ቱሪዝም የመጪው ዘመን የኢትዮጵያ የልማት ጉልበት!!
#ethiopia | ከዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ ወደ ተርክዬ የማቅናት ዕድል አጋጥሞኝ ነበር። በአንካራ እና ኢስታንቡል በተሳተፍኩባቸው ትምህርታዊ ጉብኝቶች ቀልቤን ከሳቡት መካከል ተርክዬ ወደ አሁኑ ደረጃ የደረሰችባቸው መንገዶች እና ትኩረት ተሰጥቶባቸው የተከናወኑ የልማት አውታሮች ናቸው።
ከእነዚህ መካከል የቱሪዝም ዘርፍ ፣ግብርና እና የማምረቻ ዘርፎች ናቸው። የቱሪዝም ዘርፏ በወቅቱ የነበረውን አሀዝ አስደግፈን ስንመለከት የተርክዬ ስታስቲክስ ኢንስቲትዩት ጥር 31 2019 ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ 51 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች ቱርክዬን ጎብኝተዋታል ።
ከጎብኝዎች መካከል 86.2 በመቶዎቹ የውጭ አገር ዜጎች ሲሆኑ ቀሪዎች 13.8 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ የራሷ ዜጎች እና ዳያስፖራዎቿ ናቸው። ከእነዚህ ጎብኝዎች 34.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ መሰብሰብ ችላለች። ተርክዬ እዚህ ደረጃ የደረሰችው ብዙ ውጣ ውረዶችን በማለፍ የገነባቻቸው አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ማለትም እንደነ ቦስፈረስ ድልድይ :አንታሊያ መዝናኛ መዳረሻዎች:የታደሱ እና የተገኘቡ ብሔራዊ ሙዚየሞች :ጥንታዊ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ቅርሶቿን በመጠበቋ ነው።
አንዳንዶቹ የቱሪስት መዳረሻዎች በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በሕዝብ የተቀናጀ የገንዘብ መዋጮ ጭምር የተገነቡ ናቸው።
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ብዙ የታሪክ ፀሐፍት እና የሥነ ሰብ ተመራማሪዎች በአንድ ቃል እንደሚስማሙበት ምድረ ቀደምት አገር ነች። በዚህም የተነሳ አያሌ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ የቱሪስት መዳረሻዎች አሏት። በቅርቡም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጭነት በርካታ ውብ የቱሪስት መዳረሻ በሁሉም የአገሪት አካባቢዎች ተገንብተዋል:እየተገነቡም ናቸው።
ይኸ እምቅ የቱሪዝም ሀብት በመጪው ጊዜ የኢትዮጵያ ሁነኛ የኢኮኖሚ አውታር መሆኑ አይቀሬ ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ:መልከዓ ስትራቴጂክነቷ ለሁሉም ክፍለ አህጉራት አማካኝ እና ሁነኛ መተላለፊያ ላይ ነች።
ከዚህ አኳያ ከቱርክዬ የተሳካ የቱሪዝም ዘርፍ እና ከመሰል አገራት ልምድ መቅሰም ተገቢነቱ የጎላ ነው። ወቅታዊው የኢትዮጵያ የቱሪዝም ፍኖተ መንገድም ወደዚያ የስኬት መንገድ የሚያቀናን በመሆኑ ልናጠናክረው ይገባል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) (Abiy Ahmed Ali) የቱሪዝም አዲስ ፍኖት እና የትኩረት አቅጣጫ መሠረት የኢትዮጵያ አዳዲስ ገጽታዎች ከቃል አልፈው በተግባር እየተገለጡ ነው።
አሁን ላይ በየአካባቢው እስከ አሁን ተደብቀው የነበሩ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት አቅማቸውን የመግለጥ አኩሪ ሥራ :የነበሩትን የማደስ እና መልሶ ለጎብኝዎች ክፍት የማድረግ ስኬቶችም የመጪው ዘመን የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ልሕቀት የመጀመሪያው መጀመሪያ ሥራዎች ናቸው። በእርግጥ ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ሥራ የሁላችንንም ኃላፊነት ይጠይቃል።
#ስላባት ማናዬ

4 months ago