9 days ago
#ትልቅሀገር_ትልቅሕዝብ_ታላቅርዕይ
የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስትራቴጂያዊ ትብብር ጉዞ
********************
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በደም፣ በቋንቋ፣ በባህል እና በታሪክ የተሣሠሩ የቅርብ ጎረቤቶች ናቸው። ከሰባት ዓመታት በፊት በአካባቢው የነበረው ጂኦ-ፖለቲካዊ ጫና እና የተወሳሰቡ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ግንኙነታቸውን በጥላ ሥር አድርገውት ቢቆይም፣ ዛሬ ሁለቱ ሀገራት ከጥርጣሬ እና ከውጥረት አዙሪት በመውጣት፣ በጋራ ብልጽግና እና በመተማመን ላይ የተመሠረተ አዲስ እና ታሪካዊ ምዕራፍ መጀመራቸውን በተግባር እያሳዩ ነው።
ይህ ለውጥ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ስትከተለው በቆየችው ቅድሚያ ለጎረቤት ሀገር ስትራቴጂያዊ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የመጣ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "የጎረቤት ሀገር ሰላም የራሳችን ሰላም ነው" በሚል መርሕ፣ የሶማሊያን የመልሶ ግንባታ ጉዞ የኢትዮጵያ የልማት አጋርነት አካል አድርገውታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንትን በዓለ ሢመት ላይ በመገኘት "የሶማሊያን ግንባታ ለመደገፍ እዚህ ተገኝቻለሁ፤ ጉዟችሁን ስትጀምሩ ከጎናችሁ ነን" ማለታቸው፣ ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ያላቸውን ጥልቅ መተሣሠር ዳግም ያረጋገጠ ነበር።
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሙሐመድ በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ የሰጡት አቋም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አጠናክሮታል። ፕሬዚዳንቱ ግድቡን በጎበኙበት ወቅት፣ "ግድቡ ማንንም አይጎዳም፤ የኢትዮጵያ ልማት የሶማሊያም ልማት ነው" በማለት የቀጣናዊ መተሳሰርን አስፈላጊነት በይፋ መስክረዋል።
አሁን ላይ መሪዎቹ የደኅንነት ትብብርን በማጠናከር ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማምተዋል። ከዚህ ባሻገር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በመሠረተ ልማት ትሥሥር ላይ በትኩረት በመሥራት፣ ለቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ልዕልና መሠረት የሚጥል ስትራቴጂያዊ አጋርነት ፈጥረዋል።
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ በትብብር መሥራት ለቀጣናው ሰላም ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከሯ፣ የጋራ የኢኮኖሚ ጥቅሞችን ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ቀጣናውን ከድህነት እና ከግጭት አዙሪት በማውጣት ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ታሪካዊ ውጥረቶችን በመሻገር፣ ልዩነቶቻቸውን በውይይት በመፍታት የቅርብ አጋሮች ሆነዋል።
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ያደረጓቸው ጉብኝቶች፣ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት በመፍጠር ረገድ የነበሩትን መሰናክሎች እየናደ፣ ለሁለቱ ሕዝቦች ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቅ የጋራ የልማት ምዕራፍ ጅማሮ ሆኗል።
በላሉ ኢታላ
#ethiopia #ebc #somalia #ethiopiasomalia #strategicpartnership #regionalstability #diplomacy #gerd #hornofafrica

7 months ago
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ 13ኛው በዓለ ሢመት ዛሬ በድምቀት ይከበራል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ ወደ መንበረ ፓትርያርክነቱ የመጡበት 13ኛው ዓመት የሢመት በዓል ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
በአዲስ አበባ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚከናወነው በዚህ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ፦
* ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
* የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣
* ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣
* ዲፕሎማቶችና በርካታ ምዕመናን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል
በዕለቱ የቅዱስነታቸውን የ13 ዓመታት ጉዞና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊና መንፈሳዊ አገልግሎቶች ላይ ያከናወኗቸው ተግባራት የሚዘከሩ ሲሆን፣ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችም ይከናወናሉ።
ቅዱስነታቸው በ2005 ዓ.ም ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አቡነ_ማትያስ #በዓለ_ሢመት #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን #መንበረ_ጸባዖት #eotc #abunemathias #ethiopia

Comments