Logo
AHADU RADIO FM 94.3
ራስን ማጥፋትን የተመለከቱ የሚድያ ዘገባዎች መፍትሔ አመላካች መሆን እንደሚገባቸው ተገለጸ

የመገናኛ ብዙኃን እና በጉዳዩ ላይ መረጃ የሚሰጡ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ራስን ከማጥፋት እና ከአዕምሮ ጤና ጋር የተያያዙ ዘገባዎቻቸው መፍትሔ አመላካች እና ተስፋ የሚሰጡ ሊሆኑ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የአዕምሮ ሕክምና ማኅበር ገልጿል።

የማኅበሩ ተወካይ እና የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው፣ "አሁን ላይ በመገናኛ ብዙኃን የአዕምሮ ጤናን አስመልክቶ የሚበርቡ ዘገባዎች ቁጥር ማሻቀቡ የሚበረታታ ቢሆንም፤ በተለይም ከራስ ማጥፋት ጋር ተያይዞ በልዩ ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች የሙያ ሥነ-ምግባርን ያልተከተሉ ናቸው" ብለዋል።

ራስን የማጥፋት መረጃዎችን የድርጊቱን አፈጻጸም በዝርዝር ማቅረብ ሌሎች ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ ሊገፋፋ እንደሚችል የጠቆሙት ዶክተር እስጢፋኖስ፣ "ዘገባዎች ሰዎች ከችግሩ የሚወጡበትን እና የሚታከሙበትን መንገድ የሚያመላክቱ መሆን አለባቸው" ብለዋል።

ማኅበሩ በስፋት የሚታየውን ችግር ለማቃለል ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን እና በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሠራ አስታውቋል።

በስፍራሽ ደመላሽ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.