"የሞት ቅጣት እርምጃን እንጠቀማለን" ትራምፕ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ትራምፕ በግድያ ወንጀል የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች የሞት ፍርድ እንዲፈረድባቸው አዘዙ።
ትራምፕ በዋይትሃውስ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በዋና ከተማዋ ዋሽንግተን የወንጀል ድርጊቶችን ለመቀነስ ያግዛል ያሉትን እርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዋል።
"የሞት ቅጣት እርምጃን እንጠቀማለን" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ "ይህ እርምጃ ጠንካራ የወንጀል መከላከያ ዘዴ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
በዋሽንግተን ግድያ የሚፈጽሙ ወንጀለኞች የፍርድ ውሳኔ የሚሰጣቸው በዲሲ የከተማ ፍርድ ቤት ነው። በዚህ ፍርድ ቤት ከፍተኛው ቅጣት የእድሜ ልክ እስራት ነው ተብሏል።
በአሜሪካ የሞት ፍርድ የሚተላለፈው በፌደራሉ ፍርድ ቤት ሲሆን ለሞት ቅጣት የሚዳርጉ ወንጀሎች ሲፈጸሙ ብቻ ውስን የሞት ፍርድ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ተገልጿል። በዋሽንግተን ለሞት ፍርድ የሚያበቃ አስተማማኝ ማስረጃ የለም ተብሏል።
ትራምፕ በዋና ከተማዋ ዋሽንግተን በዚህ ወር መግቢያ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ለሰላም ማስከበር አሰማርተዋል።
ፕሬዚደንቱ በምርጫ ወቅት ዲሞክራቶች ባሸነፉባቸው ባልቲሞር ቺካጎ እና ኒውዮርክ ከተሞች ለማሰማራት አማራጮችን እያዩ ነው ተብሏል።
ትራምፕ ይህ ውሳኔያቸው በዜጎች እና በአንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ ያስከተለባቸው ሲሆን፣ ዲሞክራቶችም "አምባገነን" ሲሉ ትራምፕን ተችተዋል።
ትራምፕ በበኩላቸው "አውቃለሁ ብዙ ሰዎች እንደሚተቹኝ እኔ ግን አምባገነን አይደለሁም" ብለዋል። "ወንጀልን ለማጥፋት አምባገነን ብሆን እመርጣለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።#euronews #thiqaheth

1 year ago