Logo
FastMereja
ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ባለ 21 ፎቁን የቦሌ አደይ አበባ 1 ፕሮጀክት በ18 ወራት አጠናቆ አስመረቀ
#fastmereja I ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት በ18 ወራት ውስጥ ግንባታውን ያጠናቀቀውንና ሁለተኛ ሳይቱ የሆነውን የቦሌ አደይ አበባ 1 ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።

በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ የድርጅቱ አመራሮች፣ የሳይት ኢንጂነሮች፣ አርክቴክቶች፣ የብራንድ አምባሳደሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው አጋሮች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማርሽ ባንድ ተገኝተዋል። ኩባንያው ወደ ዘርፉ በገባ በ30 ወራት ውስጥ 11 የነቁ (Active) የግንባታ ሳይቶች ያሉት ሲሆን፣ ሁለቱን ሳይቶች በጥራት አጠናቆ በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለደንበኞቹ ማስረከቡን አስታውቋል።

ዛሬ የተመረቀው ባለ 21 ፎቅ ዘመናዊ ሕንፃ ከንግድ ሱቆች እስከ ቅንጡ አፓርትመንቶች ያካተተ ሲሆን፤ የኳስ ሜዳ፣ ጂም፣ ሁለገብ አዳራሽ እና በርካታ የጋራ መጠቀሚያ አሜኒቲዎችን ያካተተ ነው።

የድርጅቱ አመራሮች በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ በዘርፉ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶችን በወቅቱ አለማስረከብ ችግር በመቅረፍ፣ በጥራት እና በፈጣን ጊዜ ውስጥ ቤቶችን ከነካርታቸው አዘጋጅቶ ማስረከብ የኩባንያው ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ኩባንያው ከደንበኞች ለቀረበለት የ"ድገሙልን" ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት "አደይ አበባ 2" የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክት እዛው በሳይት 1 ፊት ለፊት በይፋ ማስጀመሩን አብስሯል። አዲሱን ፕሮጀክት አስመልክቶ "እንደተወደደ ተደገመ" በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2, 2019 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የሚቆይ ልዩ የሽያጭ እና የጉብኝት ኤክስፖ ከልዩ ቅናሽ ጋር ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

11 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.