4 months ago
ቱሪዝም የመጪው ዘመን የኢትዮጵያ የልማት ጉልበት!!
#ethiopia | ከዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ ወደ ተርክዬ የማቅናት ዕድል አጋጥሞኝ ነበር። በአንካራ እና ኢስታንቡል በተሳተፍኩባቸው ትምህርታዊ ጉብኝቶች ቀልቤን ከሳቡት መካከል ተርክዬ ወደ አሁኑ ደረጃ የደረሰችባቸው መንገዶች እና ትኩረት ተሰጥቶባቸው የተከናወኑ የልማት አውታሮች ናቸው።
ከእነዚህ መካከል የቱሪዝም ዘርፍ ፣ግብርና እና የማምረቻ ዘርፎች ናቸው። የቱሪዝም ዘርፏ በወቅቱ የነበረውን አሀዝ አስደግፈን ስንመለከት የተርክዬ ስታስቲክስ ኢንስቲትዩት ጥር 31 2019 ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ 51 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች ቱርክዬን ጎብኝተዋታል ።
ከጎብኝዎች መካከል 86.2 በመቶዎቹ የውጭ አገር ዜጎች ሲሆኑ ቀሪዎች 13.8 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ የራሷ ዜጎች እና ዳያስፖራዎቿ ናቸው። ከእነዚህ ጎብኝዎች 34.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ መሰብሰብ ችላለች። ተርክዬ እዚህ ደረጃ የደረሰችው ብዙ ውጣ ውረዶችን በማለፍ የገነባቻቸው አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ማለትም እንደነ ቦስፈረስ ድልድይ :አንታሊያ መዝናኛ መዳረሻዎች:የታደሱ እና የተገኘቡ ብሔራዊ ሙዚየሞች :ጥንታዊ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ቅርሶቿን በመጠበቋ ነው።
አንዳንዶቹ የቱሪስት መዳረሻዎች በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በሕዝብ የተቀናጀ የገንዘብ መዋጮ ጭምር የተገነቡ ናቸው።
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ብዙ የታሪክ ፀሐፍት እና የሥነ ሰብ ተመራማሪዎች በአንድ ቃል እንደሚስማሙበት ምድረ ቀደምት አገር ነች። በዚህም የተነሳ አያሌ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ የቱሪስት መዳረሻዎች አሏት። በቅርቡም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጭነት በርካታ ውብ የቱሪስት መዳረሻ በሁሉም የአገሪት አካባቢዎች ተገንብተዋል:እየተገነቡም ናቸው።
ይኸ እምቅ የቱሪዝም ሀብት በመጪው ጊዜ የኢትዮጵያ ሁነኛ የኢኮኖሚ አውታር መሆኑ አይቀሬ ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ:መልከዓ ስትራቴጂክነቷ ለሁሉም ክፍለ አህጉራት አማካኝ እና ሁነኛ መተላለፊያ ላይ ነች።
ከዚህ አኳያ ከቱርክዬ የተሳካ የቱሪዝም ዘርፍ እና ከመሰል አገራት ልምድ መቅሰም ተገቢነቱ የጎላ ነው። ወቅታዊው የኢትዮጵያ የቱሪዝም ፍኖተ መንገድም ወደዚያ የስኬት መንገድ የሚያቀናን በመሆኑ ልናጠናክረው ይገባል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) (Abiy Ahmed Ali) የቱሪዝም አዲስ ፍኖት እና የትኩረት አቅጣጫ መሠረት የኢትዮጵያ አዳዲስ ገጽታዎች ከቃል አልፈው በተግባር እየተገለጡ ነው።
አሁን ላይ በየአካባቢው እስከ አሁን ተደብቀው የነበሩ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት አቅማቸውን የመግለጥ አኩሪ ሥራ :የነበሩትን የማደስ እና መልሶ ለጎብኝዎች ክፍት የማድረግ ስኬቶችም የመጪው ዘመን የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ልሕቀት የመጀመሪያው መጀመሪያ ሥራዎች ናቸው። በእርግጥ ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ሥራ የሁላችንንም ኃላፊነት ይጠይቃል።
#ስላባት ማናዬ

5 months ago
ከውኃ ማማ ወደ ኃይል ማማ፤ኢትዮጵያ !
ስላባት ማናዬ
#ethiopia | የመልከዓ ምድር ሁኔታ በአገራት የጂኦፖለቲካ ሚና እና ተሳትፎ ላይ ወሳኝ ነው። የኢትዮጵያ መልከዓ ምድር ከአሉታዊ ጎኑ ይልቅ አወንታዊ ጎኑ የገዘፈ ሆኖ እናገኘዋለን። ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም An Introductory Geography of Ethiopia(1972) እስከ ቲም ማርሻል The power
of Geography(2021) ስንመረምር የኢትዮጵያ መልከዓ ምድር ተፈጥሮ በብዙ ነገሮች ያደለችው ነው። ቀዳሚው የውኃ ጉዳይ ነው።
በተለይ ቲም ማርሻል ኢትዮጵያ ያላትን የውኃ ሃብት በተገቢው መንገድ ከተጠቀመች ከራሷ አልፋ ለጎረቤቶቿ እና ቀጣናው ትተርፋለች ይላል። ፀሐፊው ስለ ኢትዮጵያ ባሰፈረው ትንታኔ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውኃ ማማ የሚለውን አባባል ያላትን የውኃ ሃብት በትክክል ከተጠቀመች እና ካለማች ኢትዮጵያ የቀጣናው የኃይል ማማ (Hydro-🔋)ትሸጋገራለች ነው የሚለው ። በእርግጥ አሁን ላይ ሆነን የቲምን ትንታኔ ደግመን ስናጤነው ኢትዮጵያ በተሳካ ሁኔታ የተተነበየውን መንገድ እየተከተለች መሆኗን አመላካች ነው። ኢትዮጵያ የሕዳሴን ግድብ አጠናቃ መርቃለች፤የኮይሻ ኃይል ማመንጫም እየገሰገሰ ነው። ከጎረቤቶቿም አልፋ በቀጣናው የኃይል ትሥሥር ፕሮጀክቶቿን ከቃል ወደ ተግባር እየለወጠች ነው። መጪው ዘመን በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዲፕሎማሲ ዑደት ውስጥ ደማቅ ታሪክ የሚጻፍበት ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናው የኃይል ትስስር ፈጠረች ማለት አንድምታው ዘርፈ ብዙ ነው።

6 months ago
ቀይ ባሕር ፡ የኢትዮጵያ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ…?
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ
በስላባት ማናዬ
#ethiopia | ኢትዮጵያ የምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ መልከዓ ምድራዊ አቀማጥ ለመካከለኛው ምሥራቅ፣ለአወሮፓ እና ኤስያ ትልቅ ጂኦ ስትራቴጂካዊ ቦታ ነው። ይህ ቀጣና ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር የሚተሳሰር ነው።
ቀጣናው በወሣኛ የዓለማችን የንግድ መሥመሮች መተላለፊያ ፡በሦስቱ አብርሃማዊ ሐይማኖቶች መነሻ ቅርብ የሆነውን ያህል በታሪክ እና በገቢር በርካታ የደኀንነት ስጋቶችን በየጊዜው ደቅኖ የሚገኝ ነው።
ሽብርተኝነት፣ የባሕር ላይ ዘራፊዎች፣ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች፣ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች እና አደገኛ ዕጽ አዘዋዋሪዎች በቀጣናው ከተደቀኑ አደጋዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህ ቀጣና ከሚገኙ አገራት መካከል ሁነኛዋ መልሕቅ አገር ኢትዮጵያ ነች። ኢትዮጵያ በቀጣናው የተደቀኑ የደኀንነት ስጋቶች በራሷ እና በዓለም አቀፍ የደሕንነት ስርዓት ውስጥ ከባድ መሰናክል እንዳይፈጥር ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ሥራ ስታከናውን ቆይታለች።
በተለይ በአካባቢው የሽብርተኞች አደጋን በመዋጋት ረገድ ከኃያላንም ከመካከለኛ ኃይላት ጋር በጋር ተንቀሳቅሳለች፡እየተንቀሳቀሰችም ትገኛለች።
ይህ እንቅስቃሴዋ በተለይ ላለፉት 30 ዓመታት በየብስ እና በአየር ኃይል ብቻ ተወስኖ ቆይቷል። አሁን ኢትዮጵያ አላግባብ የተወሰደብኝን የባሕር በር መልሼ ማግኘት ይገባኛል የሚል ጥያቄ አንስታ እየተጓዘች ነው።
በቀጣናው እና በቀይ ባሕር አካባቢ ያለውን የደህንነት ሥጋት በጥሞና ለተከታተለው ኢትዮጵያ አሁን ላይ በየብስ እና በአየር ክልሉ ከምታደርገው የደህንንት ሥራ አኳያ የባሕር በሯን መልሳ ማግኘት እና የቀይ ባሕር አባል ወደ መሆን የመመለስ ጉዞዋ ጠቀሜታው ከራሷ ያለፈ በዓለም አቀፍ የደህንነት እና ጸጥታ መዋቅር ውስጥም የጎላ ሚና ይኖረዋል።
ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ መደገፍ ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱ በንቃት ሊሳተፍ ይገባል።
በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የራሴን ምልከታ አቅርቢያለሁ፡ የግላችሁን ደግሞ በአስተያየት መስጫው ሥር አስፍሩ
https://www.thereportereth...

Sponsored by
Surafel
Comments