Logo
FastMereja
11 hours ago
አዋሽ ባንክ በዶ/ር አብይ አህመድ ዳግም መመረጥ የተሰማውን ደስታ ገለጸ

​ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው በድጋሚ በመመረጣቸው የአዋሽ ባንክ ማህበረሰብ የተሰማውን ታላቅ ደስታ በይፋ ገለጸ። የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አመራር አባላትና መላው ሠራተኞች በሰጡት መግለጫ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀጣይ የስራ ዘመን ዳግም መመረጣቸው ታላቅ ኩራትና ደስታ የፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።

​ባንኩ በመግለጫው እንዳመለከተው፣ መጪው ጊዜ በእርሳቸው በሳል አመራር ሀገሪቱ የጀመረችው ሁለገብ የሀገር በቀል የኢኮኖሚና የፋይናንሺያል ሪፎርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሙሉ እምነት አለው። በተለይም በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ይህ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሂደት ሀገራችን ተወዳዳሪና የላቀ ለውጥ እንድታስመዘግብ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል።

​የአዋሽ ባንክ ማህበረሰብ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቀጣይ የስራ ዘመን የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ያስተላለፈ ሲሆን፣ ተቋማዊና ሀገራዊ ግቦችን እውን ለማድረግ ለሚደረጉ ጥረቶች ባንኩ አጋርነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

FastMereja
14 hours ago
ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተማሪዎች፣ አራሶች እና ህፃናት ዘለቄታዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገለጸ
#fastmereja :-በአሜሪካ የተመሰረተው እና በኢትዮጵያ በተግባር የእርዳታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን (Leenat Charity Foundation)፤ በደብረ ብርሃን፣ ሻሸመኔ እና ከሚሴ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ)፣ ደብተር እና ልዩ ልዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን በቀጥታ ማድረሱን አስታወቀ።

የህክምና ባለሙያ እና የፋውንዴሽኑ መስራች የእናትፋንታ አስማማዉ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ በከሚሴ ብቻ በሶስት የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ባደረገው ጉብኝት ደግሞ ለበርካታ አራሶች የንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም ለህፃናት ዳይፐር ማበርከቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም ለህፃናት እና ለአናቶች የምሳ ግብዣ በማዘጋጀት አብሮነቱን አሳይቷል።

ፋውንዴሽኑ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያዎችን በማቅረብ፣ የጤና ትምህርት እና ከኢንፌክሽን ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ግንዛቤዎችን የመፍጠር ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተመላክቷል።

በቀጣይም በገጠር አካባቢዎች የሚገኙ እና የንፅህና መጠበቂያዎችን ለመግዛት አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በዘላቂነት ለመደገፍ፣ ሞዴሶችን እዚሁ አገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ትልቅ ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ እንደሚገኝ መስራቿ አብራርተዋል።

FastMereja
9 hours ago
ጥራትና ደህንነቱ ሳይጠበቅ የሚጓጓዝ ጥሬ ወተት ለከፍተኛ የጤና አደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ ተገለፀ!
#fastmereja :- ጥራትና ደህንነቱ ሳይጠበቅ ከቦታ ቦታ የሚጓጓዝ ጥሬ ወተት ለከፍተኛ የጤና አደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ፣ የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በትራንስፖርትና አያያዝ ሂደት ላይ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

ወተት ከታለበ በኋላ ተገቢው የንፅህና እና የቅዝቃዜ ቁጥጥር (Cold Chain) ሳይደረግለት በሚጓጓዝበት ወቅት እንደ E. coli Salmonella እና Listeria ያሉ አደገኛ ባክቴሪያዎች በቀላሉ የሚራቡበት መንገድ እንደሚሆን ተመላክቷል።

በተለይም ወተቱ ከታለበበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተጠቃሚው ድረስ ከ 4°C በታች ባለው የቅዝቃዜ መጠን ካልተጠበቀ፣ በሙቀት ምክንያት ተህዋሲያኑ በፍጥነት በመራባት ለከባድ የሆድ ቁርጠት፣ ለተቅማጥ፣ ለትውከት፣ ለሳንባ ነቀርሳ እንዲሁም ለተለያዩ ህመሞች ሊዳርጉ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ይህ የጤና አደጋ በተለይ በህፃናት፣ በነፍሰ ጡር እናቶች፣ በአረጋውያን እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ከባድ ጉዳት የሚያደርስ ነው።

የወተት ደህንነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚከተሉት አበይት እርምጃዎች ሊወሰዱ እንደሚገባ ተመላክቷል፦

ወተትን ለማጓጓዝ ደረጃቸውን የጠበቁ የአሉሚኒየም ወይም የማይዝግ ብረት (Stainless steel) ዕቃዎችን መጠቀም እና የዕቃዎቹን ንፅህና በየጊዜው መጠበቅ፤ የማቀዝቀዣ ዘዴዎችን መጠቀም በትራንስፖርት ወቅት ወተቱ እንዳይበላሽ የቅዝቃዜ ሰንሰለቱን የጠበቁ የመጓጓዣ ዘዴዎችን (Refrigerated transport) መተግበር እንዲሁም ተጠቃሚዎች ጥሬ ወተትን ከመጠቀማቸው በፊት በደንብ አፍልተው የመጠቀም ልምድን ማዳበር እንደሚገባ ነዉ የተገለፀዉ።

በመሆኑም አምራቾች፣ አጓጓዦችና ነጋዴዎች የምግብ ደህንነት መመሪያዎችን በአግባቡ በመተግበርየህብረተሰቡን ጤና የመጠበቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ህብረተሰቡ ጥራትና ደህንነቱ ያልተረጋገጠ የወተት ምርት ሲያጋጥመው ወደ 8482 በነፃ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

FastMereja
9 hours ago
የእንኳን ደስ አላችሁ እና የመልካም ምኞት መግለጫ!
*****
​በአገራችን የዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ የመንግሥት ምሥረታን ምክንያት በማድረግ ለመላው የአገራችን ሕዝቦችና ለአዲሱ መንግሥት እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ ለሰላማዊ የፖለታካ ሂደቶች ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን፤ ህዝባችን በአስከፊ የፀጥታ ስጋትና መዋከብ ውስጥ ሆኖም ስልጣን የሚፀናው በድምፄ ብቻ ነው በሚል ቁርጠኝነት በነቂስ ወጥቶ ምርጫ በማድረግ ከምርጫ ውጪ ላሉ የስልጣን ፍላጎቶች ግልፅ መልእክቱን አስተላልፏል።

​በመሆኑም በዚህ የላቀ ህዝባዊ ቁርጠኝነት በታየበት ምርጫ የተመሠረተው መንግሥት አገራችንን ወደ ተሻለ ሁለንተናዊ የዕድገት እና ሰላም የሚያሸጋግር፤ የሕዝባችንን ጥያቄዎችና እውነተኛ ፍላጎቶች የሚመልስ እንዲሆን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምኞቱን ይገልጻል።

​ዛሬ ለተሾሙት የመንግሥት አመራሮች በሙሉ የተጣለባችሁን ታሪካዊና አገራዊ ኃላፊነት በታማኝነት፣ በፍትሐዊነትና በትጋት በመወጣት አገራችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የምታደርጉት ጉዞ የስኬትና የድል እንዲሆንላችሁ አብን እየተመኘ፤ በሰባተኛ ዙር አንደኛ መደበኛ መስራች ጉባኤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሜ የተመረጡትን ክቡር ዐብይ አሕመድን (ዶ.ር) ፓርቲያችን አብን እንኳን ደስ አለዎት ማለት ይወዳል።

አገራችን ያለችበትን ሁለንተናዊ ነባራዊ ሁኔታ፣ ያጋጠሙንን አገራዊና ቀጣናዊ ተፎካካሪ ሁኔታዎች እንዲሁም የሕዝባችንን የልማትና የፍትህ ጥያቄዎች በተገቢው በመረዳት አገራችንን ወደ ተሻለ የዕድገትና የሰላም ምዕራፍ ይመራሉ ብለን እናምናለን። በመሆኑም ድርጅታችን አብን፤ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት እንዲሁም የሕዝባችንን የኑሮ ውድነት የሚያቃልሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ለመተግበር በሚወሰዱ ሀገራዊ እርምጃወች በትብብር ለመሥራት ዝግጁነቱን ያረጋግጣል።

በመጨረሻ ድርጅታችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሀገራዊ ጥቅም፣ አንድነትና ህልውና በሚጠይቀው ቦታ ሁሉ ጽኑ አጋርነታችንን እየገለጽን፣ ፍትሕና እውነት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ድምፅ ሆነን መቆማችንን እንቀጥላለን። በድጋሜ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና ለአዲሱ መንግስታቸው ስኬትን እንመኛለን።

​ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
መስከረም 25/2019 ዓ.ም

FastMereja
12 hours ago
የልዕልት ሊሲ (ልሳን ተፈሪ ፍቅረ ሥላሴ) ግለ-ታሪክ

ልዕልት ሊሲ—በይፋዊ መጠሪያዋ ልዕልት ልሳን ተፈሪ ፍቅረ ሥላሴ (Princess Lissan "Lissie" Selassie)—የኢትዮጵያን የብዙ ክፍለ ዘመናት ንጉሣዊ ታሪክ፣ የትውልድ መስመር እና ባህላዊ ቅርስ አጣጥማ የያዘች የዘመናችን ወጣት ንጉሣዊ ተወላጅ ናት።

በካሊፎርኒያ አሜሪካ አድጋ በባዮሎጂ ሳይንስ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያጠናቀቀችው ልዕልት ሊሲ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ባስተዋወቀችባቸው መድረኮች፣ በሳይንሳዊ ዕውቀቷ እና በማህበረሰብ በጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎቿ የምትታወቅ ወጣት አርአያ ናት።

ታሪካዊ የትውልድ ሐረግ እና የአራት ሥርወ-መንግሥታት ትስስር

የልዕልት ሊሲ የደም መስመር የኢትዮጵያን ህብረ-ብሔራዊ ታሪክ እና ብዝሃነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ከአራት ታላላቅ የኢትዮጵያ ንጉሣውያን እና መሪዎች ሥርወ-መንግሥታት የተገኘ ልዩ የትውልድ ሐረግ አላት፦

👉የሸዋ ሰለሞናዊ ሥርወ-መንግሥት፦ የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ የአልጋ ወራሽ አምኃ ሥላሴ (አስፋው ወሰን) እና የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የበኩር የልጅ ልጅ የነበሩት የልዕልት እጅጋየሁ አስፋው ወሰን የዘር ሃገረግ ትስስር ናት።

👉የወለጋ - ኦሮሞ ሥርወ-መንግሥት፦ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ደጃዝማች ገብረእግዚአብሔር ተብለው ከተጠመቁት ከወለጋው ንጉሥ ኩምሳ ሞረዳ እና በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የመሪነት ውርስ ከነበራቸው ከአያቷ ከንጉሥ ፍቅሬ ሥላሴ የሚመዘዝ የትውልድ መስመር አላት።

👉የትግራይ ሥርወ-መንግሥት፦ የትግራዩ ንጉሥ እና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ 4 ኛ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የልዕልት ወለተ እስራኤል ስዩም የትውልድ ዘር ናት።

👉የወሎ ሥርወ-መንግሥት፦ የወሎው ንጉሥ ሚካኤል አሊ (መሐመድ አሊ) እና የልጅ ልጃቸው የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ባለቤት የእቴጌ መነን አስፋው የዘር ሃረግ ናት።

የቤተሰብ ሕይወትና አስተዳደግ

ልዕልት ሊሲ የታዋቂው አርቲስት ልዑል ይስሐቅ ፍቅረ ሥላሴ እና የቴክኖሎጂ ባለሙያ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልዕልት አስኳል ተፈሪ ልጅ ስትሆን፣ የልዕልት እጅጋየሁ ፍቅረ ሥላሴ ታናሽ እህት ናት።

በሰሜን ካሊፎርኒያ አሜሪካ ያደገች ቢሆንም፣ ከኢትዮጵያ ባህል፣ እምነት እና ማህበረሰብ ጋር ባላት ጠንካራ ቁርኝት ትታወቃለች። እናቷ ገና በለጋ ዕድሜዋ ያስተማረቻትን አማርኛ ቋንቋ አቀላጥፋ ማንበብ፣ መጻፍ እና መናገር የምትችል ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴቶችና ታሪክ ጠብቆ በማስቀጠል ረገድ ከፍተኛ ፍላጎት አላት።

ትምህርት እና ሙያዊ ፍላጎት

ልዕልት ሊሲ በትምህርቷ የላቀ ስኬት ያስመዘገበች ሲሆን

👉ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (University of California, Santa Cruz) በሶስት ዓመታት ብቻ በትምህርቷ በመግፋት በሞለኪውላር፣ ሴል እና ልማት ባዮሎጂ (Molecular, Cell, and Developmental Biology) የሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን (B.S.) አግኝታለች።

👉በአሁኑ ወቅት ትኩረቷን በቤተ-ሙከራ ምርምር (Lab Research) እና በድህረ-ምረቃ (Master's programs) ትምህርቷ ላይ ያደረገች ሲሆን፣ ወደፊት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ክሊኒክ የማቋቋም ትልቅ አልም አላት።

ዓለም አቀፍ ዝና እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች

Le Bal des Débutantes (2023)፦ እ.ኤ.አ. በ2023 በፓሪሱ ሻንግሪ-ላ ሆቴል በተካሄደውና ከዓለም ዙሪያ የተተውጣጡ የንጉሣውያን እና የታዋቂ ቢሊየነሮች ቤተሰብ ወጣቶችን በሚያስተናግደው Le Bal des Débutantes ዝግጅት ላይ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ተካፋይ ሆና በመመረጥ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በክብር ወክላለች።በዝግጅቱም የላንቪን (Lanvin) ዲዛይን ቀሚስ እና የቪ-ሙሴ (V MUSE) ጌጣጌጦችን በመልበስ የፋሽንና የዜና መጽሔቶች ትኩረት ሆናለች።

የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ፦ በራሷ ተነሳሽነት በሸዋ ሮቢት እና በደብረ ብርሃን የሚገኙ ወጣት ልጃገረዶችን ትምህርት ለማገዝ እና ራሳቸውን የመቻል አቅም ለማጎልበት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ታከናውናለች።

እ.ኤ.አበታህሳስ 2022/2023 ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የማህበረሰብ ጉብኝትና ድጋፍ አድርጋለች።

FastMereja
14 hours ago
በሀገራዊ ምክክር መሰረት በቀጣይ ህገ መንግስቱ እንደሚሻሻል ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ገለጹ።

FastMereja
15 hours ago
እኛ በ18 ወራት ተዓምር ስንሰራ ነበር… እናንተስ?

18 ወራት ህልምን ወደ እውነት፣ ሀሳብን ወደ ውጤት ቀይረናል።
አሁን የእናንተ ተራ ነው!

እኛ ማን ነን ?

ኑ፣ ከእኛ ጋር ተዓምር እንስራ! #18monthsofmiracles #letscreatemagic #ከእኛጋር_ተዓምር_እንስራ

FastMereja
18 hours ago
ዛሬ አለም አቀፍ የመምህራን ቀን ነው።

በህይወታችሁ የማትረሱትን መምህር ጽፋችሁ አመስግኑት....

FastMereja
19 hours ago
በMire corporate solution የሚሰጥ ለሶስት ቀን የሚቆይ ስልጠና
መስከረም 29፣ 30 እና ጥቅምት 1 ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ 11 ሰአት

ስልጠናዎቹም በ Leadership, Management, customer service, Marketing and sales, Emotional Intelligence

4 ሰዉ አንድላይ ከተመዘገበ 1ሰዉ ተጨማሪ በነፃ ይገባል።

ለመመዝገብ 0936363685

FastMereja
23 hours ago
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናችንን ይስማን፤ምልጃ እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች፡፡

ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ፡፡
ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ፡፡ በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በስተቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ሲወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ እንደሚሆን የተረዳው መጋቢ በታላቅ ድንግጤ ውስጥ ወደቀ፡፡ እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ በመላዕክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ምስለ ስዕል ፊት ወድቆ ተማጸነ፡፡ ታላቁ ወንዝ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርጎ የሚወወስደው ከሆነም የሚሆነውን ነገር ለመቀበልና ከዚያም ላለመውጣትም ወሰነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ፡፡ በዚህ ጊዜ የመላዕክት ሁሉ አለቃቸው ለጠራውም ፈጥኖ የሚደርሰው ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ፡፡

መጋቢውንም "ጽና አትፍራ፣ እኔ ካንተ ጋር ነኝና" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት፡፡ በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ ሲመጣ የነበረው ወንዝም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ፡፡ የሚገርመው ነገር የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሸለቆው የተፈጠረው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግን ጸንቶ ቆመ፡፡ መጋቢውም እግዚአብሔርንና ቅዱስ ሚካኤልን አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ፡፡ በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው፣ መልአኩንም አከበሩት፣ አሕዛብ ግን አፈሩ፡፡

ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ገዳማውያንና ቅዱሳን ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

FastMereja
23 hours ago
ሜሪት ኤክስፖ በተክለሃይማኖት

መስከረም 28 እና 29

አዲስ ፕሮጀክት በመገንባት ላይ ሲሆን፣ ለማየት እስኪጠናቀቅ መጠበቅ አያስፈልግም።
በቦታው ተገኝተው የግንባታውን እድገት በአካል እንዲመለከቱ፣ የተዘጋጀውን ልዩ ኤክስፖ እንዲሳተፋ ተጋብዘዋል።

መስከረም 28 እና 29
በተክለሃይማኖት
ይምጡ ይጎብኙ!

አንድ አመት፣ አንድ ራዕይ፣ ቀጣዩ ምዕራፍ

ሜሪት ፕሮፐርቲስ የታመነ ንብረት!

FastMereja
2 days ago
ሜትሮ ኬተሪንግ የኢቢኤስ ፕሮግራም አቅራቢ ጥበብ ሰለሞንን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጠ
​ #fastmereja I በምግብ ዝግጅት የኬተሪንግ አገልግሎቶች ዘርፍ የሚታወቀውና ትልቅ ተወዳጅነትን ያተረፈው "ሜትሮ ኬተሪንግ"፤ ታዋቂዋን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ጥበብ ሰለሞንን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።

ተቋሙ ባለፉት ዓመታት በሜትሮ ቤከሪ እና ፐጀዘወፔስትሪ ስር ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ ቆየት ብሎም የተለያዩ ስራዎችን በመስራት አሁን ላይ በትልልቅ ተቋማትና ኮርፖሬት ድርጅቶች ውስጥ የኬተሪንግ አገልግሎቱን በሰፊው በማዳረስ ላይ ይገኛል።

የድርጅቱ ባለቤት ​አቶ ፍጹም ተስፋዬ ባደረጉት ንግግር በምግብ ጥራት፣ በንፅህና እና በጤናማነት አጠባበቅ አሰራሩ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሜትሮ ኬተሪንግ፤ ከምግብ ጋር በተያያዙ በርካታ ስራዎች ላይ ትልቅ አሻራ ማሳረፉን ገልጸዋል።

የአምባሳደር መመረጥም ተቋሙ ለህብረተሰቡ የሚያደርሰውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ከደንበኞች ጋር ያለውን ቁርጠኝነት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል።

​በቀጣይም ተቋሙ በምግብ ዝግጅት እና በኬተሪንግ አገልግሎት መስጫዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አዳዲስ መርሆችን በመቅረጽ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት እንደሚሰራ የገለጹት የስራ ሃላፊዎች፣ በሂደቱም የድርጅቱን ዕድገትና ስኬት ከህዝብ ጋር ለማስተዋወቅ አርቲስት ጥበብ ሰለሞን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደምታበረክት ተማምነዋል።

በ2013 ዓ.ም ስራ የጀመረው ሜትሮ በሲኤምሲ እና አያት ቅርጫፍ ያለው ሲሆን በልዩ ሁኔታ አምባሳደር አከባቢ በሚገኘው ግዙፉ በንግድ ባንክ ህንጻ ላይ ሶስተኛውን ቅርጫፍ ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

FastMereja
1 day ago
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

ቤተክርስቲያናችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ በማለት ክብሯን ትገልጻለች። ኦርቶዶክሳዊያን ከሕጻንነታችን ጀምረን የእመቤታችንን ምስጋና እንማራለን፣ ሁልጊዜም በአባታችን ሆይ ጸሎት ጀምረን በመልኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ብለን ድንግል ማርያምን እናመሰግናታለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱሳን ሁሉ የምትመሰገን ናት። እርሷ ያላትን ክብር እንዴት እንደሚገልጹት ተጨንቀው በምን በምን እንመስልሻለን በማለት በሰው ህሊና የሚለካ ምሳሌ ማጣታቸውን ብዙ ቅዱሳን ተናግረዋል። የብህንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ፣ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምና ኢትዮጵያዊው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ክብሯን ገናንነቷን በስፋት ተናግረዋል፣ አመስግነዋታል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት።

ጌታችን አምላካችን ኢየሱ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሳ፤ በእርሷም የመለኮትና የስጋ ፍጹም ተዋህዶ ተፈጸመ፡፡ የማይወሰነውን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኗ ወሰነችው፡፡ ከዓለም በፊት ከአብ ያለእናት እንደተወለደ፣ ከእርሷ ደግሞ ድህረ ዓለም ያለ አባት ተወለደ፡፡ አምላክ እኛን ለማዳን ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ ስንል በተዋህዶ ነውና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አማላክ ትባላለች፡፡ እመቤታችን በሀሳብም በሥጋም ዘላለማዊት ድንግል ናት። በሀሳቧ በህሊናዋ ከአምላክ ህግና ሀሳብ በስተቀር ስጋዊ ሀሳብ ፈጽሞ ኖሮ አይውቅምና ከሰው ወገን ተለይታ የህሊና ድንግልና አላት፡፡

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች መሆኗን በመመስከር ይህን የህሊና ድንግልና ያስረዳናል። መልአኩም ልጅ ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል” ብላ መናገሯ “ስለ ወንድ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም” ማለቷ ነውና የህሊና ወይም የሀሳብ ድንግልናዋን ያስረዳናል። ከመፅነሷ በፊት፤ በፀነሰች ጊዜ፤ ከፀነሰች በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደችም ጊዜ፤ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት፡፡ ገዳማውያን ይህን ክብሯንና አማላጅነቷን አምነው ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

FastMereja
2 days ago
የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏

በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡

አባታቸው ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእ ኃረያ ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በአንድ ወቅት ታዳጊው ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለስብከተ ወንጌል እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡

ወላጆቻቸው ካረፉ በኋላም ንብረታቸውን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ሲወርዱ ገመዱ ቢበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን አጥምቀዋል፤ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገዳም አስቦ ዋሻ በዙሪያቸው ስምንት ጦሮች ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት በማሰብ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት አንድ እግራቸው ተሰብራል፡፡

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ለምነዋል፡፡ ከዚህ ዓለም ድካም በሚያርፉበት ነሐሴ 24 ቀንም ጌታችን ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጥቶ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ሁሉ ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉና ከበረከታቸው እንድንሳተፍ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

FastMereja
1 day ago
በወተት ተዋጽኦዎች አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ ህብረተሰቡ አስፈለጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ!
#fastmereja :- ህብረተሰቡ የወተት እና የወተት ተዋጽኦዎችን በሚገዛበት ወቅት በተገቢው ማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጣቸዉን ሳያረጋግጥ መግዛት ለከፍተኛ የምግብ ወለድ በሽታዎች እና ለጤና እክሎች እንደሚያጋልጥ ተገለጸ።

የወተት ተዋጽኦዎች በፍጥነት በጥቃቅን ተህዋሲያን (ባክቴሪያዎች) ሊበላሹ የሚችሉ በመሆናቸው በበቂ ቅዝቃዜ (ከ 4°C በታች) ሳይጠበቁ ሲቀሩ በፍጥነት የመበላሸት እና የምግብ መመረዝ (Food Poisoning) የማስከተል እድላቸው ከፍተኛ ነው።

የተጠቃሚዎችን ጤና ለማረጋገጥ እና ከብክለት ለመጠበቅ ህብረተሰቡ በሚገዛበት ወቅት እነዚህን ነጥቦች እንዲያስተውል ይመከራል፡

የማቀዝቀዣውን ሁኔታ ማረጋገጥ ምርቶቹ የተቀመጡበት ማቀዝቀዣ በበቂ ሁኔታ ማቀዝቀዙንና በአግባቡ እየሰራ መሆኑን ማየት፤ የአገልግሎት ማብቂያ ቀን (Expiry Date) ማየት የጽሁፍ መረጃውን በማንበብ ጊዜያቸው ያላለፈባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ

እንዲሁም የማሸጊያ ደህንነትን መፈተሸ፡ ያበጡ፣ የተቀደዱ ወይም የአየር መግቢያ ያላቸውን ማሸጊያዎች አለመጠቀም፤ የግዢ ጊዜን ማሳጠር፡ ምርቶቹን ከገዙ በኋላ ወደ ቤት እስከሚደርሱ በሙቀት ውስጥ የሚቆዩበትን ጊዜ ያህል ማሳጠር እና ወዲያውኑ ፍሪጅ ውስጥ ማስገባት እና መጠቀም እንደሚገባ ተገልጿል

ህብረተሰቡ ጥራትና ደህንነቱ ያልተረጋገጠ የወተት ምርት ሲያጋጥመው ወደ 8482 በነፃ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

FastMereja
2 days ago
ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ ቢሾፍቱ

FastMereja
2 days ago
የቅዱስ ገብርኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን፤ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን🙏

“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡

አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

FastMereja
2 days ago
ኩኩ ሰብስቤ እና ኤልያስ መልካ — «እንባዬ» የሙዚቃ ቪዲዮ ትዝታ
(ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

«ከዘፈኑ ይልቅ ኤልያስን ክሊፑ ላይ ሳየው ነው የኔ ትዝታ» — ተወዳጇ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ።

ድንቁ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ካረፈ ዛሬ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል ከእልፍ ሙዚቃዎቹ ውስጥ አንዱን መዘን እንገቃችሁ «እንባዬ» የተሰኘው የታወቀ የሙዚቃ ሥራ በመጀመሪያ በክቡር ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ የተዜመ የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ በድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ድምፅ እንደ አዲስ የተሠራ ድንቅ ሥራ ነው። ትንሽ ጊዜ ስጠኝ የተሰኘ አልበም ላይ የተካተተ ነው፡፡ ሙዚቃው በቅንብር፣ በድምፅ ጥራትና በእንቅስቃሴ ስልት ተሻሽሎና ተውቦ በመቅረቡ የብዙዎችን ቀልብ ሊስብና ትልቅ ቦታ ሊይዝ ችሏል።

ይህንን ሙዚቃ እንደ አዲስ አሳምሮ ያቀናበረው ደግሞ ባለብዙ ሙያና ተወዳጁ ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ነበር። ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስለ ኤልያስ ታስታውሳለች፤ «ገና ሙዚቃውን ሲሰማው ደስ አለው፤ የክራሩን ቅኝት እንዴት አድርጎ እንደጨመረበት አሁንም ቢሆን በዓይነ ሕሊናዬ ይታየኛል፤ እሱ ራሱ ሠርቶ እንደ አዲስ ይደሰት ነበር» በማለት ምስክርነቷን ትሰጣለች።

ሥራውን በበለጠ ለማሳመር የሙዚቃ ቪዲዮ (ክሊፕ) ለመቅረጽ ስታስብ ከኤልያስ ጋር ተወያየች። «ለዚህ ዘፈን ክሊፕ እንስራ፤ አንተ ግራንድ ፒያኖ ላይ ተቀምጠህ ሱፍህን (ቶክሲዶ) አድርገህ በንጋታው ብቅ በል» አለችው። ኤልያስም በደስታ «እሺ እንዴ! ምን ችግር አለው?» ብሎ ተስማማ። ነገር ግን በነገው ዕለት ለቀረጻ ሲመጣ ቱታ አድርጎ ነበር። ኩኩም «እንዴ! እንደዚያ ተቀጣጥረን አልነበረም ወይ?» ስትለው፣ ኤልያስ ፈገግ የሚያደርግ ምላሽ አዘጋጅቶ ነበር— «ባክሽን አሰብኩበትና ደከመኝ፤ ፊቴን አዙሬ ፒያኖው ላይ እቀመጣለሁ እንጂ ሙሉ አልታይም» አላት። ኩኩም «ይሁን፣ ይሁን፤ ዋናው የአንተ መገኘት ነው» ብላ በመስማማት ክሊፑ ተቀረጸ።

ከጊዜያት በኋላ ኤልያስ ካለፈ በኋላ ኩኩ ያንን አጋጣሚ ስታስታውስ፤ «አሁን አሁን ሳስበው ሙሉ ፊቱን አዙሮ ቢሆን ኖሮ ብዬ እቆጫለሁ፤ ይሄዳል ብለን ማን አሰበና!» በማለት በቁጭት ትናገራለች። አክላም «ከዘፈኑ ይልቅ ኤልያስን ክሊፑ ላይ ሳየው ነው ትዝታው የሚቀሰቀሰው፤ ኤልያስ በብዙ ክሊፖች ላይ አይታይም፣ በልቤ ውስጥ ግን ሁልጊዜ ይኖራል» ስትል ጥልቅ ስሜቷን ገልጻለች።

በሕይወት ውስጥ እንዲህ ዓይነት ነገሮች ቁጭት ቢፈጥሩም፣ ትልቅ ማስታወሻና መታሰቢያ ሆነው ያልፋሉ። አንድ ቀን ትዝታ ሆኖ ይጠቅመኛል ብላችሁ በማሰብ ሥራችሁን በተጠንቀቅና በነፍስ ሥሩ። የኤልያስ መልካ ድንቅ የቅንብር ሥራዎች ምንጊዜም እንደ አዲስ እትም ሲታደሱ ይኖራሉ።

ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

FastMereja
2 days ago
እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ታኅሣሥ 24 ቀን 1212 ዓ.ም ከካህኑ አባታቸው ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድና በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት ተወለዱ፡፡

ወላጆቻቸውም ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ሕፃኑ ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡

ቅዱስ ሚካኤልም ከአዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደተመረጡ፣ ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ያላቸውን ንብረት ዅሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው “አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደ ተከፈተ ተውኹልህ” በማለት ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ፈጥነው ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳምም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ከዚያ ሲወርዱ ገመዱ ገመዱ ሲበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረው በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በደብረ ሊባኖስ ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባትም በዙሪያቸው ስምንት ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማም፣ ሞትና ነገረ መስቀል በማሰብ በተመስጦ ለ22 ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት የአንድ እግራቸው አገዳ ተሰብራል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን የዐፅም ስባሪ አክብረው አኑረውታል፡፡ እግራቸው ከተሰበረ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ሌሊትና ቀን ጸንተው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ጥቂት ውኃ እንኳ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ እንደ ነበረ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ጻድቁ አባታችን ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም የሚያርፉበት ቀን ሲቃረበ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጣ፡፡

በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው፣ ስለ ተጋድሏቸው ጽናትም “በሰው እጅ የማይለካውን ይህንን የመንግሥት አዳራሽ ውሰድ” በማለት የጸጋ ልብስ አልብሷቸው፤ በመስቀል ምልክት ያጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትንም አቀዳጅቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ 24 ቀን በዘጠና ዘጠኝ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ጌታችንም ነፍሳቸውንም በክብር ተቀብሏታል፡፡ የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉ፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

FastMereja
2 days ago
በመቐለ ከተማ ለቀናት ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ ተመለሰ

​ላለፉት 10 ቀናት በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን የከተማይቱ አራት ነዋሪዎች ገልጸዋል። አገልግሎቱ ወደ ነበረበት የተመለሰው ዛሬ እሁድ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ገደማ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።

​በአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች በመንግስታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ይሰጡ የነበሩት የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች የተቋረጡት ሐሙስ መስከረም 14 ቀን ምሽት ላይ እንደነበር ይታወሳል። ሌላኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት የሆነው የሳፋሪኮም ኔትወርክም ቢሆን እስከ አርብ እኩለ ቀን ድረስ ሲሰራ ቆይቶ መቋረጡ ተገልጿል።

​የኢትዮ ቴሌኮም እና የሳፋሪኮም አገልግሎት አቅራቢዎች የኢንተርኔት እና የስልክ ኔትወርኮቻቸውን እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ የሰጠው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጭን ጨምሮ ስለጉዳዩ የሚያውቁ አራት ግለሰቦችን ጠቅሶ ሮይተርስ በወቅቱ ዘግቦ ነበር።

​ዛሬ እሁድ ማለዳ አገልግሎቱ ወደ ነበረበት መመለሱን ያረጋገጡት የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፤ በአሁኑ ወቅት በቀጥታ ስልክ መደወል እንደቻሉ እና የኢንተርኔት አገልግሎትንም በአግባቡ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ገልጸዋል።

FastMereja
2 days ago
ከኢትዮጵያ የተባረሩት የኤርትራ ዲፕሎማቶች ኤርትራ ደረሱ
#fastmereja I በኢትዮጵያ የነበሩ የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ ተወካዮች ከአዲስ አበባ ተነስተው አስመራ መግባታቸው ተገለጸ።

የኤርትራው ዲፕሎማት አስመሮም ተከስተ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ እንደገለጹት፤ ከአዲስ አበባ የተመለሱት ዲፕሎማቶች እና የስራ ባልደረቦቻቸው በአስመራ ሲደርሱ በኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በአምባሳደር እስቲፋኖስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ዲፕሎማቶቹ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የኢትዮጵያ መንግስት በሰጣቸው የ48 ሰዓታት ጊዜ ገደብ መሰረት ነው።

FastMereja
2 days ago
Magaalaa Bishooftuu jalabultii Irreecha Hora Harsadee Suuraan
📷 ENA

FastMereja
2 days ago
የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

FastMereja
2 days ago
“በራሱ ማንነትና ታሪክ የሚኮራ፣ እምነቱን የሚወድ፣ ነገር ግን በዘርና በሃይማኖት የማይለያይ፣ ስለ ነገዋ ኢትዮጵያ በጋራ የሚያስብ አዲስ ትውልድ ተፈጥሯል! ኩሩ ኢትዮጵያውያን ነን! ልዩነታችን ውበታችን፣ ባህላችን ደግሞ ክብራችን ነው:: HAPPY IRRECHA MY BEAUTIFUL PEOPLE”
አርቲስት ሳራ ቲ

FastMereja
3 days ago
በሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ሥርዓትን ዲጂታል በማድረግ የአገልግሎት ፍጥነትና ጥራትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በሲዳማ ክልል የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ሥርዓትን ዲጂታል በማድረግ የአገልግሎት ፍጥነትና ጥራትን ለማሳደግ፣ የወረቀት አጠቃቀምንና የተገልጋዮችን መንከራተት ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የጤና ሚኒስቴርና JSI Research & Training Institute, Inc. በጋራ ባዘጋጁት ሁለተኛ ዙር ሥልጠና ላይ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡሪሶ ቡላሾ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የዘርፉን ስራዎች የቁጥጥር ሥርዓቱን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻልና የተገልጋዮችን እንግልት መቀነስ እየተቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለሥልጣኑ መ/ቤት የጤና ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ፣ የጤና ባለሙያዎች ፈቃድ እድሳትና የተቋማት ቦታ ለውጥ ሂደቶችን ዲጂታል በማድረግ የወረቀት አሠራርንና ከተቋም ወደ ተቋም መመላለስን ለመቀነስ እየሰራ ያለው ስራ ውጤታማና አበረታች መሆኑን አመልክተዋል።

አቶ ቡሪሶ አክለው እንዳሉት፣ አገልግሎቶችን ዲጅታላይዝ ማድረግ የቁጥጥር ሥራን በመረጃ ማስደገፍ የቁጥጥር ሂደቱ ወቅታዊና ቀልጣፋ እንዲሆን ያግዛል ብለዋል ። በቀጣይም የቁጥጥር ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማጠናከር የተጀመሩ ሰፊ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለዘርፉ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል እንደገለጹት፣ ጥራቱን የጠበቀና ውጤታማ የጤና አገልግሎትን ለማረጋገጥ በታቀደው ሥራና በተግባራዊ አፈጻጸም መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ ያስፈልጋል።

ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ወደ ቁጥጥር ሥርዓቱ ማስገባት የቁጥጥር ሂደቶችን ከማዘመን ባለፈ ተቋማዊ ለውጥን ለማፋጠንና አገልግሎቱን ለማሳለጥ የሚያግዝ መሆኑንም ገልጸዋል።

FastMereja
2 days ago


FastMereja
3 days ago
የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏

በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡

አባታቸው ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእ ኃረያ ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በአንድ ወቅት ታዳጊው ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለስብከተ ወንጌል እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡

ወላጆቻቸው ካረፉ በኋላም ንብረታቸውን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ሲወርዱ ገመዱ ቢበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን አጥምቀዋል፤ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገዳም አስቦ ዋሻ በዙሪያቸው ስምንት ጦሮች ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት በማሰብ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት አንድ እግራቸው ተሰብራል፡፡

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ለምነዋል፡፡ ከዚህ ዓለም ድካም በሚያርፉበት ቀንም ጌታችን ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጥቶ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ሁሉ ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉና ከበረከታቸው እንድንሳተፍ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

FastMereja
3 days ago
የኢሬቻ በዓል በጅቡቲ ተከበረ

የኢሬቻ በዓል ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት በጅቡቲ በድምቀት ተከበረ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ባሕር ዳርቻ በመውረድ ለፈጣሪ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ባህላዊ ሙዚቃ እና ውዝዋዜ እንዲሁም ባህላዊ ምግቦች ቀርበዋል።

FastMereja
3 days ago
የትግራይ ቴሌቪዥን መጣው ብሎ ቀረ

ትግራይ ቴሌቪዥን ማህበራዊ ገጽ የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ ዶ/ር አብርሃም ሀጎስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሊሰጡ ነው ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይዞ ይቀርባል ተከታተሉ በማለት ለጥፎ የነበረ ቢሆንም ሳይመለስ 24 ሰዓት ሊሞላው።

FastMereja
3 days ago
ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ግብፅ ገቡ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የግብፅ አቻቸው አብደል ፈታህ አልሲሲ ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ካይሮ ገብተዋል።