11 days ago
አብራሪው አየር ላይ እያለ በስለት ተወጋ
#ethiopia | ከዱባይ ተነስተው ወደ እስራኤል በመብረር ላይ የነበረው የ"ፍላይ ዱባይ" ቦይንግ 737 MAX አውሮፕላን አየር ላይ እያለ አስደንጋጭ ክስተት አስተናግዷል።
በዋናው አብራሪ እና በምክትል አብራሪው መካከል በተፈጠረ የሃይል ግጭት ምክንያት አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ቀይሮ በሳዑዲ አረቢያ ኤርፖርት እንዲያርፍ ተገዷል።
እንደ አለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘገባ ከሆነ አውሮፕላኑ የመደበኛ በረራ መንገዱን ይዞ በመጓዝ ላይ እያለ በአየር ላይ ባለው የአብራሪዎች ክፍለ ውስጥ በሁለቱ አብራሪዎች መካከል ከፍተኛ ጭቅጭቅ ተከሰተ።
የኦማን ዜግነት ያለው ምክትል አብራሪ የኤምሬትስ ዜግነት ያለውን ዋና አብራሪ በስለት ወግቶ ከባድ ጉዳት አድርሶበታል ተብሏል።
በግጭቱ ምክንያት ዋናው አብራሪ በደረሰበት ጉዳት በረራውን መቀጠል ባለመቻሉ እና አውሮፕላኑ አደጋ ውስጥ መሆኑን የተረዱት የኩባንያው አብራሪዎች በፍጥነት ወደ ኮክፒት በመግባት ግጭቱን መቆጣጠራቸው ታውቋል።
የእስራኤል የደህንነት እና የመረጃ ተቋም (ሞሳድ) ድርጊቱን አስመልክቶ በሰጠው የመጀመሪያ ደረጃ ፍንጭ በሁለቱ አብራሪዎች መካከል የተከሰተው ጥቃት "የሽብር ድርጊት" ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።
ተቋሙ ድርጊቱ የታቀደ ይሁን ወይም አጋጣሚ በአየር ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎችን እና የበርካታ ሀገራትን ደህንነት አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ ሰፊ የምርመራ ቡድን መመደቡን አስታውቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #breakingnews #flydubai #aviationnews #dubaitotelaviv #flightsafety #saudiarabia #emergencylanding #mossad

2 months ago
በኦስትሪያ የጠፉት እናትና ልጅ ፍለጋ የሞሳድ አባላት ተሳታፊ ሆኑ
#ethiopia | በኦስትሪያ ቪየና ከተማ በድንገት የተሰወሩትን ሁለቱን እስራኤላውያን ሴቶች ለማግኘት በሚደረገው ጥረት የሀገሪቱ የደህንነት ተቋም ሞሳድ እገዛ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የእስራኤል ባለስልጣናት እና የቪየና ፖሊስ እንዳስታወቁት፣ የሴቶቹ መጥፋት ከአሸባሪነት፣ ከብሔረተኝነት ወይም ከወንጀል ድርጊት ጋር የተያያዘ ለመሆኑ እስካሁን ምንም አይነት ጥርጣሬና ማስረጃ አልተገኘም።
ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሆኑት እናት ማሊ ያሃሎሚ እና የ23 ዓመት ልጃቸው ሊኤል ያሃሎሚ በፕራግ የጀመሩትን የልደት ቀን ጉዞ በባቡር ወደ ቪየና ካደረጉ በኋላ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም (ኦገስት 7 ቀን 2026) ደብዛቸው መጥፋቱ ይታወቃል።
የእስራኤል የደህንነት አካላት ባካሄዱት የመጀመሪያ ደረጃ ማጣሪያ፣ በክስተቱ ላይ የፕሮ-ፓለስታይን ወይም የኢራን ቡድኖች እጅ እንዳለበት የሚያሳይ ምንም አይነት ፍንጭ አለመኖሩ ተረጋግጧል።
የኦስትሪያ ፖሊስ በበኩሉ የወንጀል ድርጊት ጥርጣሬ የለም ቢልም፣ ምርመራውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማሸጋገር ሊኖሩ የሚችሉ ሁሉንም አጋጣሚዎች በመፈተሽ ላይ ይገኛል።
አሁን ላይ የፍለጋ እንቅስቃሴው የሴቶቹን ስልክ አድራሻ በመከታተል እና በአካባቢው በሚገኙ ሆስፒታሎች ላይ በማተኮር እየተከናወነ ነው።
የፍለጋ ሂደቱን በዋናነት እየመራ የሚገኘው የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን፣ ይህም ክስተቱ ከደህንነት ስጋት ይልቅ ሲቪላዊ አጋጣሚ ለመሆኑ ማረጋገጫ ተደርጎ ተወስዷል። ሆኖም የደህንነት ተቋሙ ሞሳድ በፍለጋው ጥረት ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።
የእስራኤል ፖሊስ ኮሚሽነር ዳኒ ሌቪ በጉዳዩ ላይ የላቀ የስራ ግምገማ ካካሄዱ በኋላ፣ በእስራኤልም ሆነ በውጭ ሀገራት ያሉ የፖሊስ አቅሞችና ዘዴዎች በሙሉ ጥቅም ላይ እንዲውሉ መመሪያ አስተላልፈዋል።
የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤን ጊቪር በበኩላቸው ከተጠፋፊዎቹ ቤተሰቦች ጋር ተነጋግረው አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግ እና ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተሉት አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#እስራኤል #ኦስትሪያ #ቪየና #ሞሳድ #ዜና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

“ኢራን የኒውክሌር ቦምብ ለመሥራት ረዥም ጊዜ ያስፈልጋታል” የሞሳድ የቀድሞ አዛዥ
የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ የቀድሞው አዛዥ ዮሲ ኮኽን ኢራን በተፈጸመባት ተከታታይ ጥቃት ምክንያት የኒውክሌር ቦምብ የመሥራቅ አቅሟ መዳከሙን ተናገሩ።
ባለሥልጣኑ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ፎርዶ የተባለው የኢራን ከመሬት በታች የሚገኝ የኒውክሌር ተቋም ላይ በቅርበት ባደረገው ክትትል ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰበት መልሶ ለመገንባት ረዥም ጊዜ ያስፈልጋታል ብለዋል።
አሜሪካ በተቋሙ ላይ ያደረሰችውን ጉዳት ሲያልሙት የነበረው “ሕልም ስኬት ነው” ሲሉ የገለጹት ቢሆንም፤ ይህንን ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን ማብራሪያ አልሰጡም።
የቀድሞው የሞሳድ አዛዥ ተቋማቸው ኢራን ለዓመታት ከመሬት በታች ስትገነባው የቆየውን ፎርዶ የኒውክሌር ተቋምን በቅርበት እና በዝርዝር ሲከታተለው እንደቆየ ማክሰኞ ዕለት በተደረገ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
ጨምረውም ኢራን 60 በመቶ የዳበረ ዩራኒየም አዘጋጅታለች በማለት ምንም እንኳን ንጥረ ነገሩ በከፍተኛ ደረጃ የዳበረ ቢሆንም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲኖራት ያስችላል ማለት አይደለም ብለዋል።
“60 በመቶ ዩራኒየም ማዳበር ማለት ቦምቡን ለማሥራት ገና ብዙ ርቀት መጓዝ የሚሰስፈልገው ነው” ብለዋል።
አሜሪካ ፎርዶ የተባለውን ከተራሮች በታች የሚገኝ የኒውክሌር ተቋምን በልዩ እና ከባድ ቦምብ የደበደበችው ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በፈጸመችው ጥቃት ነበር።
BBC

ሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ የኢራን አዲሱን የበላይ መሪ ሙጅተባ ኻመነኢን ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረት ትኩረት ስቧል
#ዓለም | የብሪታንያው The Times ጋዜጣ የደህንነት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የአሜሪካው ሲ.አይ.ኤ (CIA) እና የእስራኤሉ ሞሳድ (Mossad) የኢራን አዲሱ የበላይ መሪ ሙጅተባ ኻመነኢ የት እንዳሉ ለማረጋገጥ እና ሁኔታቸውን ለመከታተል የስለላ ጥረታቸውን አጠናክረዋል።
ሪፖርቱ እንደሚለው፣ ሙጅተባ ኻመነኢ ከአባታቸው ሞት በኋላ የኢራንን ከፍተኛ አመራር ቢረከቡም፣ በአደባባይ አልታዩም፤ ስልክ፣ ኮምፒውተር ወይም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎችን እንደማይጠቀሙም ይገለጻል። በዚህ ምክንያት በሳተላይት እና በሳይበር መንገድ የሚደረገው ክትትል ውጤታማ እንዳልሆነ ተነግሯል።
በዚህ ሁኔታ የምዕራባውያን የደህንነት ተቋማት ትኩረታቸውን ከኤሌክትሮኒክስ ስለላ ወደ Human Intelligence (HUMINT) ወይም በሰዎች በኩል የሚሰበሰብ መረጃ ላይ ማዞራቸው ተዘግቧል። አንዳንድ የቀድሞ የሞሳድ ባለስልጣናት እንደሚሉት፣ ሙጅተባ መልእክቶችን በብዙ ደረጃ በተደራጁ ተላላኪዎች እንደሚያስተላልፉ ይገመታል።
ሆኖም እስካሁን ድረስ ሙጅተባ ኻመነኢ የት እንዳሉ፣ በምን ዓይነት የጤና ሁኔታ እንዳሉ ወይም በቀጥታ አገሪቱን እየመሩ መሆናቸው በገለልተኛ ምንጮች አልተረጋገጠም። የአሜሪካና የእስራኤል ባለሥልጣናትም እነዚህን ሪፖርቶች በይፋ አላረጋገጡም።
አንዳንድ ሚዲያዎች ሙጅተባ ኻመነኢ በሕይወት ስለመኖራቸው ወይም ስለ ምትክ ሰዎች (body doubles) የሚያነሱት ጥርጣሬ መኖሩን ቢዘግቡም፣ እነዚህ አባባሎች በገለልተኛ ማስረጃ ያልተረጋገጡ ግምቶች መሆናቸውን የዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ያስገነዝባሉ።
ተንታኞች እንደሚሉት፣ ሙጅተባ ኻመነኢ በሕዝብ ፊት አለመታየታቸው በኢራን የሥልጣን አወቃቀር፣ በአብዮታዊ ዘብ (IRGC) ያለው ተጽዕኖ እና በቀጣናው የደህንነት ሁኔታ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው። ነገር ግን ከስለላ ሪፖርቶች ባሻገር የተረጋገጠ ኦፊሴላዊ መረጃ አሁንም አልቀረበም።

7 months ago
በኢራን የእስራኤል ሰላይ በመሆን የሰነበቱት የጦር አዛዡ ኢስማይል ቃኒ እስራኤል መግባታቸው ተሰምቷል !
ለሞሳድ ይሰልሉ ነበር የተባሉት የጦር አዛዡ በአያቶላህ ሞት ላይም ቀጥተኛ የሆነ ተሳትፎ አደርጓል ነው የተባለው
ኢራን ሰውዬው በጥቃቱ ተገሎ ነበር ብላ የነበረ ቢሆንም በህይወት መኖሩን እና እስራኤል መግባቱ ነው የተገለፀው
ዴይሊ ሜይል እንደዘገበው ከሆነ አዛዡ በቴርሃን ለደረሱ ጥቃቶች ሙሉ ለእስራኤል ሲሰልል ነበር ያለ ሲሆን አሁን አስራኤል ግብቷል በእስራኤልም ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ላይ ይታሰራል ብሏል ፤ ሌሎች የኢራን አመራር ሁነው ለእስራኤል የሚሰሩ አሁንም አሉ ሲል በዘገበው አስነብቧል።
seledadotio

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የኢራን የቀድሞው የደኅንነት ኃላፊ በክህደት ወንጀል ተጠረጠሩ
#ethiopia | ለረጅም ዓመታት የኢራን የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኃይል (IRGC) የስለላ መዋቅርን በበላይነት ሲመሩ የቆዩት ሆሴን ታኢብ፣ ከእስራኤል (ሞሳድ) ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተዘገበ።
ጥርጣሬውን የቀሰቀሰው "የ20 ደቂቃ" ድራማ
ለባለሥልጣኑ መታሰር እንደ ዋነኛ መነሻ የተጠቀሰው፣ በቅርቡ አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከመፈጸማቸው ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ የታየው ያልተለመደ ክስተት ነው። ሆሴን ታኢብ ከሀገሪቱ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ጋር በስብሰባ ላይ ሳሉ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ 20 ደቂቃ በፊት "ታምሜአለሁ" በሚል ምክንያት በድንገት አቋርጠው መውጣታቸው ከፍተኛ ጥርጣሬን ፈጥሯል።
ይህ ድርጊታቸው ስለ ጥቃቱ አስቀድመው መረጃ እንደነበራቸውና ራሳቸውን ለማዳን እንዲሁም ለጠላት መረጃ አሳልፎ በመስጠት ሳይተባበሩ እንዳልቀረ ተገምቷል።
የታኢብ ተፅዕኖ እና የክስተቱ ክብደት
ሆሴን ታኢብ በኢራን የደኅንነት መዋቅር ውስጥ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ሚስጥር አዋቂ ሰው እንደነበሩ ይነገራል። እንደ አይሪሽ ታይምስ እና ኢራን ኢንተርናሽናል ዘገባ ከሆነ፣ የእሳቸው መታሰር በኢራን ከፍተኛ አመራሮች መካከል ያለውን ያለመተማመን ስሜት ከፍ ከማድረጉም በላይ፣ የሞሳድ ሰርጎ ገብነት እስከ የትኛው የሥልጣን እርከን ድረስ እንደዘለቀ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
በአሁኑ ወቅት ባለሥልጣኑ በከፍተኛ ጥበቃ ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢራን #እስራኤል #ሞሳድ #ሆሴንታኢብ #የስለላ_መረጃ #ሰበር_ዜና #iran #intelligence #mossad

"ከኻሜኒ አጠገብ የተቀመጠው ከዳተኛ"፦ እስራኤል የኻሜኒን መገኛ እንዴት አወቀች?
ለ37 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩትን የመካከለኛው ምስራቅ አንጋፋ መንፈሳዊ መሪ ኢላማ ያደረገው ይህ ኦፕሬሽን፣ በአጋጣሚ ወይም በጭፍን ወታደራዊ ኃይል የተፈጸመ እንዳልሆነ ተነግሯል። ቅዳሜ ጠዋት በኻሜኒ የሚመራው ከፍተኛ ስብሰባ እየተካሄደ በነበረበት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሰላሳ በላይ ከባድ ቦምቦች አርፈዋል።
የክስተቱ አስገራሚው ገጽታ ቦምቡ ሳይሆን፣ ኢላማው የተመረጠበት የቀዶ ጥገና ያህል ጥንቃቄ የተሞላበት ትክክለኛነት ነው። የሞሳድ ሰራተኞች ስለ ስብሰባው ሙሉ ምስል እንደነበራቸው ተዘግቧል፦ የስብሰባውን ትክክለኛ መጀመሪያ ሰዓት፣ የውይይቱን ርዕሰ ጉዳይ፣ ተሳታፊዎችን እና ሌላው ቀርቶ የክፍሉን አቀማመጥ ጭምር ያውቁ ነበር።
እንደ ኢራን ግምት ከሆነ፣ የእስራኤል የስለላ ድርጅት በጥቃቱ ወቅት ኻሜኒ የነበሩበትን ቦታ በዝርዝር ያውቅ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ መረጃ በሳተላይት ወይም በኤሌክትሮኒክስ ጠለፋ ሊገኝ አይችልም፤ ሊገኝ የሚችለው በአካባቢው በአካል ከነበረ የሰው ምንጭ ብቻ ነው።
ፍንጮቹ እውነት ከሆኑ፣ ለመንፈሳዊው መሪው የቅርብ ክበብ ውስጥ ያለ ሰው ወሳኝ መረጃን ለእስራኤል አሳልፎ ሰጥቷል ማለት ነው። ይህም ጥቃቱ እንደተለመደው በምሽት ሳይሆን በቀን የተፈጸመበትን ምክንያት ያብራራል።
የዜና ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ ከጥቃቱ በኋላ የመንፈሳዊው መሪውን ሞት የሚያረጋግጥ ምስል ወዲያውኑ ተላልፏል። ወደ ስፍራው የተጠጋው ወኪል በሞባይል ስልኩ ቪዲዮ በመቅረጽ፣ የሟቹን ማንነት ለማረጋገጥ በሟቹ እጅ ላይ የነበረውን ልዩ ቀለበት አሳይቶ ፎቶዎቹን በቀጥታ ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ልኳል።
በዚህም የአያቶላው ረዳቶች ምን እንደተፈጠረ እንኳ ከመገንዘባቸው በፊት የእስራኤሉ መሪ ስለ ኻሜኒ ሞት ቀድመው መረጃ ደርሷቸዋል።
በመቀጠል ኔታንያሁ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መረጃውን አጋርተዋል። የአሜሪካው መሪ በ"ትሩዝ ሶሻል" ማህበራዊ ገጽ ላይ የሰጡት መግለጫ የሟቹን ማንነት የሚያረጋግጡ መረጃዎች ከተለዋወጡ በኋላ እንደመጣ ተነግሯል።
ይህ ቅደም ተከተል ኢራን ይፋዊ አቋሟን ከማሳወቋ በፊት እስራኤል የተረጋገጠ መረጃ እንደነበራት ያሳያል።
ጄኔራል ቃአኒ በጥሪጣሬ ማእከል ውስጥ
ስለ ኻሜኒ እንቅስቃሴ እንዲህ ያለ ወሳኝ መረጃ ሊሰጥ የሚችለው ማን ነው? የሚለው ዋነኛው ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል። በወሬዎች መሀል ስማቸው እየተነሳ ያለው የአብዮታዊ ጥበቃ የቁድስ ሃይል አዛዥ ጄኔራል እስማኢል ቃአኒ ናቸው። የቃሲም ሶሌይማኒ ተተኪ የሆኑት ቃአኒ፣ የኻሜኒ የቅርብ ረዳት እና የኢራን የውጭ ኦፕሬሽኖች ቁልፍ መሪ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር።
የሳቸው ስም መነሳቱ እና የሞሳድ መረጃ ሰጪ ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ግምት በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ በተከታታይ በተከሰቱ አጋጣሚዎች ላይ የተመሰረተ ነው። ቀደም ባሉት የእስራኤል ጥቃቶች (በኢራን ውስጥም ሆነ በሊባኖስ) ቃአኒ ጥቃቶቹ ከመፈፀማቸው ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ እንደወጡ ይነገራል።
የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ በተገደለበት ወቅት ቃአኒ በዚያው አካባቢ ቢኖሩም ሳይመቱ መቅረታቸው ነው።
ይህ መረጃ በቴህራን ውስጥ ጥርጣሬን የጨመረ ሲሆን፣ መረጃው ከከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ደረጃ ሊሾልክ እንደሚችል ግምቶችን አቀጣጥሏል። ጄኔራሉ በቁጥጥር ስር ውለው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቃቸው የሚገልጹ ዘገባዎች ሲሰራጩ ወሬው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ምንም እንኳን ይፋዊ ማረጋገጫ ባይኖርም፣ ስማቸው በየዋና ዋና ኦፕሬሽኖች ላይ በተደጋጋሚ መነሳቱ ከፍተኛ ያለመተማመን መንፈስ ፈጥሯል።
በኤክስ (X) ማህበራዊ ገጽ ላይ ደግሞ ጉዳዩ የፌዝ መልክ ይዟል፤ ተጠቃሚዎች የሞሳድ ሰርጎ ገብነት በጣም ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ ማንም ስለ ዋና ተዋናዮቹ እውነተኛ ማንነት እርግጠኛ መሆን አይችልም በማለት እያፌዙ ይገኛሉ።
ከጥቃቱ በስተጀርባ ያለው መልእክት
ከግለሰቦቹ ባለፈ፣ ዋናው ጉዳይ የግጭቱን ባህሪ ይመለከታል። በእርግጥ ሞሳድ በጥቃቱ ወቅት ኻሜኒ የት ተቀምጠው እንደነበር እንኳ የሚያውቅ ከሆነ፣ ድርጊቱ ከወታደራዊ እርምጃ በላይ ነው። ይህም በመረጃ እና በስነ-ልቦና ጦርነት ረገድ ያለውን ስትራቴጂያዊ የበላይነት የሚያሳይ መልእክት ነው።
አንድ የውጭ የስለላ ድርጅት በዓለም ላይ ካሉ በጣም ዝግ የፖለቲካ መዋቅሮች የአንዱን ውስጣዊ ሂደት እንዲህ በጥንቃቄ መለየት መቻሉ፣ ለኢራን አገዛዝ ትልቅ የታማኝነት ውድቀት ከመሆኑም በላይ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የሃይል ፍልሚያ መልክ የሚቀይር ነው።

48 መሪዎች‼️
ማንም ላያምነን ይችላል፣በአንድ ጊዜ ጥቃት ብቻ 48 የኢራን መሪዎች ሞተዋል ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።
ሞሳድ፣ሲአይኤ እንዲሁም ኤፍቢአይ በጋራ በመሆን የኢራኑ መሪ ካሜኔይ ምን እንደሚመገብ፣የት እንደሚያድር፣ከማን ጋር እንደሚነጋገር ለወራት ሲከታተሉት እንደነበር ዘገባዎች ወጥተዋል።

ሞሳድ‼️
ኢራን የአሊ ካሜኒን መሞት ከማረጋገጧ በፊት ሞሳድ የካሜኔይን አስከሬን ፎቶግራፎች ይዞ እንደነበር ይፋ አደረገ። ይህ ፎቶግራፍ የተነሳው ካሜኔይ በመስሪያ ቤታቸው እንዳሉ ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ ነው።
ይህ ሞሳድ ወደ ኢራን በጥልቀት እንደገባ ለመረዳት ከበቂ በላይ ማስረጃ መሆኑን አመላክቷል።
የቀድሞው የኢራን ፕሬዝዳንት ማሕሙድ አሕመዲነጃድ ዛሬ እንደገለጹት፤ በኢራን ውስጥ የሞሳድ ሰላዮችን ለማደን የተቋቋመው ሚስጥራዊ የደህንነት ክፍል በራሱ በሞሳድ ወኪል እና በሌሎች 20 ሰላዮች ይመራ እንደነበር ገልፀው ነበር።
ይህ በትናንትናው ጥቃት በርካታ የኢራን መሪዎች እንዲገደሉ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

የኢራንን መንፈሳዊ መሪ አሊ ኻሜኒን ለመግደል የሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ድብቅ ሴራ እንዴት ተሳካ?
ዓለም በሰላም ተኝታ በነበረችበት በዚያ ቅዳሜ ንጋት፣ የኢራን ሰማይ በፈንጂ ድምፅና በብርሃን ነበልባል ተቀደደ። ይህ ተራ ወታደራዊ ግጭት አልነበረም፤ ይልቁንም ለዓመታት ሲታቀድ የቆየ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና በከፍተኛ የደህንነት መረጃ ብልጫ የተመራ የታሪክ መለወጫ ኩነት ነበር።
የአሜሪካው ሲ.አይ.ኤ እና የእስራኤሉ ሞሳድ የኢራንን መንፈሳዊ መሪ አሊ ኻሜኒን እና የጦር አዛዦቻቸውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተጠቀሙበት ስልት የደህንነት ተቋማቱን ጥብቅ ምስጢር ፍንትው አድርጎ አሳይቷል።
ጥቃቱ መጀመሪያ የታቀደው ለዓርብ ምሽት ነበር። ሆኖም ግን፣ በመጨረሻው ሰዓት ጥቃቱ ወደ ቅዳሜ ንጋት እንዲሸጋገር ተደረገ። የዚህ ውሳኔ ምክንያት የቴክኒክ ብልሽት ሳይሆን "የወርቅ ዕድል" ተብሎ የሚጠራው የደህንነት መረጃ ነበር።
ሲ.አይ.ኤ ከኢራን አገዛዝ የውስጥ ክበብ ባገኘው መረጃ መሰረት፣ አሊ ኻሜኒ እና የኢራን ከፍተኛ የደህንነት ምክር ቤት አባላት በቴህራን እምብርት በሚገኝ አንድ ህንፃ ውስጥ ለድንገተኛ ስብሰባ እንደሚቀመጡ አረጋገጠ።
ይህንን መረጃ ተከትሎ 200 የሚጠጉ የእስራኤል F-15 እና F-35 የጦር ጄቶች ወደ ኢራን ሰማይ ተመዘገዘጉ።
የአየር መከላከያ ስርአቶችን በመጣስ በቀጥታ የኻሜኒ ቢሮ የሚገኝበትን ህንፃ ኢላማ አደረጉ።
ለወራት ሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ የኻሜኒን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሲከታተሉ ቆይተዋል። ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት፣ እንዲህ ያለውን ጥብቅ ጥበቃ የሚደረግለት መሪ በትክክል ባለበት ቦታ ማግኘት የሚቻለው በሳተላይት ብቻ ሳይሆን "በመሬት ላይ ባለ ምንጭ" ነው።
ይህ ማለት በአያቶላዎች አገዛዝ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው ግለሰቦች መረጃውን ለምዕራባውያን አሳልፈው ሰጥተዋል ማለት ነው። ይህ የተቀናጀ ስራ እንደ ቬንዙዌላው ኒኮላስ ማዱሮ የግዞት ሙከራ ሁሉ፣ በስርአቱ ውስጥ ከፍተኛ መቃቃር እና የደህንነት መላላት መኖሩን ማሳያ ሆኗል።
በጥቃቱ ሳቢያ አሊ ኻሜኒ ብቻ ሳይሆኑ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ጀነራል መሐመድ ፓክፑር እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ጀነራል አዚዝ ናሲርዛዴህ መገደላቸው ተረጋግጧል።
በተለይም አድሚራል አሊ ሻምካኒ መገደላቸው ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል፤ ምክንያቱም እርሳቸው ኢራን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በድርድር እንድትመለስ ሲወተውቱ የነበሩ ቁልፍ ሰው ነበሩ።
የአገዛዙ ደጋፊዎች በቴህራን አደባባዮች ቁርአን እየቀሩና እያለቀሱ "በቀል" ሲሉ እየዛቱ ነው።
ደበአንጻሩ አገዛዙ ያሰቃየናል የሚሉ ወጣቶችና ሴቶች በድብቅ ደስታቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ የአያቶላዎች ዘመን ማክተሙን እንደ አዲስ ጅማሮ እያዩት ነው።
ሲ.አይ.ኤ ለዋይት ሃውስ ባቀረበው ማስጠንቀቂያ፣ የኻሜኒ ሞት ያስከተለው የፖለቲካ ክፍተት ጉዳዩን ይበልጥ አደገኛ ሊያደርገው እንደሚችል ገልጿል። በስርአቱ ውስጥ የቀሩት ወታደራዊ አዛዦች ስልጣኑን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ጥረት ቀጠናው ወደ ከፋ ጦርነት ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት አለ።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጥቃቱን "የሰው ልጅ የሞራል እሴቶችን የጣሰ" ሲሉ ቢኮንኑም፣ እንደ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዝዳንት ያሉ መሪዎች ደግሞ "የአምባገነኖች ዘመን ማብቂያ" ሲሉ ገልጸውታል።
የካቲት 21/2018 ዓ.ም በታሪክ መዝገብ ላይ የሚሰፍረው የቴክኖሎጂ እና የደህንነት መረጃ ጥምረት የታላቅ ሀገርን እጣ ፈንታ በሰዓታት ውስጥ የለወጠበት ቀን ሆኖ ነው።አሜሪካንም እንደ አሸባሪ እና የጎበዝ አለቃ የቆጠሩ ብዙ አሉ።
ኢራን አሁን የቆመችው በማይታወቅ ማዕበል መካከል ነው፤ ቀጣዩ መሪ ማን ይሆናል? ጦርነቱስ ወዴት ያመራል? የሚለው የዓለም ቀዳሚ ጥያቄ ሆኗል።

8 months ago
ለአለም ስልጣኔ ያስተማረችዉ ሀገር !
" ዛን ዜንዲጊ አዛዲ ሴት ህይወት ነፃነት "/ኢራናውያን /
በሰዉ ልጆች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆስፒታል ገንብታ ማከም የጀመረች ።
#ethiopia | በአልጀህብራን ቀመር ሂሳብ አስልታ ለአለም ያስተማረች ። ኬሚካል በማዋሀድ የጥበብ የተራቀቀች ። በአርክቴክቸር ሳይንስና ዲፕሎማሲ በመካከለኛው ምስራቅ አሀዱ ያለች ።በጠቢባን ልጆቿ በቀጠናው ለመጀመሪያ ጊዜ ድሮን አምርታ ለገበያ ያቀረበች የሴቶችን የመማር ነፃነት በመስጠት 70 % ሴቶች በዲግሪ ደረጃ ያስመረቀች ። ሴቶችን ማስተማር እንብዛም ባልሆነበት ቀጠኒ 25% የሀገሪቱን የኒኩሊየር ሳይንቲስቶች ለሴት ልጆቿ የሰጠች ።በፕላኔታችን በምዕራባውያን ማዕቀብ ብዛት ቀዳሚ የሆነች የአለም ፖለቲካ የወሬ ማጣፈጫ ሀገረ ኢራን ።
እነሆ በዛሬው አለምን እንወቅ ዝግጂታችን ወገንተኛዉ የአዉሮጳዉያን ሚዲያዎች ክፉዋን ብቻ እየጠቀሱ የሚነግሩን ጥንታዊቷን ኢራንን ልንጎበኝ ወድደናል ።
አብራችሁን ስትዘልቁ ቀደምት ኢትዮጵያዊን ሀበሾች መኖርያ የሆነችዉን በባህል ከእኛ ጋር የምትመሳሰለዉን ከእግር እስከ እራሷ እየቃኘን ስለሀገሪቱ ሰምታችሁት የማታዉቁትን ታሪክ እንነግራችኋለንና ከፓለቲካ ምልከታ ገለል ብላችሁ ሌላ ገፅታዋን ለማየት አብራችሁን ዝለቁ ።
መቼም እኛ ኢትዮጵያዊያን ከምንታወቅበት አንዱ መግደርደርና እንብላ እንጠጣ የሚል ሰወኛ ግብዣችን ነዉ ታዲያ ይህ ባህል በእኛ ብቻ አይደለም ኢራንም ዉስጥ ወላ በሬስቶራን ወይም በካፌ እንብላ እንጠጣ መባባል ። እየፈለጉም ቢሆን መግደርደርን ከእነ ሙሉ ክብሩ እናገኘዋለን ።
ደግሞ ሌላ መቼም እንግዳ በቤት ለማስተናገድ ቡና ማፍላት የተለመደ ነዉ እነሱም ታሮፍ በሚሉት የእኛን መሰል ባህል ሻይ አፍልተዉ እግር አጥበው አልጋ ለቀው ያስተናግዳሉ ።
እንደ ታሪክ አዋቂዎች ከሆነ በኢራን ከሚገኙ በርካታ ዝርያዎች መካከል በደቡባዊ ኢራን ሆርሙዝጋን ግዛት የሚኖሩት ከ4 ክፍለዘመን ጀምሮ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ጉዳይ የሚሳተፉ መነሻቸው ከኢትዮጵያ እንደሆነ የሚነገርላቸው በአሴርያዉያን ስርዎ መንግስት ጎልተዉ የነበሩ ከሀበሻ የሄዱ አፍሮ ኢራናውያን አስተምረዋቸዉ ይሆናል ።
ወጋችን ከተገረምኩበት ጉዳይ ልሰልስ
ከሰሞኑ አንዳንዶቹ የኢራንን 1 ዶላር በሚሊዮን ተመነዘረ የሚል የገንዘብ ጉዳይ አንስተው ሙድ ለመያዝ ሲሞክሩ አይቻለሁ ። በእርግጥ ማዕቀቡ ጉዳት ቢኖረውም የኢራን የገንዘብ ቁጥር የሚጀምረው ከአምስት ሽህ ሪያል ነዉ ማለትም የእኛ አስር ሳንቲም እንደማለት ። ለማንኛውም ኢራን የብር ኖቶ በቁጥር ሲሰማ ቢያስደነግጥም የ ሁለት ሚሊዮን ድረስ ኖቶች አሉ ።
ከአሜሪካ ጋር በገባችበት እሰጣ ገባ ያልተጣለባት የማዕቀብ ናዳ የለም ። ምናልባት ሀገሪቱ ኢራን ባትሆን ኑሮ የማዕቀቦቹን ናዳ የሚሸከም ጫንቃ ሊኖራት አይችልም ።
ይህ ማዕቀብ ያላጎበጣት ኢራን ምንም ጥሬ እቃ ከዉጭ ማስገባት ባትችልም 50 ዶላር ባልሞላ ወጭ ተምዘግዛጊ ሰዉ አልባ ድሮኖች ። ሰማይ ሰንጣቂ ሚሳኤሎች ቀላልና ከባድ መሳርያዎች ተሻግራ 60% የተብላላ ኒኩሊየር ባለቤት መሆን ችላለች ።
የአያቶላሆቹ በራስ መቆም ምሳሌዎች ናቸዉ ። ዘጠና ከመቶ የመኪናውን ክፍል በራሷ የምትሰራቸዉ የጭነት የትራንስፖርት ሞተርና የግል "ኢራን ኮድሮ" ሳይፓ "ፋርስ ኮድሮ " የመኪና ብራንዶችን በአመት 1 ሚሊዮን መኪኖች አምርታ ትሸጣለች ።
ሀገሪቱ ትላንቷን አጥብቃ ትወዳለች ። ዋና ከተማዋ ታሪክን ከባህል ዘመናዊነትን ከፓለቲካ ጋር ያጣመረች ከተማ ናት ። ከእነዚህም መካከል የከተማዋ እንብርትና የሀገሪቱ የእርቀት ስሌት ዜሮ ዜሮ ተብሎ የሚጀመርበት የፋርስን ስልጣኔ ለማስታወስ የተገነባው አዛዲ ታወር የአለማችን ስድስተኛው ረጂሙ ታወር ሚላት ታወር ጨምሮ ማንነቷን ገላጭ አርክቴክቸር ዉጤቶች ። ከ400 አመታት በላይ እድሜ ያለዉ የግራንድ ባዛር ዛሬም በድምቀት የፋርስ ምንጣፎችን የሀገር በቀል ምርቶች ይሸጡበታል ።
ከ60 በላይ ዩንቨርስቲዎች መገኛ የሆነችው ቴህራን በመካከለኛው ምስራቅ ትልቅ እንደሆነ የሚነገርለት ሜትሮ ዘመናዊ ትራንስፖርት በከረሜላ መግዣ ዋጋ ለህዝብ አገልግሎት ይሰጣል ።
የዱባይን ዱባይ ሞል የቻይናውን ሳዉዝ ቻይና ሞል በመብለጥ የአለማችን ትልቁ የገበያ ሞል በኢራን ይገኛል 2ሚሊዮን ካሬ ይሰፋል ።
በቴህራን የፐርሺያን ስልጣኔ 2050 አመት መታሰቢያ ባከበረችበት ወቅት በ24 አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ንድፉ የተሰራ የነፃነት ሀዉልት የከተማዋ ግርማ ነዉ በየቀኑ አምስት ሚሊዮን ተሳፋሪዎች የሚያስተናግደው ዘመናዊ የምድር ዉስጥ ባቡርና ሜትሮ አገልግሎት በመስጠት ከጎረቤቶቿ ትለያለች ።
ከቴህራን ወጣ ስንል ደግሞ የኢራንን መንፈሳዊ ከተማ ማሻድን እናገኘዋለን ። በአመት 25 ሚሊዮን ጎብኝዎችነ የምታስተናግድ ከምድራችን ትላልቅ የእምነት ስፍራዎች አንዱ የሆነዉን መስጊድ የያዘች በሽአ አማኞች ቅድስት የተባለች ከተማ ናት ።
ኢስፋሀን ደግሞ የሀይማኖት መቻቻል የሚታይባት የአይሁዶች ቤተ እምነት የክርስትያን አብያተክርስቲያናት መሳጂዶች ጎን ለጎን የሚገኙባት ዩኔስኮ በቅርስነት የመዘገባት ከተማ ናት ።
የአያቶላሆቹ ሀገር በሀገርነት ሽህ አመት የሚለው ቁጥር ከሚያዉቁት ጥቂቶች አንዷ ከጫካ ወጥቶ ቤት ቀልሶ መኖር የጀመረባት የመግስታዊ ስርአት አስተዳደር በመስኖ ማረስ ከቃል አልፎ በፅሁፍ መግባባት መነሻው ከዚሁ ነዉ ።
አለማችን ላይ ለዘመናት የራሷን የቀን አቆጣጠር እስካሁን የምትጠቀም የራሷ ካላንደር ያላት ባህልን ከታሪክ በራስ የመቆም መቻልን ከዘመናዊነት በማዋሀድ እልፍ የቱሪስት መዳረሻዎች የያዘች ብትሆንም የአለም ስርአት በጣለባት ማዕቀብ ተጠቃሚ አልሆነችም
ለማሳረግያ አንድ ታሪክ እናካፍላችሁ ።
እስራኤል እና ኢራን የዛሬን አያድርገው እና ወዳጅ ሀገራት ነበሩ ያዉም የአሜሪካዉን ሲአይኤ ያልደረሰበት ምስጢር የተጋሩ ወዳጆች ።
ዛሬ ካልተጋደልን የሚሉት ሁለቱ ፍቅራቸዉ ለአይታ ያስቀና ነበር እስራኤል ዙርያውን ያሉ የአረብ ሀገራት ነዳጅ አንሸጥም ባሏት ወቅት ኢራን በሯን ከፍታ ከመስጠት ባሻገር ከአሜሪካ ተደብቀው ፕሮጀክት ፍላወር የተባለ የአሜሪካን ሚሳኤሎች እስራኤላውያን በእዉቀት ኢራን በገንዘብ ተባብረው ያመርቱም ነበር ።
ከአራት አስርታት ዓመታት በፊት እስራኤል ሀገር ለመሆን እና በአንድ እግሯ ለመቆም ስትጣጣር በነበረበት ወቅት ለእስራኤል የሀገርነት እውቅና ለመስጠት ቀዳሚ ከነበሩ ሁለት የእስልምና እምነት ተከታይ ሀገራት መካከል ኢራን አንዷ ነበረች።
ኢራን የአየር መቃወሚያ መርከቦች ራዳሮች ሌሎችም መሳርያዎች በእስራኤል በኩል ይቀርብላት ነበር ዛሬ ላይ የሁለቱ ሀገራት ግጭት መንስኤ የሆነው ኒኩሊየር እንድታመርትም የእስራኤል ተሳትፎ አለበት ።
ሞሳድ በመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራትን የሚሰልልበት ቢሮዉ ቴህራን ላይ ነበረው በአሁኑ ጊዜ በቴህራን ከ30 ሽህ በላይ እስራኤላዉያን ይኖራሉ ትላንት ተመልካችና ሰሚ የሚቀናባቸዉ ሁለቱ ሀገራት በሀይማኖት የተጀቦነ ፖለቲካ ነጠላቸዉ እንጂ ህዝብ ለህዝብስ ጥላቻ የለባቸውም ። ማን ያዉቃል ነገ ደግሞ ፍቅራቸው ሊመለስ ይችላል ።
ታዴ የማመይ ልጅ

9 months ago
9 months ago
እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠት እና የቀይ ባሕር ቀጠና አዲሱ የጂኦፖለቲካዊ ለውጥ
ከመሀመድ ካህላፍ ፅሁፍ የተወሰደ
ሶማሊላንድ ማን ናት?
ሶማሊላንድ በሰሜናዊ ሶማሊያ፣ በኤደን ባህረ ሰላጤ ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ቀጠና ነው። በምስራቅ ከፑንትላንድ፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በምዕራብ ከጂቡቲ ጋር ይካለላል። ቀጠናው እ.ኤ.አ. በ1991 የማዕከላዊ ሶማሊያ መንግስት መፈራረስን ተከትሎ፣ ነጠላ የነጻነት አዋጅ አውጇል። ይህ ውሳኔ የተመሰረተው እስከ 1960 ድረስ የእንግሊዝ ጥበቃ የሚደረግለት ራሱን የቻለ ግዛት እንደነበረና በኋላም ከጣሊያን ሶማሊላንድ ጋር በመቀላቀል የሶማሊያ ሪፐብሊክን መመስረቱን ታሪክ በማጣቀስ ነው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቀጠናው ከቀሪው የሶማሊያ ክፍል ጋር ሲነጻጸር በአንጻራዊ ሁኔታ ውጤታማ የሆኑ የራስ-አስተዳደር ተቋማትን መገንባት ችሏል። እነዚህም የሚመረጥ መንግስት፣ ፓርላማ፣ የጸጥታ አገልግሎት፣ የሀገር ውስጥ ገንዘብ እና የተረጋጋ የአስተዳደር ስርዓትን ያካትታሉ።
ይህም በምዕራባውያን ጽሑፎች ውስጥ ግጭት በበዛበት አካባቢ እንደ "የመረጋጋት ደሴት" ተደርጎ እንዲገለጽ አድርጎታል። ሆኖም ግን፣ እስካሁን ድረስ ይፋዊ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላገኘ ሲሆን፣ በህግ ደረጃም የሶማሊያ ሪፐብሊክ አካል ሆኖ ይቆጠራል።
የእስራኤል እውቅና መስጠት
ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን የዲፕሎማሲ ግንብ የሰበረ ታሪካዊ እርምጃ በመውሰድ፣ እስራኤል ሶማሊላንድን ዋና ከተማዋ ሃርጌሳ የሆነ ሉዓላዊ እና ገለልተኛ ሀገር አድርጋ በይፋ ማወቋን አስታውቃለች።
እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ያሳለፈች የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገር ሆናለች።
ይህ ለውጥ ሊመጣ የቻለው በኅዳር 2024 በሶማሊላንድ ውስጥ በተካሄደው ምርጫ የሥልጣን መዋቅሩ በመቀየሩና እስካሁን ከነበረው የተለየ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን መንገድ በመከፈቱ ነው። በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው የዋታኒ ፓርቲ መሪ የሆኑትና በሶማሊያ የዲፕሎማሲ መስክ ልምድ ያላቸው የተቃዋሚው ዕጩ አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ (በቅጽል ስማቸው "አይሮ") ማሸነፋቸው ለዚህ ምክንያት ሆኗል።
እንደ እስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፣ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ መስኮች ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት በፍጥነት ለማስፋፋት አቅዳለች።
ከዚህም በተጨማሪ በኤደን ባህረ ሰላጤ እና በባብ አል-መንደብ ሰርጥ አቅራቢያ ካለው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ጋር የተያያዙ ያልተገለጹ የደኅንነት ትብብሮችንም ታደርጋለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለዚህ "የዲፕሎማሲ ስኬት" አስተዋጽኦ ላደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩና ለሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ ምስጋና አቅርበዋል።
የዓረብ እና የቱርክ ቁጣ - የግዳጅ ጥምረት
ለዚህ ውሳኔ ከቀጠናው የተሰጠው ምላሽ ፈጣንና ጠንካራ ነበር። ግብፅ፣ ሶማሊያ፣ ቱርክ እና ጅቡቲ በጋራ ባደረጉት ስብሰባ የእስራኤልን ውሳኔ አውግዘዋል። የሶማሊያን አንድነትና ሉዓላዊነት የሚጥስ ማንኛውንም እርምጃ እንደሚቃወሙና ለሶማሊያ ሕጋዊ ተቋማት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ ይህ የእስራኤል እውቅና ግብፅና ቱርክን "የግዳጅ ጥምረት" ውስጥ በመክተት በሞቃዲሾ የሚገኘውን የፌዴራል መንግሥት በወታደራዊ ኃይል እንዲደግፉ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህ ደግሞ በተለይ በሶማሊላንድና በፑንትላንድ መካከል በሚገኘው "ሱል" ግዛት ላይ ቀጠናዊ ኃይሎችን ወደ ውክልና ጦርነት ሊያስገባ ይችላል ተብሎ ይፈራል።
የምስጢራዊ ጉብኝት ውጤት
በዚህ ወር የተሰጠው እውቅና በድንገት የመጣ ሳይሆን፣ በከፍተኛ የደኅንነትና የዲፕሎማሲ ሥራዎች የታጀበ ነበር። ፕሬዝዳንት አይሮ ጥቅምት ላይ ወደ እስራኤል ምስጢራዊ ጉብኝት በማድረግ ከሞሳድና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። ይህ ጉብኝት "እውቅና በስትራቴጂካዊ ቦታ" በሚል ቀመር የደኅንነትና የፖሊሲ መሠረቶችን ጥሏል።
ለኔታንያሁ ይህ ስምምነት ዲፕሎማሲያዊ ድል ሲሆን፣ ይህም በዋሽንግተን ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት ስብሰባ እንደ ትልቅ ስኬት ይዘውት ያቀረቡት ጉዳይ ነው።
ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማዛወር ዕቅድ
የእስራኤል ውሳኔ ከወራት በፊት እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ወደ የአፍሪካ ቀንድ (ሶማሊላንድ እና ፑንትላንድን ጨምሮ) ለማዛወርና ለማስፈር እያሰበች ነው ከሚለው ዘገባ ጋር ተያይዟል። እስራኤል ለሶማሊላንድ ለሰጠችው እውቅና እና የገንዘብ ድጋፍ በምትኩ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ፍልስጤማውያን ሶማሊላንድእንድትቀበል ለማድረግ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማሕሙድ አባስም ይህንን የእውቅና እርምጃ ፍልስጤማውያንን ለማፈናቀል የሚደረግ የቴል አቪቭ ተስፋ የቆረጠ ሙከራ አካል ነው በማለት ተቃውመዋል።
የሦስቱ ዋና ዋና ተግባራት መድረክ
ከሁሉም በላይ ሶማሊላንድ ለእስራኤል በርካታ መልክዓ ምድራዊ ጥቅሞችን ትሰጣለች። የ850 ኪሎ ሜትር የባሕር ጠረፍ ያላት ሶማሊላንድ፣ የባብ አል-መንደብ መግቢያን ለመቆጣጠር ትረዳለች። የእስራኤል ብሔራዊ የደኅንነት ጥናት ተቋም (INSS) እንደሚለው፣ ይህ አካባቢ ለእስራኤል ሦስት ዋና ዋና ጥቅሞችን ይሰጣል፦
ከየመን የሚተኮሱ ሚሳይሎችንና ድሮኖችን ለመከታተልና የራዳር መሣሪያዎችን መትከል።
በጠላት ዒላማዎች (በተለይም በሁቲዎች) ላይ ለሚደረጉ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች እንደ መነሻ መጠቀም።
ቀይ ባሕር "የኢራን ሐይቅ" እንዳይሆንና ለሁቲዎች የሚደርሰውን የባሕር ላይ የአቅርቦት መስመር መቁረጥ።
ወታደራዊ ካምፕ... በርበራ ወይስ ዘይላ?
አንዳንድ ዲፕሊማቶች እንደሚሉት ይህ እውቅና ከእስራኤል ውጭ ትልቁን ወታደራዊ ካምፕ ለመመሥረት የሚደረግ የፖለቲካ ዝግጅት ነው። ምርጫው በሁለት ቦታዎች መካከል ነው፦
የበርበራ ወደብ፦ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የፈሰሰበት፣ ዘመናዊ መሠረተ ልማትና ወታደራዊ አየር ማረፊያ ያለው፣ እንዲሁም ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደው አውራ ጎዳና መነሻ በመሆኑ የተመረጠ ነው።
የዘይላ ከተማ፦ ከጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝና ለባብ አል-መንደብ በጣም ቅርብ የሆነች ታሪካዊ ቦታ ናት። ይህም ለየመንና ለኤርትራ ቅርብ በመሆኑ ለኤሌክትሮኒክስ የስለላ ሥራዎች ተመራጭ ያደርጋታል።
የኢኮኖሚ ማበረታቻዎች እና የኢትዮጵያ ሚና
እስራኤል በ "በርበራ ኮሪደር" አማካኝነት ኢኮኖሚዋን ከአፍሪካ ገበያ ጋር ለማገናኘት ትፈልጋለች። ይህ ኮሪደር ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ ሲሆን፣ እስራኤል በጅቡቲ ላይ ብቻ ከመደገፍ እንድትወጣና የቴክኖሎጂ ምርቶቿን ወደ ሰፊው የኢትዮጵያ ገበያ እንዲሁም ወደ ኬንያና ኡጋንዳ እንድታደርስ ይረዳታል።
የቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ምላሾች
ሶማሊያ፦ እርምጃውን "የሉዓላዊነት ጥሰት" በማለት አውግዛለች። ከግብፅ ጋር የፈረመችውን የጋራ መከላከያ ስምምነት ወደ መተግበር ተሸጋግራለች።
ግብፅ፦ በእስራኤልና በኢትዮጵያ መካከል የሚፈጠር ጥምረት ከደቡብ በኩል ይከበኛል የሚል ስጋት አላት። ይህም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ የኢትዮጵያን አቋም ሊያጠናክር ይችላል ብላ ታምናለች።
የአፍሪካ ሕብረት፦ የቅኝ ግዛት ድንበሮች መከበር አለባቸው የሚለውን መርህ በመጥቀስ እውቅናውን ውድቅ አድርጓል። ይህም በሌሎች ሀገራት (እንደ ናይጄሪያና ካሜሩን) የመገንጠል እንቅስቃሴን ሊያነሳሳ ይችላል የሚል ስጋት አለው።

10 months ago
እስራኤል ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና በይፋ መስጠቷን አስታወቀች
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክን እንደ ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገር በይፋ መቀበሉን አስታወቁ። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ለውጥ መሆኑ ተገልጿል።
ኔታንያሁ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ዕውቅናው የተረጋገጠው ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እና ከሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ ጋር በጋራ በተፈረመ "የሁለትዮሽ ስምምነት" አማካኝነት ነው።
ጠ/ሚሩ በመግለጫቸው ቀደም ሲል በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አነሳሽነት የተፈረመውን "የአብርሃም ስምምነት" መንፈስን የተከተለ መሆኑን ገልፀዋል።
ነታንያሁ ፕሬዝዳንት አብዲራህማንን "ታሪካዊ መግለጫ" ባሉት በዚህ ስምምነት ላይ እንኳን ደስ ያለዎት ያሏቸው ሲሆን፤ ለሰላም እና ለመረጋጋት ላሳዩት ቁርጠኝነትና አመራር ምስጋና አቅርበውላቸዋል። በተጨማሪም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።
እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን በወሰዱት እርምጃ ደስታቸውን ገልጸው፤ እስራኤል ሽብርተኝነትን በመዋጋትና ቀጣናዊ ሰላምን በማስፈን ረገድ ለምትጫወተው ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ሂደት መሳካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ሳር፣ የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ እና የእስራኤል የደህንነት ተቋማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል።
ነታንያሁ እንደገለጹት፤ እስራኤል በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በሚደረጉ ሰፊ ትብብሮች አማካኝነት ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስፋፋት አቅዳለች።
Via አዲስ ስታንዳርድ

1 year ago
ኢራን ለእስራኤል ከዋነኞቹ ሰላዮች መካከል አንዱን በስቅላት ቀጣች
ኢራን ባህማን ቹቢ-አስል የተባለውን ሰው ሰኞ እለት በሞት መቀጣቱን የኢራን የፍትህ አካላት የዜና ማሰራጫ ሚዛን ዙግቧል። ተከሳሹ በኢራን ውስጥ ለእስራኤል በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ሰላዮች መካከል አንዱ ነው ።። ከእስራኤል ጋር ለአስርት አመታት በዘለቀው የጥላቻ ጦርነት ውስጥ የተዘፈቀችው ኢራን ከእስራኤል የሞሳድ የስለላ አገልግሎት ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን እና በሃገሪቱ ያለውን እንቅስቃሴ አመቻችተዋል የተባሉ በርካታ ግለሰቦችን በሞት ቀጥታለች።
ሞሳፍ የተከሳሹን ትብብር በማግኘት ዋና አላማው የመንግስት ተቋማትን የመረጃ ቋት ማግኘት እና የኢራን የመረጃ ማእከላት ጥሰት መፍጠር ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን መንገድ መመርመርን ጨምሮ ሌሎች ሁለተኛ ደረጃ ግቦችን አሳክቷል ሲል ሚዛን ዘግቧል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተከሳሹን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ የሙስና ወንጀል በሚል ክስ የሞት ቅጣቱን ተግባራዊ አድርጓል። የኢራን እና የእስራኤል ግጭት በሰኔ ወር እስራኤል በኢራን ውስጥ የተለያዩ ኢላማዎችን ስትመታ፣ ሞሳድ በሀገሪቱ ውስጥ በጥልቅ የተመሰረተ ኦፕሬሽን በማድረግ ወደ ቀጥታ ጦርነት ተሸጋግሯል። በዚህ አመት ለእስራኤል በመሰለል የተፈረደባቸው ኢራናውያን ላይ የሚደርሰው ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ ቢያንስ 10 የሞት ፍርድ ተበይኗል።

ባባክ ሻህባዚ የተባለ ግለሰብ ለእስራኤል ብሄራዊ መረጃ ድርጅት (ሞሳድ) በመሰለልና በመተባበር ወንጀል ተከስሶ በኢራን የሞት ፍርድ ተፈጽሞበታል።
የኢራኑ የዜና ወኪል ታስኒም እንደዘገበው ከሆነ ለሞሳድ ተባባሪዎች መረጃ ሲያቀብል የነበረው ሻህባዚ፣ የፍርድ ሂደቱ ከተጠናቀቀና ውሳኔው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጸና በኋላ ትናንት ጠዋት ላይ የሞት ፍርዱ ተፈጽሞበታል።
ባባክ ሻህባዚ በቴሌኮምዩኒኬሽን፣ በወታደራዊና በጸጥታ ድርጅቶችና ማዕከላት ውስጥ ከሚሰሩ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የኢንዱስትሪ ማቀዝቀዣ መሳሪያዎችን ዲዛይንና ተከላ በሚመለከት ተቋራጭ ሆኖ ይሰራ ነበር።

ሰበር መረጃ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገደሉ
የየመኑ የሕውቲ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ አል-ራሃዊ ትናንት በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የየመን ቴሌቪዥን ጣቢያ አል-ጁምሁሪያ ዘግቧል።
የእስራኤል አየር ሀይል ትናንት 10 የሀውቲ መሪዎች ስብሰባ ላይ በነበሩበት ወቅትና የየመን የሐውቲዎች መሪ አላ ሐውቲ ትናንት ምሽት 10 ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን ሰብስቦ ንግግር እያደረገ በሚገኝበት ሰዓት የእስራኤል አየር ኃይል ከሞሳድ በደረሰው መረጃ መሰረት አየር ላይ ሁለት ሺህ ማይል እርቀት ላይ ሆኖ በምሽግ ደርማሽ እና መሬት ሰርጓጅ ቦንብ ከባድ ጥቃት ሰንዝሯል። በዚህ ጥቃት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የመከላከያ ሚንስትሩ፣ ወታደራዊ አዛዡን ጨምሮ የታጣቂው ቡድን ከፍተኛ አመራሮች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ዩሮ ኒውስ የየመን እና የእስራኤል የመረጃ ምንጮቹን ጠቅሶ
ዘግቧል።
Seledadotio

የእስራኤል ድንገተኛ ጥቃት‼️
የየመን የሐውቲዎች መሪ አላ ሐውቲ ትናንት ምሽት 10 ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን ሰብስቦ ንግግር እያደረገ በሚገኝበት ሰዓት የእራኤል አየር ኃይል በምሽግ ደርማሽ እና መሬት ሰርጓጅ ቦንብ ከባድ ጥቃት ሰንዝሯል።
የእስራኤል አየር ኃይል 2 ሺህ ማይል አይር ላይ ነዳጅ እየሞላ ሐውቲው መሪ አላ ሐውቲን ንግግር እያደረገና ባለሥልጣኖችን ስብሰባ እንደተቀመጡ ነው ጥቃት የተፈፀመው።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ባለሥልጣኖች በቀጥታ የሐውቲዎችን ስብሰባ ቀደም ብሎ ሞሳድ በተከለው ካሜራ ስብሰባ ያዩ ነበር ከዚያም ጠቅላዩ የአየር ኃይሉ በቀጥታ ወደ የመን እየበረረ መድረሱን ይመለኩቱ እንደነበር ተሰምቷል።
አየር ኃይሉ ከላይ ልክ እንደ ዝናብ በለቀቀው ምሽግ አፍራሽና መሬት ደርማሽ ቦንብ በሐውውቲዎች ላይ ሲለቅ ጠቅላይ ሚ/ር ቤናሚር ናታናሁን ይመለከቱ ነበር ተብሏል ::
በጥቃቱ ሁሉም የሀውቲ መሪዎች እንደተገደሉ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተገለፀ ቢሆንም ከእስራኤል ማረጋገጫ አልተሰጠም።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱ የሀውቲ መሪዎችን ያነጣጠረ መሆኑን ጠቁመው የሀውቲ መሪዎች ስለመገደላቸው መረጃ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሀውቲ በበኩሉ መሪዎቼ አልተገደሉም እስራኤል እንደተለመደው በንፁሃን ላይ ነው ጉዳት ያደረሰችው ሲል ማስተባበያ ሰጥቷል።

እስራኤል ፍልስጤማውያን ወደ ደቡብ ሱዳን ለማዛወር እያሰበች ነው ተባለ
የእስራኤል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሻረን ሃስኬል በጦርነትና በድርቅ ለታመሰችው የአፍሪካ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ ጉብኝት በማድረግ የጋዛ ነዋሪዎችን የማዛወር እድልን እየተነጋገሩ ነው። ጁባ ለጉብኝቱ ምክንያት ይህ አይደለም ብላ ብትክድም፣ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ በርካታ የዜና ድረ-ገጾች የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሳብን ዳግም አንስተውታል።
የእስራኤል መንግስት ከጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያንን “በፈቃደኝነት” ወደ ጦርነት ወደተመሰችው የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ለማዛወር ከደቡብ ሱዳን ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የአሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የእስራኤል ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻረን ሃስኬል ዛሬ በጁባ ተከታታይ ስብሰባዎችን አካሂደዋል። ይህ የእስራኤል መንግስት ተወካይ ወደ አፍሪካ ሀገር ያደረጉት የመጀመሪያው ይፋዊ ጉብኝት ነው። ሃስኬል ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ከፓርላማው አፈ-ጉባዔ እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ይገናኛሉ።
ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚሰራ የአሜሪካ የሎቢ ድርጅት መስራች የሆኑት ጆ ስዝላቪክ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፣ የውይይቱ ዋና ትኩረት የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ዳግም ለማቋቋም የስደተኞች ካምፖች ግንባታ ነው። እነዚህ ካምፖች በራሱ በአይሁድ ሀገር የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል። ይህ ዕቅድ ተግባራዊ ከሆነ፣ ለወራት በቦምብ ድብደባ ደክሞና ተርቦ የነበረውን ህዝብ ከአንድ ወድሞና በድርቅ ከታመሰ አካባቢ ወደ ሌላ በኃይለኛ ግጭት እና አስከፊ ሰብአዊ ቀውስ ወደታመሰ አካባቢ ማዛወርን ያስከትላል።
ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤልም ደቡብ ሱዳን ከጋዛ ሰርጥ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ዳግም ለማቋቋም እስራኤል ከምትደራደርባቸው ሀገራት አንዷ መሆኗን አረጋግጧል።
ቴል አቪቭ ለወራት ጋዛውያንን ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነች ሶስተኛ ሀገር ስትፈልግ ቆይታለች፣ ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኔትንያሁ ዕቅድ ዓለም አቀፍ ህግን የሚጻረር በቀላሉ በግድ የማባረር ተግባር ነው ብለው ቅሬታ ቢያቀርቡም። ከዚህ ስልት ጀርባ ያለው፣ ድርጅቶቹ እንደሚያወግዙት፣ ሌላ ሳይሆን ጋዛን ባዶ የማድረግ እና አዲስ የእስራኤል ሰፈራዎች በጋዛ እንዲፈጠሩ የመፍቀድ ፍላጎት ነው።
ግብፅ እምቢ ካለች በኋላ፣ አይሁድ ሀገር በሌሎች ቦታዎች ውሃውን ለመፈተሽ ወስኗል። በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ፣ የአሜሪካው ድረ-ገጽ አክሲዮስ የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኔአ እና የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ስብሰባን በተመለከተ ዘግቧል። በዚህ ስብሰባ ላይ ባርኔአ የእስራኤልን ከኢትዮጵያ፣ ከኢንዶኔዥያ እና ከሊቢያ ጋር የሚያደርጉትን ውይይት ለዋይት ሃውስ ረዳቱ አሳውቋል።
ደቡብ ሱዳን ጋዛውያንን ለመቀበል ፍቃደኛ እንደምትሆን የሚጠቁሙ ሀሳቦችን “መሰረተ ቢስ” በማለት ውድቅ አድርጋለች። በX ላይ በወጣ መግለጫ መሰረት እነዚህ ዘገባዎች “የጁባን መንግስት ይፋዊ አቋም ወይም ፖሊሲ አያንጸባርቁም” ብላለች።
ከሃስኬል ጋር የሚደረጉት ንግግሮች ይፋዊ ዓላማ “በጤና፣ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና በሃይል መስኮች ትብብርን ማጠናከር፣ በሲቪል ልማት እና በደህንነት መስኮች የጋራ ተነሳሽነቶችን ማስተዋወቅ፣ ክልላዊ ትብብርን ማጠናከር እና ሀገሪቱ ከጎረቤት ሱዳን ጋር ባለው ጦርነት ምክንያት ለምትገጥማቸው ተግዳሮቶች የእስራኤልን ሰብአዊ እርዳታ አማራጮች መገምገም” ነው ብላለች ።
ደቡብ ሱዳን በዓለም ላይ ካሉ በጣም ፖለቲካዊ ችግር ያለባቸው ሀገራት አንዷ ነች። ከ2011 ጀምሮ ነጻ ብትሆንም፣ ከ400,000 በላይ ሰዎችን የገደለ እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለ፣ ምግብና ውሃ የሌላቸው አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ጥልቅ ጠባሳ ጥሏል። በሰኔ ወር፣ ኤፍኤኦ፣ ዩኒሴፍ እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን የናይል ግዛት ያለው ግጭት በመባባሱ ምክንያት በደቡብ ሱዳን በሚገኙ ሁለት አውራጃዎች የሚኖሩ ሰዎች በቀጣይ ወራት በድርቅ አደጋ ላይ መሆናቸውን አስጠንቅቀዋል።
ይህ ጦርነት ቤቶችን እያወደመ፣ የኑሮ ሁኔታዎችን እያበላሸ እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን እያደናቀፈ ነው። በቅርቡ፣ ድንበር የለሹ የሀኪሞች ቡድን ድርጅት በደቡብ ሱዳን የመካከለኛው ኢኳቶሪያ ግዛት በሚገኙ የየይ ወንዝ እና ሞሮቦ አውራጃዎች ውስጥ አንድ ሰራተኛ ለብዙ ሰዓታት ታፍኖ በመቆየቱ ምክንያት ሁሉንም ተግባራቶቹን ለጊዜው—ቢያንስ ለስድስት ሳምንታት—ለማቆም መገደዱን አስታውቋል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንደገለጸው፣ በምግብ እጥረት ስጋት ውስጥ ያሉ ሰዎች ቁጥር ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ህፃናት ይገኙበታል።

አዲስ ፍጥጫ
ኢራን በትናንትናው ዕለት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ አጠቃላይ አስር ከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮችን ለመግደል ማቀዷን ስም ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጋለች።
ይህን ተከትሎ እስራኤል ከኢራን ሊመጣ ከሚችል ጥቃት እራሷን ለመከላከል ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሁሉም የጦር አመራሮች እና የሞሳድ የስለላ ድርጅት ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በኢራን ከሚገደሉ ስም ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር "የኢራኑን መሪ አያቶላህ አልካሜኒ ከተደበቁበት ጥልቅ ዋሻ(Bunker)ሲወጡ ሰማዩን እንዲመለከቱና ማንኛውንም ድምፅ በትኩረት እንዲያዳምጡ እመክራለሁ፣የቀዩ ሰርግ ደጋሾች(Israel air force & Mossad) ዛሬም አሉ"ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢራን በቅርቡ 40 የሚጠጉ J-10C የተባለ የቻይና ስውር ተዋጊ አውሮፕላን መረከቧ የሚታወስ ነው።

እስራኤል ያጠቃችን ከራሳችን ሰዉ ባገኘችው መረጃ ነዉ ! / ቴህራን 7
የኢራን ከፍተኛ ጄኔራሎች፣ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጣቢያዎቿን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ከዉስጥ በመሆን እየሰለለ ለእስራኤል የስለላ ድርጅት መረጃ በማቀበል ያስደበደበዉ ኢራናዊ የኒውክሌር ሳይንቲስት መሆኑ ታወቀ ።
የፍትህ አካላት የዜና ማሰራጫ ሚዛን ረቡዕ እለት እንዳስታወቀው ቫዲ ለእስራኤል በመሰለል እና በእስራኤል በሰኔ ወር በእስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት የተገደለውን የኒውክሌር ሳይንቲስት መረጃ በማስተላለፉ የተከሰሰ ሲሆን
በሀገር ክህደት የተከሰሰውን ሰው በሞት መቀጣቷን የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።
ሚዛን እንደዘገበው የሞት ፍርድ የተፈረደበት ቫዲ በኢራን “አስፈላጊ እና ቁልፍ ድርጅቶች” ውስጥ በአንዱ ውስጥ ሰርቷል ።“በአገሪቱ የውስጥ እና የውጭ ደህንነት ላይ በርካታ ወንጀሎችን ፈጽሟል ይህም በሕዝብ ጸጥታ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል ፈጥሯል” ብሏል።
ከአሚር ከቢር የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኒውክሌር ኢንጂነሪንግ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት ቫዲ የሞት ፍርድ ከተፈረደባቸዉ በኋላ ሰጡት ተብሎ የፍትህ አካላት የዜና ማሰራጫ በተላለፈው የቪዲዮ የእምነት ክህደት ቃል “የኑክሌር ቁሳቁሶችን ወደ ዩራኒየም መለወጥ ፋሲሊቲ (ዩሲኤፍ) እና የነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካ (ኤፍኤምፒ) መግባቱ እና መውጣቱ በመግለፅ ይህ መረጃ ለእነሱ በጣም አስፈላጊ ነበር። ብሏል
አክለዉም ከሞሳድ ወኪሎች ጋር አምስት ጊዜ እንደተገናኘ ሞሳድ በጥብቅ ይፈልጋቸዉ የነበሩ"ቁልፍ መገልገያዎች ፎርዶው እና ናታንዝ (የዩራኒየም ማበልፀጊያ ፋብሪካዎች) መረጃዎች ነበር፣ ለዚህም መረጃ ልኬያለሁ። ይህን እና ስለ ፎርዶው እንደማውቀው ነገርኳቸው፣ እነሱ (የሞሳድ ወኪል) ሁሉንም ነገር እንድልክ ነግረውኛል" ሲል ቫዲ በአየር ላይ እንደ ሚሰራ የኑዛዜ ቪዲዮ በገለጸው ላይ ተናግሯል።
ቫዲ በቪየና በነበረበት ወቅት የእስራኤል የስለላ አገልግሎት ጋር አምስት ጊዜ እንደተገናኘ እና ለአገልግሎቶቹ ክፍያ ለመቀበል ምስጠራ አካውንት እንዲከፍት እንደተጠየቀ በቪዲዮው ላይ አንድ ድምጽ ተናግሯል። ተከሳሹ በቪዲዮው ላይ ሞሳድ የረጅም ጊዜ ትብብር ካጠናቀቀ የውጭ ፓስፖርት ቃል እንደገባለት ገልጿል ።
ቫዲ የሀገሪቱ ከፍተኛ የኒውክሌር አካል በሆነው በኢራን የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ውስጥ የኑክሌር ተመራማሪ እንደነበር በሰነዱ ውስጥ ማግኘታቸውን የገለፁት ባለስልጣኖች እንዳሉት የኢራን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቶችን የቅጣት ውሳኔ በማፅደቅ ሁለቱንም ሰዎች ከመገደሉ በፊት ሙሉ ህጋዊ አካሄዶችን መከተሉን ሚዛን ዘግቧል።
በዚህ አመት ለእስራኤል በመሰለል የተፈረደባቸው ኢራናውያን ላይ የሚደርሰው ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ የተነገረ ሲሆን ከቅርብ ወራት ወዲህ ቢያንስ ስምንት ሰዎች የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸዋል ሲል የዘገበው የመንግስት ብሮድካስት IRIB ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

የሞሳድ ኃላፊ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያና ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸው ተዘግበ
የእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ኃላፊ ዴቪድ ባርኔያ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ የሀገሪቱን ልዩ መልዕክተኛ መጠየቃቸው ተዘግበ።
የሞሳድ ኃላፊው ይህን ጥያቄ ያቀረቡት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ባደረጉት ጎብኝት ወቅት መሆኑን አክሲዮስ ዘግቧል።
እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማዘዋወር የትራምፕን አስተዳደር እርዳታ እየፈለገች መሆኑን ጉዳዩን የሚያውቁ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ የዜና አውታሩ ዘግቧል፣
ሁለቱ ምንጮች እንደገለፁት፤ የሞሳዱ ኃላፊ ባርኔያ፤ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኔዥያ እና ሊቢያ ከጋዛ የፍልስጤማውያን ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኝነት አሳይተዋል ሲሉ ለአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል። እናም ዋሽንግተን እነዚህ ሀገራት ስደተኞችን ለማዛወር እንዲስማሙ “ማበረታቻ” መስጠት አለባት ማለታቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ስቲቭ ዊትኮፍ በጉዳዩ ላይ ቁርጠኛ አልነበረም ሲሉ አንደኛው ምንጭ ገልጿል።
የአሜሪካ ባለስልጣናትም ከአረብ ከሀገራት ተቃውሞ የሚያከትል በመሆኑ ዋይት ሀውስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል ሲል ዘገባው አክሏል።
ከወራት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ግንባት ሲጀመር የጋዛ ነዋሪዎች በሙሉ ላልተወሰነ ጊዜ ወደሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ሀሳብ ማቅረባቸው ይታወቃል። ሀሳቡን የእራኤሉ መሪ ኔታንያሁ እና ጥምረታቸው ሲደግፉ፣ የአረብ ሀገራት እና አብዛኛው የምዕራቡ ዓለም በብርቱ ተቃውመውታል።
ዘገባው የአዲስ ስታንዳርድ ነው

የሞሳድ ኃላፊ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያና ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸው ተዘገበ
የእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ኃላፊ ዴቪድ ባርኔያ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ የሀገሪቱን ልዩ መልዕክተኛ መጠየቃቸው ተዘገበ።
የሞሳድ ኃላፊው ይህን ጥያቄ ያቀረቡት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ባደረጉት ጎብኝት ወቅት መሆኑን አክሲዮስ ዘግቧል።
እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማዘዋወር የትራምፕን አስተዳደር እርዳታ እየፈለገች መሆኑን ጉዳዩን የሚያውቁ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ የዜና አውታሩ ዘግቧል፣ ሁለቱ ምንጮች እንደገለፁት፤ የሞሳዱ ኃላፊ ባርኔያ፤ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኔዥያ እና ሊቢያ ከጋዛ የፍልስጤማውያን ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኝነት አሳይተዋል ሲሉ ለአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል። እናም ዋሽንግተን እነዚህ ሀገራት ስደተኞችን ለማዛወር እንዲስማሙ “ማበረታቻ” መስጠት አለባት ማለታቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ስቲቭ ዊትኮፍ በጉዳዩ ላይ ቁርጠኛ አልነበረም ሲሉ አንደኛው ምንጭ ገልጿል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ዋይት ሃውስ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዲሁም የኢትዮጵያ፣ የኢንዶኔዥያና የሊቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ምላሽ አልሰጡም።
የአሜሪካ ባለስልጣናትም ከአረብ ከሀገራት ተቃውሞ የሚያከትል በመሆኑ ዋይት ሀውስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል ሲል ዘገባው አክሏል።
ከወራት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ግንባት ሲጀመር የጋዛ ነዋሪዎች በሙሉ ላልተወሰነ ጊዜ ወደሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ሀሳብ ማቅረባቸው ይታወቃል። ሀሳቡን የእራኤሉ መሪ ኔታንያሁ እና ጥምረታቸው ሲደግፉ፣ የአረብ ሀገራት እና አብዛኛው የምዕራቡ ዓለም በብርቱ ተቃውመውታል።
Via Axios

Comments