ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በተጠራጣሪነቱ ይታወቃል፡፡
በቀዳሚ ስሙ “ዲዲሞስ” ወይም ጨለማ የሚባል ስም ቢኖረውም በኋላ ግን ቶማስ ወይም ፀሐይ ተብሏል፡፡ ቅዱስ ቶማስ ሲጠራ ከሰዱቃውያን ወገን ስለነበር በትንሣኤ ሙታን ከማያምኑት ወገኖቹ የወሰደውን ትምህርት ይዞ ጌታችን ከሙታን በተነሳ ጊዜ እጆቹን ካልዳሰስኩ በጦር የተወጋ ጎኑን ካልነካሁ አላምንም ብሎ ዳሶ ካረጋገጠ በኋላ ግን ጌታዬ አምላኬ ብሎ ሰግዷል፡፡ ቶማስ አንድን ነገር ለመቀበል በቂ እውቀት የሚፈልግ ሲሆን ላመነበት ነገርም ቆራጥ የሆነ ሐዋርያ ነው። ቶማስ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ሞት እንደሚያስከትል እያወቀ እውነት ከሆነው አምላክ ጋር የሚጓዝነሰ ከክርስቶስም ጋር ለመሞት ዝግጁነቱን የገለጠ፣ ደፍሮ ሌሎችንም በማደፋፈር የሚታወቅ ሕይወቱንም ትቶ የተከተለ ሐዋርያ ነው።
በዮሐንስ 11፡16 ጌታ ወደ አልዓዛር መቃብር እንደሚሄድ በተናገረ ጊዜ “ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ” አለ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስታርግም ከሁሉም ቀድሞ ያየው እርሱ ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱ ሕንድ ሲሆን እንደ ባሪያ በ30 ብር ተሽጦ ነበር የገባው፡፡ ሉክዮስ የተባለ የገባበት አካባቢ አስተዳዳሪ አሳዳሪው ነበር፡፡ በቤቱ ሲያገለግልም ምን መሥራት እንደሚችል ሲጠይቀው ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እንደሚችል ስለነገረው ብዙ ወርቅና ብር በማቅረብ ሰርቶ እንዲጠብቀው ነግሮት የተለየ ጥበብኛ ሰው አገኘሁ ለማለት ወደ ንጉሥ ሄደ፡፡ ቅዱስ ቶማስ ግን ገንዘቡን ለነዳያን መጸወተው የሉክዮስ ሚስትና ልጆች ጨምሮም በርካቶችን አስተምሮ አሳምኗቸዋል፡፡
በአሳዳሪው ቤት ያሉ አገልጋዮች ሁሉ አምነው ተጠመቁ፡፡ ሉክዮስ ከሄደበት ተመልሶ ሕንጻውንና ሐውልቶቹን እንዲሳየው ጠየቀው፡፡ ሐዋርያው በወርቅና በብርህ ያነጽኳቸው ሕንጻዎች እኒህ ናቸው ብሎ ያመኑትን አገልጋዮች አሳየው፡፡ ይህ ክፉ ባሪያ ተጫወተብኝ ብሎ እጅ እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አስፍቶ በአሸዋ መልቶ አሸክሞ በገበያው ሲያዞረው ሚስቱ አርሶንዋ አይታ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡ መስፍኑም ደንግጦ ሚስቴን ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለሁ አለው፡፡ ጌታ ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነሥታለች በዚህም ሉክዮስ አምኖ ተጠምቋል፡፡ ከዚህም በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ሙት እያነሣ ድውይ እየፈወሰ አሕዛብን አሳምኖ አጠመቀ፡፡
በቀንጦፍያ የተገደሉ የአንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆች ስልቻውን እያስነካ አስነሥቷል፡፡ በኢናስም የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው ከንጉሱ ሚስት ጀምሮ እስከ ተራ ገባር ድረስ ያሉት ሁሉ አምነው ተጠመቁ፡፡ በኋላም የጣኦት ካህናተ በተንኮል ከንጉሡና ከመኳንንቱ ጋር አጣልተው በሰይፍ አስመትተውታል፡፡ ዛሬም ድረስ ሕንድ ውስጥ በመንበሩ ላይ የጌታችንን የተወጋ ጎኑን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ ቀኝ ቅድስት እጅ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች፡፡ በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሲሾሙም የቅዱስ ቶማስን ቀኝ እጅ በሚሾመው ፓትርያርክ ላይ ጭነው ነው፡፡ የቅዱሳን ሐዋርያትን ትምህርት አክብረው የሚኖሩት ገዳማውያን እናቶችና አባቶች በእምነታቸው ጸንተው ወንጌልን ኖረው ነው የሚያልፉት፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታችውን ስናጽና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

11 months ago