2 months ago
ትራኦሬ ከኤለን መስክ‼️
ኢብራሂም ትራኦሬ በቡርኪና ፋሶ ውስጥ ከኤሎን መስክ ጋር የተገናኙትን የንግድ ኩባንያዎችን በሙሉ አግዷል።
ይህ የሆነው በቴክኖሎጂ ዘርፉ በጣም ትርፋማ የሆነው እና የአለም ቁጥር አንድ ባለሃብት ኢሎን መስክ በደቡብ አፍሪካ ለስታርሊንክ ፍቃድ አለማግኘቱን ተከትሎ "ፍቃድ ያልተሰጠኝ ጥቁር ስላልሆንኩ ነው" የሚል ስድብ አዘል ንግግር በማድረጉ ነው።
የቡርኪናፋሶው መሪ ትራኦሬ እንዲህ ብሏል፣ "ፍትሃዊ ጨዋታ ነው፣የትኛውንም የአፍሪካን ሀገር እየተሳደቡ ንግድዎን በቡርኪና ፋሶ እንዲቀጥል መጠበቅ አይቻልም። ይህ አዲስ አፍሪካ ነው፣የለመድከው አፍሪካ አይደለችም።" ብለዋል።
seledadotio

5 months ago
🛰️ ኤሎን መስክ በደቡብ አፍሪካን ተበደልኩ አለ
#ethiopia | የዓለማችን ቁንጮ ባለሀብት ኤሎን መስክ፣ የሳተላይት ኢንተርኔት ኩባንያው ስታርሊንክ (Starlink) በትውልድ ሀገሩ ደቡብ አፍሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ መከልከሉን "ዘረኝነትን መሠረት ያደረገ ውሳኔ" ሲል በድጋሚ ነቀፈ።
⛔ የእገዳው መንስኤ ምንድነው?
ስታርሊንክ በደቡብ አፍሪካ የሥራ ፈቃድ የተከለከለው በአገሪቱ ካለው የቴሌኮም ሕግ ጋር ባለመስማማቱ ነው። ሕጉ ማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት፦
* 30 በመቶ የሚሆነውን የባለቤትነት ድርሻ ቀደም ሲል በነበረው የዘረኛ (Apartheid) ሥርዓት ለተበደሉ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን መስጠት እንዳለበት ይደነግጋል።
ኤሎን መስክ ይህንን መስፈርት "የቆዳ ቀለምን መሠረት ያደረገ የኢኮኖሚ ፖሊሲ" ሲል የጠራው ሲሆን፣ ኩባንያው የባለቤትነት ድርሻ ከመስጠት ይልቅ 121.8 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ እና ለ5,000 የገጠር ትምህርት ቤቶች ነፃ ኢንተርኔት ለመስጠት ያቀረበው አማራጭ በመንግሥት ውድቅ ተደርጓል።
🌍 በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያለው ሁኔታ
ደቡብ አፍሪካ በሩን ብትዘጋም፣ ስታርሊንክ በአህጉሪቱ እያደረገ ያለው መስፋፋት ግን አልተገታም። ማስክ እንዳስታወቀው ኩባንያው በሚከተሉት ሀገራት የሥራ ፈቃድ አግኝቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፦
* ናሚቢያ፣ ካሜሩን፣ ሌሴቶ፣ ሶማሊያ እና ኮንጎ።
💡 "በሳምንታት ውስጥ ማዳረስ እንችላለን"
መንግሥት መጠነኛ የአሠራር ማሻሻያ ካደረገ ስታርሊንክ በሳምንታት ውስጥ መላውን ደቡብ አፍሪካ የማዳረስ አቅም እንዳለው ማስክ ገልጿል። ይሁን እንጂ የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት በሕጉ ላይ ያላቸው አቋም እስካሁን አልተለወጠም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኤሎንመስክ #ስታርሊንክ #ደቡብአፍሪካ #ኢንተርኔት #ቴክኖሎጂ #starlink #elonmusk #southafrica #technews #africaconnect

በኢራን የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ፤ በመንግስት ደጋፊዎች የሚመራ ግዙፍ ሰልፍም ተካሂዷል
ለተከታታይ ሳምንታት በኢራን የተለያዩ ከተሞች ሲካሄድ የቆየው የፀረ-መንግስት ተቃውሞ እየቀነሰ መምጣቱን ተንታኞች ገለጹ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በመዲናዋ ቴህራንን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች መንግስትን የሚደግፉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተሳተፉበት መጠነ-ሰፊ ሰልፍ ተካሂዷል።
የተቃውሞው መቀዝቀዝ እና የኢንተርኔት እገዳ
የአሜሪካው የጥናት ተቋም (Institute for the Study of War) ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ካለፈው እሁድ (ጥር3 ቀን) ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ማገዱ እና የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት ኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ የጣለው ጥብቅ ቁጥጥር መሆኑ ተመልክቷል።
የመንግስት ደጋፊዎች አፀፋዊ ሰልፍ
የአልጀዚራ ዘጋቢ ከቴህራን እንደዘገበው፣ በመንግስት ጥሪ መሰረት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት ለመንግስት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። በተለይም በታዋቂው የኤንገላብ አደባባይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈበትና "ፀረ-ሽብር" የተሰኘ ሰልፍ መካሄዱ ታውቋል።
የመንግስት አቋምና የወደፊት እርምጃ
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በሰጡት መግለጫ፣ እየተካሄደ ያለው ግጭት "ተቃውሞ" ሳይሆን በሀገር ላይ የታወጀ "የሽብር ጦርነት" ነው ሲሉ ገልጸውታል። ሚኒስትሩ አክለውም፣ ታጣቂዎች በመንግስት ተቋማትና በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የሚያረጋግጥ የድምፅ ማስረጃ በእጃቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በኳታር የሚገኘው የጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ ተንታኝ መህራን ካምራቫ በበኩላቸው፣ "መንግስት ኢንተርኔቱን የዘጋው ህዝባዊ ስብሰባዎችን ለመበተን ነበር፤ አሁን ሁኔታው በቁጥጥር ስር መዋሉን ለማሳየት ኢንተርኔቱን መልሶ ለመልቀቅ እየተዘጋጀ ነው" ብለዋል።
ይህም መንግስት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ "ሁኔታውን ተቆጣጥሬያለሁ" የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የያዘው ስልት ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ውጥረት በመንግስት ጠንካራ እርምጃ እና በደጋፊዎች ሰልፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንዳላት ትራምፕ ገለጹ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት እሁድ ምሽት በሰጡት መግለጫ የኢራን ገዢዎች ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውን በስልክ እንደገለጹላቸው አስታውቀዋል።
ይህ መግለጫ የወጣው በኢራን ውስጥ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በከፍተኛ ሁኔታ እየተፋፋመ ባለበት ወቅት ነው።
የድርድር ጥያቄ፦ ትራምፕ በኤር ፎርስ ዋን ላይ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ "ኢራን መደራደር ትፈልጋለች" ብለዋል። ይሁን እንጂ ስለ ድርድሩ ዝርዝር ሁኔታ የገለጹት ነገር የለም።
የሬዛ ፓህላቪ ጥሪ፦ የኢራን የቀድሞው ሻህ ልጅ ሬዛ ፓህላቪ ለትራምፕ ባስተላለፉት መልዕክት "ኢራንን እንደገና ታላቅ አድርጓት" በማለት አሜሪካ ተቃዋሚዎችን እንድትደግፍ ጠይቀዋል።
የኢንተርኔት እገዳ እና ኢሎን ማስክ፦ በኢራን ውስጥ ኢንተርኔት በከፊል በመዘጋቱ፣ ትራምፕ ከቢሊየነሩ ኢሎን ማስክ ጋር በመነጋገር የስታርሊንክ ሳተላይት ኢንተርኔት ለኢራን ተቃዋሚዎች እንዲቀርብ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
ከባድ መስዋዕትነት፦ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች (Hrana) እንደሚሉት ከሆነ እስካሁን በነበረው ግጭት ከ544 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ10,000 በላይ ታሳሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ስታርሊንክ ለቬንዙዌላውያን የነፃ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በቬንዙዌላ እየታየ ያለውን ድራማዊ የፖለቲካ ለውጥ ተከትሎ ታዋቂው ቢሊየነር ኢሎን ማስክ የጠፈር ምርምር ተቋሙ ስፔስ ኤክስ (SpaceX) በስታርሊንክ ሳተላይቶች አማካኝነት ለሀገሪቱ ህዝብ የነፃ ኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ። ይህ ውሳኔ የተሰማው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ሀገሪቱ በከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ባለችበት ወቅት ነው።
በሀገሪቱ ሊከሰት የሚችለውን የመረጃ እገዳ፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እና የኢንተርኔት መዘጋት ስጋት ለመቀነስ ስታርሊንክ የሳተላይት ግንኙነትን ክፍት ማድረጉ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል። ይህ አገልግሎት ዜጎች ከቤተሰቦቻቸውና ከውጭው ዓለም ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዳይቋረጥ የሚያግዝ ሲሆን የግል የቴክኖሎጂ ተቋማት በዓለም አቀፍ ጂኦ-ፖለቲካ ላይ ያላቸውን እያደገ የመጣ ተፅዕኖ በግልጽ ያሳየ ክስተት ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት መረጃ ማግኘት ለዜጎች እንደ ቅንጦት ሳይሆን እንደ መብትና የጥንካሬ ምንጭ ተደርጎ የተወሰደ ሲሆን የግል ኩባንያዎች እንዲህ ባሉ ዓለም አቀፍ ግጭቶች ወቅት ጣልቃ መግባታቸው የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። የስታርሊንክ እርምጃ በቬንዙዌላ ያለውን የመረጃ ፍሰት ነፃ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
በኤሎን ማስክ ባለቤትነት የሚተዳደረው የሳተላይት የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ስታርሊንክ ለቬንዙዌላ ሕዝብ ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።
ቢቢሲ እንደዘገበው ከሆነ፣ ይህ ውሳኔ የተላለፈው በቅርቡ አሜሪካ በቬንዙዌላ ካካሄደችው ከፍተኛ የወታደራዊ ዘመቻ እንዲሁም ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ኒው ዮርክ ከተወሰዱ በኋላ ነው።

7 months ago
ኤሎን መስክ የፀሐይን ብርሃን በሳተላይት ለመቆጣጠር ሐሳብ አቀረቡ
የቴክኖሎጂ ባለጸጋውና የ SpaceX ኃላፊ የሆኑት ኤሎን መስክ፣ ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የሚያስችል አወዛጋቢ ሐሳብ አቅርበዋል።
ይህ ሐሳብ የፀሐይ ጨረር አስተዳደር በመባል ከሚታወቀው የጂኦኢንጂነሪንግ ስትራቴጂ አንዱ ሲሆን፣ በሳተላይቶች አማካኝነት ወደ ምድር የሚደርሰውን የፀሐይ ብርሃን መጠን መቆጣጠርን ያካትታል።
ሐሳቡ በህዋ ላይ የሚያንጸባርቁ መስተዋቶችን ወይም አንጸባራቂ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የፀሐይን ብርሃን ከምድር ላይ እንዲያፈነግጥ ማድረግ ነው።
ከ6,000 በላይ የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይቶችን የሚያንቀሳቅሰው የSpaceX ኩባንያ ኃላፊ በመሆናቸው፣ የመስክ አስተያየት እንደዚህ ያሉ ትልልቅ የአየር ንብረት ጣልቃ ገብነቶች ውስጥ የኮርፖሬት ተሳትፎ ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁም ሆኗል።
ይሁን እንጂ ባለሙያዎች የፀሐይ ጨረር አስተዳደር ታላላቅ ቴክኒካዊና ሥነ ምግባራዊ ስጋቶች እንደሚያስከትል ያስጠነቅቃሉ። ለምሳሌ፣ እጅግ በጣም አነስተኛ ስህተቶች እንኳ በዓለም አቀፍ የአየር ሁኔታ ስርዓቶች ወይም የዝናብ ስርጭት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ።
ከዚህም ባሻገር በፕላኔቷ ደረጃ ያለውን ይህን የፀሐይ መጋረጃ የሚመራው ወይም የሚቆጣጠረው ማን ይሆናል? የሚለው ወሳኝ የሥነ ምግባርና የአስተዳደር ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።
እነዚህ ስጋቶች ቢኖሩም፣ በርካታ አዳዲስ የንግድ ተቋማት ከስትራቶስፌሪክ ኤሮሶል መበተን እስከ ህዋ ላይ የሚገኙ አንጸባራቂዎች ድረስ ባሉት የፀሐይ-ማጥቆር ቴክኒኮች ላይ ሙከራ እያደረጉ ሲሆን፣ ሳይንሳዊ መሰረቱ በአብዛኛው የንድፈ ሐሳብ ደረጃ ላይ ቢሆንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን የፋይናንስ ድጋፍ እያገኙ ነው።

8 months ago
ስፔስ ኤክስ በጠፈር ላይ ከሚገኙት አጠቃላይ ሳተላይቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛው ባለቤት ሆነ
#ethiopia | የኢሎን መስክ ኩባንያ ስፔስ ኤክስ 10 ሺኛ የስታርሊንክ ሳተላይቱን ወደ ሕዋ በማምጠቅ፣ በጠፈር ላይ ከሚገኙት አጠቃላይ ሳተላይቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛው ባለቤት ሆኗል።
በመሬት ምህዋር ላይ ስራቸውን እያከናወኑ ከሚገኙ 12 ሺ 955 ሳተላይቶች ውስጥ 8 ሺ 562 የሚሆኑት የስፔስ ኤክስ ንብረቶች መሆናቸው ተመላክቷል።
ከስፔስ ኤክስ ቀጥሎ ያለው የቅርብ ተፎካካሪ የሆነው ዋን ዌብ 651 ሳተላይቶች ብቻ አሉት ሲል የዘገበው ኢንዲፔንደንት ነው።
የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ የሳተላይት ፍርስራሾች ከባቢ አየርን በመጉዳት ለዓለም ሙቀት መጨመር አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል ብለው ያስጠነቅቃሉ።
በሴራን ታደሰ
#ebc #space

ዓለም ባንክ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኪሳራ እና ፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር እየተፈተነ መሆኑን አሳወቀ
የዓለም ባንክ እና የዲጂታል ልማት አጋርነት በቅርቡ ባወጡት "የኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ግምገማ" ሪፖርት መሠረት፣ አዲስ የገባው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የገበያ ፈተናዎችን እየገጠመው ነው።
ሪፖርቱ ሳፋሪኮም በ2024 በጀት ዓመት 325 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጿል፤ አመታዊ ገቢው (53.6 ሚሊዮን ዶላር) ለፈቃድ ክፍያው ወጪ እንኳን በቂ አይደለም ይላል።
ለዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ በመንግሥት ከተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ጋር እኩል ያልሆነ የመወዳደሪያ ሜዳ አለመፈጠሩ ነው። ኢትዮ ቴሌኮም የፈቃድ ክፍያ አለመክፈሉ እና ሳፋሪኮም ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በሚደረጉ ጥሪዎች አማካኝነት በወር 1.6 ሚሊዮን ዶላር እንዲያጣ የሚያደርግ የጥሪ ዋጋ (MTR) ቅናሽ ማድረጉ የውድድሩን ፍትሐዊነት ጎድቶታል።
በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም የሳፋሪኮም መተግበሪያዎችን አግዷል እና በቴሌብር የዳታ ግዢ ላይ ቅናሽ በማድረግ ደንበኞችን በኔትወርኩ ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ተብሏል።
ዓለም ባንክ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን (ECA) እንደ ስታርሊንክ ላሉ የሳተላይት ኦፕሬተሮች ፈቃድ እንዲሰጥ፣ የፍቃድ አሰጣጥ ሥርዓቱን እንዲያስተካክል እና በፍትሐዊ ባልሆነ ውድድር ዙሪያ የተነሱትን ስጋቶች በጥልቀት እንዲመረምር መክሯል።

(ቅዳሜገበያ)

የኢሎን መስክ ኩባንያ 28 ሳተላይቶችን አመጠቀ
#ethiopia | "ስፔስ ኤክስ" የተባለው የቢሊየነሩ ኢሎን መስክ ኩባንያ፣ በካሊፎርኒያ ከሚገኘው የጠፈር ጣቢያ 28 የስታርሊንክ ሳተላይቶችን አምጥቋል።
ሳተላይቶቹን የተሸከመው "ፋልኮን 9" የተሰኘው ሮኬት፣ የስፔስ ኤክስን ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማስፋፋት ወደ ሕዋ መምጠቁ ተዘግቧል።
ስፔስ ኤክስ በተለያዩ ሀገራት የኢንተርኔት አገልግሎት እያቀረበ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

9 months ago
የፀሃይ ኃይል በህዋ ላይ ስጋት እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ
📌የኤሎን መስክ ስታርሊንክ ሳተላይቶች የፀሃይ ቁጣ ገፈት ቀማሾች ሆነዋል
#ethiopia | የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑት የህዋ ላይ ሳተላይቶች፣ በተፈጥሮ የፀሃይ እንቅስቃሴ ሳቢያ አደጋ ላይ መውደቃቸውን ሳይንቲስቶች አስታወቁ። በተለይም የኤሎን መስክ ስፔስኤክስ ኩባንያ በዝቅተኛ ምህዋር ላይ ያሰማራቸው ስታርሊንክ ሳተላይቶች ለዚህ ተፈጥሯዊ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተመላክቷል።
ፀሃይ በተፈጥሮ የ11 ዓመት የኃይል ዑደት አላት። በአሁኑ ወቅት የዑደቱ ከፍተኛው ምዕራፍ ላይ በመሆኗ፣ ኃይለኛ የፀሃይ ንፋስ እና የኮሮናል ስብስብ መውጣት እየተከሰተ ነው። እነዚህ ኃይለኛ የኃይል ፍንጣቂዎች ወደ ምድር ሲደርሱ የከባቢ አየርን የላይኛውን ክፍል ያሞቁታል እንዲሁም እንዲለጠጥ ያደርጉታል ነው የተባለው፡፡
የስታርሊንክ ሳተላይቶች እንደ ሌሎች ሳተላይቶች በከፍተኛ ከፍታ ላይ ሳይሆን፣ በዝቅተኛ ምህዋር ላይ በመሆናቸው ለዚህ የከባቢ አየር ለውጥ በቀጥታ ይጋለጣሉ ተብሏል። የከባቢ አየር መለጠጥ ሳተላይቶቹ በሚበሩበት አካባቢ የአየር ውፍረት እንዲጨምር ስለሚያደርግ፣ ሳተላይቶቹ ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የመጎተት ኃይል ይፈጠርባቸዋል። ይህም ሳተላይቶቹ ከመደበኛው ጊዜ ቀደም ብለው ከምህዋራቸው እንዲወጡ እና በከባቢ አየር ውስጥ ወድቀው እንዲያርፉ ያደርጋል ነው የተባለው።
የናሳን ጨምሮ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ እ.ኤ.አ. በ2022 የተከሰተው አንድ የፀሃይ ኃይለኛ ንፋስ ብቻ ከ40 በላይ አዳዲስ ስታርሊንክ ሳተላይቶችን ከጥቅም ውጪ አድርጓል። ሳተላይቶቹ ምህዋራቸውን በማጣት ወደ ምድር ከባቢ አየር በመውደቅ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ነው የተባለው።
በህዋ ላይ ያለው የፀሃይ እንቅስቃሴ አሁንም እየጨመረ በመምጣቱ፣ ባለሙያዎች ወደፊት የሳተላይት ኔትወርኮች ላይ ከባድ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። ይህ ሁኔታ በህዋ ትራፊክ ቁጥጥር እና ደህንነት ላይ አዲስ ፈተናዎችን እየፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ህዋ ማለቂያ የሌለው ቢመስልም፣ በውስጡ ያሉ የሰው ሰራሽ ሳተላይቶች ግን ለተፈጥሮ ኃይሎች ሙሉ በሙሉ የማይበገሩ አይደሉም ነው የተባለው ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ዘግቧል ።

11 months ago
የዓለም የህዋ ሳተላይቶች ቁጥር እያሻቀበ፡ ኢትዮጵያም የህዋ ባለቤትነቷን እያረጋገጠች ነው ተባለ
#ethiopia | በዓለም ዙሪያ በህዋ ላይ በሥራ ላይ የሚገኙ የሳተላይቶች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት ማደጉን የአሁኑ ግምቶች ያሳያሉ።
በአሁኑ ወቅት ከ11,700 በላይ የሚሆኑ ንቁ ሳተላይቶች በምድር ዙሪያ በሚገኙ ምህዋሮች ላይ እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል።
ይህ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ በህዋ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ፈጣን ዕድገት የሚያመለክት ነው ተብሎለታል።
ከነዚህ ንቁ ሳተላይቶች ውስጥ፣ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት የኤሎን መስክ ስፔስ ኤክስ (SpaceX) ኩባንያ የሆኑት የስታርሊንክ (Starlink) ህብረ ከዋክብት አካል ናቸው። እነዚህ ሳተላይቶች ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማቅረብ ያለመ ፕሮጀክት አካል ናቸው ተብሏል።
ምንም እንኳ የንቁ ሳተላይቶች ቁጥር ይህን ያህል ቢሆንም፣ በጠቅላላው በምድር ዙሪያ በሚሽከረከሩ ቁሶች ውስጥ ስራ ላይ ያልዋሉ ሳተላይቶች እና የተለያዩ የህዋ ፍርስራሾች በመኖራቸው የጠቅላላው የህዋ ቁሶች ብዛት ከዚህም የላቀ ነው ተብሏል።
በመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ወደ 14,904 የሚጠጉ ሳተላይቶች ምድርን ይሽከረከሩ እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።
የሳተላይት የማምጠቅ ስራዎች ቁጥር በቅርብ ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ይህ የሆነበት ምክንያት በዋናነት ለቴሌኮሙኒኬሽን እና ለኢንተርኔት አገልግሎት የሚውሉ ግዙፍ የሳተላይት ህብረ ከዋክብቶች መብዛት የመጣ ለውጥ ነው ተብሏል።
ባለሙያዎች የንቁ ሳተላይቶች ቁጥር ከመረጋጋቱ በፊት እስከ 100,000 ሊደርስ እንደሚችል ይተነብያሉ። ይህ ፈጣን የሳተላይቶች ቁጥር መጨመር በህዋ ላይ ትራፊክ፣ የፍርስራሽ ክምችት መጨመር እና የስነ ከዋክብት ጥናቶችን የማደናቀፍ ስጋቶችንም እያስከተለ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያም በህዋ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን ምኞት በተግባር እያሳየች ሲሆን፣ እስካሁን ሁለት የመሬት ምልከታ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ በማምጠቅ ስኬታማ ሆናለች ነው የተባለው።
ኢቲአርኤስኤስ-1 (ETRSS-1): ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷን ሳተላይት ወደ ህዋ ያመጠቀችው ታህሳስ 2012 ዓ.ም. (December 2019) እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለግብርና ክትትል፣ ለአካባቢ አያያዝ እና ለአየር ንብረት ለውጥ ጥናት የሚያገለግል ሲሆን፣ የሀገሪቱን የህዋ ቴክኖሎጂ ጉዞ መነሻ ሆኗል ተብሎለታል።
ኢቲ-ስማርት-አርኤስኤስ (ET-SMART-RSS): ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን የመሬት ምልከታ ናኖ-ሳተላይት ታህሳስ 2013 ዓ.ም. (December 2020) ወደ ህዋ አምጥቃለች ነው የተባለው።
ኢትዮጵያ በህዋ ዘርፍ ያላትን ቁርጠኝነት በማሳየት፣ በ2026 ሶስተኛ የመሬት ምልከታ ሳተላይት የሆነውን ኢቲአርኤስኤስ-2 (ETRSS-2) ለማምጠቅ ማቀዷንም በዘርፉ የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ይህ የሀገሪቱ በህዋ ቴክኖሎጂ ላይ ያለው ዕድገት ማሳያ ሲሆን፣ እስከ 2035 ድረስ በአጠቃላይ አስር ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ለማምጠቅ የረጅም ጊዜ እቅድ እንዳላትም ተመላክቷል።
ይህ የኢትዮጵያ የህዋ ጉዞ ለሀገሪቱ የልማት ጥረቶች ዘመናዊ መረጃዎችን ከማቅረቡም በተጨማሪ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅሟን በማሳደግ በዘርፉ ግንባር ቀደም አፍሪካዊት ሀገር የመሆን ምኞቷን ያንፀባርቃል ነው የተባለው። #menahriafm

ኢሎን መስክ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቋመ
ኢሎን መስክ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያለው የቅርብ ወዳጅነት በአለመግባባት ከተጠናቀቀ ከሳምንታት በኋላ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁሜያለሁ አለ።
ቢሊየነሩ የፖለቲካ ፓርቲን ማቋቋሙን ለሪፐብሊካን እና ዲሞክራቲክ የሁለት ፓርቲ ስርዓት ፈተና እንደሆነ በመግለጽ በማህበራዊ ሚዲያው ኤክስ ገጹ ላይ አስታውቋል።
ሆኖም ፓርቲው በይፋ በአሜሪካ የምርጫ ባለሥልጣን መመዝገቡ ግልፅ አይደለም
ከአሜሪካ ውጭ በመወለዱ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ብቁ ያልሆነው መስክ ፓርቲውን ማን እንደሚመራው አልተናገረም።
መጀመሪያ ከትራምፕ ጋር በነበረው አለመግባባት ወቅት ፓርቲ የመመስረት ሃሳብን አንስቶ የነበረው መስክ፣ አለመግባባቱ እየተካረረ መጥቶ በአስተዳደሩ ውስጥ የነበረውን ኃላፊነት ለቅቆ ከቀድሞ የቅርብ ወዳጁ ጋር የተካረረ አለመግባባት ውስጥ መግባቱ የአደባባይ ሚስጥር ነበር።
መስክ ከፕሬዚደንት ትራምፕ ጋር የተካረረ አለመግባባት ውስጥ በነበረበት ወቅት የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን በአሜሪካ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መኖር ይኖርበት እንደሆን የሚጠይቅ አስተያየት ለጥፏል።
መስክ በቅዳሜው ልጥፍ ላይ ያንን የሕዝብ አስተያየት በመጥቀስ "2 ለ 1 በሆነ ውጤት፣ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲኖር ፍላጎታችሁን አሳይታችኋል! አገራችንን በቆሻሻና በሌብነት ወደ ኪሳራ ስለመውሰድ ስንነጋገር የምንኖረው በአንድ ፓርቲ ስርዓት እንጂ በዲሞክራሲ አይደለም።" ሲል ጽፏል።
አክሎም "ዛሬ የአሜሪካ ፓርቲ የተመሰረተው ነፃነታችሁን ሊመልስላችሁ ነው" ብሏል።
ከቅዳሜ ጀምሮ የፌዴራል ምርጫ ኮሚሽን ፓርቲው በይፋ መመዝገቡን የሚጠቁሙ ሠነዶችን ይፋ አላደረገም።
በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ከተለምዷዊው የሁለት ፓርቲ ስርዓት ውጪ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችም ቢኖሩም፣ እውነተኛ ጫና ለመፍጠር በአገር አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ተቀባይነት ማግኘት አዳጋች ነው።
ባለፈው ዓመት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደ ሊብሪተያን ፓርቲ፣ ግሪን ፓርቲ እና ፒፕልስ ፓርቲ ያሉ እጩዎች ትራምፕን ወይም የዴሞክራቲክ ተቀናቃኛቸውን ካማላ ሃሪስን እንዳያሸንፉ ለማድረግ ያልተሳካ ሙከራ አድርገዋል ።
መስክ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የትራምፕ ዋና ደጋፊ ነበር።
ባለፈው ዓመት በተደረጉ የምርጫ ቅስቀሳዎች ወቅት ከፕሬዚደንቱ ጎን በአጋፋሪነት የነበረው መስክ ሥልጣን ከያዙ በኋላም የአራት ዓመት ልጁ ትራምፕን እንዲያገኝ ኦቫል ኦፊስ ድረስ ይዞት መጥቷል።
መስክ የትራምፕን የምርጫ ቅስቀሳ በገንዘብ ከደገፉ ባለሀብቶች መካከል ዋነኛው ነው። ፕሬዚደንቱ ዳግም ሥልጣናቸውን እንዲይዙ 250 ሚሊዮን ዶላር አውጥቷል።
ከምርጫው በኋላም በፌዴራል በጀት ውስጥ የሚታዩ ወጪዎች ላይ ቅነሳዎችን የመለየት ኃላፊነት የተሰጠውን የመንግስት ቅልጥፍና (ዶጅ) ተብሎ የሚጠራውን ተቋም እንዲመራ ተሾመ።
ከትራምፕ ጋር የነበራቸው ውዝግብ የጀመረው በግንቦት ወር አስተዳደሩን ለቅቆ በወጣበት ጊዜ እና የትራምፕን ግብር እና የወጪ ዕቅዶችን በይፋ መተቸት ሲጀምር ነው።
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ትልቅ ቆንጆ" ሲሉ በይፋ የሰየሙት ረቂቅ በጀታቸው በአገሪቱ በምክር ቤት ጸድቋል።
ሕጉ ከፍተኛ ወጪን እና የግብር ቅነሳን ያካተተ ሲሆን በአሜሪካ በጀት ላይ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከሦስት ትሪሊየን ዶላር በላይ ጉድለት እንደሚያስከትል ተገምቷል።
በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ መኪኖችን የሚያመርተው ግዙፉ ቴስላ ባለቤት የሆነው መስክ የትራምፕ ሕግ በአረንጓዴ ሽግግር ላይ ወይም እንደ ቴስላ ላሉ ምርቶች ድጎማ ማድረግ ላይ አያተኩርም ሲል ይተቻል።
ትራምፕ በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ትሩዝ ሶሻል ላይ "ኤሎን በታሪክ ውስጥ ከየትኛውም የሰው ልጅ የበለጠ ድጎማ ሊያገኝ ይችላል" ሲሉ ጽፈዋል። "ያለ ድጎማ ኤለን ምናልባት ሱቁን ዘግቶ ወደ አገሩ ደቡብ አፍሪካ መመለስ ይኖርበታል።"
ትራምፕ የቢሊየነሩን ሌሎች ንግዶችን በመጥቀስ ለመስክ ኩባንያዎች የሚደረጉ ድጎማዎችን እንዲመለከት የቅልጥፍና ቢሮውን እንደሚያዙ ዝተዋል።
በተጨማሪም መስክ ለአሜሪካ መንግሥት ሮኬቶችን የሚያመጥቀውን ስፔስ ኤክስ እና ለአሜሪካ እና አውሮፓ የመከላከያ ኃይሎች የሳተላይት አገልግሎት የሚሰጠውን ስታርሊንክ ባለቤት ነው።
BBC