በደቡባዊ ናይጄሪያ 32 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ የወታደራዊ አውሮፕላን ተከሰከሰ
25 ተሳፋሪዎችን እና 7 የካቢን አባላትን አሳፍሮ የነበረ ወታደራዊ አውሮፕላን ትናንት በደቡባዊ ናይጄሪያ የተከሰከሰ ሲሆን፤ይህም አስቸኳይ የፍለጋ እና የማዳን ሥራ እንዲጀመር ማድረጉን ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
የጉዳት መጠን ወይም በሰው ሕይወት ላይ ስለደረሰው አደጋ እስካሁን የተረጋገጠ መረጃ የለም።
አውሮፕላኑ ወደ ሌጎስ መደበኛ በረራ በማድረግ ላይ እያለ መከሰከሱን የናይጄሪያ አቪዬሽን ሚኒስቴር አስታውቋል።
የናይጄሪያ አየር ኃይል ወዲያውኑ የፍለጋ እና የማዳን ሥራ መጀመሩን አስታውቋል። በአውሮፕላኑ ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ግን እስካሁን ግልጽ አልሆነም።
ሚኒስትሩ እንደገለጹት አውሮፕላኑ በሀገር ውስጥ ሰዓት አቆጣጠር ጠዋት 3 ሰዓት ገደማ ከራዳር የተሰወረ ሲሆን፤ከኤዶ ግዛት ወደ ሌጎስ ያደርገው በነበረው በረራ እኩሌታ ላይ ደርሶ መከሰከሱ ታውቋል።
Seledadotio

4 hours ago