Logo
FastMereja
"እኔ እኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ!" በኢትዮጵያ ሀገር ባህል ልብስ የደመቁት ምክትል ፕሬዝዳንት

ለኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር በተለያዩ መንገዶች ከሚገልፁና ከሚያንፀባርቁ የአገራት መሪዎች አንዷ የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው። ም/ፕሬዝዳንቷ በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ላይ ለመካፈል ዛሬ አዲስ አበባ ሲገቡ በኢትዮጵያ ሸማ የተሰራና በአገራቸው የቀለም ፈርጥ (Color tone) የተጠለፈ ቀሚስ ለብሰው በምጣት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ክብርና ፍቅር አንፀባርቀዋል።

ወ/ሮ #jessica Rose Epel Alupo ባለፈው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ለመሳተፍ ሲመጡ ለተቀበሏቸው ሚኒስትር "እኔኮ ኢትዮጵያዊ ነኝ"! ለአገራችን ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር ደጋግመው ሲገልፁ ሰምቻቸዋለው። #ugandan #ethiopia

📷 Abdi Ali Ibrahim
Via: ኃይለሚካኤል ዴቢሳ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.