Logo
YeneTube
በስህተት ወደ ባንክ አካውንቷ የገባውን 158ሺ ብር የፖሊስ አባሏ ለባለቤቱ መመለሳን የአዲስ በባ ፖሊስ ዋና መመሪያ አስታወቀ፡፡

ዋና ሳጅን ደገፈች ደሳለኝ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የቄራ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ ስትሆን መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም  ወደ ስራዋ እያመራች አንድ የስልክ ጥሪ ይደርሰታል። ደዋዩ ሚኪያስ አንዳርጌ የተበለ ግለሰብ ሲሆን በስህተት 158ሺህ ብር ወደ እሷ አካውንት ገንዘብ ማስተላለፉን ይነግራታል።

በጋምቤላ ክልል እንደሚኖርና ወደ አዲስ አበባ መምጣት እንደማይችል፣ ገንዘቡን ያስተለለፈው ጋምቤላ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲማ ቅርንጫፍ መሆኑንም ያስረዳታል።

የባንኩ ዲማ ቅርንጫፍ ከዋና ሳጅን ደገፈች ደሳለኝ ጋር በስልክ ከተነጋገረ በኋላም አዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ቅርንጫፍ በመሄድ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ ለባለቤቱ መልሳለች።

ፖሊስ የቆመለትን የህዝብ አገልጋይነትና ታማኝነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ያለችው ዋና ሳጅን ደገፈች ገንዘቡን መመለሴ እንደ ትልቅ ጀብድ መታየት የሌለበትና ኃላፊነቴን የተወጣሁበት አግባብ ነውም ብላለች፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ለዋና ሳጅን ደገፈች ደሳለኝ ባሳየችው ታማኝነትና የግለሰቡን ገንዘብ ያለ ምንም ጉድለት በመመለሷ የምስጋና የዕውቅና ሰርተፍኬት አበርክቶላታል።

@Yenetube Fikerassefa
20 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.