በውጭ ምንዛሬ ወቅታዊ አቅርቦት ዙሪያ የተሰጠ አጭር መግለጫ
ባንካችን እ.ኤ.አ ከሐምሌ 1፣2025 እስከ ሐምሌ 31፣2025 ድረስ ከደንበኞቹ ከቀረቡለት ጥያቄዎች ውስጥ አብዛኛዎቹን ያስተናገደ ሲሆን በዚህም በሐምሌ ወር ብቻ በድምሩ ከ125 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለደንበኞች በጥያቄያቸው መሰረት ማቅረቡ ይታወሳል።
የሃገራችን የውጭ ምንዛሪ የመጠባበቂያ ክምችት ከመሻሻሉ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች በቂ የውጭ ምንዛሪ ከማቅረቡ በተጨማሪ በአጠቃላይ የባንካችን የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ ይገኛል። በመሆኑም ለሂሳብ ዓመት 2025/26 የነሐሴ ወር ባንካችን በአጠቃላይ ከ110 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ጥያቄ ለሚያቀርቡ ደንበኞች አዘጋጅቶ በአሁኑ ወቅት ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞች እየሰጠ ይገኛል። በመሆኑም ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚፈልግ የባንካችን ደንበኛ መመዝገብ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ለመግለጽ እንወዳለን።
አዋሽ ባንክ !
ስልክ: +251-11-557-0167 ፋክስ፡ +251-11-557 0136 ኢሜይል:solomonjawashbank.com

1 year ago