Logo
Getu Temesgen
በሐሰተኛ ሰነድ ሀገር ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ከ12 ሺሕ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ
#ethiopia | ‎ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በሕገ-ወጥ መንገድ ሀገር ውስጥ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ12 ሺሕ 127 በላይ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል

ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በትናንትናው ዕለት አካሂዷል፡፡

በመድረኩም ከውጭ ሀገር ዜጎቹ በተጨማሪ፤ ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተገናኘ ዜጎችን ለእንግልት የዳረጉና ብልሹ አሰራር ውስጥ የተገኙ 26 የተቋሙ ሠራተኞች በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት 3 ሺሕ 868 ሰዎች የተጭበረበረ ሰነድ በመጠቀም ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር በማዋል በሕግ ተጠያቂ መደረጋቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሠረት በግለሰቦቹ ላይ በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ፣ ከሀገር ማስወጣት እና ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲገቡ በማድረግ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡

ባለፉው አንድ ዓመት በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ሰዎች መካከል 2 ሺሕ 77 ሃሰተኛ ሰነድ በማቅረብ፣ 275 ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ ፓስፖርት ለማውጣት በመሞከር እንዲሁም የተቀሩት በተለያየ መንገድ ለማጭበርበር ሲሞክሩ የተያዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት አዲስ ሪፎርም ተግባራዊ በማድረግ፤ በርካታ ሥራዎችን መስራቱንም አስታውቀዋል፡፡ #ahaduradio

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.