(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ከኢራን ወይም ከሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ጋር የንግድ ግንኙነት ባላቸው የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያለ ምንም ቅድመ ማሳወቂያ በዋሽንግተን ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሚችል አስጠንቅቋል።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ ማዕቀብ ከተጣለባቸው የኢራን ተቋማት ጋር ግብይት ማድረጋቸውን የሚቀጥሉ የውጭ የፋይናንስ ተቋማት በማንኛውም ጊዜ ያለቅድመ ማሳወቂያ የእርምጃ ዒላማ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ ይህንን እንቅስቃሴ እና ግንኙነት በአፋጣኝ ሊያቋርጡ ይገባል ብሏል። በተጨማሪም፣ ከኢራን ጋር የሚደረጉ ግብይቶች የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማትን ወይም አሜሪካውያንን የማዕቀብ ህጎችን እንዲጥሱ የሚያደርጉ ከሆነ፣ እነዚህ የውጭ ተቋማት የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ህግ ቅጣቶች ሊጠብቃቸው እንደሚችል አስገንዝቧል።
የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት ፣ ኢራን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች ያላትን ተደራሽነት ይበልጥ ለመገደብ እና ቴህራን ጦርነቱን የሚያስቆም ስምምነት ላይ እንድትደርስ ጫና ለመፍጠር በማሰብ ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ "ኦፕሬሽን ኢኮኖሚክ አውትካስት" የተሰኘ የኢኮኖሚ ዘመቻ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

4 hours ago