውን ሰምቶ ይደመማል፣ ሶስተኛው ደግሞ "ይህንን የመሰለ ወርቅ በደሞዝ ወይንስ በምን?" ብሎ በዝምታ ይተክዛል።
ያም ሆነ ይህ ሰዓቱ ግን አሁንም ስራውን በትክክል እየሰራ ነው ሰከንዶችን ያለ ማቋረጥ ይቆጥራል ጊዜ ደግሞ ሁሉንም ነገር ..

ሁቲዎች በቀይ ባሕር ላይ የእስራኤል የባሕር ጉዞን ‹‹ሙሉ በሙሉ›› ማገዳቸውን አስታወቁ
የየመኑ ሁቲ በቀይ ባሕር በሚደረግ በእስራኤል የባሕር ጉዞ ላይ ‹‹ፍፁም እና ሙሉ እገዳ›› እንደሚጥል ያስታወቀ ሲሆን፤ በውሃ መንገዱ ላይ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች ዳግም ኢላማ እንደሚደረጉ ገልጿል።
ቡድኑ ባወጣው መግለጫ፤ የእስራኤል ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረ የሚሳዔል ጥቃት ማድረሱን ገልጾ፣ ‹‹የሚሳዔል ጥቃቶቹ የተፈለገውን ግብ በዝርዝር መትተዋል››ብሏል።
በእስራኤል ላይ የተፈፀመው የሚሳዔል ጥቃት እስራኤል በኢራን፣ በፍልስጤም፣ በሊባኖስ፣ በኢራቅ እና በየመን ለፈፀመችው ‹‹ወረራ›› ምላሽ መሆኑን ቡድኑ ገልጿል።
ሁቲ ‹‹በሕዝባችን እና በፍልስጤም፣ በጋዛ፣ በኢራን፣ በሊባኖስ እና በኢራቅ ባሉ የትግል አጋሮቻችን ላይ የተጫነውን ፍትሃዊ ያልሆነ ከበባ እያየን በዝምታ አንቀመጥም›› ሲል ገልጿል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም በዓይነቱ ለየት ያለ እና በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ የአርሰናል ደጋፊዎችን ያሰባሰበ ደማቅ የድል ማክበር እና የሙዚቃ ድግስ ተካሂዷል። ይሁን እንጂ ይህን ያህል ግዙፍ ህዝባዊ ዝግጅት መዲናዋን በቀይ እና ነጭ ቀለማት ቢያደምቃትም የእንግሊዙ ክለብ አርሰናል በይፋዊ ድረ-ገጹም ሆነ በሚሊዮኖች በሚከተሉት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ለኢትዮጵያውያን ደጋፊዎቹ አንዳችም እውቅናም ሆነ አጭር የምስጋና ቃል ሳይሰጥ በዝምታ ማለፉ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ የአርሰናል ደጋፊዎች ማህበር እና አፍቃሪዎቹ፣ ታዋቂ ድምጻውያን በተገኙበት እና ከፍተኛ ወጪ በፈሰሰበት ዝግጅት የክለባቸውን ድል በከፍተኛ ድምቀት አክብረዋል። የዝግጅቱ ድባብ፣ የደጋፊው ስሜት፣ እና የተዘመረው መዝሙር በእንግሊዝ አደባባዮች ከሚታየው ድባብ በምንም የማያንስ፣ አልፎ ተርፎም በልዩ ኢትዮጵያዊ ስሜት የታጀበ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የደጋፊዎች ድካም፣ ጊዜ፣ ገንዘብ እና ልባዊ ፍቅር የአርሰናልን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ትኩረት ሊስብ አልቻለም።
የዘመናዊ እግር ኳስ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተንታኞች ይህንን የአርሰናልን ዝምታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለአፍሪካውያን ደጋፊዎች ያላቸውን የጥቅም ብቻ አመለካከት የሚያሳይ ጥብቅ ማሳያ ነው ሲሉ ይተቹታል። አርሰናልን ጨምሮ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ከአፍሪካ የቴሌቪዥን ስርጭት መብት ዕይታ እና ከማሊያ ሽያጭ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያፍሳሉ። ክለቡ እንደ ሩዋንዳን ጎብኙ ካሉ ከፍተኛ የገንዘብ ክፍያ ከሚያስገኙ የንግድ ስምምነቶች ጋር በተያያዘ ለአፍሪካ ሀገራት ሽፋን ሲሰጥ ቢታይም፣ እንደ ኢትዮጵያ ካሉ ሀገራት በደጋፊው አነሳሽነት የሚመነጨውን እውነተኛ እና ህዝባዊ ፍቅር ግን ችላ ማለቱ፣ ክለቡ የንግድ ትርፍን እንጂ እውነተኛ የስፖርት ቤተሰባዊነትን እንደማያበረታታ ያጋልጣል። በእንግሊዝ ወይም በአሜሪካ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የተሰበሰቡበትን ዝግጅት በድረ-ገጻቸው የሚያሞካሹት እነዚህ ክለቦች፣ በአፍሪካ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ስታዲየም ሲሞላ ለማየት አለመፈለጋቸው በደጋፊው ዘንድ የንቀት ስሜት ፈጥሯል።
ይህንን የክለቡን ዝምታ ተከትሎ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ኢትዮጵያውያን ደጋፊዎች እና የስፖርት ቤተሰቡ ከባድ ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ብዙዎች ሁኔታውን ያልተመለሰ ፍቅር ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ አርሰናል እኛን የሚፈልገው ለቴሌቪዥን ዕይታ እና ለገንዘባችን ብቻ ነው እንጂ ለስሜታችን እና ለድካማችን ምንም አይነት ክብር የለውም የሚሉ ሀሳቦች በስፋት ተንጸባርቀዋል። በተጨማሪም ለንደን ላይ አምስት ሺህ ሰው ቢሰበሰብ ሰበር ዜና የሚያደርገው ክለብ፣ አዲስ አበባ ላይ ስታዲየም የሞላ ህዝብን ለማመስገን አንዲት አጭር መልዕክት ሊነፍገው አይገባም ነበር በማለት ቁጭታቸውን ገልጸዋል። በርካታ የስፖርት ጋዜጠኞችም በበኩላቸው፣ አፍሪካውያን ደጋፊዎች የውጭ ክለቦችን ከማምለክ ወጥተው ይህንን ግዙፍ አቅም፣ ጉልበት እና ፋይናንስ ወደሚያከብራቸው እና የራሳቸው ወደሆነው የሀገር ውስጥ ሊግ ቢያዞሩት ለሀገር ኢኮኖሚም ሆነ ለእግር ኳስ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ላይ ናቸው።
ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የታየው ደማቅ ዝግጅት የኢትዮጵያውያንን ለእግር ኳስ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር እና የማደራጀት አቅም በድጋሚ ያረጋገጠ ቢሆንም፣ የአርሰናል ክለብ የሰጠው ቀዝቃዛ ምላሽ ግን አፍሪካውያን ደጋፊዎች ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ክለቦች ጋር ስላላቸው የአንድዮሽ ትስስር በድጋሚ ቆም ብለው እንዲያስቡ በር የከፈተ አጋጣሚ ሆኗል። ፍቅርን በንቀት የመለሰው የአርሰናል እርምጃ፣ የአውሮፓ እግር ኳስ ገበያ አፍሪካን እንደ ሸማች እንጂ እንደ ባለድርሻ እንደማይቆጥራት በድጋሚ ያረጋገጠ የታሪክ ማስታወሻ ሆኖ ያልፋል።

የተገለጠው እውነታ
በ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
በምሥራቃዊው ኢትዮጵያ ይልቁንም በሐረር፣ አርሲና ባሌ አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርጎና አቅዶ ክርስቲያኖችን የሚገድል፣ የሚያፈናቅል እና የሚያሳድድ የአክራሪ ክንፍ መኖሩ ተደጋግሞ ሲነገር ኖሯል። ይህ አካል ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ከተተካበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛዋንም የለውጥ፣ የምርጫ እና የመሳሰሉትን የጫና ወቅቶች ጠብቆ አደጋ ያላደረሰበት ጊዜ የለም።
ከተቻለ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀምና በየዘመኑ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም እና ለሚገድላቸው አካላት ከወቅቱ ፖለቲካ አንጻር የሚስማማ ታርጋ በመስጠት የሚቻለውን ያህል ይገድላል፣ ያፈናቅላል፣ ያሳድዳል።
ይህ የተገለጠ እውነት ነው። ተደጋግሞም ተነግሯል፣ ተገልጿል። ሆኖም እንደዚህ ዘመን እንደ ልቡ ክርስቲያኖችን የሚያጸዳበት ስለመኖሩ ግን አላውቅም። በእኔ እምነት ኢህአዴግ ከመጣበት ጀምሮ የተፈጸሙት ተደምረው በዚህ ዓመት ብቻ የፈጸመውን የመግደልና የማሳደድ ተግባር የሚያክሉ አይመስለኝም። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም መንግሥታዊ ተቋም ሐዘኔታ ሲያሳዩ፣ አንድም አካል ተጠያቂ ሲደረግ ዓይተንም ሰምተንም አናውቅም።
ይህም የተገለጠ እውነት ነው።
ምንም ቢሆን፣ ማንም ቢሆኑ ይህ ሁሉ መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች ደግሞም ዜጎች ነበሩ። በደቡብ አፍሪካ ላለው ከሀገራችን ውጡ የሚል ዐመጽ ዜጎቹን ለመከላከል መንግሥት በኢንባሲው በኩል እየሠራ እንደሆነ የሚገልጽ ዜና ከሰማንና ለዚህኛው መንግሥት በዝምታ የሚያልፍ ከሆነ ድርጊቱን የሚፈጽመው እርሱም ጭምር ነው የሚለውን ወቀሳ እውነት ነው ብሎ በአዎንታ እንደተቀበለው ለመረዳት ግዴታችን ጭምር ይሆናል። ይህ በእውነት ከልብ ያሳዝናል።
አንድ የተረጋገጠና የትገለጠ እውነት ደግሞ አለ። የሰው ደም በከንቱ ፈስሶ አይቀርም። እግዚአብሔር የሚባል ተበቃይ አምላክ አለና። ለንስሐ ጊዜ ቢሰጥም "በቀል የእኔ ነው" ያለውና "ከኦሪትና ከነቢያት አንዲት ቃል ከምታልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል" ያለው አምላክ ቃሉ የታመነ ነውና አይቀርም። እርሱ ሁላችንንም ይቅር ይበለን፣ የመከራውንም ወቅት አሳልፎ ለሰላምና ለፍቅር ያብቃን።

5 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በ"ስትሬት አውታ ኮምፕተን" እና "ቤተር ኮል ሶል" በተሰኙ ታዋቂ ፊልሞች እና ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ ባሳየው አስደናቂ የትወና ብቃት የምናውቀው የ64 ዓመቱ አንጋፋ ተዋናይ ራስል አንድሪውስ፣ ያልተጠበቀ እና ልብ የሚሰብር የህይወት ፈተና ገጥሞታል። ከካሜራ ጀርባ በዝምታ ሲያሰቃየው የነበረውን ይህንን ከባድ ሚስጥር፣ ቅዳሜ ሜይ 16 በሲኤንኤን 'ዘ ስቶሪ ኢዝ ዊዝ ኤሌክስ ማይክልሰን' ፕሮግራም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአደባባይ ይፋ አድርጓል። ከጎኑ እጮኛው ተዋናይት ኤሪካ ታዜል ተቀምጣ ነበር። ራስል በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ አድናቂዎቹ "እኔ ከኤኤልኤስ በሽታ ጋር የምኖር ሰው ነኝ" ሲል ያልተጠበቀውን መርዶ አረዳ።
ይህ ኤኤልኤስ ወይም በሌላ ስሙ 'ሉ ጌህሪግስ' ተብሎ የሚጠራው በሽታ፣ በአንጎል እና በአከርካሪ አጥንት ውስጥ ያሉ የነርቭ ሴሎችን በማጥፋት የጡንቻ መድከምን፣ የንግግር መለዋወጥን እና በመጨረሻም ሙሉ የሰውነት ሽባነትን የሚያስከትል አደገኛ እና ፈውስ የሌለው የነርቭ በሽታ ነው። የጡንቻ ዲስትሮፊ ማህበር እንደሚለው፣ ታማሚዎች በሽታው እንዳለባቸው ከታወቀ በኋላ ብዙውን ጊዜ ከሶስት እስከ አምስት ዓመት ብቻ የመኖር እድል ቢኖራቸውም፣ አንዳንዶች ግን ለአስርት ዓመታት ሊቆዩ ይችላሉ።
ነገሩ የጀመረው እጅግ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ነበር። ራስል በኮቪድ ወረርሽኝ እና የሆሊውድ ተዋንያን የስራ ማቆም አድማ በተደራረቡበት በዚያ አስጨናቂ ወቅት፣ ድንገተኛ የስትሮክ በሽታ የመታው ወይም በአንገቱ አካባቢ ነርቭ የተቆነጠጠበት መስሎት ነበር። ማታ ማታ ብርጭቆዎች ከእጁ ማምለጥ እና መውደቅ ጀመሩ፤ በእጁ ላይ ያልተለመደ እና የሚሮጥ ስሜት ይሰማው ነበር። እጮኛው ኤሪካ ታዜል ይህን ጊዜ ስታስታውስ፣ የመዋኛ ገንዳውን ለማጽዳት የሚወስድበት ጊዜ መርዘሙን እና የአረማመድ ስልቱ መቀየሩን አስተውላ "በእርግጠኝነት የሆነ ችግር አለ" ብላ መጨነቅ እንደጀመረች ትናገራለች።
በታሪካዊው የስራ ማቆም አድማ ምክንያት የህክምና መድን ሽፋን አጥቶ የነበረው ራስል፣ መድኑን መልሶ እንዳገኘ ወደ ሀኪም ሲሄድ በ15 ደቂቃ ውስጥ ወደ ነርቭ ስፔሻሊስት እንዲመራ ተደረገ። ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ የተሰጠው የህክምና ውጤት አስደንጋጭ ነበር፤ በሽታው ALS መሆኑ ተረጋገጠ። ሆኖም ይህ አስደንጋጭ ዜና የኤሪካን ፍቅር አላናወጠውም። መፍትሄ ወደሌለው የህመም ጉዞ እየገቡ መሆኑን እያወቀች፣ "ቢያንስ አሁን ምን እንደሆነ አውቀናል፤ አሁንም ሚስትህ መሆን እፈልጋለሁ" በማለት እውነተኛ እና ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ በተግባር አሳይታዋለች። አሁን ኤሪካ የህይወት አጋሩ ብቻ ሳትሆን፣ ዋነኛ አስታማሚውም ሆናለች። ራስልም ይህንን ፈታኝ ጊዜ ከ'ኤኤልኤስ ኔትወርክ' ከተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በተገኘው አስገራሚ ቤተሰባዊ ፍቅር እና እንክብካቤ ታግዞ እያሳለፈው መሆኑን በስሜት ተናግሯል።

Comments