ኢትዮጵያ ከጄኔቫው የፈንጂ ማስወገድ ማዕከል ጋር የፈጸመችው ስምምነት የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት እንደሚያጎለብት ተገለጸ
ኢትዮጵያ ከጄኔቫ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ፈንጂ ማስወገድ ማዕከል ጋር የፈጸመችው ስምምነት በምሥራቅ አፍሪካ የዘርፉ ዋና ማዕከል እንድትሆን እና ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነቷን እንድታጎለብት እንደሚያግዛት ተገልጿል።
ስምምነቱ የፈንጂ ማስወገድ ሥራዎችን ለማጠናከር፣ የመረጃ አያያዝን ለማዘመንና የባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ያስችላል ተብሏል።
የጂኦፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ ዶክተር ተሻለ ሰብሮ እንደገለጹት፣ ስምምነቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ በማሳደግ ለሌሎች ሀገራት ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ዕድል ይፈጥራል። በተለይም ጦርነት በተካሄደባቸው የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ መስጠት በሰብዓዊ ሥራዎች ያላትን ተሳትፎና ዓለም አቀፍ ተሰሚነት ያጠናክራል።
ፖለቲከኛ እና መምህር ዶክተር ጌትዬ ትርፌ በበኩላቸው፣ ከማዕከሉ ጋር የሚደረገው ትብብር የሀገሪቱን የሙያ፣ የልምድ እና የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ባለሙያዎች እና ተቋማት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመቅሰም አቅማቸውን እንደሚያጎለብቱም ጠቁመዋል።
ትብብሩ የሀገር ውስጥ የፈንጂ አደጋን ከመቀነስ ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአካባቢውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የዲፕሎማሲ ተሰሚነት ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ባለሙያዎቹ አብራርተዋል።
በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

2 days ago