Logo
YenetaTube
የሞስኮ ጎዳና በዝማሬና በእልልታ ተሞላ !

‎የሩሲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
‎ከፈረንጆቹ ሚሊኒየም ወዲህ በዓይነቱ ትልቁ የሆነውን ታላቅ ሰልፍ በሞስኮ ከተማ አካሄደች ።

‎በፓትርያርክ ኪሪል መሪነት ቡራኬ በክርስቶስ አዳኝ ካቴድራል ጀምሮ ኪሎ ሜትር (ሦስት ማይል) በዘለቀው በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተሳተፉበት ታላቅ ስልፍ ኦርቶዶክስ የሰላምና የአብሮነት የፍቅር ሀይማኖት እንደሆነች የሚያሳዩ በርካታ ኩነቶች ተካሂደዋል ።

‎ሰልፉ በ 1525 ስሞልንስክ ከተያዘ በኋላ በግራንድ ዱክ ቫሲሊ III የተመሰረተውን ከክሬምሊን ማስታወቅያ ካቴድራል ወደ ኖቮዴቪቺ ገዳም የቅዱስ የአምላክ እናት የስሞልንስክ አዶን ታሪካዊ ሽግግር ወቅት ይከበር የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 1917 ከሩሲያ አብዮት በኋላ የተቋረጠውን ወግና ስርአት ዳግም ለመመለስ በማሰብ እሑድ ዕለት በተዘጋጀው ሰልፍ ከ 40,000 በላይ የሚሆኑ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ካህናት መዘምራን የሞስኮ ቅዱሳን ምክር ቤት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ጨምሮ በርካቶች በተዘጋጀ ትልቅ ሰልፍ ላይ ተሳትፈዋል። ተብሏል ።

‎ሰልፉን የተመራው በፓትርያርክ ኪሪል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪ ሲሆን ከሞስኮ ሀገረ ስብከት የተውጣጡ ቀሳውስት፣ ገዳማውያን እና ምእመናን ተሳትፈውበታል። አዘጋጆቹ እንደገለጹት ከሆነ በሰልፉ ከመላው ሩሲያ እና ከቼክ ሪፐብሊክ፣ ኡዝቤኪስታን፣ ሰርቢያ፣ ጣሊያን እና ሌሎች ሀገራት የመጡ ተሳታፊዎች እንደነበሩ ተናግረዋል ።

‎ከመነሻው ማዕከላዊ ሞስኮ በሚገኘው የክርስቶስ አዳኝ ካቴድራል እስከ መዳረሻው የኖቮዴቪቺ ገዳም ድረስ የሶቭየት ሜይ ዴይ ሰልፍን በሚያስንቅ ዉበትና መንፈሳዊ ዝማሬዎች የእምነቱ መግለጫዎች በስፋት ተንፀባርቆበታል ።


‎ ቀሳውስት እና ምእመናን ቅዱሳንን የሚያሳዩ በቀለማት ያሸበረቁ ባንዲራዎችን ይዘው፣ ህዝቡ “ክርስቶስ ተነሥቷል” የሚለውን መዝሙር ሲዘምሩ መዘምራን “በእውነት ተነሥቷል” የሚል ምላሽ ሲሰጡ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችም ታይተዋል ።

‎ፓትርያርኩ ከዝግጅቱ ቀደም ብለው እንደተናገሩት ሰልፉ የሞስኮ የኦርቶዶክስ ዋና ከተማ ሆና የምትጫወተውን ሚና በማጉላት ጥንታዊ ባህልን እንደሚያድስ ተስፋ ገልፅዋል ።

‎"ሞስኮ የትውልድ አገራችን የኦርቶዶክስ ዋና ከተማ ናት" ሲሉም ከአገልግሎቱ በኋላ ለጋዜጠኞች የተናገሩት ሲሆን አክለዉም. "በአንድ በኩል ከሌሎች ሃይማኖቶች የመጡ ወንድሞቻችን ለጋራ ታሪካችን ያበረከቱትን አስተዋፅዖ በመገንዘብ ክርስቲያናዊ ውርሶቿን ፈጽሞ የማይሽር ከተማ ነች።" ብለዋል ።

‎"በብዙ አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞስኮ ቅዱሳን መታሰቢያ በዋና ከተማው ውስጥ 40,000 ሰዎች የተሳተፉበት ሃይማኖታዊ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር" በማለት የሞስኮ የብሔራዊ ፖሊሲ እና የአካባቢ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ቪታሊ ሱችኮቭ ተናግረዋል ሲሉ የዘገቡት ሞስኮ ታይምስና Russian Orthodox Church ናቸዉ ።



‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ


11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.