ኢትዮ ቴሌኮም እና ሁዋዌ በሰሜን አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የላቀ የ4G ቴክኖሎጂ ዘረጉ
#ethiopia | ኢትዮ ቴሌኮም እና ሁዋዌ በሰሜን አፍሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የላቀውን "GigaAAU FDD Tri-Band Massive MIMO" የተሰኘው ቴክኖሎጂ በስራ ላይ ማዋላቸው ተገልጿል።
ይህ በዘርፉ ታሪካዊ ነዉ ተብሎ የተገለጸው መፍትሄ፣ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ አፈጻጸም እና የተጠቃሚ ልምድ ላይ ከፍተኛ መሻሻል አስመጥቷል ተብሏል።
የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው፣ የ4G ትራፊክ ፍሰት በ70% ያደገ ሲሆን፣ አማካይ የኔትወርክ ፍጥነት ደግሞ በ68% ጨምሯል።
ይህም ተጠቃሚዎች ቪዲዮዎችን ያለመቆራረጥ እንዲመለከቱ፣ የኦንላይን ጨዋታዎችን ያለምንም ችግር እንዲጫወቱ እና ፋይሎችን በፍጥነት እንዲያወርዱ ማስቻሉንም ተመላክቷል።
የሁዋዌ GigaAAU ቴክኖሎጂ ሦስት የተለያዩ የኔትወርክ ባንዶችን (1.8 GHz፣ 2.1 GHz እና 2.6 GHz) በአንድ ላይ በማዋሃድ የኔትወርክ አቅምን ከማስፋት ባሻገር፣ የኃይል ቁጠባ ስርዓት በመጠቀም የኃይል ፍጆታን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተገልጿል።
ይህ ዘመናዊ መፍትሄ በዓለም ዙሪያ ከ20 በላይ ኔትወርኮች ላይ ተፈትኖና እውቅና አግኝቷል ሲል ካፒታል አስነብቧል።

12 months ago