በትግራይ ክልል በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) መጋዝን ላይ ከትላንት በስቲያ እሁድ ዘረፋ መፈጸሙን የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ ምክትል ቃል አቃባይ ገለጹ።
በክልሉ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ የዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ድርጅቶች መጋዘኖች እና መገልገያዎች በተመሳሳይ መልኩ መዘረፋቸውንም ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ምክትል ቃል አቃባይ ፋራህን ሃቅ ይህንን የተናገሩት፤ ትላንት ሰኞ መስከረም 25፤ 2019 ምሽት በሰጡት ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
የእሁዱ ዘረፋ በትግራይ ክልል የትኛው አካባቢ እንደተፈጸመ እና በጋዜጣዊ መግለጫቸው ያልጠቀሱት ምክትል ቃል አቃባይ ፋራህን፤ ሆኖም በክስተቱ የሰብአዊ አቅርቦቶች መጥፋታቸውን አስረድተዋል።
በዘረፋው ከተሰረቁት ውስጥ ምግብ፣ ምርጥ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያዎች እና የውሃ ፖምፖች እንደሚገኙበት የተመድ ዋና ጸሀፊ ምክትል ቃል አቃባይ ገልጸዋል።
የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች፣ ተቋማት እና ንብረቶች “በፍጹም የጥቃት ኢላማ ሊሆኑ አይገባም” ያሉት ፋራሃን፤ በሁሉም ጊዜያት “ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ” ጨምረው አሳስበዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube FikerAssefa

1 day ago