ሳፋሪኮም በኬኒያ የኢንተርኔት አገልግሎት ጥቅል የሚያቀርብበትን አሰራር ሊቀይር ነው
#ethiopia | ኬንያ ግዙፉ የቴሌኮም ተቋም ሳፋሪኮም ከዚህ በፊት ሰዎች የኢንተርኔት ክፍያን በተጠቀሙበት መጠን ያስከፍል የነበረ ሲሆን በአዲሱ ስርዓት ሰዎች ለተጠቀሙበት መጠን ሳይሆን ለተጠቀሙበት ሰዓት ይከፍላሉ ተብሏል።
ሳፋሪኮም በአዲሱ ሥርዓት ሰዎች በተለመደው ከሜጋባይት እና ጊጋባይት የኢንተርኔት ጥቅል ስርዓት ወጥተው በተጠቀሙበት ሰዓት ልክ ይከፍላሉ ብሏል።
በአዲሱ የክፍያ ሥርዓትም ሰዎች ምን ያህል የኢንተርኔት ፍጆታ እንደተጠቀሙ መቆጣጠር አይጠበቅባቸውም ተብሏል።
ሳፋሪኮም አዲሱ የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ ልክ እንደ ስልክ ጥሪ ሰዎች በቆዩበት ልክ የሚከፍሉበት ነው ብሏል።
አዲሱ ሥርዓት ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማውረድ ለሚፈልጉ እንደዚሁም ቪዲዮዎችን ለሚያሰራጩ ሰዎች ይበልጥ ይጠቅማል ሲባል የኔትዎርክ መጨናነቅንም ይቀንሳል ተብሏል።
በአዲሱ የሳፋሪኮም ስርዓት መሰረት ሁለት የተለያዩ ሰዎች አንዱ ለአንድ ሰዓት የዩቲዩብ ቪዲዮ ቢመለከት እና ሌላኛው ደግሞ ለአንድ ሰዓት ቴሌግራም ላይ ቢቆይ ተመሳሳይ ክፍያ ይከፍላሉ ተብሏል።
ይህ የሳፋሪኮም አዲስ አሰራር በርከት ያሉ ደንበኞችን እንደሚያስደስት ሲጠበቅ ኢንተርኔትን አብዝተው ለማይጠቀሙ ወይም መልዕክቶችን ለመላክ ብቻ የሚጠቀሙ ሰዎችን ግን የማያስደስት ነው ተብሎ ተገምቷል።
The Kenyans #tm

12 months ago