Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በሱዳን ሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን አወገዘ

ምክር ቤቱ በሱዳን ሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የድሮን እና ሌሎች ጥቃቶችን በማውገዝ በሀገሪቱ ላለው ቀውስ “ምንም ዓይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ” አስጠንቅቋል።

መግለጫው የወጣው የዓለም የምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኮርዶፋን የምግብ አቅርቦት ጭኖ በነበረ የጭነት መኪና ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ባስታወቀበት ወቅት ነው።

በጄኔቫ በተካሄደው ስብሰባ 47 አባላት ያሉት ምክር ቤቱ ለሱዳን ያዋቀረውን ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የእውነታ አጣሪ ተልዕኮ የስራ ጊዜ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በ28 የድጋፍ እና በ10 የተቃውሞ ድምጽ አጽድቋል።

ሱዳን ምክር ቤቱ ያቀረበችውን ቅሬታ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለመቻሉን በመግለጽ አባል ሀገራቱ ይህን እርምጃ ውድቅ እንዲያደርጉት አሳስባለች።እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2023 በሱዳን ጦር እና በከፊል-ወታደራዊው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተጀመረው ጦርነት የአስር ሺዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ደግሞ አፈናቅሏል።

የተመድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዚህ ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ውስጥ ብቻ በድሮን ጥቃቶች ከ1,100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

በሚኪያስ ጸሐዬ
#ዳጉ_ጆርናል
13 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.