ሳትማሩ ‘ባለሙያ ነን’ አትበሉ
ገንዘብ ለማግኘት ብላችሁ የወላጆችን ሸክም አታክብዱ
መቼም በጣም ደፋር ሰዎች የሞሉበት ሃገር ላይ ነን ያለነው፡፡ አንድ 'ማህበራዊ ቀዳዳ’ ሲገኝ ለመክበር ስንል በሱ በኩል ‘ያለሳይዛችን’ ለማለፍ ስንታገል ቀዳዳውን የምናሰፋ ሰዎች ነን፡፡
ይህንን ጽሁፍ እንደክፍል ሁለት ውሰዱት፡፡ በክፍል አንድ ላይ እንደነገርኳችሁ ኦቲዝም ለኢትዮጵያውያን ወላጆች በጣም ውድ ችግር ነው፡፡ እንኳን ለወጣል የሃገራቸውን ኦቲዝምን ማህበረሰብ ጫና ለተሸከሙ እንደእንግሊዝ እና አሜሪካ ላሉ መንግስታትም ኦቲዝም በየዓመቱ ቢሊዮን ዶላሮችን የሚያስወጣ ብሄራዊ ችግር ሆኗል፡፡
እንደኛ ባለ መቆም ቀርቶ ዳዴ ማለት ባቃተው ሃገር ላይ ደግሞ የችግሩን ጥነት ማሰብ ራሱ ያደክማል፡፡ በዚህ ውድነት ላይ አላግባብ መነገድ ነው እንግዲህ ዋናው ሃጢአት፡፡
በሃገራችን ከኦቲዝምና ተያያዠ የዐዕምሮ ዕድገት ስርዓት መዛባት ጋር የተያያዙ ማህበራዊ ችግሮች በዝተዋል፡፡ ያንን ተከትሎ ምርመራና ልየታን ጨምሮ የቋንቋና ንግግር ፤ የባህሪ ማረቅ (ABA) ፣ የተግባቦትና የክወና ክህሎትቴራፒ የሚሰጡ ባለሙያዎችን የመጠቀም ፍላጎትም በጣም ጨምሯል፡፡
ከዚህ የፍላጎት ዕድገት ጋር ተያይዞም 'ባለሙያ ነን' የሚሉ ሰዎች እዚህም እዚያም እንደአሸን እየፈሉ ነው፡፡ከነዚህ መካከል ስራውን ለመስራት ትምህርቱም፣ ልምዱም፣ ብቃቱም ያላቸው ባለሙያዎች ቢኖሩም ከነርሱ በእጥፍ የሚበዙት ግን ለዚህ የሚያበቃ ምንም ብቃት የላቸውም፡፡
ቲክቶክ ላይ መድረክ አገኘን ብለው “ኦቲዝምን እንመረምራለን፣ የንግግር ፣ የክዋኔ፣ የተግባቦት፣ የማህበራዊ ክህሎት ቴራፒ እንሰጣለን” እያሉ ራሳቸውን በድፍረት ሲያስተዋውቁ የሚውሉ አሸን ናቸው፡፡ ያንን አይቶ የተጎዳ ልጁን ይዞ የሚጎርፍላቸውን ወላጅ በውድ ዋጋ ቆዳውን እንደበግ ገፍፈው ያለውጤት የሚሸኙና የብዙሃኑን ኪስ የሚያራቁቱ ‘የልምድ አዋላጆች’ በርክተዋል፡፡
በድፍረት የማሰልጠኛ ማኑዋል የሚያዘጋጁ፣ “በኦቲዝም ‘ቴራፒስትነት’ አሰልጥነን ስራ እናስቀጥራለን” የሚል ማስታወቂያ ሰርተው ፣ሰርተፍኬት ሰጥተው የእነዚህን ህጻናትን ዕድሜ በነርሱ የለብለብ ሰልጣኞች እጅ ላይ የሚጥሉ ራስወዳድ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡
ሃሜት አይደለም የማወራው ፣ ምናልባት ይህንን አንብበው የሚሰሩት ስራ ተገቢ አለመሆኑን ቆም ብለው ቢያስቡ እድል ለመስጠት እንጂ አስፈላጊ ሲሆን በስም ልዘረዝራቸው እችላለሁ፡፡
መቼም የትኛውም ቢዝነስ የሚፈጠረው አንድ ችግር ለመፍታትና ገቢ ለማግኘት ነው፡፡ አገልግሎት ፈላጊ ሲኖር አገልግሎት ሰጪ በዚያው መጠን መፈጠሩ የሚበረታታ ነው፡፡ ነገር ግን ለነዚህ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች አገልግሎት እንሰጣለን የሚሉት እውን ባለሙያዎች ናቸወይ?...
እየተሰጠ ያለውና ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠየቅበት ‘አገልግሎትስ’ በርግጥም ልጆቹን የሚጠቅም ነወይ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
እየታዘብኩት "ሳያውቁ የመስራት፣ ሳይማሩ የማስተማር" ጎጂና አደገኛ 'የቢዝነስ መረብ' በጣም የሚያሳስበኝም ለዚህ ነው፡፡
ይህ 'ኦቲዝምን ቢዝነስ የማድረግ' ተግባር ወላጆችን ለአላስፈላጊ ወጪና ልፋት ፣ ወርቃማ የሆነውን የኦቲዝም ልጆችን ለጋ እድሜ ደግሞ ለመሻሻል በማይጠቅማቸው 'መግባት መውጣት' አዙሪት ውስጥ እየከተተ ነው፡፡
በባለሙያ ቢታገዝ ፍሬ ሊገኝበት የሚችለውን ኦቲዝም ለተግባር የማይበቃ ዕውቀት የያዙ “ኦቲዝም ላይ እንሰራለን” የሚሉ ሰዎች ውጤት አልባ እያደረጉት ነው፡፡ የብዙሃን ወላጆችን እና የኦቲዝም ልጆችን ተስፋም እያጠወለጉት ነው፡፡
እዚህ ጋር መንግስትን እጠራለሁ!!
እንዳለመታደል ሆኖ በሃገራችን እንደ ኦቲዝም እና ሌሎች ከዐዕምሮ ዕድገት ስርዓት መዛባት ጋር የተያያዙ ኹኔታዎች ላይ ጥርት ያለ ፖሊሲ፡ መርህ ወይም መመሪያ የለም፡፡ ጤና ሚኒስቴር በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ አንዳችም እንቅስቃሴ ሲያደርግ አይታይም ፡፡
ማን ምርመራ ማካሄድ እንደሚችል ፣ ማን የባህሪ፣ የክዋኔ ፣ የቋንቋና ንግግር፣ የማህበራዊ ተራክቦ ወዘተ ህክምና(ቴራፒ) የመስጠት ብቃት እንዳለው ፣ ማን የኦቲዝም የምግብ ዕቅድ (Diet plan) ማውጣትና ማዘዝ እንደሚችል ወዘተ የሚደነግግ መመሪያ የለም፡፡
በኦቲዝምና ተዛማጅ የዐዕምሮ እድገት ጉዳዮች ላይ ለመስራት ምን ዓይነት ስልጠናና የትምህርት ዝግጅት ፣ የስንት ጊዜ የተግባር ልምምድ እንደሚያስፈልግ የተቀመጠ መመሪያም የለም፡፡
ምርመራና ቴራፒ የሚሰጥባቸው ተቋማት ለዚህ ስራ ማሟላት በሚገባቸው መሰረታዊ ግብዓቶችና መሰረተ ልማቶች ላይም ይህ ነው ተብሎ የተቀመጠ መስፈርትም የለም፡፡ ዝም ብሎ ዴይኬር በሚቋቋምበት መስፈርት ነው የሚፈቀደው፡፡ ከጤና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባለው በዚህ ዘርፍ ላይ ለመስራት በርካታ መመዘኛዎች ያስፈልጉ ነበር፡፡
በኦቲዝም ላይ እየሰሩ ላሉ ሃኪሞችም ቢሆን ከጤና ሚኒስቴርም ይሁን ከሌሎች መንግስታዊ አካላት የተሰጠ ፍቃድ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ ለቴራፒስቶችም ቢሆን (ቀጥታ ከጤና ኹኔታ ጋር የሚያያዝ ስራ ስለሚሰሩ) የሙያና የስራ ፍቃድ እንደሚያስፈልግ አልታሰበበትም፡፡
በዚህ ሳቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ ኦቲዝም ‘እችላለሁ’ ያለ ሁሉ እየተነሳ “ቢዝነስ’ የሚሰራበት ‘ያልተበላ የንግድ ዘርፍ’ (Lucrative Business) እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ቁጥራቸው ከሚሊዮኖች ለሚበልጥ ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆች፣ ወጣቶችና ወላጆቻቸው እጅግ ተስፋ አስቆራጭና አሳሳቢ ተግባር ነው፡፡
ዛሬ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲን እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በልዩ ፍላጎት ትምህርት (Special need Education) እና በንግግርና ቋንቋ ህክምና (Speech-language pathology) ዘርፎች በሁለተኛ ዲግሪ ጭምር ትምህርት ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያ ትምህርታቸው ስነልቡና እና ስነዐዕምሮ ላይ የሆኑ የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎች ይህንን ትምህርት ሲጨምሩበት ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ይወጣቸዋል ፡፡
ችግሩ ግን አሁን በስራ ላይ ያሉት ‘ቴራፒስቶች’ የት ተምረው ቴራፒስት ሆኑ? ‘የልዩ ፍላጎት ማሰልጠኛ’ ከፈትን የሚሉትስ ምን ያህሉ በዚህ መደበኛ የትምህርትና ስልጠና ሂደት አልፈዋል?" ብለን ብንጠይቅ መልሱ አሳዛኝ ነው፡፡
በየሰፈሩ ‘የንግግር፣ የባህሪ ምናምን ቴራፒ እንሰጣለን’ ብለው ቢሮ የከፈቱ ፣ ከጨነቀው ወላጅ ላይ በሰዓት ከፍተኛ ገንዘብ እየተቀበሉ የሚመዘብሩ ግለሰቦችንስ ማን ፍቃድ ሰጥቷቸው ነው ወደዚህ ስራ የገቡት ? ማንም! ምክንያቱም ፍቃድ ሰጪም ነሺም አካል የለማ!!
የቅድመመደበኛ ወይም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሆነው ሳለ ‘የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት እንሰጣለን’ በማለት እንደኦቲዝም ያለ ከዐዕምሮ ዕድገት ጋር የተያያዘ ጉዳይ ያላቸውን ህጻናት ከመደበኞቹ ጋር አንድ ላይ አጅለው የሚያስተምሩና የወላጅ ትከሻን የሚያደቅቅ ገንዘብ በየወሩ የሚቀበሉ ትምህርት ቤቶችስ “በምን መለኪያና የቁጥጥር ስርዓት አልፈው ነው ይህንን ‘ንግድ’ የሚያከናውኑት ?” የሚለውም እስካሁን ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
ስለዚህ እንደኔ እንደኔ መንግስት በዚህ ማህበራዊ ችግር ውስጥ በአስቸኳይ እጁን ማስገባት አለበት፡፡ የግል አገልግሎት ሰጪዎችን ፍቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ላይ አስገዳጅ መመሪያ ማውጣት አለበት፡፡
ለውሣኔም ለተግባርም መነሻ ስለሚሆን የኦቲዝም ስርጭት መጠን ( prevalence rate) ማሳያ ብሔራዊ መረጃ (National Data) አስጠንቶ ይያዝ ።
ማሰልጠኛዎችን መክፈት አለበት፣ እነዚህ ልጆች አግባብ ያለው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉባቸውን ማዕከላት መክፈት በመንግስት ትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ በተጓዳኝ ዘርፍ ማደራጀት አለበት፡፡
በአጠቃላይ ልጆቹ ዜጎች ናቸውና ከሌሎች ልጆች እኩል የመማርና አገለግሎት የማግኘት መብታቸውን ማስከበር አለበት፡፡ መንግስት ካልገባበት ይህ ልምምድ ሰፍቶ ነገ ወላጅንም፣ ማህበረሰቡንም ሃገርን ዋጋ እንዳያስከፍላት እሰጋለሁ፡፡
በነገራችን ላይ!
ከነዚህ የኦቲዝም ልጆች መካከል እኮ ልዩ IQ የታደሉ እነ ኤይንስታይን አሉ፣ እነሜሲ አሉ፣ እነዳቬንቺ አሉ፣ እነሞዛርት አሉ፣ እነስቲቭ ጆብስ አሉ፣ እነኤሎን መስክ አሉ፣ እነቢል ጌትስ አሉ…. ምቹ ሁኔታ ሲያገኙ አለምን የሚለውጡ ብሩህና ስማርት ልጆች ባሉበት ኦቲዝም ላይ መንግስት ዝምታውን ሊሰብር፡ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴም ማድረግ አለበት ባይ ነኝ፡፡
ግድ የላችሁም! ነገ ሃገርን የሚጠቅማት ሰው ከነዚህ መካከል ይወጣል፡፡
Ministry of Education EthiopiaMMinistry of Health,EthiopiaMMayor Office of Addis AbabaAAddis Ababa Education BureauAAddis Ababa Trade Bureauየየሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs@followers@highlight

12 months ago