ሃያ ስድስት ሀገራት ወደ ዩክሬን በባህር፣ በመሬት እና በአየር ወታደሮችን ለማሰማራት ተስማሙ
#ethiopia | የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ እንዳስታወቁት ሃያ ስድስት የምዕራባውያን ሀገራት ወደ ዩክሬን ወታደሮችን “በመሬት፣ በባህር ወይም በአየር” ለማሰማራት በይፋ ቃል ገብተዋል።
“የፈቃደኞች ጥምረት” እየተባለ በሚጠራው 35 ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ማግስት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ሩሲያ ተጨማሪ የዩክሬን ግዛትን ለመንጠቅ ተጨማሪ ጊዜ ለመግዛት የሰላም ሂደቱን ለማዘግየት እየሞከረች ነው ሲሉ ከሰዋል።
ሆኖም ማክሮን የትኞቹ ሀገራት ወታደሮችን ለማቅረብ እንደተስማሙ አልተናገሩም።
በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ጦርነቱን ለማስቆም የመሪዎች ጉባዔ ይደረጋል የሚለው ተስፋ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቅርቡ በአላስካ ከተገናኙ በኋላ ቀንሷል።
ትራምፕ ዛሬ ከምዕራባውያን አጋሮቻቸው ጋር በስልክ ተነጋግረዋል፤ ማክሮን ደግሞ አሜሪካ ስምምነቱን እንደምትደግፍ ወይም እንደማትደግፍ በቀጣይ ቀናት ይፋ ይደረጋል ብለዋል።
ስምምነት ላይ ከተደረሰ ወደ ዩክሬን ወታደሮችን ለመላክ በይፋ ቃል የገቡ ጥቂት አገራት አሉ። አሜሪካ ግን እንዲህ አይነት እርምጃ እንደማትወስድ አስቀድማ ገልጻለች።
ሞስኮ ምንም ዓይነት የምዕራባውያን ኃይሎች ወደ ዩክሬን መላክ እንደሌለባቸው በግልጽ አስቀምጣለች፤ ኪየቭ እና አጋሮቿ ግን ይህን ሐሳብ ተቀባይነት የለውም ብለው አጣጥለውታል። #fidelpost

1 year ago