የ«መልካም ወጣት» ፕሮጀክት ግንባታ ለማጠናቀቅ አዲስ የገቢ ማሰባሰቢያ ሊካሄድ ነው!
#fastmereja I ለዘጠኝ ዓመታት በሐገር ውስጥ እና በውጭ ሐገር እንዲሁም በማርሲል ቲቪ ጨምሮ ከ500,000 በላይ ወጣቶችን ተሳታፊ ያደረገው «የመልካም ወጣት» አገልግሎት፣ በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ይበልጥ ለማስፋፋት አዲስ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ሊጀምር መሆኑ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነገረ።
በመድረኩ ላይ እንደተነገረው ባለፉት ዓመታት ከ60,000 በላይ ሰዎች ጌታን እንደግል አዳኛቸው እንዲቀበሉ ምክንያት የሆነው ይህ አገልግሎት በወጣቶች ትውልድ ግንባታ ላይ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተነግሯል።
የአገልግሎቱ መሪዎች እንዳስታወቁት፣ በሀዋሳ ከተማ 5,000 ሰዎችን የሚይዝ አዳራሽ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ አሁን ላይ አቅሙን ወደ 15,000 ሰዎች ለማሳደግ ተጨማሪ የግንባታ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከ5 ባለ 5 ወለል የተማሪዎች ማደሪያ ሕንፃዎች መካከል 3ቱ ተጠናቀው የመጨረሻ ስራዎች እየተከናወኑላቸው ይገኛል፤ ቀሪዎቹ 2ቱ ሕንፃዎች አሁንም በግንባታ ላይ ናቸው። እንዲሁም 10,000 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ትልቅ አሬና እና ለአእምሮና ሰውነት ማጎልመሻ የሚሆን ስፍራም በመገንባት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ከ250 ሚሊዮን እስከ 300 ሚሊዮን ብር የሚደርስ በጀት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። ገንዘቡን ለማሰባሰብም በቀጣዮቹ 10 ወራት ውስጥ በጅማ፣ ቦንጋ፣ ቡታጅራ፣ ባስኬቶ፣ ዳውሮ፣ ጅጅጋ፣ ጊዶሌ፣ ሻኪሶ፣ ሳውላ እና ቡሌ ሆራን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉዞ ይደረጋል። የዚህ ጉዞ መነሻ ጥቅምት 6፣ 7 እና 8 ቀን 2019 ዓ.ም በጅማ ከተማ እንደሚጀመር ታውቋል።
ይህ የወጣቱን ትውልድ በስነ-ምግባር እና በእውቀት ለመገንባት የሚደረግ የጋራ አህጉራዊና ሀገራዊ ጉዞ በመሆኑ፣ በተጠቀሱት ከተሞች የምትገኙ ማህበረሰቦች ሁሉ በጸሎት፣ በገንዘብ፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በአቅማችሁ ሁሉ ከጎናችው እንድትቆሙ አስተባባሪዎቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

6 hours ago