ፋይዳን ከባንክ ሂሳብ ጋር ለማስተሳሰር የነበሩ ሰልፎችን ማስቀረት እንደተቻለ ተገለጸ
ፋይዳ መታወቂያን ከባንክ የሂሳብ ጋር ለማስተሳስር የነበረው ሰልፍ እና መጉላላት በተገልጋይዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በተገናኘ ባንኮች ላይ የነበሩ ሰልፎችን በማስቀረትና የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በፍጥነት ምላሽ በመስጠት በአሁኑ ወቅት የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ጋር የማስተሳሰር ሂደቱ መሻሻል የታየበት መሆኑ ተገልጾዋል፡፡
የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም መጀመሩን ያስታወሱት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላትና የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ናቸው።
ባንኮች ከሚሰሩት ስራ በተጨማሪ በኦንላይን ሊንክ ወይም ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ሲሰራበት መቆየቱን ተናግረዋል።
ስራው በሚገባው ልክ እንዲጠናቀቅ ለማድረግም የማብቂያ ቀናቶች መራዘማቸውን ያስታወሱ ሲሆን በመጨረሻዎቹ ቀናት በደንበኞች አገልግሎት ላይ ጫና ፈጥሮ እንደነበር አንስተዋል።
ይሁን እንጂ ችግሩን በቶሎ በመፍታት አሁን ላይ በተለያዩ ባንኮች ውስጥ ከፋይዳ ማስተሳሰር ጋር የተገናኙ ሰልፎች እንደማይታዩና የሚቀርቡ ጥያቄዎችም በፍጥነት ምላሽ እያገኙ መሆኑን አመላክተዋል።
ለአገልግሎቱ ምቹ የሆነ ሁኔታ እስከተፈጠረ ድረስ ወዲያውኑ ወደትግበራ መግባት የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል።
የፋይዳ መታወቂያን ከባንክ ጋር የማስተሳሰር ሂደቱን በዋነኛነት ብሔራዊ ባንክ በበላይነት እየመራው እና በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
#አሐዱ

2 days ago