በአድዋ ከተማ ሶሎዳ ሆቴል ላይ ከትናንት በስቲያ እኩለ ሌሊት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 5 ሰዎች መገደላቸውን ዋዜማ ሠምታለች። በድሮን ጥቃቱ፣ ከታጠቁ የጸጥታ ጥበቃ አባላት በተጨማሪ በሆቴሉ ሲስተናገዱ የነበሩ ሌሎች 3 ሰዎች አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ተቋም መወሠዳቸውን ምንጮች ነግረውናል።
በሆቴሉ ውስጥ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልና ሌሎች የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እንደነበሩና በጥቃቱ የተገደሉት የአመራሮቹ የጥበቃ አባላት መሆናቸውን ዋዜማ መረጃ የደረሳት ቢሆንም፣ የቡድኑ አመራሮች በወቅቱ በሆቴሉ ውስጥ ስለመኖራቸው ወይም በጥቃቱ የተገደሉት በትክክል የአመራሮቹ የጥበቃ አባላት ስለመሆናቸው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ዋዜማ ከገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አልቻለችም።
@Yenetube Fikerassefa

13 hours ago